TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" 4 ሰዎች ወዲያው ሲሞቱ ፤ 18 ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል " - ዶክተር ዑቕባይ ሓጎስ

ዛሬ ህዳር 21/2016 ዓ.ም ጠዋት በትግራይዋ የሓውዜን ከተማ አጠገብ የ4 ሰዎች ህይወት የቀጠፈ ከባድ የመኪና አደጋ አጋጥመዋል።

የሓውዜን ከተማ ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ባለሞያ  ተኽለማርያም ተካ ፤ አደጋው በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ሓውዜን ወረዳ ልዩ ቦታ " ቀያሕታይ " በጭነት ሲኖ መኪናና 5L የህዝብ ማመላለሻ ሚኒባስ መካከል በተፈጠረ ግጭት የተከሰተ ነው ብለዋል።

የሓውዜን ከተማ ዋና ፓሊስ አዛዥ ሻምበል ተኽላይ እንዳሉት ደግሞ ፤ በተለያዩ አቅጣጫዎች ሲጓዙ የነበሩት ሲኖ ትራክ የጭነት መኪናና 5L ሚኒባስ የህዝብ ማመላለሻ በቁልቁለት ቦታ በመጋጨታቸው የተፈጠረ አደጋ ነው። 

የአደጋው መነሻ ምክንያት በመጣራት ያለ ቢሆንም ፍጥነትና በማጠፍያ ቦታ የትራፊክ ህግ ባለማክበር የተከሰተ አደጋ መሆኑ አመላካች መረጃዎች አሉ ፤ ስለሆነም አሽከርካሪዎች መስመራቸው ይዘው በሃላፊነት መንፈስ መንዳት አለባቸው ሲሉ አክለዋል የከተማው ፓሊስ አዛዥ። 

የሓውዜን የፍረሰማእታት ሆስፒታል ሜዲካል ዶክተር ዑቕባይ ሓጎስ አደጋው አስመልክተው በሰጡት ሞያዊ መረጃ ፤ በአሰቃቂ አደጋው 4 ሰዎች ወድያው ሲሞቱ ፤ 18 ሰዎች ከባድና ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ከከተማው ሆስፒታል አቅም በላይ የሆኑት 8 የአደጋው ሰለባዎች ሪፈር ተብለው ዓይደር መቐለ ሆስፒታል እንደተላኩ የገለፁት ሜዲካል ዳይሬክተሩ ፤ የሓውዜን ከተማ ህዝብ የአደጋው ሰለባዎች ለማዳን ያደረገው ያላሰለሰ ጥረት ምስጋና አቅርበዋል።

መረጃው በመቐለ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባል ተዘጋጅቶ የተላከ ነው።

@tikvahethiopia            
ፈጥነው ይመዝገቡ !
=============
የታታሪዎቹ/ቀጠሌዋን የሁለተኛ ዙር የአዋሽ ባንክ የስራ ፈጠራ ውድድር በበርካቶች ጥያቄ መሠረት ምዝገባው እስከ ህዳር 30, 2016 ዓ.ም መራዘሙን እየገለጽን በ Online ማመልከት ለምትፈልጉ በባንኩ ድህረ ገጽ ላይ ማስፈንጠሪያውን በመጫን 👉 https://tatariwochu.awashbank.com
እንዲሁም በአካል ማመልከት ለምትፈልጉ በአቅራቢያችሁ ወደሚገኘው የባንካችን ቅርንጫፎች በመቅረብ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ
ውስጥ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እያሳወቅን ከዚህ በተጨማሪ ከዚህ በታች በአማራጭነት በቀረቡት የመመዝገቢያ ፎርም በመሙላት ማመልከት ይችላሉ፡፡

For English : https://formfacade.com/sm/4W_WcxfNq

For Afaan Oromoo: https://formfacade.com/sm/ABVPRxLmh

For Amharic: https://formfacade.com/sm/KWWld-W-v

https://www.tiktok.com/@awashbank_tiktok
#ኢትዮቴሌኮም

የመጀመሪያዋ ባለ3 እግር ተሽከርካሪ ደብረታቦር ገባች !

ሁለተኛና ሶስተኛ ዙር የጥሪ ማሳመሪያ ዕድለኞች ሽልማታቸውን ዛሬ አስረክበናል!

