#ትግራይ
የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ በፅሁፍና ለትግራይ ቴሌቪዥን በድምፅ በሰጡት መግለጫ ፤ " ለነገና እና ለነገ በስቲያ (ጥቅምት 17 እና 18 /2016 ዓ.ም) የሚካሄድ የካድሬ ስብሰባ የለም ፤ የተጠራውም ህጋዊ አይደለም " ብለዋል።
የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል በበኩላቸው ለቅዳሜና እሁድ የተጠራው የካድሬዎች ሰብሰባ እንደሚካሄድ በፃፉት ደብዳቤ አስታውቀዋል።
ብዙዎች በጊዚያዊ አስተዳደሩና በህወሓት መካከል እየተፈጠረ ያለው ልዩነት እንዳሳሰባቸው ሰጋታቸው በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።
" ልዩነቱ ወዴት ያመራ ይሆን ? " ብለው በመጠየቅ ላይም እንደሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዘግቧል።
@tikvahethiopia