TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ ብሔራዊ የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና / Graduate Admission Test ከመስከረም 28 እስከ 30/2016 ዓ.ም በበይነ-መረብ ይሰጣል። ትምህርት ሚኒስቴር ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ምርምር ኢንስቲትዩት- የፈተና ማዕከል ጋር በመተባበር የሚሰጠው ፈተና በተጠቀሱት ቀናት በተለያዩ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ይከናወናል። ለፈተናው የተመረጡ ተፈታኞች ከመስከረም 21 እስከ 25/2016…
#MoE

ትምህርት ሚኒስቴር ከነገ መስከረም 23 ጀምሮ የብሔራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ የልምምድ ፈተና (Mock Exam) መሰጠት እንደሚጀመር አሳውቋል።

በሀገር አቀፍ ደረጃ ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሠጠው ብሔራዊ የድህረ-ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 28 እስከ 30 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ይሰጣል።

ሚኒስቴሩ ፤ በሁሉም የመንግስትና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የሚሰጡ የድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞችን ለመማር የብሄራዊ ድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና መውሠድ ቅድመ ሁኔታ መሆኑን ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስገንዝቧል።

በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለሚሠጠው ብሔራዊ የድህረ ምረቃ ትምህርት መግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 ጀምሮ እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የሚቆይ ምዝገባ እየተካሄደ ነው ያለው ትምህርት ሚኒስቴር ፤ ከነገ መስከረም 23 እስከ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የልምምድ ፈተና ይሰጣል ብሏል።

ተፈታኞች በተመዘገቡበት ዩኒቨርሲቲ በመገኘት User name እና Password በመጠቀም የልምምድ ፈተና መውሰድ ይችላሉ ሲል ገልጿል።

(የፈተና አሰጣጡን ዝርዝር መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia