TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ሞሮኮ

እጅግ አስደንጋጭ ነው በተባለው የሞሮኮ መሬት መንቀጥቀጥ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ሞቱ።

በሞሮኮ በመሬት መንቀጥቀጥ እስካሁን  ባለው 1,305 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል።

ቢቢሲ ኒውስ ፤ የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴርን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው የተከሰተው 6.8 የተለካ የመሬት መንቀጥቀጥ ሲሆን በዚህም እጅግ በጣም ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።

በዋነኛነት የመሬት መንቀጥቀጡ የተሰማው በአትላስ ተራራ አካባቢ ነው ተብሏል።

ይህም ከማራኬሽ በደቡብ ምዕራብ 71 ኪሎ ሜትር ርቆ ይገኛል። ጥልቀቱም 18.5 ኪሎ ሜትር ነው። በማራኬሽና በሌሎችም ደቡባዊ አካባቢዎች ሰዎች መሞታቸው ተገልጿል።

አል-ሀውዝ፣ ማራኬሽ፣ ኦራዛቴ፣ አዚል፣ ክሪቾዋ እና ታራውዳንት በተባሉት አካባቢዎች በርካታ ሰዎች ሞተዋል።

በመሬት መንቀጥቀጡ ሕንጻዎችና ጎዳናዎች ሲናዱ ታይተዋል።

ሞሮኮ በደረሰው አደጋ የ3 ቀን ሀዘን አውጃለች።

በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት በደረሰው ጉዳት የኢትዮጵያ መሪን ጨምሮ የሀገራትና ተቋማት መሪዎች ሀዘናቸውን እና ለሞሮኮ ህዝብ ያላቸውን አጋርነት እየገለፁ ይገኛሉ።

NB. የሟቾች ቁጥር አሁን ካለውም ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
#CBE

እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳቸሁ!
===========

የበዓል ሸመታዎን
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ POS ማሽኖች ይፈፅሙ!

መልካም በአል ይሁንላችሁ!

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
#commercialbankofethiopia #digitalbanking #Ethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#GERD🇪🇹

" በተያዘው በጀት ዓመት ሌሎች ተጨማሪ ተርባይኖች ወደ ስራ ይገባሉ " - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ

ኢትዮጵያ ዛሬ 4ኛውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ (የአባይ ግድብ) የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን በይፋ አብስራለች።

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይኸኛው 4ኛ ዙር ሙሌት የመጨረሻው ስለመሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።

ሙሌቱ በስኬት በመጠናቀቁ በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው ፣ በጉልበታቸው ፣ በፀሎታቸው በስራው ለተሳተፉ ምስጋና አቅርበው " እንኳን ደስ አላችሁ " ብለዋል።

ለኢዜአ ቃላቸውን የሰጡት የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን መሪና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ዳግሞ ፤ ባለፉት 4 ዓመታት የውሃ ሙሌት ስራውን ለማከናወን የሚያስችል በቂ የዝናብ መጠን መገኘቱን አስረድተዋል።

የውሃ ሙሌት ስራው በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ ምንም አይነት ጉዳት በማያደርስ መልኩ መከናወኑን ገልጸዋል።

ለአብነትም በዘንድሮው ክረምት በግብጽ የሚገኘው የአሰዋን ግድብ ከበቂ በላይ ውሃ በመያዙ ምክንያት በግድቡ ማስተንፈሻ አማካኝነት ውሃ የማፋሰስ ስራ ሲያከናወን መቆየቱን ጠቁመዋል፡፡

ይህም ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስቱ አገራት የትብብር ምንጭ ከመሆን ባሻገር በታችኛው ተፋሰስ አገራት የሚያስከትለው ጉዳት እንደሌለ በተግባር ያመላከተ ስለመሆኑ አብራርተዋል፡፡

