TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#አክሱም የአክሱም ህዳር ፅዮን በዓልና የቱሪስት እንቅስቃሴ ምን ይመስላል ?  አክሱም ከተማ ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም አመታዊ የህዳር ፅዮን በዓለ ንግስ ታከብራለች። አክሱምና ዙሪያዋ ለአገር ውስጥና ውጭ  ጎብኚዎች የሚማርኩ በርካታ ቅርሶች የሚገኙባት በኢትዮጵያ ካሉ ታላላቅ የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎች አንዷ ነች። የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አባል ከአውዳሚው ጦርነት በኃላ የአክሱምና ዙሪያዋ…
"  ምእመናንና ቱሪስቶች በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ባጋጠመው ድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ባላቸው አቅም ያግዙ " - የአክሱም ከንቲባ

አክሱም እንግዶቿን አክብራ እየተቀበለች ነው።

የህዳር ፅዮን በዓል ለማክበር ወደ አክሱም የሚሄድ ሰው በቆየው ትውፊት መሰረት በወጣቶች እግሩ እንዲታጠብ ይደረጋል። ይህ ተግባር የእንግዳ ተቀባይነት መገለጫ ነው። 

የዘንድሮ የህዳር ፅዮን በዓል ለማክበር ወደ አክሱም ያቀኑ እንግዶች በአራት አቅጣጫ ለፅዮን ክብር ሲባል በወጣቶች በተዘጋጀው የእግር አጠባ እየተደረገላቸው ሲገቡ ውለዋል።

አክሱም ከጦርነቱ በኃላ የተሻለ በዓል ለማክበር ተዘጋጅታለች የሚሉት የከተማዋ ከንቲባ አቶ አበበ ብርሃነ፤ መንፈሳዊ በዓሉ ለማክበር የሚመጡት ምእመናንና ቱሪስቶች በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ባጋጠመው ድርቅ የተጎዱ ወገኖች ባላቸው አቅም የመርዳት ሰብአዊ ሃላፊነት አንዳለባቸው ገልጸዋል።

በተያያዘ መረጃ ከአክሱም በ60 ኪሎሜትር ርቀት በሽረ እንዳስላሰ ከተማ በሚገኘው የሜጀር ሐየሎም አርአያ አውሮፕላን ማረፍያ በኩል ለሚገቡ እንግዶች የአቀባበል ስነ-ስርዓት ሲከናወን ውሏል።

የአቀባበል ስነ-ስርአቱ በሽረ ከተማ  አስተዳደር መሪነትና አስተባባሪነት የተካሄደ ሲሆን የሽረ የከተማ ነዋሪ እንግዶቹ በደስታ ተቀብሎ ወደ አክሱም ሲሸኙ ውለዋል።

የህዳር ፅዮን በዓል ከመቐለና ሽረ አውሮፕላን ማረፍያዎች ወደ  አክሱም እንግዶች ለሚያጓጉዙ የመኪና ባለቤቶች ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ሆኖ መመልከቱን የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

የፎቶ ባለቤት ፦ DW TV

@tikvahethiopia            
#CBE

ነጋዴ ነዎት?

እንግዲያውስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መርቻንት አፕ (Merchant APP) ተጠቅመው ክፍያዎትን ይቀበሉ።
==========

መርቻንት አፕ ነጋዴዎች ወይም የሽያጭ ባለሙያዎች ለሸጡት እቃ ወይም አገልግሎት ክፍያ የሚቀበሉበት የሞባይል መተግበሪያ ነው፡፡

መተግበሪያውን ከ https://play.google.com/store/apps/details?id=prod.cbebirr.merchantapp አውርደው በመጫን ባቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ይመዝገቡና መለያ ቁጥር (Till No.) ይውሰዱ ። ከዚህ በፊት መለያ ቁጥር (Till No.) ወስደው ከሆነ በቀጥታ መተግበሪያው ላይ ይመዝገቡ፡፡

አጠቃቀሙ

1. መተግበሪያውን ከፍተው የደንበኛውን ስልክ ቁጥር በማስገባት ክፍያውን ያስጀምሩ፣

2. ገዥው የነጋዴውን መለያ ቁጥር (Till No.) እና የክፍያውን መጠን የያዘ መልእክት ስልኩ ላይ ይደርሰዋል። ትክክለኛነቱን አረጋግጦ የሚስጥር ቁጥሩን (PIN) በማስገባት ክፍያውን ያከናውናል፡፡

