TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ትግራይ

" መንግስት የማያውቀው ፤ የህዝብ ሃብት በማባከን ከቀበሌ እስከ ዞን ስብሰባ መጥራት ምክንያቱ ግልፅ አይደለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

በትግራይ የተጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ።

ፕረዚደንቱ ዛሬ ጥቅምት 16 /2016 ዓ.ም በፅህፈት ቤታቸው በኩል ባወጡት መግለጫ ፤ " የተሰው ታጋዮች መርዶ በተነገረበት ማግስት ያሉ የመንግስት ስራዎች ወደ ጎን በመተው መንግስት የማያውቀው የህዝብ ሃብት በማባከን ከጥቅምት 14/2016 ዓ.ም ጀምሮ ከቀበሌ እስከ ዞን ስብሰባ መጥራት ምክንያቱ ግልፅ አይደለም " ብለዋል።   

የሰብሰባው ዋነኛ ተሳታፊ በየደረጃው ያሉ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዎች ሲሆኑ ፣ መንግስትና ህዝብ የሰጣቸው ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው በራሳቸው መንገድ በሄዱ ሃላፊዎች እርምጃ ተወስዷል፤ የተጀመረውም ህግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ አረጋግጠዋል። 

እነዚህ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዎች ህዝብ በማስተባበር  ያጋጠመን ችግር መፍታት ትተው ወደ መቐለ በመምጣት መንግሰት የማያውቀው ስብሰባ ማካሄድ አላማው ግልፅ እንዳልሆነ ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ጨምረው ገልፀዋል።  

ለስብሰባው በተደረገው ጥሪ " በአንዳንዱ አከባቢ ስንቃቸውን ይዘው እንዲመጡ " መነገሩን የገለፁት አቶ ጌታቸው ፤ የመንግስት አሰራር ጥሰው በተገኙ ሃላፊዎች በተወሰደው እርምጃ ምክንያት የአመራር ክፍት እንዳይፈጠር ማስተካከያ እርምርጃ እየተወሰደ ነው ብለዋል። 

" አሁን ያጋጠመው ችግር ለማስተካከል ሰራዊቱ ፣ ድርጅቱ ህዝቡ በማንቀሳቀስ ይሰራል " ያሉት ፕረዚደንቱ " ሁሉም ነገር በህግና አሰራር ብቻ መከናወን ይገባል " ብለዋል። 

" በየደረጃው የሚገኝ የመንግስት አካል ህዝብና መንግስት የሰጠው ሃላፊነት በአግባቡ በመወጣት ህዝብ የሚጠቅም ስራ መስራት አለበት " ያሉት አቶ ጌታቸው ረዳ " ይህንን ለማደናቀፍ በሚሞክር ማንኛውም አካል ጥንካራ ህግ የማስከበር እርምጃ ይወሰዳል " ማለታቸው የጊዜያዊ አስተዳደሩም ፕረዚደንት ፅህፈት ቤት መግለጫ በመጥቀስ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል። 

ፕረዚደንት ጌታቸው ረዳ ጥቅምት 15 /2016 ዓ.ም ጊዚያዊ አስተዳደሩ በማያውቀው እንቅስቃሴ ተገኝተዋል ያሉዋቸውን 6 የክልሉ ዞኖች የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዎች በደብዳቤ ከስራ አስነብተዋቸዋል።
                   
@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ትግራይ " መንግስት የማያውቀው ፤ የህዝብ ሃብት በማባከን ከቀበሌ እስከ ዞን ስብሰባ መጥራት ምክንያቱ ግልፅ አይደለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ የተጀመረው ህግ የማስከበር እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ገለፁ። ፕረዚደንቱ ዛሬ ጥቅምት 16 /2016 ዓ.ም በፅህፈት ቤታቸው በኩል ባወጡት መግለጫ ፤ " የተሰው ታጋዮች መርዶ በተነገረበት…
#ትግራይ

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በፅሁፍና ለትግራይ ቴሌቪዥን በድምፅ በሰጡት መግለጫ ፤ " ለነገና እና ለነገ በስቲያ (ጥቅምት 17 እና 18 /2016 ዓ.ም) የሚካሄድ የካድሬ ስብሰባ የለም ፤ የተጠራውም ህጋዊ አይደለም " ብለዋል።

የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በበኩላቸው ለቅዳሜና እሁድ የተጠራው የካድሬዎች ሰብሰባ እንደሚካሄድ በፃፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል።

ብዙዎች በጊዚያዊ አስተዳደሩና በህወሓት መካከል እየተፈጠረ ያለው ልዩነት እንዳሳሰባቸው ሰጋታቸው  በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።

" ልዩነቱ ወዴት ያመራ ይሆን ? " ብለው በመጠየቅ ላይም እንደሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Update

ኢትዮጵያ #ድምፀ_ተአቅቦ ያደረገችበት የተመድ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባኤ ተካሄደ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ዓርብ ምሽት በእስራኤል እና ሃማስ የጋዛ ጦርነት ጉዳይ  አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ አካሂዷል።

በዚህም ጉባኤ በ " ዮርዳኖስ " አቅርቢነት በጋዛ " አስቸኳይ የሰብአዊ ተኩስ አቁም " እንዲደረግ የሚጠይቅ የውሳኔ ሃሳብ ቀርቦ ነበር።

የሰብዓዊ ተኩስ አቁም ጥሪ የቀረበበት የውሳኔ ሀሳቡ ፦
- በ120 ድጋፍ፣
- በ14 ተቃውሞ
- በ45 ድምጸ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ጸድቋል።

በዚህም መሰረት ተመድ በጋዛ አስቸኳይ የሰብዓዊ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ውሳኔ አሳልፏል።

የውሳኔ ሃሳቡን ከተቃወሙት ውስጥ አሜሪካ ፣ እራሷ እስራኤል ፣ ሃንጋሪ ፣ ኦስትሪያ ይገኙበታል።

ድምፅ ተአቅቦ ካደረጉት መካከል ደግሞ ሀገራችን #ኢትዮጵያ ፣ ጀርመን ፣ ካናዳ፣ ግሪክ፣ ፊንላንድ፣ ዴንማርክ፣ ስውዲን፣ ኢራቅ፣ ጃፓን፣ ጣልያን፣ ሕንድ ፣ዩናይትድ ኪንግደም፣ ዩክሬን፣ ቱኒዝያ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ዛምቢያ ይገኙበታል።

የተመድ አስቸኳይ እና ልዩ ጉባዔ የተካሄደው በእስራኤል እና ሃማስ መካከል ጦርነቱ ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ነው።

እስራኤልም በጋዛ የምድር ዘመቻ ማካሄድ ጀምራለች።

የእስራኤል ጠ/ሚ ቤንያሚን ኔታንያሁ አማካሪ ማርክ ሬጅቭ  የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን #ሃማስ በሰብአዊነት ላይ በርካታ የግፍ ወንጀሎችን መፈፀሙን ገልጸው ለዚህም ደግሞ ከዓርብ ምሽት (ትላንት) ጀምሮ ክፍያውን #እንደሚከፍል እና እስራኤልም መመለስ መጀመሯን ተናግረዋል።

ሀማስ እስራኤል ለምታካሂደው የምድር ላይ ዘመቻ አፀፋውን ለመስጠት ሙሉ ዝግጁነት እንዳለው ገልጿል።

የሀማስ የፖለቲካ ቢሮ ከፍተኛው አመራር ኢዛት አል-ሪሻቅ " ኔታንያሁ ወደ ጋዛ ለመግባት ከወሰነ እኛም ዝግጁ ነን " ያሉ ሲሆን " የወታደሮቹ ሬሳ በጋዛ ምድር ይዋጣል " ብለዋል።

