TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የ2015 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተና 33 የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ወደ ፈተና ማረሚያ አዳራሽ ሊገባ ነበር የተባለ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ሠራተኛ ተከሰሰ።

በተደረገው ክትትል በፍተሻ " የመልስ መስጫ ወረቀቶችን " ደብቆ ወደ እርማት አዳራሽ ሊገባ ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል የተባለው የተቋሙ ሠራተኛ ስልጣንን ያለአግባብ መገልግል የሙስና ወንጀል ተከሷል።

ተከሳሹ ይድነቃቸው ተኮላ የሚባል ሲሆን ክሱ የተመሰረተው በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ተረኛ ችሎት ነው።

የፍትህ ሚኒስቴር የሙስና የወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ህግ ተከሳሹን በሙስና ወንጀል ከሷል።

በቀረበው ክስ ላይ እንደተመላከተው ተከሳሹ ተገቢ ያልሆነ ብልፅግና ለራሱ ወይም ለሌላ ሰው ለማስገኘት በማሰብ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሰኔ 29 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው የስራ ማስታወቂያ ተመዝግቦ በፈተና አመቻችነትና ለእርማት ስራ በጊዜያዊነት መቀጠሩ ተጠቅሷል።

በተለይም ከነሐሴ 1 እስከ ነሐሴ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ውስጥ በብርሀንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ውስጥ የተቀመጡና ለእርማት የተዘጋጁ የ18 ተማሪዎች የ2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መልስ መስጫ ወረቀቶችን ይዞ መውጣቱ በክሱ ሰፍሯል።

ከዚህም በኋላ በነሐሴ 8/2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 2 ሰዓት ከ 30 አካባቢ በፈተና ወቅት የተፈታኝ ተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶች ያልሆኑና የፈተና መልስ ተቀልሞባቸው (ተሞልቶባቸው) የተዘጋጁ 33 የመልስ መስጫ ወረቀቶችን ደብቆ ወደ ፈተና ማረሚያ አዳራሽ ሊገባ ሲል በተደረገ ቁጥጥር በፍተሻ የተያዘ በመሆኑ በክስ ዝርዝሩ ላይ ተገልጿል።

በተጨማሪም በተከሳሹ በመኖሪያ ቤት ውስጥ በተደረገ ብርበራ 44 የ2015 ዓ.ም ብሔራዊ ፈተና የተማሪዎች የመልስ መስጫ ወረቀቶችና 10 ደግሞ ተመሳስለው የተዘጋጁ ሀሰተኛ የመልስ መስጫ ወረቀቶች የተገኙ መሆኑን ጠቅሶ ዐቃቤ ህግ በክስ ዝርዝሩ ላይ አስፍሯል።

በዚህ መልኩ ተከሳሹ ሥልጣንን አላግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል የተከሰሰ ሲሆን ፥ በተረኛ ችሎት ክሱ እንዲደርሰው ከተደረገ በኋላ የዋስትና መብት ጥያቄ አቅርቧል።

በተከሳሹ የዋስትና ጥያቄ ላይ አቃቤ ህግ ዋስትና ሊፈቀድ እንደማይገባ ገልጾም ተከራክሯል።

ተረኛ ችሎቱ የግራ ቀኝ ክርክሩን መርምሮ በዋስትናው ላይ ብይን ለመስጠት በይደር የቀጠረ ሲሆን ፥ ተከሳሹ በቀረበበት ክስ ላይ የክስ መቃወሚያ ካለው ለመጠባበቅ ደግሞ ለጥቅምት 8 ቀን 2016 ዓ.ም ተቀጥሯል።

መረጃው የፋና ብሮድካስቲንክግ ኮርፖሬት ነው።

@tikvahethiopia
#CANAL+

ካናል ፕላስ በዓለም ላይ በ40 ሀገራት እየሰራ የሚገኝ ግዙፍ የክፍያ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲሆን በኢትዮጵያ የተጀመረውን አዲሱን የ2016 የትምህርት ዘመን አስመልክቶ በአዲስ አበባ እና በ 7 የክልል ከተሞች (አዳማ፣ ሀዋሳ፣ ቢሾፍቱ፣ ሶዶ፣ ጅማ፣ሐረር እና ድሬዳዋ) በሚገኙ 45 በሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ተገኝቶ ከKG እስከ 4ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላቸው በመመኘት አዝናኝ እና አስተማሪ ዝግጅቶችን እያካሄደ መሆኑ ገልጿል።