3. የክፍያ ማረጋገጫ መልዕክት ይደርስዎታል። አለቀ፡፡
" ... ክልሎች ትኩረት እና የተሻለ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ' ይህንን ያህል ሰዎች ሞተውብኛል፣ ይህንን ያህል ተጎድተውብኛል ' የሚል መረጃ ያቀርባሉ " - አቶ አታለል አቡሃይ

የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከፍተኛ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ አታለል አቡሃይ ከሪፖርተር ጋዜጣ ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሯቸው ፦

- በአገር አቀፍ ደረጃ በድርቅ፣ በጎርፍና በግጭት ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች ትኩረት እንዲያገኙና የተሻለ ድጋፍ እንዲኖራቸው፣ ክልሎች የተጎጂዎችን ቁጥር #በማጋነን ያቀርባሉ።

- ክልሎች ትኩረት ለማግኘትና የተሻለ ድጋፍ ለማግኘት ሲሉ ' ይህንን ያህል ሰዎች ሞተውብኛል፣ ይህንን ያህል ተጎድተውብኛል '  የሚል መረጃ ይሰጣሉ።

- እስካሁን ሁሉም ክልሎች ' ይህንን ያህል ሰዎች ሞተውብኛል ' ብለው ለኮሚሽኑ ሪፖርት አላቀረቡም። የቅድሚያ ቅድሚያ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልገናል ብለው ለላኩ ክልሎች አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገን ነው።

- የዓለም የምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ ሌሎች ለጋሽ ድርጅቶች ዕርዳታ መስጠት ካቆሙበት ጊዜ ጀምሮ፣ መንግሥት በራሱ አቅም ያለውን ክምችት በመጠቀም አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ ለሚፈልጉ ክልሎች አሰራጭቷል። (7.9 ቢሊዮን ብር የሚያወጡ ግብዓቶች ድጋፍ ተደርጓል)

- በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ 7.3 ሚሊዮን ሰዎች የቅድሚያ ቅድሚያ የምግብ ዕርዳታ ያስፈልጋቸዋል። እስካሁንም ለእነዚህ ሰዎች በሁለት ዙሮች የምግብና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል።

(በአጠቃላይ 7.3 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ ድጋፍ ይሻሉ)

* በአማራ ክልል ለ1.8 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በድርቅ የተጎዱ ናቸው።

* በትግራይ ክልል ሰሜን ምዕራብ፣ ማዕከላዊና ደቡብ ምሥራቅ ዞኖች የሚገኙ 981 ሺሕ ሰዎች በድርቅ ምክንያት ትልቅ ችግር ውስጥ ይገኛሉ።

* በአፋር ክልል ዞን አንድ፣ ዞን ሁለት፣ ዞን ሦስት፣ ዞን አራትና ዞን አምስት የሚገኙ 225 ሺሕ ሰዎች ለከፍተኛ ረሃብ የተጋለጡ ናቸው።

- በድርቅ፣ በጎርፍና በሌሎች ችግሮች የተጎዱ የማኅበረሰብ ክፍሎች ድጋፍ እንዲያገኙ የሚንቀሳቀሱ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ መንግሥት የሚከተለውን አሠራር ተከትለው ከሠሩ አብሮ ለመሥራት ዝግጁ ነን።

- በተለያዩ ጊዜያት ከክልሎች ጋር ተከታታይ ስብሰባ ስናደርህ ይህንን " ያህል ሰዎች ሞተውብኛል " በማለት ያነሳ ክልል የለም። ብዙ ጊዜ ጉዳዩን ለሌላ አጀንዳ ይጠቀሙበታል።




በኢትዮጵያ በተለያዩ ክልሎች በድርቅ፣ በጎርፍ እና እንዲሁም ከቄያቸው ተፈናቅለው የሚገኙ ወገኖች ድጋፍ ባለማግኘታቸው በራሃብ ህይወት እጠፋ መሆኑን መነገሩ ይታወቃል።

ለአብነት ከሰሞኑን በትግራይ ክልል ድርቅ በከፋባቸው ወረዳዎች በረሃብ ምክንያት የሰዎች ህይወት ስለመጥፋቱ በርካቶችም ለልመና መውጣታቸው፣ ተማሪዎችም መበተናቸው መነገሩ አይዘነጋም።

በተጨማሪ ከኦሮሚያ ክልል ማንነትን መሰረት ባደረግ ጥቃት ተፈናቅለው አማራ ክልል ቻግኒ በየጅምር ፎቅ እና ቤት ፍርስራሽ ስር የሚገኙ ከ2000 በላይ ተፈናቃዮች እርዳታ ከተደረገላቸው ወራት ማለፉን ፣ የህፃናትን ጨምሮ የአዋቂዎች ህይወት መጥፋቱን ተፈናቃዮች ሪፖርት ማድረጋቸውና የከተማው አስተዳደርም ለበላይ አካላት ሪፖርት ማድረጉ መዘገቡ አይዘነጋም።

