TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Irreecha2016

አባ ገዳዎች እና ሃዳ ሲንቄዎች ዛሬ በጋራ በሰጡት መግለጫው የዘንድሮ የኢሬቻ በዓል አንድነትንና ሕብረትን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል ብለዋል።

የዘንድሮው ኢሬቻ በዓል መስከረም 26 እና 27/2016 ዓ.ም በሆራ ፊንፊኔ እና ሆራ አርሰዲ እንደሚከበር ይፋ አድርገዋል።

የቱለማ አባገዳና የኦሮሞ አባ ገዳዎች ህብረት ፀሓፊ አባገዳ ጎበና ሆላ ፤ " የዘንድሮውን ኢሬቻ በዓል የገዳ ስርዓት እሴትን በጠበቀ መልኩ ለማክበር ዝግጅት ተጠናቋል " ሲሉ ገልጸዋል።

'' ኢሬቻ እርቅና ሰላም በመሆኑ የዘንድሮው ኢሬቻ በደስታ፣ በአንድነትና በፍቅር ይከበራል '' ብለዋል።

የሲኮ መንዶ አባገዳና የህብረቱ አባል አባ ገዳ አሊይ መሐመድ ሱሩር ፤ "  ሁሉም የበዓሉ ታዳሚዎች የእርቅ፣ የፍቅርና የአንድነት ተምሳሌት በመሆን በዓሉን ማክበር አለባቸው " ሲሉ ተናግረዋል።

የኦሮሞ ቄሮዎች፣ ቀሬዎችና ፎሌዎች ኢሬቻ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ እንዲከበር የበኩላቸውን እንዲዉ ጥሪ አቅርበዋል።

ሃዳ ሲንቄ አፀዱ ቶላ በበኩላቸው ፤ '' ኢሬቻ ሰላም መሆኑንና የሰላም እናት መሆናችንን በአንድነት የምናሳይበት በዓል ነው '' ብለዋል።

'' ኢሬቻ የይቅርታ፣ የተጣለ የሚታረቅበት፣ የተለያዩ የሚገናኙበትና ፈጣሪ የሚመሰገንበት በዓል ነው '' ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህም  " በዓሉ ያለምንም ችግር እንዲከበር፣ በሀገራችን ሰላም፣ አንድነትና ፍቅር እንዲፀና ሃዳ ሲንቄዎች በትብብር ይሰራሉ  " ብለዋል።

ሃዳ ሲንቄ ጫሊ ቱምሳ ፤ " ኢሬቻ የኦሮሞ ህዝብ ማንነት መገለጫ በመሆኑ ባህላዊ እሴቱን ጠብቆ መከበር አለበት " ሲሉ ተናግረዋል።

ወጣቶችና ሴቶች ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በዓሉ ያማረና የተሳካ እንዲሆን ማስቻል እንደሚገባቸው ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ፎቶ ፦ ኢዜአ / ፋይል

@tikvahethiopia
#Irreecha2016

በኦሮሚያ ክልል የሚዋጉ አካላት " በኢሬቻ ሥርዓት ወቅት እንቅፋት የሚሆን ተጽእኖ እንዳያደርሱ " ሲሉ አባገዳዎች ጥሪ አስተላለፉ።

አባገዳዎቹ ጥሪውን ያስተላለፉት መስከረም 26 እና 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ የሚከበረውን የኢሬቻ ሥርዓት በማስመልከት ነው ።

የጉጂ አባገዳ እና የኦሮሞ አባገዳዎች ኅብረት ሰብሳቢ አባገዳ ጂሎ ማንኦ ለዶይቼ ቬለ ሬድዮ በሰጡት ቃል ፤ " እኛ አባገዳዎች ሥራችን ሰላም ነው፡፡ በኦሮሚያ የሚዋጉ ሁለቱም አካላት በኢሬቻ ስርዓታችንም ምንም አይነት እንቅፋት የሚሆን ተጽእኖ እንዳያደርሱብን ጠይቀናል፡፡ " ብለዋል።