🎁 1 የ5ጂ ስማርት ስልክ ለአዳማዋ እድለኛ፣
🎁 2 ስማርት ቴሌቪዥኖች ለአዲስ አበባ እና ለአምቦ እድለኞች እንዲሁም
🎁 1 ባለሶስት እግር ተሸከርካሪ ደብረታቦር እድለኛ አስረክበናል!

በተጨማሪም እስከአሁን 2,352 የድምጽ ጥቅል፣ 1,030 የዳታ ጥቅል፣ 30 ዕጣዎች እያንዳንዳቸው የ5000 ብር ዋጋ ያለው የኤሌክትሮኒክ ገንዘብ  ሽልማት ለዕድለኞች አበርክተናል፡፡

አሁንም ወደ 822 ወይም *822# በመደወል አልያም በ www.crbt.et ለአገልግሎቱ ተመዝግበው ሙዚቃዎችን ወይም መንፈሳዊ ዜማዎች እንደገዙ ወደ 645 Y ብለው በመላክ ለሚደርስዎት ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ በመስጠት ዕድልዎን ይሞክሩ!

#ጥሪ_ማሳመሪያ_ጥሪት_ያተርፋል!

#Ethiotelecom #telebirr #RealizingDigitalEthiopia
#ሺርካ

✦ " 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል " - የቲክቫህ ቤተሰብ አባል

✦ " ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር እናቶች ይገኙበታል " - ቃላቸውን የሰጡ ነዋሪ (ለቪኦኤ)

✦ " ጥቃቱን ያደረሰው አሸባሪው ሸኔ ነው " - የኦሮሚያ ክልል ኮሚኒኬሽን (ለቪኦኤ)

✦ " እኛ ንፁሃን ላይ ጥቃት አላደረስንም " - የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት (ለቪኦኤ)

✦ " ባለሞያ መድበን ምርመራ ጀምረናል " - ኢሰመኮ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ


በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ፤ ሺርካ ወረዳ ፤ በተፈጸመ ጥቃት ንጹሐን ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ መሞታቸውን እና የዐይን እማኞችና መልክታቸውን ያደረሱ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጠቁመዋል።

አንድ #የአካባቢው ነዋሪ የቤተሰባችን አባል በላኩልን መልዕክት ፤ " ህዳር 13 /2016 በግምት ከምሽቱ 2:30 አካባቢ ማንነታቸው ባልታወቁ እና በታጠቁ ኢ - መደበኛ ሀይሎች በሽርካ ወረዳ ሶሌ ዲገሉ ጉና እና ጢጆ ለቡ በተባሉ የገጠር ቀበሌዎች በተፈፀመ ጥቃት 11 የአንድ ቤተሰብ አባላት (አያት ፣ ልጅ፣ የልጅ ልጅ ፣ የ 39 ቀን ጨቅላ) ጨምሮ 17 ስዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ሲገደሉ በተመሳሳይ ሰዓት በተፈፀመ በሌላኛው ጥቃት ደግሞ 11 በድምሩ 28 ሰው ሲልፍ ሁለት ህፃናት ደግሞ ቆስለው ህክምና ላይ ይገኛሉ " ሲሉ ገልጸዋል።

ቪኦኤ አማርኛ አገልግሎት ክፍል በጉዳዩ ላይ በሰራው ዘገባ በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ሦስት ቀበሌዎች ሐሙስ ህዳር 13 እና ሰኞ ህዳር 17 ቀን በተፈጸመ ጥቃት #36_ሰዎች መሞታቸውን ገልጿል።

ከሟቾቹ ገሚሶቹ የሁለት ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን በዘገባው ጠቅሷል።

ቃላቸውን የሰጡ አንድ ስሜ አይጠቀስ ያሉ ነዋሪ ፤ " ህዳር 13 ለ 14 አጥቢያ ለቡ በተባለው ቀበሌ ላይ 11 ሰው አንድ ላይ ሰብስበው እነዚህ ታጣቂዎች አንድ ላይ ረሽነዋል። ሶሌ ዲገሉ በተባለው ቀበሌ ደሞ 17 ሰው አስሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው ሰብስበው ረሽነዋል። እነዚህ 17ዱ በአንድ ጉድጓድ 11ቱ በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል። የዚህን ሀዘን ሳንጨርስ እንደገና በሦስተኛው ቀን ለቡ በተባለው ቀበሌ የአንድ ቤተሰብ አባላት 8 ሰዎች ረሽነዋል። እነዚህም በአንድ ጉድጓድ ተቀብረዋል " ሲሉ ተናግረዋል።

ነዋሪው አክለው፤ " ከእነዚህ ከሟቾቹ ውስጥ ከ70 ዓመት አዛውንት እስከ 26 ቀን ህጻን ነፍሰጡር  እናቶች ይገኙበታል" ያሉ ሲሆን " የሦስቱ ቦታ ጥቃቶች በተመሳይ መልኩ ቤት እየገቡ አንድ ቦታ ያሉ ሰዎችን መረሸን ነው። ህጻን የለም አዋቂ የለም ገብተው መረሸን ነው። የአማርኛ ስም ያላቸው፣ የአማራ ስም ያላቸውና የኦርቶዶክስ እምነት አማኝ ላይ ያተኮረ ነው " ሲሉ ተናግረዋል።

ጥቃቱን ማን እንደፈጸመ የተጠየቁት ነዋሪው " ምንም የሚታወቅ ነገር የለም የታጠቁ ኃይሎች ናቸው እከሌ ልንላቸው አንችልም። " ሲሉ ምላሻቸውን ሰጥተዋል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ፣ ለጥቃቱ መንግሥት ' ሸኔ ' እያለ ከሚጠራው (እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን) ተጠያቂ አድርገዋል።

ኃላፊው ለቪኦኤ በሰጡት ምላሽ " በሽርካ ወረዳ ሶሌ ዲገሉ፤ ጢጆ ለቡ፤ ሲላ ዋጂ አሸባሪው ሸኔ ንጹሐን ላይ ጥቃት ፈጽሟል። ከ2 ዓመት ህጻንን እስከ አቅመ ደካማ ሴቶችን ላይ አነጣጥሮ እኔ ባለኝ መረጃ የ27 ሰዎች ህይወት አልፏል " ብለዋል።

አክለውም " ይኼ አሸባሪ ቡድን ባሳለፍነው ሳምንት ቡኖ በደሌ ጨዋቃ ወረዳ ላይ በኢትዮጵያ የጸጥታ አካል በተወሰደበት እርምጃ ብዙ ኃይሉ ሙትና ቁስለጫ በመሆኑ ይሄንን ለመበቀል ብሎ በአርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ይሄንን ጥቃት ፈጽሟል።" ሲሉ ከሰዋል።

በመንግሥት " ኦነግ ሸኔ " የተባለውና ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው የታጠቀ ኃይል ቃል አቀባይ የሆኑት ኦዳ ታርቢ ለቪኦኤ ኦሮምኛ ክፍል በሰጡት ምላሽ ውንጀላውን #አስተባብለዋል፡፡

" እኛ ኃይላችን በተባለው አከባቢ #በሰላማዊ ሰዎች ላይ የወሰደው እርምጃ፤ ያጠፋው የሰላማዊ ሰዎች ህይወትም የለም። ከህዳር 14 - 17 ድረስ በሥርዓቱ ኃይል ብዙ ሰው ተገሏል፤ ብዙ ቤትም ተቃጥሏል። ይህም በምስራቅ አርሲ ሽርካ ወረዳ ነው የተፈጸመው አዛውንቶችም ተገለዋል። ይህንን ለማድበስበስ ነው ጣታቸውን በእኛ ላይ የሚጠቁሙት " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ሓላፊ አቶ ኃይሉ አዱኛ ግን ይህ ኃይል የሚፈጸጸምማቸውን ጥቃት መካድ ባህሪው ነው ሲሉ ገልጸውታል።

አስተያየታቸውን የሰጡን የቲክቫህ ቤተሰቦች ፤ " እዚሁ ወረዳ ከዚህ በፊትም ተመሳሳይ ግድያ እንደነበረ ቢታወቅም በአካባቢው ያሉ የመንግስት ታጣቂዎች ለጉዳዩ የሰጡት ትኩረት አነስተኛ ስለነበር ይህ ሁሉ ሰው ጭካኔ በተሞላበት ሁኔታ ተጨፍጭፈዋል። የአካባቢው ህዝብም በአካባቢው ለመኖር ዋስትና ስለሌለው አካባቢውን ለቆ ለስደት እየተዳረገ ነው፡፡" ሲሉ ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል ፤ ምሥራቅ አርሲ ዞን ፤ ሽርካ ደረሰ ስለተባለው ጥቃት ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ( #ኢሰመኮ ) ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን የኮሚሽኑ የክትትልና ምርመራ ስራ ክፍል ሲኒየር ዳይሬክተር ሚዛኔ አባተ (ዶ/ር)፣ " መረጃ ደርሶናል እያየነው ነው " የሚል አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