ከዚህ ባለፈ በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በራሃብ ምክንያት ሰዎች መሞታቸው፣ የሚበላ የሚቀመስ መጥፋቱን የቀበሌና ዞን አመራሮች ማሳወቃቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Amhara በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከ2ኛ እስከ 6ኛ ዓመት የህክምና ተማሪዎች ከትምህርት ውጪ ከሆኑ ረጅም ግዜ እንደሆናቸው በመግለፅ መፍትሔ እንዲፈለግላቸው ጥሪ አቀረቡ። ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላኩት መልዕክት በአማራ ክልል በተፈጠረው ችግር ለሦስት ወራት (ለ12ኛ ክፍል ፈተና 1 ወርን ጨምሮ) ቤት መቆየታቸውን ገልጸዋል። "እስካሁን ማንም ስለእኛ የሚናገር…
" መፍትሄ ሳይሰጠን የዓመቱ አራተኛ ወር ሊገባ ነው " - ተማሪዎች

በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እስካሁን ለተማሪዎቻቸው ጥሪ አላደረጉም።

ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ያልጠሩት በክልሉ ባለው ተለዋዋጭ የፀጥታ ሁኔታ ምክንያት እንደሆነ ይታመናል።

በክልሉ በሚገኙት ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች ጊዜው ሳይሄድ መፍትሄ እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርቡም እስካሁን መፍትሄ የሚሰጥ ቀርቶ ጉዳዩን አንስቶ በግልፅ ማብራሪያ የሚሰጥ አካል እንዳጡ ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በሚገኙ 10 ዩንቨርሲቲዎች የሚማሩት ተማሪዎች " ያለ ትምህርት ቁጭ ብለን ወራት አልፈዋል ፤ ፍትህ እንሻለን " ብለዋል።

መፍትሄ ሳይሰጣቸው የአመቱ አራተኛ ወር መዳረሱን ገልጸዋል።

" ስለእኛ ጉዳይ ጀርባ ተሰጥቷል " ያሉት ተማሪዎቹ " ከትምህርት ገበታችን ከራቅን 5ኛ ወራችን ላይ እንገኛለን " እስካሁን ከሚመለከትው አካል የተሰጠ ቁርጥ ውሳኔ የለም ይህ ደግሞ ተማሪዉን ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የስነ ልቦና ጫናና ጭንቀት እንዲገባ እያደረገውን ነው " ሲሉ አስረድተዋል።

" ህልም አለን ተስፋችንን አታጨልሙብን ትምህርታችንን እንደ እኩዮቻችን የምንከታተልበት መንገድ ፈልጉልን " ሲሉ ጥሪ ያቀረቡት ተማሪዎቹ " በእነሱ የትምህርት ጉዳይ ምክንያት ወላጅም እየተጨነቀ መሆኑን አስረድተዋል።

ቃላቸውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰጡ አንዳንድ ወላጆች በበኩላቸው ምንም እንኳን የአማራ ክልል ሁኔታ እና ህዝቡ በፀጥታ ችግር እያሳለፈ ያለውን አሰቸጋሪ ሁኔታ ቢረዱም ልጆቻቸው ያለ ትምህርት መቀመጣቸው ከምንም በላይ ቀጣይ መፍትሄ አለመታወቁ እንደሚያስጨንቃቸው ገልጸዋል።

ቢያንስ በጉዳዩ ላይ ትምህርት ሚኒስቴር ግልጽ የሆነ ማብራሪያ ወጥቶ መስጠት አለበት ፤ መፍትሄ ካለውም ማሳወቅ ይገባዋል ፤ ልጆቻችን የሀገር ተረካቢዎች በሰሜኑ ጦርነት ወቅት የነበረው ዕጣ ፋንታ እንዲደርሳቸው አንፈልግም ብለዋል።

ሌሎች ወላጆች በበኩላቸው ከምንም በፊት " ሰላም እና ደህንነት ይቀድማል ሰላም በሌለበት ሰው በየቀኑ በሚሞትበት ፣ ዛሬም ነገም የግጭት ስጋት ባለበት ሁኔታ ትምህርት ማማር አይደለም ፤ ለደቂቃ ቁጭ ብሎ ማሰብ አይቻልም ፤ ስለሆነም የሰላሙ ሁኔታ እስካልተረጋገጠና ለልጆች ደህንነት ሙሉ ዋስትና እስከሌለ ጥሪ ቢደረግ እንኳን አንልካቸውም " ብለዋል።