21ኛ ቀኑን በያዘው በእስራኤልና ሃማስ ጦርነት በእስራኤል ጥቃት ጋዛ የተገደሉ ሰዎች ከ7300 መብለጣቸውን በሃማስ ስር ያለው የጤና ሚኒስቴር የገለፀ ሲሆን በእስራኤል በኩል በሃማስ የተገደሉም ከ1400 በልጠዋል።

ℹ️ ተጨማሪ #የውጭ_ሀገር_መረጃዎችን በዚህ መከታተል ይችላሉ 👉https://publielectoral.lat/+LM-bJ8NzZMcxMjA8

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እርዳታ ለሚፈልጉ ወገኖች ምን ያህል ድጋፍ እየተደረገ ነው ? በኦሮሚያ ክልል በወለጋ ዞን፦ - ኪረሙ፤ - ሁሙሩ እና አጋምሳ፣ - ቤጊ፤ - ጊዳሚ፤ - ቆንዳላ፤ - ሆሮ ሊሙ በተሰኙ ቦታዎች፣ በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር፣ ዋግኽምራ ብሔረሰብ ዞን አስተዳደር እንዲሁም በትግራይና በአፋር ክልሎች የተከሰተውን ድርቅ ተከትሎ ዜጎች ለከፍተኛ ረሃብ መጋለጣቸው፣ በሰዎችና በእንስሳት ላይ ሕልፈተ ሕይወት መድረሱ…
#አማራ #ዋግኽምራ

" ሰው ሁሉ ግራ ተጋብቶ የሚበላውንም አጥቶ ነው ያለው፤ ታይቶም ተሰምቶ የማይታወቅ በጣም የሚዘገንን ድርቅ ነው ያጋጠመን  " - የዋግኽምራ ምሽሃ ቀበሌ ነዋሪ

በአማራ ክልል፣ ዋግ ኽምራ ብሄረሰብ አስተዳደር ፤ ሰሀላ ሰየትም ወረዳ ውስጥ ስላለው አስከፊ የድርቅ ሁኔታ በተደጋጋሚ መነገሩ ይታወሳል።

በአካባቢው ስለሚገኙ ዜጎች ሁኔታ ፣ የሰብዓዊ ድጋፍ ጉዳይ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ተደጋጋሚ መልዕክቶችን ማጋራቱም ይታወሳል።

አሁንም ችግሩ በከፋ ሁኔታ ላይ ሲሆን በርካታ ወገኖች በድርቁ ችግር ውስጥ ይገኛሉ። ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ እንስሳትም መኖ ፍለጋ ወደ አጎራባች ወረዳዎች ተሰደዋል።

በዚሁ አካባቢ ስላለው አስከፊ የድርቅ ሁኔታ ከሰሞኑን ቃላቸውን ለቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ የሰጡ ወገኖች " ቀጣይ ኑሯችን ተስፋም የለው " ብለዋል።

አርሶ አደር ደሴ ፈንቴ ፤ የምሸሃ ቀበሌ ነዋሪ ሲሆኑ ባለፈው ክረምት በቀበሌው ምንም አይነት ዝናብ ባለመጣሉ እርሳቸውም ሆኑ ከብቶቻቸው የሚበሉት እንደሌላቸው ተናግረዋል።

በድርቁ ምክንያት የጎረቤቶቻቸው ህይወት እንዳለፈም የገለፁት አርሶ አደሩ ፤ የቤት እንስሳቶቻቸው በመሞታቸው ቀጣይ ኑሯቸው ተስፋ እንደሌለው ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ሌላው የ01 ቀበሌ ነዋሪ አርሶ አደር ነጋሽ ጎበዙ ፤ " 2015 ለ2016 ምንም አይነት ሳርም ሆነ ሌላ ነገር ያልበቀለበት ፤ ታይቶም ተሰምቶ የማይታወቅ በጣም የሚዘገንን ድርቅ ነው ያጋጠመን። ሰው ሁሉ ግራ ተጋብቶ የሚበላው አጥቶ እስሳቱንም ትቶ፣ ሰውም በየቦታው እየሞተ፣ እንስሳቱም እየሞቱ በጣም የከፋ ሁኔታ ላይ ነው ደርሰን ያለነው። በጣም በጣም አስከፊ ነው። " ብለዋል።