የዝግጅቱ ዋና ዓላማ ለትምህርታቸው ጥሩ እገዛ ያበረክታል ብሎ በፅኑ ያመነበትን አዲሱን "የእውቀት ዛፍ" የተሰፕውን የልጆች ትምህርታዊ ፕሮግራም ለማስተዋወቅና በትምህርታቸው ጥሩ  ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት መስጠት ሲሆን ከዚያ ባለፈ ግን ተማሪዎች የምሳ ሰአት እረፍታቸውን ተዝናንተው እንዲያሳልፉ እንደሆነም ታውቋል።

ካናል ፕላስ በተለያየ የእድሜ ክፍል ላይ ላሉ ልጆች የሚሆኑ አስተማሪና አዝናኝ የቴለቪዥንኘሮግራሞች ያሉት ሲሆን ልጆች የቋንቋ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ የሚረዳቸው መሆኑንም ገልጿል።
ፎቶ፦ የአውሮፓ ህብረት ለኢትዮዮጵያ 650 ሚሊዮን ዩሮ አመታዊ የባለብዙ ዘርፍ የድጋፍ መርሃ-ግብር ይፋ አድርጓል።

የድጋፍ ማዕቀፉን ኢትዮጵያ የሚገኙት የአውሮፓ ህብረት የዓለም አቀፍ ትብብር ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን ከገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ጋር ፈርመዋል።

ድጋፉ ፦

- ለአረንጓዴ ልማት ፣
- ለአየር ንብረት ለውጥ ፣
- ግብርና ፣ አካባቢ ጥበቃና ታዳሽ ኃይል ልማት፣
- ለሰው ኃይል ልማት እንዲሁም አስተዳደር፣
-ለሰላም ግንባታና የዴሞክራሲ ስርአት ግንባታ የሚውል ይሆናል ነው ያሉት።

ኮሚሽነር ጁታ በዛሬ ውሎዋቸው  ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ፣ ከአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙሳ ፋኪ ማሃማት ጋር መምከራቸው ተነግሯል።

ኮሚሽነር ጁታ ኡርፒላይነን በኢትዮጵያ ይፉዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ  ትላንት ነው አዲስ አበባ የገቡት።

Via EU in Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና / Graduate Admission Test ከመስከረም 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም በበይነ-መረብ ይሰጣል። ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ምርምር ኢንስቲትዩት- የፈተና ማዕከል ጋር በመተባበር የሚሰጠው ፈተና በተጠቀሱት ቀናት በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይከናወናል። ለፈተናው የተመረጡ ተፈታኞች ከመስከረም 21 እስከ 25/2016…
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከነገ መስከረም 23 ጀምሮ የብሔራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ የልምምድ ፈተና (Mock Exam) መሰጠት እንደሚጀመር አሳውቋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሠጠው ብሔራዊ የድህረ-ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 28 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ሚኒስቴሩ ፤ በሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጡ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞችን ለመማር የብሄራዊ ድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መውሠድ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስገንዝቧል።

በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚሠጠው ብሔራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 ጀምሮ እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ ምዝገባ እየተካሄደ ነው ያለው ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከነገ መስከረም 23 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የልምምድ ፈተና ይሰጣል ብሏል።

ተፈታኞች በተመዘገቡበት ዩኒቨርሲቲ በመገኘት User name እና Password በመጠቀም የልምምድ ፈተና መውሰድ ይችላሉ ሲል ገልጿል።