" አሁን ላይ በዝርዝር የምናገረው ነገር የለም። ነገር ግን እኛ ጉዳዮች እንደዚህ በሚደርሱን ሰዓት ጉዳዩን የሚከታተል ባለሙያ እንመድባለን፣ በዚህም ምርመራ እናደርጋለን። ያ ነገር የተጀመረ መሆኑን ነው መናገር የምችለው " ሲሉ ገልጸውልናል።

@tikvahethiopia
#ጊዳሚ

በምዕራብ ኦሮሚያ ቄለም ወለጋ ዞን ጊዳሚ ወረዳ ጊዳሚ ከተማ ውስጥ በሚገኘው የመካነ ኢየሱስ ቤተ-ክርስቲያን ጸሎት ላይ የነበሩ ዘጠኝ ሰዎች ተወስደው ተገድለዋል።

ድርጊቱ የተፈፀመው አርብ ኅዳር 14/2016 ዓ.ም. ሌሊት 8 ሰዓት አካባቢ ነው።

የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ የወንጌል እና ቲዎሎጂ ክፍል ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ለሊሳ ዳንዴል ምን አሉ ? (ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ክፍል)

- በቤጊ-ጊዳሚ ሲኖዶስ በጊዳሚ ሰባካ ስር የምትገኘው የሃሞ ቶኩማ አጥቢያ ቤተ-ክርስቲያን የአዳር ጸሎት ላይ የነበሩ የቤተ-ክርስቲያኗ አባላት በታጠቁ ኃይሎች ከተወሰዱ በኋላ ተገድለዋል።

-  ዘጠኙ ሰዎች የተገደሉት ኅዳር 14/2016 ዓ.ም. ሌሊት 8 ሰዓት አካባቢ ከቤተ ክርስቲያኗ ከተወሰዱ በኋላ ነው።

- የቤተክርስያኗ ሽማግሌዎች፣ የወጣቶች ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ሌሎች አገልጋዮችን ጸሎት ላይ ሳሉ ሌሊት ስምንት ሰዓት ላይ በታጠቁ ሰዎች ተወስደዋል።

- ጸሎት ላይ የነበሩትን ምዕመናን ከቤተ ክርስቲያን አውጥቶ የገደለው ታጣቂ ቡድን ማን እንደሆነ ግልጽ አይደለም።

- መገደላቸውን ነው ያረጋገጥነው። ይህን ግድያ ግን ማን እንደፈጸመ እስካሁን አላረጋገጥንም።

- ለሟቾቹ ቤተሰቦች መጽናናትን እንመኛለን፤ ጭካኔ በተሞላበት መልኩ ሕይወታቸውን ላጡ የቤተ ክርስቲያኗ አባላት ፍትሕ እንዲሰጥ መንግሥት ግድያውን እንዲመረምር እንጠይቃልን።

የተገደሉ ሰዎችን በቅርበት አውቃለሁ ያሉና ለደህንነታቸው ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ አስተያየት ሰጪ ደግሞ ተከታዩን ብለዋል (ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ክፍል) ፦

° ዘጠኙ ሰዎች የተገለዱት ከሌሎች መካከል ተመርጠው ከተወሰዱ በኋላ ነው።

° ለቅዳሜ የአምልኮ ሥነ ሥርዓት ዝጅግት ጸሎት ላይ የነበሩት ሰዎች 12 ነበሩ።

° ሁለት ሴቶች እና አንድ በዕድሜ የገፉ አዛውንት እንዲቀሩ ተደርገው ሌሊት 8 ሰዓት ላይ ዘጠኙ ሰዎች ተመርጠው ተወስደዋል።

° ዘጠኙን ሰዎች በመውሰድ የገደለው ማን እንደሆነ አላውቅም። ግን ሟቾቹ በሙሉ ምንም ዓይነት ፖለቲካዊ ተሳትፎ የሌላቸው ናቸው።

° የተገደሉት የቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች እንጂ ምንም አይነት የፖለቲካ ተሳትፎ የላቸውም።

ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ የሟች ቤተሰቦች የሚሉት ካለ እንዲሁም ደግሞ በአካባቢው ላይ የሚንቀሳቀሱት የመንግሥት ሆነ የOLF-OLA ኃይሎች የሚሰጡት ምላሽ ካለ ተከታትለን እናቀበርባለን።

@tikvahethiopia
#AddisAbaba #እድታውቁት

" ነገ ህዳር 22 ቀን 2016 ዓ/ም የመሬት ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመሮች ጥገና ስለሚከናወን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉና በከፊል ይቋረጣል " ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳውቋል።

የመሬት ውስጥ የኤሌክትሪክ መስመሮች ጥገና የሚከናወነው ከጧቱ 12፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ እንደሆነ አገልግሎቱ ገልጿል።

በዚህም ፦
-  ሜክሲኮ ደብረወርቅ ሕንጻ፣
- ለገሐር ጀርባ፣
- ለገሐር አሸዋ ተራ፣
- ኤግዝቢሽን ሴንተር፣
- ፍላሚንጎ፣
- ኦሎምፒያ፣
- ደንበል፣
- ደንበል ጀርባ፣
- ፐርፕል  ካፌ፣
- ቦሌ ማተሚያ ቤት፣
- ተወካዮች ምክር ቤት መኖሪያ፣
- ፒኮክ መናፈሻ፣
- አስቴር ቡና፣
- ልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣
- ኮካኮላ፣
- ኢዩበልዩ ቤተ መንግስ፣
- ኢትዮጵያ ሆቴል፣
- ኢቢሲ፣
- ቤተዛታ ሆስፒታል፣
- ኦሮሚያ ባሕል ማዕከል ጀርባ፣
- ጊዮን ሆቴል፣
- እስጢፋኖስ ድልድይ አካባቢ፣
- ኃይለ ዓለም ሕንጻ እና አካባቢዎቻቸው የኤሌክትሪክ ኃይል ሙሉ በሙሉና በከፊል እንደሚቋረጥ ተገልጿል።

" ደንበኞች አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ " ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኤሌክትሪክ አገልግሎት አሳስቧል።

@tikvahethiopia
ሰላም ሚኒስቴር ምን አለ ?

* ጋዜጠኞች ምላሽ እንዳይሰሙ እንዲወጡ ተደርጎ ምላሽ በዝግ ተሰጥቷል።

የሰላም ሚኒስቴር የ2016 ዓ.ም የ3 ወራት እቅድ አፈፃፀሙን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ዛሬ አቅርቦ ነበር።

የሰላም ሚኒስቴር ባቀረበው ሪፖርት፦
- የጎሣ ግጭቶች #ስለመቀነሳቸው
- በክልሎች ውስጥ እንጂ፣ በክልሎች መካከል የሚደረግ ግጭትም እየቀነሰ ስለመሆኑ አስታውቋል።

ከቋሚ ኮሚቴው ግን ብዙ ጥያቄዎች ቀርበው ነበር። 

በኢትዮጵያ ውስጥ በንፁሐን ላይ ጉዳት እየደረሰ፤ እየሞቱ፤ እየታገቱ ገንዘብ እየተጠየቀባቸው ስለመሆኑ እንዲሁም የሕዝብ የመንቀሳቀስ መብት እየተገደበ ፣ መንገድም የተዘጋባቸው አካባቢዎችም ያሉ መሆናቸው ተነስቶ ችግሩን ለመፍታት የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ምን ሠሩ ? የሚሉ ጥያቄዎች ቀርበው ነበር። 

ግጭቶች መታየት እና የታጠቁ ኃይሎች ሕግን የመጣስ፣ ሰላምን የማደፍረስ ምክንያት ፤ በንፁሃን ዜጎች ሕይወት፣ ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱ፣ ንፁሃን እየታገቱ ገንዘብ እየተጠየቁ ስለመሆኑ ሚኒስቴር መ/ቤቱ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቋል።

ለሚኒስቴሩ አመራሮች ሌሎች ጥያቄዎችም ቀርበው ነበር።

" ኢትዮጵያ ውስጥ የሚነሱ ግጭቶች በተለይ አሁን አማራ ክልል ያለው ፣ ኦሮሚያ ክልል አንዳንድ አካባቢዎች ያለው ጉዳይ ከግጭትም አልፎ የውስጥ የትጥቅ ግጭት-ከዚያም ሲያልፍ ወደ የእርስ በርስ ወደሚመስል ነገር የሚሄዱ ነገሮች ናቸው የሚመስሉት " የሚል ጥያቄ ተነስቷል።