እሳቸው የነበራቸው በርካታ ከብቶች እና ፍየሎች በረሃብ ሞተውባቸው እንዳለቁ ተናግረው ፤ " የከብቱስ ይሁን እሳሳት ናቸውና እጅግ የሚያሳዝነው የሰዎች ህይወት እያለፈ መሆኑ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

በዚህ ሳምንት እሳቸው ባሉበት አካባቢ 2 ህፃናት እና 3 አዛውንቶች በአጠቃላይ 5 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ተናግረዋል።

ከሰሞኑን በዋግኽምራ ድርቅ ያስከተለውን ጉዳት ከመንግስታዊና 18 ከሚደርሱ መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የተውጣጣ የባለሞያዎች ቡድን በአካል ተገኝቶ ጥናት ማድረጉ ተነግሯል።

በዚህም ጥናት በሰው እና እስሳት ሞት ላይ ዳሰሳ ተደርጓል።

ምንም እንኳን የክልሉ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ለድርቅ ተጎጂዎች በሚል የዕለት እርዳታ እንደላከ ቢያሳውቅም የዋግኽምራ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ፅ/ቤት ድጋፉ በቂ እንዳልሆነ አሳውቋል።

ያለው ችግር የእንስሳት መኖ እጥረት፣ የሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እጥረት ...ሌሎችም ዘርፈ ብዙ ችግሮች እንደሆነ የገለፀው ፅ/ቤቱ " የክልሉ መንግስት 600 ኩንታል ስንዴ፣ ፌዴራል መንግስት 675 ኩንታል ስንዴ አቅርበዋል፣ ረጂ ድርጅቶች 42 ሚሊዮን ብር የሚሆን በካሽ የሚከፈል አቅርበዋል። አሁን ላይ ለአንድ ወር የሚሆን 25,834 አካባቢ ሰዎችን ሊያግዝ የሚችል ድጋፍ አግኝተናል ይህ ግን ካለው ችግር አንፃር በቂ አይደለም " ብሏል።

ተጨማሪ ድጋፍ ካልተደረገ ተጨማሪ ጥፋት ሊደርስ ይችላል ሲልም ፅ/ቤቱ መግለፁን ቪኦኤ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በማንኛውም ቀንና ሰዓት የሳፋሪኮም የሞባይል ካርድ ለመሙላት M-PESA መጣልን!

M-PESAን ለመጠቀም የሞባይል አፑን ያውርዱ ወይም *733# ይደውሉ

ጉግል ፕለይ ስቶር/ አፕል ስቶር https://bit.ly/M-PESA_SafaricomEthiopia

#MPESASafaricom
#FurtherAheadTogether
#ግሎባል_ባንክ_ኢትዮጵያ

እሁድ ምሽት ማንችስተር ዩናይትድ ከማንቺስተር ሲቲ የሚያደርጉትን ጨዋታ በቴሌግራም ቻናላችን ብቻ ውጤቱን እና በጨዋታው 1 ጎል አስቆጣሪ ተጫዋች በትክክል ለሚገምቱ 3 አሸናፊዎች የ300 ብር ካርድ እንሸልማለን፡፡

የቴሌግራም ቻናላችን https://publielectoral.lat/Globalbankethiopia123

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን
TIKVAH-ETHIOPIA
#AAU በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲ የሆነው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሽግግር ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ በነባሩ አሰራር እንደሚቀጥል ተጠባባቂ ፕሬዝደንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ ተናግረዋል። በዚህም የ2016 የትምህርት ዘመን ተማሪ ቅበላ ከዚህ ቀደም በነበረው ነባሩ ስርአት የሚከናወን ሲሆን ፤ አዲስ አሰራሮች ከመጡ በየጊዜው ይፋ እንደሚደረግ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ አሳውቀዋል። @tikvahethiopia
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ሁለት ሚኒስትር ዴኤታዎች ተሹመውለታል።

