TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ፓስፖርት

ከዚህ ቀደም ፓስፖርት ለማግኘት ይጠየቅ ነበረው የድጋፍ ደብዳቤ ቀርቶ በመታወቂያና በልደት የምስክር ወረቀት መሰጠት መጀመሩን የኢሚግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳን ኩነት ኤጀንሲን ገልጿል። ከዚህ በኋላም ፓስፖርት ለመውሰድ ጥያቄ የሚያቀርቡ ግለሰቦች ሕጋዊ መታወቂያና የልደት የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው ተብሏል፡፡

ፓስፖርት በአስቸኳይ ለሚፈልጉ ሰዎችም ከ3 እስከ 5 በሚደርሱ ቀናት ውስጥ ምላሽ እንደሚያገኚ ኤጀንሲው የገለጸ ሲሆን በመደበኛ ጊዜም ሆነ በአስቸኳይ ፓስፖርት ለማደስ እና አዲስ ለመጠየቅ ሕጋዊ መታወቂያና የልደት የምስክር ወረቀት መያዝ እንደሚያስፈልግ ተነግሯል።

ይህ አሰራርም ዜጎች የልደት የምስክር ወረቀት እንዲኖራቸው እንዲሁም ሕገ ወጥ መታወቂያዎችን ለመከላከል የልደት የምስክር ወረቀቱ እንደሚያግዝ ተገልጿል። ከዚህ ቀደም ፓስፖርትን ያለ አሳማኝ የድጋፍ ደብዳቤ መስጠት ተከለከለበት ምክንያት ሕገ ወጥ ስደትን ለመከላከል ሲሆን የውጪ ምንዛሪ እጥረትም ሌላኛው ምክንያት እንደነበር የኤጀንሲው ገልጾ ነበር።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፓስፖርት በአቋራጭ...🤔

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የዜግነት መብት የሆነውን #ፓስፖርት ለማውጣት ለወራት በቀጠሮ የሚጉላሉ እያሉ ጥቂቶች በአቋራጭ ሲወስዱ ይስተዋላል። ይህ አሰራር የኅብረተሰቡን እሮሮ እያባባሰ መጥቶ በመንግስት ላይም ጫና እያሳደረ ይገኛል!

https://telegra.ph/ETH-11-05-5

(ENA)

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ፓስፖርት

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ፥ የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት በኦንላይን ላይ ቀጠሮ አስይዘው በተለያየ ምክንያት የቀጠሮ ጊዜ ያለፈባቸው ተገልጋዮች ከዚህን ቀደም በቅጣት በማንኛውም የስራ ቀን አገልግሎት ሲያገኙ መቆየታቸውን ገልጾ ከፊታችን ሰኞ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ግን በስራ ሰዓት አርብ አርብ ቀን ብቻ በቅጣት አገልገሎት የሚያገኙ መሆኑን አሳውቋል።

ተገልጋዮች ይህን አውቀው በዕለቱ ብቻ እንዲገኙ መልዕክት አስተላልፏል።

በተጨማሪም ፦ የቀጠሮ ጊዜያቸው ከ1 ወር በላይ ያለፈባቸው ተገልጋዮች #በኦንላይን ላይ ዳግም ማመልከት እንዳለባቸው ገልጿል።

#ማስታወሻ፦ ከዚህ ቀደም " የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ " ይባል የነበረው ተቋም ስያሜው የፌዴራል መንግስት አስፈፃሚ አካላትን ሥልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው አዋጅ 1263/2014 ዓ.ም መሠረት " የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት / Immigration and citizenship service " በሚል ስያሜ ተቀይሯል።

@tikvahethiopia
#ፓስፖርት

የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያዎችን በ " ቴሌ ብር " አማካኝነት መፈፀም እንዲቻል በኢትዮ ቴሌኮም እና በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መካከል ዛሬ ስምምነት ተፈፅሟል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሪት ፍሬህወት ታምሩ ፤ ስምምነቱ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፣ እድሳት ለመፈፀም እና ሲጠፋ ሌላ ለማውጣት አገልግሎት ሲፈልጉ በቴሌ ብር ክፍያ መፈፀም እንደሚያችል ገልፀዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሙሉጌታ በበኩላቸእ አገልግሎቱ በቀን ከ1,500 እስከ 2,000 የሚጠጉ ደምበኞች የሚስተናገዱበት መሆኑን በመግለፅ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የተደረገው ስምምነት አገልግሎቱን ለማግኘት የሚፈጠረውን መጨናነቅ ይቀንሰዋል የሚል እምነት እንዳላቸዉ መናገራቸው ኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ፓስፖርት

ከዓለም አገራት ፓስፖርቶች ሁሉ ሴንጋፖር ፓስፖርት " ጠንካራው " ነው ተብሏል።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ደግሞ ከነበረበት ደረጃ መሻሻል አሳይቷል።

ከዓለም አቀፉ የአየር ትራንስፖርት ማኅበር / ሄንሌይ እንደተገኘው መረጃ የሲንጋፖር ፓስፖርትን የያዙ ሰዎች ከ227 መዳረሻዎች 192 ወደሚሆኑት ያለ ቪዛ ለመጓዝ በማስቻል ከሁሉ ልቆ ተገኝቷል።

በዓለም ካሉ ደካማ ፓስፖርቶች መካከል የሚመደበው የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከዚህ ቀደም ከነበረበት 97ኛ ደረጃ ጥንካሬው ተሻሽሎ ወደ 89ኛ ከፍ ብሏል።

የሀገራት የፓስፖርት ደረጃ ምን ይመስላል ?

- በጥንካሬው አንደኛ ደረጃ የተቀመጠው የሲንጋፖር ፓስፖርት ነው። ከ227 መዳረሻዎች ወደ 192ቱ ያለ ቪዛ ማስገባት ይችላል።

-  የጀርመን፣ የጣሊያን እና የስፔን ፓስፖርትን የያዙ ተጓዞች ወደ 190 መዳረሻዎች ያለ ቪዛ መጓዝ ይችላሉ።

- ጃፓን ለበርካታ ዓመታት ቁጥር አንድ ባለ ጠንካራ ፓስፖርት የነበራት ሲሆን አሁን ላይ ከኦስትሪያ፣ ከፊንላንድ፣ ከፈረንሳይ፣ ከላክሰመበርግ፣ ከደቡብ ኮሪያ እና ከስዊድን ጋር በእኩል 189 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች።

- ዩናይትድ ኪንግደም 4ኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጠ አሜሪካ ደግሞ 8ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች።

የኢትዮጵያ ፓስፖርት ደረጀ . . .

ከዚህ ቀደም ድርጅቱ ባወጣው የደረጃ ሰንጠረዥ የኢትዮጵያ ፖስፖርት ከ109 ፓስፖርቶች ጋር ተነጻጽሮ በ46 ነጥብ 97ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጦ ነበር።

በ2023 ሦስተኛ ሩብ ዓመት ሪፖርቱ ላይ የኢትዮጵያ ፓስፖርት በ47 ነጥብ 14 ደረጃዎችን አሻሽሎ ከ103 ፓስፖርቶች 89ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ይህ ማለት የኢትዮጵያን ፓስፖርት የያዙ ተጓዦች አሁን ላይ ቀድሞ ቪዛ ሳያስፈልጋቸው ወደ 47 መዳረሻዎች መጓዝ ይችላሉ ማለት ነው።

ደካማዎቹ ፓስፖርቶች የትኞቹ ናቸው ?