በአማራ ክልል ያለውን ግጭት በተመለከተ ግጭቱን #አመላካች ነገሮች አልነበሩም ወይ ? በሚል የግጭት ቅድመ መከላከል ላይ ምን ተሰራ የሚል ጥያቄም ቀርቦ ነበር።

ለዚህና ለሌሎች የቀረቡ ዋና ዋና ጥያቄዎች የሰላም ሚኒስቴር የሥራ ኃላፊዎች የሰጡት ምላሽ ምን እንደሆን እንዳይከታተሉ ጋዜጠኞች የሰላም ሚኒስቴርን ሪፖርት እና የቋሚ ኮሚቴውን ጥያቄዎች ብቻ ታድመው እንዲወጡ በሕ/ተ/ም/ቤት የውጭና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በመታዘዙ ምላሹን ምን እንደነበር አልታወቀም።

ለምን ይህ ለምን ይሆናል ? ተብሎ ለቀረበው ጥያቄ " በዝግ የሚደረግ " መሆኑን ከመግለጽ በቀር ዝርዝር ማብራሪያ አልተሰጠም። 

የሰላም ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ታየ ደንደአ ከቋሚ ኮሚቴው ለተነሱ ጥቂት ጥያቄዎች ለመገናኛ ብዙኃን አጭር ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ታዬ ምን አሉ ?

- መገናኛ ብዙሃን የሚኒስቴሩን ምላሽ እንዳይዘግቡ ተቋማቸው አለመከልከሉን ገልጸዋል።

- በአማራ ክልል ያለው ጦርነት ሊከሰት እንደሚችል ቅድመ ትንተና እንደነበር፣ ሆኖም ግን " በሚመለከተው " ባሉት በግልጽ ባልጠቀሱት አካል ፋጣን ርምጃ ባላመውሰዱ እዚህ ደረጃ ላይ መድረሱን ገልፀዋል።

-  የአማራ ክልል ጉዳይ- " የተ/ም/ቤት ጭምር ሄዶ ህዝብ ባነገረትበ ጊዜ እንደዚህ አይነት አዝማሚያዎች መኖራቸው ቀድም ብሎ ተለይቶ ነበር። ግን ችግሮችን ከመፍታትና አፋጣኝ ምላሽ ከመስጠት አኳያ በሚመለከታቸው አካላት የፍጥነትና የቅንጅት ችግር ስለሚታይ እዚህ ደረጃ ደርሷል " ብለዋል።

- መንግሥት ከሕወሓት ጋር እንዲሁም ከኦነግ ሸኔ ጋር የዘለቀበትን ግጭት ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት በበጎ ጠቅሰዋል። በአማራ ክልል ያለውም በዚያው መንገድ " ሊታይ ይችላል የሚል እምነት " እንዳላቸው ገልፀዋል።

- " በመንግሥትም በኩል ረጅም መንገድ ሄዶ፣ በሌላ ወገን ያለውም ያለበት መንገድ አዋጭ እንዳልሆነ በማመን መሀል መንገድ ላይ መነጋገር ያስፈልጋል ተብሎ አቅጣጫ ተሰጥቶ በዛ ደረጃ እየተሰራ ይገኛል የአማራ ክልልም ጉዳይ በዚሁ ማዕቀፍ ሊታይ ይችላል የሚል እምነት አለኝ " ሲሉ ተናግረዋል።

Credit - DW RADIO / ሰለሞን ሙጬ

@tikvahethiopia
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ

ለስኬትዎ ብርቱ አጋር ነን!

የቴሌግራም ገፃችንን ይጎብኙ: https://publielectoral.lat/Globalbankethiopia123

#globalbankethiopia #bankinEthiopia #financeinEthiopia
M-PESA መጣልን! 

ከንግድ ባንክ፣ ከአቢሲኒያ ባንክ፥ ከዳሽን ባንክ፣ ከአዋሽ ባንክ እና ከአባይ ባንክ አካውንትዎ ወደ M-PESA አካውንትዎ እንዲሁም ከM-PESA አካውንትዎ ወደ ባንክ አካውንትዎ ገንዘብ በቀላሉ መላክና መቀበል ይችላሉ።

ፕለይ ስቶር/ አፕ ስቶር https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia     

#MPESASafaricomET #FurtherAheadTogether