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እንዲሁም አቶ ኮራ ጡሹኔ የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ከጥቅምት 12/2016 ዓ.ም ጀምሮ ተሹመዋል፡፡

ወ/ሮ አየለች እሸቴ የሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሲያገለግሉ ቆይተዋል።

አቶ ኩራ ጡሹኔ በጅማ ዩኒቨርሲቲ በምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲሁም በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ለረጅም ዓመታት አገልግለዋል።

ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) የከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ እንዲሁም ፈንታ ማንደፍሮ (ዶ/ር) የአጠቃላይ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ከጥቅምት 2014 ዓ.ም ጀምረው ሲያገለግሉ መቆየታቸው ይታወቃል።

ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ከነሐሴ 24/2015 ዓ.ም ጀምሮ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ሆነው መሾማቸው ይታወሳል።

Via @tikvahuniversity
" በኤሌክትሪክ አገልግሎት እጦት እየተሰቃየን ነው " - ነዋሪዎች

በመተከል የተለያየ ወረዳ ያሉ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ካገኙ ከ2 አመት በላይ እንደሆናቸው ገለፁ።

በመተከል ዞን ቡለን፣ ድባጤ እና ወንበራ ወረዳዎች ውስጥ ያሉ ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት በቋሚነት ካገኙ ከ2 አመት በላይ እንደሆናቸው በመግለፅ በኤሌክትሪክ አገልግሎት እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልፀዋል።

ስማቸው እንዲገለፅ ያልፈለጉ በወንበራ ወረዳ የሚኖሩ የጤና ባለሙያ እንደነገሩን ከሆነ በኤሌክትሪክ አገልግሎት እጦት ምክንያት የህክምና አገልግሎት ለመስጠት እጅግ አዳጋች እንደሆነባቸው አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በወንበራ ቡለን እና ድባጤ ወረዳ ያሉ የተለያዩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ነዋሪዎችን ያናገረ ሲሆን በቋሚነት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ካገኙ ከ2 አመት በላይ እንደሆናቸው አመልክተው በመሃል ለጥቂት ወራት አየተቆራረጠ መምጣቱን በመግለፅ በኤሌክትሪክ አገልግሎት እጦት እየተቸገሩ መሆኑን ገልፀዋል።

በእነዚህ ወረዳዎች የሚገኙ ያናገርናቸው ነዋሪዎች ማታ ማታ ሻማ የሚጠቀሙ እንደሆነ ሲገልፁ የእሌክትሪክ አገልግሎት ማጣታቸው የህይወት እንቅስቃሴአቸውን እያከበደው እንደሚገኝ በማስረዳት ከሚዲያ እንዲርቁ እንዳደረጋቸውና ተንቀሳቃሽ ስልኮቻችውን 15 ብር ከፍለው ጀነሬተር ባለባቸው ቦታዎች ሃይል እያስሞሉ እንደሚገኙ አስረድተዋል።

ጉዳዩን አስመልክተን የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ ካሳሁን ከበደን ያናገርን ሲሆን አቶ ካሳሁን ከዳዝባጉና እስከ ዲባጤ ባለው 43 ኪ.ሜ ርቀት ቦታ የመስመር ጥገና እንደሚያስፈልግ ገልፀው የኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቋረጠባቸው አካባቢዎች መጋቢ መስመር ይህ መሆኑን በማስረዳት አካባቢው ላይ ባለ የፀጥታ ችግር ምክንያት መስመሩን መጠገን እንዳልተቻለ አመልክተዋል።