አፍጋኒስታን፣ ኢራቅ፣ ሶሪያ፣ ፓኪስታን እና የመን አምስቱ እጅግ ደካማ ፓስፖርት ያላቸው አገራት ሆነዋል።

ከአፍሪካ ደካማ ፓስፖርት ያላቸው 10 አገራት፦
- ሊቢያ
- ሱዳን
- ኤርትራ
- ደቡብ ሱዳን
- ናይጄሪያ
- ኢትዮጵያ
- ጅቡቲ
- ላይቤሪያ
- ኮንጎ ሪፓብሊክ እና ቡሩንዲ ናቸው።

ሄንሌይ ደረጃው እንዴት ነው የሚያወጣው ?

ሄንሌይ የፓስፖርቶችን ጥንካሬ የሚለካው፤ ተጓዦች በያዙት ፓስፖርት ምክንያት ቪዛ ቀድመው ሳያስፈልጋቸው ወደ ስንት አገራት መጓዝ ይችላሉ የሚለውን በማጤን ነው።

ቀድሞ ቪዛ አለማስፈለግ ማለት ወደ መዳረሻ ለመጓዝ ቪዛ አለመጠየቅ አልያም በመዳረሻ ቪዛ የማግኘት መብት ማለት ነው።

ተቋሙ የፓስፖርት ደረጃን የሚያወጣው ያለ ቪዛ ለሚደረግ የጉዞ መዳረሻ አንድ ነጥብ በመስጠት ነው።

የፓስፖርት ጥንካሬ የሚወሰነው በምንድን ነው ?

የዓለም ባንክ እንደሚለው የአንድ አገርን የፓስፖርት ጥንካሬ ከሚወስኑ ዋነኛ ጉዳዮች መካከል እነዚህ ይጠቀሳሉ።

- ዜጎች የሚያገኙ የነፍስ ወከፍ ገቢ መጠን ፤ ከፍተኛ የነፍስ ወከፍ ገቢ ያላቸው አገራት ከደሃ አገራት በተሻለ ወደ በርካታ አገራት ቪዛ ቀድሞ ማግኘት ሳይጠበቅባቸው መጓዝ ይችላሉ።

- የአንድ የአገር #ሁለንተናዊ_ሰላም ከአገሪቱ የፓስፖርት ጥንካሬ ጋር በቀጥታ ይገናኛል። በአንድ አገር የሽብር ጥቃቶች እና የውስጥ ግጭቶች የበረከቱ ከሆነ እንዲሁም በተደራጁ ቡድኖች የሚፈጸሙ ወንጀሎች ካሉ የዚያች አገር ዜጎች ዓለም አቀፍ ጉዟቸው የተገደበ ይሆናል።

- ጠንካራ ማዕከላዊ መንግሥት የሌላቸው እና ከፍተኛ ተፈናቃይ ያለባቸው አገራት ዜጎችም በተመሳሳይ ቪዛ የሚጠየቁባቸው መዳረሻዎች ከፍተኛ እንዲሆኑ አድርጓል።

ሪፖርቱን በዚህ ይመልከቱ ፦ www.henleyglobal.com/passport-index/ranking

Via BBC

@tikvahethiopia
#ፓስፖርት

" 190 ሺህ ፓስፖርት በአንድ ወር ውስጥ ታትሞ ወደ ሀገር ቤት ገብቷል " -የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በተገልጋዮች ሲነሱ ለነበሩ ቅሬታዎች ዋናው ምክንያት የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት ነው አለ።

ይህን ያለው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ሲሰራቸው የነበሩ ስራዎች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በዚህም ለተገልጋዮች ቅሬታ " የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት ዋና ችግር " መሆኑን ገልጸዋል።

የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ችግር ፣ ሌብነት እና ብልሹ አሰራርም ለቅሬታዎቹ በምክንያትነት እንደሚጠቀሱ ተናግረዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍም 190 ሺህ ፓስፖርት በአንድ ወር ውስጥ ታትሞ ወደ ሀገር ቤት መግባቱን አስታውቀዋል።