አሁን ላይ ኃይል ማመንጨት የጀመሩት ሁለቱ ተርባይኖች በስራ ላይ መሆናቸውን ጠቅሰው፤ በተያዘው በጀት ዓመት ሌሎች ተጨማሪ ተርባይኖች ወደ ስራ እንደሚገቡ አሳውቀዋል።

4ኛው ዙር የውሃ ሙሌት በስኬት መጠናቀቁ በግድቡ ግንባታ ሂደት ሌላኛውን አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከዚህ በኋላ የሚኖሩት ስራዎች ከዚህ ቀደም ከተለፈባቸው የተሻሉ እንደሚሆኑ የጠቀሱት ዶ/ር ኢንጅነር ስለሺ ፤ " ይህ ለኢትዮጵያዊያን ትልቅ ስኬት ነው " ብለዋል፡፡

@tikvahethiopia
" በአዲሱ ዓመት የሰው ሕይወትን የሚቀጥፉ የመሳሪያ አፈ ሙዞች በሙሉ ወደ መጋዝን መግባት አለባቸው " - ቅዱስነታቸው

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2016 ዓመተ ምሕረት የዘመን መለወጫን በማስመልከት  አባታዊ  ቃለ በረከት አስተላለፉ።

ከመልዕክታቸው የተወሰደ ፦

" ... ያለፈው ዓመት ያሳረፈብንን ሁለንተናዊ ተጽዕኖ በሚገባ አስተውለን፣ ዳግም ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገርብን ካላደረግን አዲሱ ዓመት ለኛ የሚሰጠን ትርጉም ምንድን ነው ?

ባለፉት ዓመታት በሃይማኖት፣ በባህል በታሪክ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊና ፖለቲካዊ እንዲሁም በሕዝባችን ሥር የሰደደውን የእርስ በርስ መጠራጠር ከልብ መርምረን ወደ ድሮው እኛነታችን ካልተመለከትንስ አዲስ ዘመን እያልን ማክበራችን ምን ፋይዳ አለው ?

ይህንን ሁሉ በአዲሱ ዓመት በማጤን ያለፈውን ጎጂ ነገር በመተው፤ ጠቃሚውን ግን ይበልጥ በማጠናከር አዲሱን ዓመት መቀበል አለብን።
 
ከሁሉ በላይ ለሀገራችንና ለሕዝባችን የሚጠቅመው ምንድነው ? በሚለው በምር መስራት አለብን፤ በመለያየት፣ በመፎካከር፣ በመበቃቀል፣ በመናናቅ፣ የራስን ጥቅም ብቻ ለማስጠበቅ በመጣር፣ ጊዜ አገኘሁ ብሎ ኃይልን በመጠቀም፣ የሕዝብን ጥቅም ማስከበርና የሀገርን አንድነት ማስቀጠል አይቻልም ፤ ሀገራችንንና ሕዝባችንን ወደ ዕመቀ ዕመቅ እየከተቱ ያሉ እንደዚህ ያሉ አስተሳሰቦች ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ ከአሮጌው ዓመት ጋራ አብረው መወገድ አለባቸው።

በአዲሱ ዓመት የሰው ሕይወትን የሚቀጥፉ የመሳሪያ አፈ ሙዞች በሙሉ ወደ መጋዝን መግባት አለባቸው፤ ችግሮችን በውይይት፣ አሊያም በሕግ እየተፈቱ የሀገርና የሕዝብ ሉዓላዊነት ነጻነትና አንድነት መረጋገጥ አለበት፤ ሀገርንና ሕዝብን ለዘለቄታው በአንድነት የሚያስቀጥሉ የሕግ የበላይነትን ማክበር፣ እኩልነትን ማረጋገጥ፣ የጋራ ተጠቃሚነትን እውን ማድረግ፣ የተጐዳውን መደገፍ፣ ሆድ የባሰውን ማለዘብ፣ የተጠቃውን ማጽናናት ሲቻል ነው፡፡ 