አቶ ከበደ በተጠቀሱት ወረዳዎች የኤሌክትሪክ የአገልግሎት መቋረጡን ያረጋገጡ ሲሆን ፥ ቲክቫህ ለዋና ስራ አስፈፃሚው "ይሄ የኤሌክትሪክ መቋረጥ ችግር መች ይፈታል?" ብሎ ለጠየቃቸው ጥያቄ "እኛ አናውቅም" የሚል መልስ ሰጥተው በአካባቢው ለመንቀሳቀስ የፀጥታ አካላት ትብብርና እጀባ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

በጉዳዩ ላይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኝት የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዲስትሪቢውሽንና ሜንተናንስ ሀላፊ የሆኑትን አቶ የኔጌታን ያናገርን ሲሆን በአካባቢው ለ3 አመት የተቋረጠው የኤሌክትሪክ አገልግሎት በጥር 2015 ዓ/ም ጀምሮ እንደነበር አስረድተው ከዛ በኋላ ስላለው አገልግሎት መቆራረጥ ተጨባጭና ትክክለኛ መረጃ እንደሌላቸው ገልፀዋል።

ኃላፊው ከወረዳው የየኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ ሃላፊዎች ጋር ተነጋግረው መረጃ እንደሚሰጡ ለቲክቫህ ቃል ቢገቡም ከዛ በኋላ እርሳቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።

የመተከል ዞን መስተዳድር ከወረዳዎች ጋር በመተባበር አስፈላጊውን የፀጥታ ትብብርና ድጋፍ በማድረግ የኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚጀመርበት ሁኔታ እንዲመቻች የየወረዳው ነዋሪዎች ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
#አማራ

በአማራ ክልል፤ ሰሜን ጎንደር ዞን ፤ የተከሰተውን አስከፊ ድርቅ ተከትሎ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ የመሆን ዕድላቸው ሰፊ መሆኑን የዞኑ አመራሮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል።

የዞኑ አደጋ መከላከልንና ምግብ ዋስችና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሰላምይሁን ሙላት በገለጹት መሠረት፣ " ድርቅ ባለባቸው አካባቢዎች ወደ 105 የትምህርት ተቋማት ወደ 51 ሺሕ ለሚሆኑ ተማሪዎች ምገባ ይሰጥ ነበር " ብለዋል።

" ነገር ግን ከወራት በፊት 202 ሺሕ ዜጎች የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብለው ተለይተው ነበር። አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ድጋፍ ተደራሽ እየተደረገ ያለው ቅድሚያ ለሚያስፈልገው የማኅበረሰብ ክፍል ነው" ያሉት  ኃላፊው፣ " ለተማሪዎች እገዛ ማድረግ ያስፈልጋል፣ ነገር ግን ድጋፍ ተጠናክሮ ካልቀጠለ ምግብ ካላገኙ ሊማሩ አይችሉም " ሲሉ አስረድተዋል።

አክለውም፣ " የትምህርት ተቋማት ችግር ላይ ነው ያሉት፣ ቁሳቁስ ያስፈልጋቸዋል። የጤና ተቋማት መድኃኒት ያስፈልጋቸዋል። እስከ 2017 የምርት ዘመን 452, 950 የሚሆኑ ዜጎች እርዳታ ያስፈልጋቸዋል። ለግብርናው ዘርፍም የማዳበሪያና የዘር ድጋፍ ያስፈልጋል " ብለዋል።

አቶ ሰላምይሁን ዞኑ ተደራራቢ ችግር እንዳለበት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ማብራሪያ፣ " በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ተፈናቅለው ከነበሩት ሰዎች መካከል ከ104 ሺሕ በላይ ዜጎችን ወደየቄያቸው መልስናል። ነገር ግን በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንዲሉ ከትግራይና ከኦሮሚያ ክልሎች የመጡ ከ41 ሺሕ በላይ፣ ከሱዳን የተመለሱ ከ4ሺሕ በላይ፣ ከ20ሺሕ በላይ የኤርትራ ተፈናቃዮች በዞኑ አሉ። እነዚህ ከድርቁ ጋ በተያያዘ ችግሩን ክብደት የሰጡት ጉዳዮች ናቸው " ነው ያሉት።