" በሁሉም አቅጣጫ ያለው ኦሮሞ ሰላምና መግባባት ሰፍኖለት አንድነቱን እንዲያጠናክር እንፈልጋለን፡፡ " ያሉት አባገዳ ጂሎ " አገር ውስጥም ሆነ ከውጪም ያለው ኦሮሞ እንዲግባባ ነው የኛ መሻታችን፡፡ የሰላምና አንድነት አርማ በሆነው እሬቻ ስምም መጎዳዳቱ ቆሞ መግባባቱ እንዲሰፍን ነው የምንጠይቀው፡፡ ስለዚህ በዚህ በመጪው ኢሬቻችን ኦሮሞ በሙሉ ተስማምቶ በአንድ ሃሳብ እንዲግባባ ነው ፍላጎታችን። " ሲሉ ተናግረዋል።

አባገዳ ጂሎ ማንኦ ከኦሮሞም ባሻገር በመላው አገሪቱ ሰላም ሰፍኖ ወንድማማቾች መካከል ደም መፋሰሱ እንዲቀር ለማሸማገል አባገዳዎች ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

" እኛ ያላደረግነው ጥረት የለም፡፡ ከዚህ በፊት በትግራይ ጦርነት ነበር፡፡ ያንንም ለማሸማገል ከጦርነት በፊትም ሆነ ከጦርነት በኋላ ጥረናል፡፡ " ያሉ ሲሆን " አሁንም በአማራ ክልል የሚደረገውን የወንድማማች ግጭት እንዲቆም ነውና ፍላጎታችን ለሰላሙ የምንችለውን እንጥራለን፡፡ " ብለዋል።

" ተፋላሚዎች ችግራቸው ላይ እንዲነጋገሩ ነው የምንጠይቀው፡፡ ስለዚህ አሁንም በሰላሙ ጥረታችን ይቀጥላል፡፡ " ሲሉ ለሬድዮ ጣቢያው ገልጸዋል።

@tikvahethiopia
#Irreecha2016

በኦሮሞ ህዝብ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠዉና በዓለም ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገለት ያለዉ " ኢሬቻ " ሲከበር ስጋት ይሆናሉ ተብለዉ የተለዩ ጉዳዮች ላይ እየተሰራ እንደሆነ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮምኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

ከዚህ ቀደም ዜጎች ለኢሬቻ ያላቸዉ አመለካከት የተዛባ እንዲሆን የተደረገበት አግባብ ልክ አልነበረም ያለው ቢሮው ይህንን መቅረፍና ኢሬቻን የሁሉም ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የዓለም ህዝብ ሀብት ማድረግ ይገባናል ብሏል።

የዘንድሮዉ የ2016 ኢሬቻ ሲከበርም ፦
- በዓሉን እንደ ችግር መነሻ መመልከት ፣
- የፖለቲካ ማራመጃ ማድረግ ፤
- የጥላቻ ዘመቻ መንዛት፤
- ያልተገባ ጥቅም ለማግኝት መጣርና የመሳሰሉት እንደ ስጋት የሚነሱ በመሆናቸዉ አስቀድሞ ተገቢዉ ስራ በሚመለከተዉ አካል ብቻ እየተሰራ ይገኛል ሲል አሳውቋል።

ኢሬቻ እሴቶችን የሚያጠናክር በመሆኑ እንደ ፀብ መነሻና እንደ ስጋት መታየት እንደሌለበት ቢሮው ገልጾ የዘንድሮው በዓልም በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች በተገኙበት ለማክበር ዝግጅት እንደተደረገ ማመልከቱን አሀዱ ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፤ ከዚሁ ከኢሬቻ በዓል ጋር በተገናኘ በአዲስ አበባ ከተማ በክ/ከተማ እና በወረዳ ደረጃ የበዓሉን አከባበር አስመክቶ ውይይቶች እየተደረጉ ይገኛል።

የበዓሉ መዳረስን ተከትሎም የተለያዩ የበዓል ዝግጅቶች በከተማይቱ እየተከናወኑ ይገኛሉ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም " የሆራ ፊንፊኔ " ኢሬቻ በዓል ቅድመ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መሆኑን አሳውቋል።

የዘንድሮ 2016 የኢሬቻ በዓል ቅዳሜ በአዲስ አበባ በነጋታው እሁድ ደግሞ በቢሾፍቱ ይከበራል።

@tikvahethiopia