በአዲሱ ዓመት ይህንን ለማድረግ በቊርጥ ከተነሣን ሰላማችን ወደነበረበት ይመለሳል፡፡ ሀገራችንም በበረከት ትሞላለች፤ ስለዚህም ኢትዮጵያውያን የሆናችሁ ልጆቻችን ሁሉ ይህንን ጥሪያችንን ተቀብላችሁ የጥፋት መሳሪያችሁንም አስቀምጣችሁ ወደ ሰላም ማእድ ቀርባችሁ በወንድማማችነት መንፈስ ችግራችሁን በክብ ጠረጴዛ በውይይት በመፍታት የሀገሪቱንና የሕዝቡን አንድነት እንድታስቀጥሉ ሁሉን በሚያይ እግዚአብሔር ስም እንማጸናችኋለን፡፡ "

(ሙሉ መልዕክታቸውን ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD🇪🇹 " በተያዘው በጀት ዓመት ሌሎች ተጨማሪ ተርባይኖች ወደ ስራ ይገባሉ " - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያ ዛሬ 4ኛውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ (የአባይ ግድብ) የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን በይፋ አብስራለች። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይኸኛው 4ኛ ዙር ሙሌት የመጨረሻው ስለመሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። ሙሌቱ በስኬት በመጠናቀቁ በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው ፣ በጉልበታቸው…
#GERD🇪🇹

ግድቡ ከዚህ በኃላ ውሃ አይዝም ?

" 4ኛና የመጨረሻው ሲባል ከዚህ በኋላ የውሃ ሙሌት አይደረግም ማለት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት " - ዶ/ር ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋ

የታላቁ ሕዳሴ ግድብ አራተኛ ዙር ሙሌት መጠናቀቅን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የመጨረሻ ሙሌት " ሲሉ መግለፃቸውን ተከትሎ በርካቶች " ግድቡ ከአሁን በኃላ ውሃ አይዝም ? " የሚል ጥያቄ ፈጥሮባቸዋል።

ይህንን በተመለከተ ቃላቸውን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ሬድዮ ጣቢያ የሰጡት የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ሃብታሙ ኢተፋ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ዶ/ር ኢ/ር ሃብታሙ ኢተፋ ፦

" አራተኛና የመጨረሻው የውሃ ሙሌት የተባለው  አራቱ ዙሮች ከፍተኛ የውሃ መጠን የሚያስፈልጋቸው በመሆኑ ነው።

በእነዚህ አራት ዙሮች ግድቡ መያዝ ያለበትን የውሃ መጠን መያዝ ችሏል።

አራተኛና የመጨረሻው ሲባልም ከዚህ በኋላ የውሃ ሙሌት አይደረግም ማለት እንዳልሆነ መታወቅ አለበት።

ይልቁንም ግድቡ #እየተጠናቀቀ በመሆኑ ፣ ከፍተኛ የውሃ መጠን ሳያስፈልግ ይከናወናል። "

Credit - Ethio FM 107.8

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የኛ በሆነው አዲስ ዓመት በአዲስ ተስፋ እንደ አደይ ፈክተን ማርሻችንን ወደላቀ ስኬት እንቀይር!

መልካም አዲስ ዓመት።

#SafaricomEthiopia #FurtherAheadTogether
#OFC

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ (ኦፌኮ) ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና አሜሪካ መግባታቸውን ለማወቅ ተችሏል።