የሰሜን ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ክቡር አሰፋ በበኩላቸው፣ " በተለያዩ አካላት የተጀመሩ ድጋፎች አሉ፣ በዚህ ካልቀጠለ 51, 336 ተማሪዎች ትምህርት ያቋርጣሉ " ብለዋል።

" በሦስት ወረዳዎች ማለትም ጃንአሞራ፣ በየዳና ጠለምት አካባቢዎች አንደኛ ደረጃ ላይ ወደ 105፣ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ሰባት ትምህርት ቤቶች፣ በአጠቃላይ ከ51 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ለድርቁ ተጋላጭ ናቸው " ሲሉ አብራርተዋል።

አክለውም፣ " ተማሪዎች በመጀመሪያ የመምጣት አዝማሚያ ነበራቸው፣ ድርቁ በጣም በባሰባቸው አካባቢዎች (ለምሳሌ ጃን አሞራ ወረዳ 13 ቀበሌዎች አሉ፣ ከእነዛ  ውስጥ ወደ ሰባት ቀበሌዎች ላይ ድርቁ የከፋ ነው " ብለዋል።

ድጋፍ ካልተደረገ ተማሪዎች ወላጆቻቸው ጋር ይፈናቀላሉ የሚል ሥጋት እንዳለ የተናገሩት ኃላፊው፣ " ድርቅ ባለባቸው አካባቢዎች ያሉት ተማሪዎች እርግጠኛ ነኝ ትምህርት ቤት ይመጣሉ የሚል እምነት የለንም " ነው ያሉት።

በመሆኑም፣ መንግሥትን ጨምሮ ሁሉም ድጋፍ አድራጊዎች ለወላጆች የኢኮኖሚ፣ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፋቸውን በመቀጠል ትምህርት እንዳይቋረጥ ከፍተኛ ሚና እንዲጫዎቱ ጠይቀዋል።

አቶ ሰላምይሁን በበኩላችሁ፣ ከ104 ሺሕ ሕጻናት መካከል በጠለምት 49 በመቶው የከፋ ችግር ላይ እንደሆኑ፣ ጃንአሞራ 33 በመቶ የሕመም ችግር እንዳለባቸው፣ የድጋፍ ችግር ያለባቸው እናቶች የምግብ ፍላጎት ወደ 30 በመቶ እየደረሰ መሆኑን ገልጸዋል።

በመጨረሻም መንግሥት፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ቲክቫህ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሁሉም ሚዲያዎች በቦታው በመገኘት እንዲዘግቡ፣ ድጋፍም እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

ዘገባው በአ/አ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ ተዘጋጅቶ የቀረበ ነው።

@tikvahethiopia
#ኮንታ

" እናትን ጨምሮ ሁለት ልጆች ህይወታቸውን አጥተዋል "

በመሬት መንሸራተት አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት አለፈ።

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ በኦፓላሸ ቀበሌ በግምት በሊቱ 9 ሰዓት አካባቢ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉን የዞኑ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል።

የመሬት መምሸራረት አደጋው ሰሞኑን የጣለ ከባድ ዝናብ ተከትሎ እንደደረሰ የተነገረ ሲሆን በአደጋው እናትን ጨምሮ ሁለት ልጆች ህይወታቸውን አጥተዋል።

ሟቾች የ11ኛ ክፍል ተማሪ የሆነችው ተማሪ አግኔ አሉላ፣ ታናሽ ወንድሟና የ6ኛ ክፍል ተማሪ አማኑኤል አሉላ እና እናታቸው ወ/ሮ ዳምአሌ ደስታ ናቸው።

በደረሰው አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ በኦፓ ላሸ እና በኮዳ ማጂ ቀበሌ 25 አባዎራዎችና 175 የቤተሰብ አባላት ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በቀበሌ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ እንደሚገኙ ተረጋግጧል።

በአደጋው አምስት የቤት እንስሳት መሞታቸውንና በ5 ነጥብ 5 ሄክታር ማሳ ላይ የነበረ ሰብል መውደሙም ተጠቁሟል

የዚህ መረጃ ባለቤት የኮንታ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ነው።

@tikvahethiopia
#NBE

በቅርቡ በብሔራዊ ባንክ ምክትል ገዥና ዋና ኢኮኖሚሰት አቶ ፈቃዱ ደግፌ ተፈርሞ ለሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት በተላከ ደብዳቤ አገልግሎቱ የወለድ ክፍያ ያለበትን የብድር ውል ማዋዋል እንደማይችል ተገልጿል።

" የወለድ ክፍያ ያለበትን ብድር ማበደር የሚችለውና ገንዘብ መሰብሰብ የሚችለው ባንክና ማይክሮ ፋይናንስ ብቻ በመሆኑ፣ ግለሰቦች ወለድ በማስከፈል ማበደር አይችሉም " ሲሉ አቶ ፈቃዱ ደግፌ አስረድተዋል፡፡

በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ግለሰቦች ወይም ከፋይናንስ ተቋማት ውጪ ያሉ የንግድ ድርጅቶች፣ በመካከላቸው የሚያደርጉትን የወለድ ክፍያ ያለበትን ብድር ማዋዋል እንደሚቻልና እንደማይቻል ብሔራዊ ባንክን ጠይቆ እንደነበር ገልጸዋል፡፡

በዚህም መሠረት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የተሰጠ የባንክ ወይም የአነስተኛ የፋይናንስ ሥራ ፈቃድ ካልተያዘ በስተቀር፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የባንክ ወይም አነስተኛ የፋይናንስ ሥራ መሥራት በሕግ የተከለከለ ተግባር ነው ሲል በደብዳቤው ተገልጿል፡፡

የፌዴራል ገቢ ግብር አዋጅ ቁጥር 979/2008 እንደሚገልጸው፣ ብሔራዊ ባንክ ዕውቅና ከሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማት ውጪ፣ ቁጠባ እንዲሰበስቡና ብድር እንዲሰጡ በልዩ ሕግ የተፈቀደላቸው የኅብረት ሥራ ማኅበራት ናቸው፡፡

ግለሰቦችም ሆኑ ድርጅቶች ፈቃድ በተሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማት ሥራ በሕገወጥ መንገድ እንዲሰማሩና ሕገወጥ የፋይናንስ ሥርዓት ለመፍጠር የወጣ ሕግ አለመሆኑን፣ አገልግሎቱ ለብሔራዊ ባንክ የላከው ደብዳቤው ይገልጻል፡፡

ብሔራዊ ባንክም ከሕግ ድንጋጌዎች ውጭ በብድር መልክ ገንዘብ መሰብሰብና የብድር ተመን አውጥቶ በወለድ ማበደር፣ በብሔራዊ ባንክ ፈቃድ የተሰጣቸው የፋይናንስ ተቋማት ሥራ ብቻ መሆኑን አስታውቋል፡፡

በተመሳሳይ መንገድ ገንዘብ የሚያበድሩ ግለሰቦች በወንጀል የሚያስቀጣቸው ተግባር በመሆኑ፣ በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት ማንኛውም የወለድ ክፍያ ያለበት የብድር ውል ማዋዋል እንደሌለበት ብሔራዊ ባንክ ገልጿል፡፡

ከዚህ በፊት በወለድ ሲያበድሩ የነበሩ ግለሰቦች በምን ዓይነት መንገድ ሊጠየቁ እንደሚችሉ አቶ ፈቃዱ መረጃ እንደሌላቸው ገልጸዋል፡፡

የዚህ መረጃ ባለቤት " ሪፖርተር ጋዜጣ " ነው።

@tikvahethiopia