ከምንም በፊት የሚቀድመው ለተከታታይ አመታት በጦርነትና ግጭት ውስጥ እያለፈ የሚገኘው የአማራ ህዝብ ሰላሙን አግኝቶች እፎይ እንዲል ጥሪ ማድረግና ድምፅ ማሰማት ነው ብለዋል።

ምን አይነት መፍትሄ አለው ? ለሚለው ጥያቄችንም ጦርነት እና ግጭት በዘለቄታዊ መንገድ በንግግር ተፈቶ በቅድሚያ ህዝቡ ሰላም እንዲያደገኝ እንዲደረግ ፤ ሰላም ከተረጋገጠ በኃላ ተማሪዎችን መጥራት ፤ እስከዚያው ግን አመቱ እንዳይገፋ በሌሎች ተቋማት ገብተው እንዲማሩ ቢደረግ ብለዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎችን እና የወላጆችን ቅሬታ አስመልክቶ ትምህርት ሚኒስቴርን ለማነጋገር ሰፊ ጥረት የሚያደርግ ይሆናል።

@tikvahethiopia
25 ዓመታት በሕብረት

ሕብረት ባንክ
በሕብረት እንደግ !

ቴሌግራም- https://publielectoral.lat/HibretBanket
ፌስቡክ፦ https://www.facebook.com/HibretBank
ሊንክዲን- https://www.linkedin.com/company/hibretbank/
ዌብሳይት- https://www.hibretbank.com.et/
#Hibretbank
TIKVAH-ETHIOPIA
"  ምእመናንና ቱሪስቶች በተለያዩ የትግራይ አከባቢዎች ባጋጠመው ድርቅ የተጎዱ ወገኖችን ባላቸው አቅም ያግዙ " - የአክሱም ከንቲባ አክሱም እንግዶቿን አክብራ እየተቀበለች ነው። የህዳር ፅዮን በዓል ለማክበር ወደ አክሱም የሚሄድ ሰው በቆየው ትውፊት መሰረት በወጣቶች እግሩ እንዲታጠብ ይደረጋል። ይህ ተግባር የእንግዳ ተቀባይነት መገለጫ ነው።  የዘንድሮ የህዳር ፅዮን በዓል ለማክበር ወደ አክሱም ያቀኑ…
ፎቶ፦ የ2016 ዓ/ም የአክሱም ፅዮን ንግስ በዓል እጅግ በድመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

የዘንድሮው በዓል ጦርነት እንዲቆም የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ ሁለተኛው ሲሆን ካለፈው አመት የበለጠ ቁጥር ያለው ምዕመን በዓሉን መታደሙ ተነግሯል።

ወደ ከተማው የገቡ ቱሪስቶችም ካለፈው ዓመት የተሻለ ነው።

የፎቶ ባለቤቶች ፦ ሚካኤል መታፈሪያ እና ትግራይ ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሶማሌክልል በሶማሌ ክልል በተከሰተው የጎርፍ አደጋ እስካሁን 28 ሰዎች ሲሞቱ ከ300,000 በላይ ሰዎች መፈናቀላቸው ተጠቆመ። በሶማሌ ክልል ከ33 ወረዳዎች በላይ ተከሰተ የተባለውን የጎርፍ አደጋ በተመለከተ ተጎጂዎችና ተፈናቃዮች በምን ሁኔታ እንደሚገኙ ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው እርዳታ እያደረገ የሚገኘውን Save the Childrenን ጠይቋል። የድርጅቱ ምሥራቅ ኢትዮጵያ ዳይሬክተር አቶ አብዲራዛቅ…
#ሱማሌ_ክልል

" እስካሁን ከ700 በላይ ሰዎች በኮሌራ ተጠቅተዋል። 23 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። ከ23ቱ ወደ 11 የሚሆኑት #ህፃናት ናቸው " - አቶ አብዲሪዛቅ አህመድ

በሱማሌ ክልል በሚገኙ ተፈናቃዮች ላይ የከፋ ኮሌራ ወረርሽኝ መከሰቱን፣ ወረርሽኙን ለመከላከል የመድኃኒት እጥረት ፈተና በመሆኑ ርብርብ ካልተደረገ ከ500,000 በላይ ተፈናቃዮች በወረርሽኙ የመጠቃት ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን ሴቭ ዘ ችልድረን (Save the children) የሱማሌ ክልል ቅርንጫፍ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

የሱማሌ ክልል ሴቭ ዘ ችልድረን ቅርንጫፍ ዳይሬክተር አቶ አብዲሪዛቅ አህመድ ምን አሉ ?

- እስካሁን #ከ700 በላይ ሰዎች በኮሌራ ተጠቅተዋል። 23 ሰዎች መሞታቸው ተረጋግጧል። ከ23ቱ ወደ 11 የሚሆኑት ህፃናት ናቸው። ከ700ዎቹ ተጠቂዎች መካከል 319ኙ ህፃናት ናቸው።

- በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ምክንያት ብዙ መጸዳጃ ቤቶች ወድመዋል። የተፈናቀሉ ሰዎች መጸዳጃ ቤት የላቸውምና ይሄ ሁኔታ በጣም አሳሳቢ ሆኗል። ተፈናቃዮቹ የሚኖሩበት ቤት የላቸውም።

ኮሌራ የተከሰተው መቼ ነው ?

- ኮሌራ ከተከሰተ ከሁለት እስከ ሦስት ወራት አስቆጥሯል። ሆኖም ግን ዝናብ መዝነብ ከጀመረ በኋላ ነው ኬዞቹ በጣም እየበዙ የመጡት።

- ሕክምና ካላገኙ #ይሞታሉ። ኮሌራ በጣም መጥፎ ተላላፊ በሽታ ነው። መድኃኒት እንዴት ይገኛል የሚለው ግን አሁንም አጠያያቂ ጥያቄ ነው። 

- በተለይ ቀላፎ ወረዳ መንገዱ ስለተጎዳ አክሰስ የለም፣ የመድኃኒት እጥረት ሲያጋጥም ለማድረስ እንኳ ለትራንስፖርት ያስቸግራል። ተፈናቃናቃዮቹ በጠባብ መጠለያ ውስጥ ከአሥር ሰዎች በላይ ሆነው ተጣበው ነው የሚኖሩት። መጸዳጃ ቤት የላቸውም፣ ኮሌራው የመዛመት ዕድሉ ከፍተኛ ነው።

በጎርፍ ሳቢያ የተፈናቃዮችና የተጎጂዎች ቁጥር  ጨመረ ወይስ ቀነሰ ?

-የተፈናቃዮች ቁጥር ከ300,000 ወደ #500,000፣ የተጎጂዎች ቁጥር ከ600,000 ወደ #1.4 ሚሊዮን ደርሷል። ካሉበት ቦታ እስከመቼ እንደሚቀመጡ አይታወቅም፣ ምክንያቱም ጎርፉ እስካሁን እንደቀጠለ ነው።

- ከእነዚህ ተጎጂዎች መካከል እስካሁን ድጋፍ ያገኙት #10 በመቶዎቹ ብቻ ናቸው። ቀሪዎቹ #90 በመቶዎች አፋጣኝ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል።

- የጎርፍ አደጋው እስካሁን እየተስፋፋ ነው። ብዙዎች እየተጎዱና እየተፈናቀሉ ነው።  ሰሞኑን ዝናቡ ስለቀነሰ ምናልባት ከዚህ በኋላ አደጋው ሊቀንስ ይችላል የሚል ተስፋ አለ።

ምን ተሻለ ?

ከፍተኛ የሆነ እንቅስቃሴ ስላለ ማኅበረሰቡ የሚዛመትበትን መንገድ እንዲያውቅ አዌርነስ እንዲፈጠር፣ መድኃኒትና ነርስ በቂ ስላልሆነ እንዲጨመር፣ ኬዙ ያለባቸው ቦታዎች ኮሌራ ትሪትመንት ሴንተር እንዲገነባ፣ የታመመ ሰው ቶሎ ወደ ሆስፒታል እንዲደርስ የሚያስችል ቲም እንዲቋቋም አቶ አብዲሪዛቅ ጠይቀዋል።

የተከሰተው ኮሌራ ዋና ምንጩ ምን እንደሆነ መለየትና በአፋጣኝ ከምንጩ ማድረቅ ዋነኛው ተግባር መሆን እንዳለበት ጠቁመው፣ ንጹህ የውሃ ችግር ስላለ ተፈናቃዮች የተበከለ ውሃ እንዳይጠቀሙ የውሃ ሳኒታይዘር እንደሚያስፈልግም አክለዋል።

ድጋፍ ካልተገኘ በቀጣዮቹ ሳምንታት ብዙ ሰዎች ሊሞቱ ይችላሉ ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ችግሩ ሰፊና የከፋ፣ ከመንግሥት አቅም በላይ ስለሆነ አለም አቀፍ ኤጀንሲዎች ጋር ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃውን የላከው የአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ነው።

@tikvahethiopia