ፓስፖርት ለመውሰድ ከተመዘገቡ ከስድስት ወር በላይ ለሆናቸው ዜጎች ፓስፖርት የመስጠት ስራ እንደሚሰራም ተገልጿል፡፡

ከመስከረም 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ የቀጥታ (online Visa) አገልግሎት ይጀመራል ብለዋል።

የፓስፖርት ቀጠሮ ያለፈበት ሰው ዘወትር #ቅዳሜ ቀን እየመጣ መስተናገድ ይችላልም ሲሉ አሳውቀዋል።

ከሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘም በርካታ ደላሎች ፣ እና ህገ ወጥ አሰራር ላይ የተሳተፉ አካላት በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን መግለፃቸውን ኤፍቢሲ ዘግቧል።

በዚህ ተቋም ውስጥ አለ ባለው ሙስናና ብልሹ አሰራር ምክንያት በርካታ ዜጎች ከፍተኛ ቅሬታ እንደሚያቀርቡ ይታወቃል። ፓስፖርት ለማግኘትም ያለው የጊዜ ርዝመት እና እንግልት እጅግ በርካቶችን ያማረረ ነው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፓስፖርት " 190 ሺህ ፓስፖርት በአንድ ወር ውስጥ ታትሞ ወደ ሀገር ቤት ገብቷል " -የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት በተገልጋዮች ሲነሱ ለነበሩ ቅሬታዎች ዋናው ምክንያት የፓስፖርት ህትመት ዕጥረት ነው አለ። ይህን ያለው ዛሬ በሰጠው መግለጫ ነው። የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት ተቋሙ ባለፉት 30 ቀናት ውስጥ ሲሰራቸው የነበሩ…
#ፓስፖርት

300 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ፓስፖርት እየጠበቁ ናቸው።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፤ 300 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች #ፓስፖርት ለማግኘት ተመዝግበው እየተጠባበቁ ነው ሲል አሳውቋል።

በዚህ ተቋም ባለው እጅግ በጣም ከፍተኛ ሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ ዜጎች እጅግ እንደሚማረሩ ይታወቃል።

ተቋሙን እየመሩ ያሉት አዳዲስ አመራሮች ከፓስፖርት አሰጣጥ ጋር ሲነሳ የነበረውን ችግር ለመቅረፍ እየሰራን ነው ብለዋል።

ዛሬ በተቋሙ በተሰጠው መግለጫ ፤ ከተቋሙ ውጭ የሆኑ ደላሎች የሀሰት ማስረጃዎችን፣ ፓስፖርቶችን ፣ የተቋሙ በማስመሰል ሀሰተኛ ዌብሳይቶችን በማዘጋጀት ህብረተሰቡን ለህገወጥ ድርጊት እየዳረጉ መሆኑን ገልጿል።

በዚህ ድርጊት የተሰማሩትም በርካታ መሆናቸውን ዛሬ በተሰጠው መግለጫ ላይ መጠቆሙን ከኢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ቅሬታ የፓስፖርት ጉዳይ ... ከፓስፖርት አሰጣጥ ጋር በተያያዘ ቅሬታ አለን ያሉ ወገኖች አሰፈላጊው ማስተካከያ እንዲደረግ አሳሰቡ። " የተሰራ ፓስፖርት ለመስጠት ህዝቡ እጅግ በጣም ዘግናኝ በሆነ መልኩ እየተንገላታ ይገኛል። " ያሉት ለቲክቫህ መልዕክታቸውን ያደረሱ ወገኖች ፤ በቀን የሚሰጠው ፓስፖርት ውስን ነው ብለዋል። " በቀኑ ስለማይሰጥም ባስቀመጡት ቀን ተገልጋዩ እየተመላለሰ መከራ እየበላ…
#ፓስፖርት

ፓስፖርት ፈልገው/ በሥራ ምክንያት ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጎራ ካሉ ረዥም ሰልፍ እና መጨናነቅ ማየት የተለመደ ነው።

የሰልፍ አሰላፊዎች ዱላም ሊያጋጥም ይችላል።

ወጣት፣ሴት፣ወንድ፣ልጅ ያዘሉ እናቶች እንዲሁም " ፓስፖርት ፈልገው ነው ? " እያሉ እግር በእግር የሚከተሉ ሕገወጥ ደላሎችም በአካባቢው ውር ውር ይላሉ።

አገልግሎቱ 24 ሰዓት የፓስፖርት ህትመትና በበይነ መረብ ምዝገባ አሠራር ዘርግቻለሁ ቢልም አሁንም በርካታ ተገልጋዮችን አገልግሎቱ ደጃፍ ላይ መመልከት አልቀረም።

ተገልጋዮች ዐሻራ ለመስጠት እና ፎቶ ለመነሳት በመ/ቤቱ መገኘት ግዴታቸው በመሆኑ ከተለያዩ አካባቢዎች መጥተው በወረፋው ምክንያት ላልተፈለገ እንግልት ይዳረጋሉ።

እንግልቱ ከሌሊቱ 10 ሰዓት ከእንቅልፍ ተነስቶ ረዥም ሰልፍ ከመሰለፍ ይጀምራል።

በሌቦች መዘረፍም የሚያጋጥም ክስተት መሆኑን ተገልጋዮች በምሬት ይናገራሉ።

ለአላስፈላጊ እንግልት እና ወጪ ተዳርገናል የሚሉ ተገልጋዮች ሃሳባቸውን አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት በበይነ መረብ አማካኝነት ከተመዘገቡ ወራት እንዳለፋቸው ይገልጻሉ።

ተገልጋዮቹ አገልግሎቱ አካባቢ ወረፋ ለመያዝ ስንሞክር " እኔ ቅድሚያ ወረፋ ልያዝላችሁ ክፈሉኝ " በሚሉ ደላሎች እንዋከባለን ይላሉ።

እነሱ እንደሚሉት የመሥሪያ ቤቱን ሰልፍ አሰላፊዎች ወከባና ዱላ አልፎ ውስጥ መግባት መቻል መታደል ነው።

ተገልጋዮቹ በሌሊት ለመነሳት ሲሉ በአካባቢው ለአልጋ ኪራይ ከፍለው እንደሚያድሩና ለአላስፈላጊ ወጪም እንደሚዳረጉም ይገልጻሉ።

ሰልፉ ረዝሞ ወረፋ ሳይደርሳቸው ከቀረም ቅጣት እንደማይቀርላቸው ይናገራሉ።

በርካታ አገልግሎት ፈላጊ ሕዝብ በተገቢው መንገድ ከማስተናገድ ይልቅ በዱላ በመደብደብ ሥርዓት ለማስያዝ ሲሞከር ይታያል። ወደ መግቢያ በሩ ተጠግቶ መረጃ ማግኘት የማይታሰብ ነው።

የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደቱ ተስተካክሏል ይባል እንጂ አሁንም ችግሮቹ እንደነበሩ ናቸው ይላሉ ተገልጋዮች።

የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደቱ ሳይዘምን እንደዘመነ አድርጎ ማስተዋወቅም ፍጹም ተገቢነት እንደሌለውና ሕዝብ በለውጥ እንዳያምን እንደሚያደርግም ያስገነዝባሉ።

ሰሞኑን የፓስፖርት አሰጣጥ ሂደቱን ለመመልከት በመ/ቤቱ የተገኙት የኢፕድ ጋዜጠኞች መረጃ ለመሰብሰብ ያደረጉት ሙከራ በፖሊሶች ክልከላ ተደርጎበታል።

የተቋሙ ኮሙኒኬሽን ዳሬክተር ወ/ሮ ማስተዋል ገዳ ምን ምላሽ ሰጡ ?