(የፈተና አሰጣጡን ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DigitalLottery አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ወጥቷል። 4 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 0140621904 ሆኖ ወጥቷል። 👉 4 ,000,000 ብር - 0140621904 👉 2,000,000 ብር - 0140163695 👉 1,000,000 ብር - 0140946766 👉 700,000 ብር - 0141151136 👉 350,000 ብር - 0140607557 👉 250,000 ብር - 0140928442…
#DigitalLottery

አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ወጥቷል።

4 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 0150143960 ሆኖ ወጥቷል።

👉 4 ,000,000 ብር - 0150143960
👉 2,000,000 ብር - 0151052252
👉 1,000,000 ብር - 0150894268
👉 700,000 ብር - 0150596781
👉 350,000 ብር - 0150608082
👉 250,000 ብር - 0150715350
👉 175,000 ብር - 0150997042
👉 100,000 ብር - 0150896057

(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#MoE ትምህርት ሚኒስቴር ከነገ መስከረም 23 ጀምሮ የብሔራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ የልምምድ ፈተና (Mock Exam) መሰጠት እንደሚጀመር አሳውቋል። በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሠጠው ብሔራዊ የድህረ-ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 28 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል። ሚኒስቴሩ ፤ በሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት…
" ፈተናው የምርጫ ጥያቄዎችን የያዘ ነው " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ከመስከረም 28 እስከ 30 /2016 ዓ/ም በሀገር ደረጃ የሚሰጠው የድህረ ምረቃ ትምህርት የመግቢያ ፈተና ወጥ በሆነ መንገድ በአንድ የፈተና መተግበሪያ የሚከወን መሆኑን ገልጿል።

ፈተናው #ምርጫ_ጥያቄዎችን የያዘ ነው ብሏል።

ለፈተናው 53 የፈተና ማእከላት እና 84 የፈተና ጣቢዎች የተዘጋጁ ሲሆን በግማሽ ቀን ውስጥ የሚጠናቀቅ ይሆናል ተብሎ ታቅዷል።

አይነስውራን ተፈታኞች የቃል እና ምክንያታዊ አስተሣሠብ ክህሎቶቻቸው ላይ ያተኮሩ ፈተናዎችን ይወስዳሉ ያለው ሚኒስቴሩ በወሠዱትም ፈተና ከ100% ይመዘናሉ ብሏል።

ብሄራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ጥያቄዎች አመልካቾች መርጠው በሚያመለክቱበት የትምህርት መስክ ላይ ትኩረት ያደረገ እንዳልሆነ ትምህርት ሚኒስቴትር ገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ዓላማ ፦

- በግል እና በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተው የድህረ ምረቃ ትምህርት በ2ኛ እና 3ኛ ዲግሪ የትምህርት ፕሮግራሞች ገብቶ ትምህርት ለመከታተል ፍላጎት ያላቸውን አመልካቾች ብቃት ለመመዘን፤

- ድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች የሚገቡ ተማሪዎች ሂሣባዊ ትንተና (Quantitative reasoning) ፣ ምክናያታዊ አስተሳሠብ (Analytical reasoning) ፣ የቃልና የጹህፍ ከህሎት ለመመዘን ነው ሲል አስታውሷል።

@tikvahethiopia
በአዲስ ዓመት አዲስ ገፅታ!!

በአዲስ ዓመት አዲስ አስተሳሰብ ፤ አዲስ ስያሜና የንግድ ምልክት!!
ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ !!

በከፍተኛ የዕድገትና የለውጥ ጉዞ  ላይ ከሚገኘው ባንካችን ጋር አብረው በመስራት ማሳካት ወደሚፈልጉት ራዕይ ይድረሱ ፡፡

ባንካችን የሚሰጣቸውን ዘርፈ ብዙ የባንክ አገልግሎቶች ፤ የተለያዩ ጨረታዎችና የስራ ማስታወቂያዎች  እንዲሁም ፈጣንና አዳዲስ መረጃዎችን ለማግኘት የባንካችንን የቴሌግራምና የፌስቡክ ቻናሎቻችን አሁኑኑ ይቀላቀሉ ፡፡

https://publielectoral.lat/Globalbankethiopia123  

ግሎባል ባንክ ኢትዮጵያ
ለጋራ ስኬታችን!!
#ኦሮሚያ

" በቤጊ ሁለት ቀበሌዎች ረሃብ ተከስቷል "

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ረሃብ መከሰቱ ተነገረ።

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት የተፈረጀውና ራሱን " የኦሮሞ ሕዝብ ነጻ አውጪ " ብሎ የሚጠራው ታጣቂ ቡድን ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ሲንቀሳቀስባቸው ከነበሩ አካባቢዎች መካከል በቤጊ ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች ረሃብ መከሰቱን የምዕራብ ወለጋ ዞን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገለጸ።

የምዕራብ ወለጋ ዞን አስተዳዳሪ አቶ ሰለሞን ታምሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል፣ " ሸኔ የያዛቸውና ለጥቂት ጊዜያት ያስተዳደራቸው ወረዳዎች ነበሩ።  እነዛ ወረዳዎች ብዙ ችግሮች ገጥሟዋቸዋል " ብለዋል።

ለአብነት ታጣቂ ቡድኑ ሲንቀሳቀስባቸው በነበሩ አንዳንድ አካባቢዎች #ረሃብ መከሰቱን ገልጸዋል።

አቶ ሰለሞን ፣ " እስፔሻሊ ጠረፍ ላይ የሚገኙ ቀበሌዎች ተጎድተዋል። በምዕራብ ወለጋ ዞን ቤጊ ወረዳ ተጋባና ሻንታ ቀበሌዎች ረሃብ አለባቸው " ብለዋል።

ረሃብ ተከሰተበት የተባለውን የቤጊ ወረዳ ሁኔታን ሲያስረዱም አቶ ሰለሞን ፣ " መሰረተ ልማት፣ ቀበሌዎች፣ የአስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች ጤና ኬላዎች፣ ጤና ጣቢያዎች ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ በጣም ጉዳት የደረሰበት ወረዳ ነው " ብለዋል።

" ከጤና ጋር በተያያዘ ቢያንስ 45 የሚሆን ጤና ኬላ ወድሟል ወደ አምስት ጤና ጣቢያዎች ተቃጥለዋል " ሲሉ አስታውሰው፣ ወረዳውን ታጣቂ ቡድኑ ሲቆጣጠረው አርሶ አደሩ እንዳያርስ በማዳበሪያ እንዳይጠቀም፣ ማኅበረሰቡ የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኝ ማድረጉን አስረድተዋል።

" ሸኔ አገሪቱን ወደ ድህነት የሚመራ እንጂ ምንም አላማ የሌለው ነው " ያሉት የዞኑ አስተዳዳሪ ታጣቂ ቡድኑ " በቄለም ወለጋና  በቤጊ፣ በቆንዳላ በተለይ ገጠሩን አካባቢ ተቆጣጥሮ ጉዳት አድርሷል። ሰው ገድሏል። ብዙ ንብረቶች በዚህ ታጣቂ ቡድን ወድመዋል " በማለት ተናግረዋል።

ረሃብ የተጋረጠባቸው የሰሊጥ አምራቾች ናቸው ያሉት የዞኑ አስተዳዳሪ፣ " ሸኔ አርሶ አደሩ ማዳበሪያ በሚወስድበት ጊዜ ቀቅሎ እንዲበላ ሲያደርግ ነበር። መብላት ማለት እንደ ምግብ እንዲበላ በማድረግ እንዳያርስበት፣ እንዳይጠቀምበት ማድረግ ነው " ብለዋል።

ነዋሪዎች በበኩላቸው በተከሰተው ረሃብ የሰዎች ሕይወት ማለፉን ገልጸው፣ መንግሥት የምግብ ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

አክለውም፣ በወባ ወረርሽኝም የሰው ሕይወት እያለፈ መሆኑን አስረድተዋል።

በረሃብ የሞተ ሰው እንዳለና እንዴሌለ ማብራሪያ እንዲሰጡ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ሰለሞን ፣ " ከረሃብ የተነሳ የሞተ ሰው ሪፓርት አልደረሰኝም። ከምግብ ጋር በተያያዘ ግን የኦሮሚያ ቡሳ ጎኖፋ ሰሞኑን 400 ኩንታል ዱቄት አድርሷል። እርዳታ ግን አሁንም ያስፈልጋል " ብለዋል።

