#CANAL+

ካናል ፕላስ በዓለም ላይ በ40 ሀገራት እየሰራ የሚገኝ ግዙፍ የክፍያ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሲሆን በኢትዮጵያ የተጀመረውን አዲሱን የ2016 የትምህርት ዘመን አስመልክቶ በአዲስ አበባ እና በ 7 የክልል ከተሞች (አዳማ፣ ሀዋሳ፣ ቢሾፍቱ፣ ሶዶ፣ ጅማ፣ሐረር እና ድሬዳዋ) በሚገኙ 45 በሚሆኑ ትምህርት ቤቶች ተገኝቶ ከKG እስከ 4ተኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላቸው በመመኘት አዝናኝ እና አስተማሪ ዝግጅቶችን እያካሄደ መሆኑ ገልጿል።

የዝግጅቱ ዋና ዓላማ ለትምህርታቸው ጥሩ እገዛ ያበረክታል ብሎ በፅኑ ያመነበትን አዲሱን "የእውቀት ዛፍ" የተሰፕውን የልጆች ትምህርታዊ ፕሮግራም ለማስተዋወቅና በትምህርታቸው ጥሩ  ውጤት ላመጡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት መስጠት ሲሆን ከዚያ ባለፈ ግን ተማሪዎች የምሳ ሰአት እረፍታቸውን ተዝናንተው እንዲያሳልፉ እንደሆነም ታውቋል።

ካናል ፕላስ በተለያየ የእድሜ ክፍል ላይ ላሉ ልጆች የሚሆኑ አስተማሪና አዝናኝ የቴለቪዥንኘሮግራሞች ያሉት ሲሆን ልጆች የቋንቋ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ የሚረዳቸው መሆኑንም ገልጿል።