- ተገልጋዮች ወደ ተቋሙ በሚመጡበት ወቅት በክብር መስተናገድ እንዳለባቸው እናውቃለን። ተገልጋዮችን በአግባቡ ባለማስተናገድ የዲሲፕሊን ችግር ያለባቸው ሠራተኞች ላይ እርምጃ እየተወሰደ ነው።

- ተገልጋዮች ቅሬታ ሲኖራቸው ቅሬታ ለተቋሙ ማቅረብ አለባቸው።

- አዲስ ፓስፖርት ፈልገው በድረ ገጽ ሲያመለክቱ ፎቶግራፍ የሚነሱበትን እና ዐሻራ የሚሰጡበትን ቀንና ሰዓት የሚያሳውቅ በመሆኑ ተገልጋዮች በሰዓቱ ብቻ ቢመጡ ሰልፉ ሊቀንስ ይችላል። የተቀጠሩ ተገልጋዮች ሳይስተናገዱ አይቀሩም።

- በአካባቢው መጨናነቅ የሚፈጠረው ቀጠሮ ባላቸው ተገልጋዮች ብቻ ሳይሆን " ፓስፖርት ዘግይቶብናል "  ብለው ለመጠየቅ በሚመጡ ተገልጋዮች ነው። አንድ ጉዳይ ለመጨረስ ከአንድ በላይ ሰው ስለሚመጣ ነው።

- የሌሊት ሰልፉ ከአገልግሎቱ እውቅና ውጪ ነው። ለሰልፉ ሰዓት የመገደቡን ጉዳይ በቀጣይ በጋራ የሚታይ ነገር ነው።

- ተገልጋዮች ለአስቸኳይ ፓስፖርት በሕገ ወጥ ደላሎች በኩል ለማስጨረስ ከመሞከር ይልቅ እራሳቸው በጥቂት ቀናት መጨረስ ይችላሉ።

ያንብቡ https://telegra.ph/EPA-03-04

ይህ መረጃ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ነው።

ፎቶ፦ Tikvah Family

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፓስፖርት ፓስፖርት ፈልገው/ በሥራ ምክንያት ኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ጎራ ካሉ ረዥም ሰልፍ እና መጨናነቅ ማየት የተለመደ ነው። የሰልፍ አሰላፊዎች ዱላም ሊያጋጥም ይችላል። ወጣት፣ሴት፣ወንድ፣ልጅ ያዘሉ እናቶች እንዲሁም " ፓስፖርት ፈልገው ነው ? " እያሉ እግር በእግር የሚከተሉ ሕገወጥ ደላሎችም በአካባቢው ውር ውር ይላሉ። አገልግሎቱ 24 ሰዓት የፓስፖርት ህትመትና በበይነ መረብ ምዝገባ…
#ፓስፖርት

አዳማ ላይም ፖስፖርት ለመውሰድ አስቸጋሪ መሆኑን ተገልጋዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት ቅሬታ አመላክተዋል።

" ሰው ከመብዛቱ የተነሳ ሰው በየቀኑ ፓስፖርቱን ሳይወስድ ሳምንት ተመለሱ ይባላል። " ያሉት ቅሬታ አቅራቢዎች " ፓስፖርት ለመስጠት የሚጠሩት በአልፋቤት ብሆንም Order የጠበቃ አይደለም። " ብለዋል።

" አንዱ የጠረውን በድጋሚ ሌላም አንስቶ የመጥራት ክስተት እንዳለ " አመላክተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አንድ ተገልጋይ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ይህንን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አጋርቷል።

N ከአዳማ ፦

" አዲስ ፓስፖርትን ለመውሰድ ያለው እንግልት አለ።

አዲስ ፓስፖርት ካመለከትኩ አሁን ላይ 11 ወራት ሆኖኛል፡፡

በየካቲት ወር 7ኛው (February 15) ቀን በቴሌግራም አካውንት ላይ አዲስ ፓስፖርት የመጣላቸው ስም ዝርዝር ውስጥ ስሜን ስላገኘሁት ልቀበል አውራ ጎዳና በሚገኘው አዳማ ቢሯቸው ሄድኩኝ፡፡