ከረሃብ ባሻገርም በዞኑ በሚጉኙ ወረዳዎች የወባ ወረርሽኝ እንደተከሰተ፣ #የሞቱ ሰዎችም እንዳሉ ገልጽው፣ መንግሥትና መንግስታዊ ያልሆኑ የተራድኦ ድርጅቶች እርብርብ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

መንግሥት " ኦነግ ሸኔ " እያለ የሚጠራውና እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት የሚለው ታጣቂ ቡድን ከላይ በምዕራብ ወለጋ ዞን በቀረበበት ክስ ዙሪያ ይፋዊ ምላሽ የሚሰጥ ከሆነ ተከታትለን እናሳውቃለን።

@tikvahethiopia
#ነዳጅ📈

የነዳጅ ዋጋ እያሻቀበ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል ሲሉ የነዳጅ ላኪዎች ህብረት መሪ አስጠነቀቁ።

የ23 ነዳጅ ላኪ ሀገራት ህብረት የሆነው ኦፔክ+ ዋና ፀሀፊ ሄይታም አል ጋይስ ፤ ለሃይል አቅርቦት ያለው ፍላጎት በመጨመሩ የነደጅ ዋጋ እንዳሻቀበ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።

ዋና ጸሃፊው " በቀን የነዳጅ ፍላጎት ወደ 2.4 ሚሊዮን በርሜል ሲያድግ እየተመለከትን ነው " ብለዋል።

ሁለቱ ዋነኛ የነዳጅ አምራችና ' ኦፔክ+ ' አባል የሆኑት ሳዑዲና ሩሲያ የወሰኑት ውሳኔ በዚህ ዓመት መጨረሻ ከፍተኛ የአቅርቦት እጥረት ያስከትላል ሲል ዓለም አቀፉ የኢነርጂ ኤጀንሲ አስታውቋል።

" ይህ ሁለት ሉአላዊ ሀገራት ሳዑዲ አረቢያ እና ሩስያ በፍቃደኝነት የወሰኑት ነው። ይህ ውሳኔ እርግጠኛ ልንሆንበት በማንችልበት ሁኔታ ምክንያት የተደረገ ጥንቃቄ ወይም ቅድመ ዝግጅት ብለን ልንገልጸው እንችላል " ሲሉ የኦፔክ+ ዋና ጸሃፊ ተናግረዋል።

ሰሞኑን በምርት እጥረት ምክንያት የአንድ በርሜል ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ 95 ዶላርን አልፎ የነበረ ሲሆን ዋጋው 100 ዶላርን ሊያልፍ ይችላል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።

ይህ የዋጋ ለውጥ በሚቀጥሉት 10 ወራት ውስጥ የነዳጅ ዋጋ ሊያሻቅብ እንደሚችልና በወሳኝ የኢኮኖሚ መስኮች ያለው የዋጋ ግሽበት ለረዥም ጊዜ እንዲቀጥል ምክንያት ይሆናል የሚል ስጋትን ማጫሩን #ቢቢሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" እስካሁን ውጤት አልተገለፀም " - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2015 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት እስካሁን #አልተገለፀም ሲል አሳውቋል።

ተፈታኞችና መላው የትምህርት ማህበረሰብ #በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጠይቋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በፀጥታና ሌሎች ምክንያቶች ፈተና ሳይወስዱ የቆዩ ተማሪዎች ፈተናቸውን መውሰዳቸው ይታወቃል።

የነዚህ ተማሪዎችን ፈተና ውጤት በሐምሌ 2015 ዓ.ም ከተፈተኑ ተማሪዎች ጋር አብሮ ይፋ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ከዚህ ቀደም " እስከ መስከረም መጨረሻ ድረስ ውጤቱ ይፋ ሊደረግ እንደሚችል " የአገልግሎቱ ከፍተኛ ኃላፊ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

@tikvahethiopia