ሆኖም ግን እዛ ስድርስ የመ/ቤቱ ጥበቃዎች በዱላ ጥያቄ ለመጠየቅ ግራ ገብቶት ያለውን ሰው መምታቱትን ተያይዘውታል፡፡

ከዛም ብቸኛ የመረጃ ምንጭ የሆኑት እነርሱ (ጥበቃዎቹ) ስለሆኑ ዱላው ሳያገኘኝ ጥያቄዬን ለመጠየቅ ተጋፍቼ ሳበቃ የአንተ ዛሬ አይደለም የሚቀጥለው ሳምንተ ከሰኞ በኃላ ና አሉኝ የሄድኩት ማክሰኞ እለት ነበር (February 19)፡፡

ወደ መስሪያ ቤቱ የሚያስገባው በር ሁለት ሰው እንኩዋን የማያስገባ ነው እናም መረጃ ለማግኘት ወደ ውስጥ መግባት የማይታሰብ ነው፡፡

ቀጥሎም አርብ እለት (February 23) ሄድኩ እንደምንም ተጋፍቼ ስጠይቅ አንድ ጊዜ ረቡህ አንዴ ሃሙስ አለኝ ጥበቃው፡፡

በቀጣይ ስለተጠራጠርኩ ቀደም ብዬ ማክሰኞ (February 26) ሄድኩ ከዛም በዛ ቀን የነበረው ጥበቃ አርብ እለት ነው አለኝ፡፡አርብ ስሄድ(March 01) ስሄድ ሰልፍ ያዝ ተባልኩ፡፡

ሰልፍ ከያዝኩ በኃላ ተሰላፊዎቹን ስጠይቅ የአንተ እኮ ሀሙስ ነበር አሉኝ(February 29)፡፡

መስሪያ ቤቱ ቅጥር ግቢ ላይ ያለ ማስታወቂያ አሳኙኝ ማስታወቂያውን አነበብኩት የተለጠፈው February 23 ነው፡፡ እናም ጥበቃዎች ቢያንስ ተገልጋይ ማስታወቂያ እንዲያይ ቢያደርጉ የሰውን እንግልት ይቀንሳሉ፡፡

እኔ ቤተሰብ አዳማ ስለሆነ መመላለስ እችላለሁ ነገር ግን ከሩቅ ቦታ ለሚመጡ ምን ያህል ከባድ ነው በዚ ላይ የጥበቃዎቹ ዱላ ተጨምሮበት ?

አመሰግናለሁ፡፡ "

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የአዲስ አበባ ፖሊስ " የከንቲባዋ ታናሽ ወንድም እና የከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ነኝ " በማለት ከ4 ግለሰቦች ላይ ከ970 ሺ ብር ያታለለን ተጠርጣሪ መያዙን አሳወቀ።

እንደ ፖሊስ መረጃ ተጠርጣሪው ግለሰብ ታደለ ጌታነህ ይባላል፡፡

በስሙ ግን " ታደለ አቤቤ " እንደሚባል ሐሰተኛ መታወቂያ አዘጋጅቷል።

ይኸው ግለሰብ የግል ተበዳይ አቶ ልዑል ኪሮስን የከንቲባዋ ወንድም እንደሆነ እና መንግስት ለቤት መስሪያ 140 ካሬ ሜትር ቦታ ስለሰጠው ለሊዝ የሚክፍለው 800 ሺ ብር እንዲያበድሩት ይጠይቃል።

የግል ተበዳይም የተባሉትን በማመን 600 ሺ ብሩን አስናቀ ጌታነህ ቀሪውን 200 ሺ ብር ደግሞ በላይ ጣሰው በተባሉት ግብራበሮቹ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ እንዲያደርጉ በነገራቸው መሰረት ብሩን ገቢ ያደርጋሉ፡፡

በተመሳሳይ የማታለያ ዘዴ አቶ ፈለቀ ሃይሉ የተባሉ ግለሰብን በመቅረብ ቤት ለመገንባት 4 ሚሊዮን ብር እንደሚያስፈልገውና 500ሺ ብር ብድር እንዲሰጡት ጠይቆ 105 ሺ ብር መቀበሉን በማስረጃ ማረጋገጡን ፖሊስ ገልጿል።

በተመሳሳይ አዳማ ላይ የተዋወቀቃቸውን አቶ ለገሰ ሲሳይ የተባሉ ግለሰብን ደግሞ " የከንቲባዋ ወንድም ስለሆነኩ በቀላሉ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ መሬት አሰጥሃለሁኝ " ብሎ 10 ሺ ብር ወስዷል።

እንዲሁም ለቤተሰባቸው ' #ፓስፖርት ' ለማውጣት ኢሚግሬሽን ላይ ያገኛቸውን አቶ ፈለቀ ዝናቡ የተባሉ ግለሰብን " የከንቲባዋ ወንድም ነኝ በተጨማሪም እኔም ዳኛ ነኝ ምናልባት ያለ አግባብ የሚያጉላሉህ ካሉ አሳውቀኝ ሰብስቤ አሳስራቸዋለሁኝ " የሚል የማታለያ ቃል በመናገር ጉዳያቸው በፍጥነት እንዲያልቅል 80 ሺህ ብር እንዲሰጠው ጠይቆ 10 ሺህ ብር አታሎ ወስዷል።

ፖሊስ ግለሰቡ ከከንቲባ አዳነች ጋር ምንም አይነት ዝምድና የሌለውና በድለላ ስራ የተሰማራ መሆኑን ገልጿል።

ግለሰቡን ጨምሮ በዚህ ወንጀል ተሳትፎ ያላቸው ሦስት ተጠርጣዎችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራውን መቀጠሉን አዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

#AddisAbabaPolice

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ፓስፖርት

የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ያደረገው የዋጋ ጭማሪ ፦

➡️ አዲስ ፓስፖርት ፦ መደበኛ 5000 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 25 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 20 ሺህ ብር

➡️ የፓስፖርት እድሳት ፦

1ኛ. እድሳት ፦ መደበኛ 5000 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 25 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 20 ሺህ ብር

2ኛ. የፓስፖርት ገጽ ያለቀባቸው ፦ መደበኛ 5000 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 25 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 20 ሺህ ብር

3ኛ. እድሳት የሚፈልጉ እና እርማት የሚያስፈልጋቸው ፦ መደበኛ 12 ሺህ 500 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 32 ሺህ 500 ብር ፤ 5 ቀን 27 ሺህ 500 ብር

4ኛ. ፓስፖርት ቀን ያለው እና ፓስፖርታቸው የተበላሸ ፦ መደበኛ 13 ሺህ ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 33 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 28 ሺህ ብር

5ኛ. ፓስፖርቱ ቀን ያለው ፤ ፓስፖርታቸው የተበላሸ እርማት የሚፈልጉ ፦ መደበኛ 20 ሺህ 500 ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 40 ሺህ 500 ብር ፤ 5 ቀን 35 ሺህ 500 ብር

➡️ የጠፋ ፓስፖርት

1ኛ. የጠፋ ፓስፖርት ፦ መደበኛው 13 ሺህ ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 33 ሺህ ብር ፤ 5 ቀን 28 ሺህ ብር

2ኛ. የጠፋ ፓስፖርት እርማት ፦ መደበኛ 20 ሺህ ብር ፤ አስቸኳይ 2 ቀን 40 ሺህ 500 ብር ፤ 5 ቀን 35 ሺህ 500 ብር

@tikvahethiopia