ፕሮፌሰሩ በአሜሪካ ለአንድ ወር እንደሚቆዩ የፓርቲው ዓለም አቀፍ ድጋፍ ቡድን አሳውቋል።

በአሜሪካ ቆይታቸው ፦
- ወደ ተለያዩ ግዛቶች በማቅናት ከኦሮሞ ተወላጅ ዳያስፖራዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።
- ይፋዊ / መደበኛ ባልሆኑ የተለያዩ ግብዣዎች ላይ በመገኘት ከወዳጆቻቸው እና ከፓርቲው ደጋፊዎች ጋር ይነጋገራሉ።
- በኦፌኮ-ዓለም አቀፍ የድጋፍ ቡድን አዘጋጅትነት የሚካሄድ ቨርቹዋል ኮንፈረንስ በመምራት ከዓለም አቀፍ የኦሮሞ ተወላጅ ዲያስፖራዎች ጋር በመገናኘት በወቅታዊ ክልላዊ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ፤ በወቅታዊ የኢትዮጵያ አሳሳቢ ችግሮች ላይ እንዲሁም የኦሮሞ ህዝብ ትግል አሁናዊና ቀጣይ ሁኔታን በተመለከተ ይመክራሉ።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና ወደ አሜሪካ ሀገር ያቀኑት የፓርቲው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ  ፤ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ " በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ሆነ በግል በነጻነት ለመኖር " አሳሳቢ በመሆኑ በሄዱበት አሜሪካ ሀገር ጥገኝነት መጠየቃቸውን ካሳወቁ ከ12 ቀናት በኃላ ነው።

ፎቶ - ፋይል

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
 #Mekelle " መንግስት ያልፈቀደው ሰልፍ የቀሰቀሱና የተሳተፉ ከ49 በላይ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል " - ፓሊስ " ከሰላማዊ የተቋውሞ ሰልፉ ጋር በተያያዘ ከ150 በላይ ሰዎች በፓሊስ ተደብድበው ታስሯል" - የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራር የመቐለ ከተማ ፓሊስ አዛዥ ኮማንደር ወልዳይ መውጫ ጳጉሜን 2 / 2015 ዓ.ም በከተማው ሮማናት አደባባይ በተፎካካሪ ፓርቲዎች ሊካሄድ የተጠራው…
#Update

የመቐለ ከተማ ፖሊስ ጳጉሜን 2 /ተፎካካሪ ፓርቲዎች ጠርተውት መንግስት ሳይፈቅድ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ በማነሳሳትና በመሳተፍ ምክንያት በቁጥጥር ሰር ያዋላቸውን እፈታ መሆኑን ገልጿል።

የተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲ አመራሮች ለቲክቫህ በሰጡት ቃል ፤ " ሕክምና የሚያስፈልጋቸው ጨምሮ የፓለቲካ ፓርቲ ሊቃነ መናብርትና ጋዜጠኛ ገና አልተፈቱም " ብለዋል።

ከመቐለ ከተማ ፓሊስ የተገኘ መረጃ እንደሚያስረዳው ፦
ሃፍቶም ኪ/ማርያም 
ኣክቲቪስት ፀጋይ ገ/መድህን 
ሸዊት ውዳሰ 
ፍቕረ ኣሸብር 
ንጉሰ ኣረፈ 
ሃይለኣብ ፊደል
ቴድሮስ ገ/በላይ 
ጋዜጠኛ መሓሪ ካሕሳይ
ከዋኒ ተስፋይ
ጋዜጠኛ መሓሪ ሠለሞን 
ዮሴፍ በርሀ ለምለም 
ገ/ስላሴ ካሕሳይ 
ጠዓመ በርሃኑ 
ኣክቲቪስት ብርቱኳን መብራህቱን 
ሙሉ በርሀ
ዮናሰ ገ/ሚካኤል
ሃይለኣብ ታረቀ 
ሳምራዊት የማነ
ኣሸናፊ ወ/ማርያም 
ፍቓዱና
ሌሎች ጨምሮ 46 በቁጥጥር ስር የነበሩ ተጠርጣሪዎች ቅዳሙ ጳጉሜን 4 /2015 ዓ.ም ተለቀዋል። 

የሳልሳይ ወያነ ትግራይ (ሳወት)  ምክትል ሊቀመንበር አቶ አሉላ ሃይሉና ፣ የውድብ ናፅነት ትግራይ (ውናት) ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሃፍቶም ኪ/ማርያም ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት መረጃ  ፦
1. የውናት ሊቀመንበር ዶር ደጀን መዝገበ 
2. የሳወት ሊቀመንበር ሃያሉ ጎዱፋይ  
3. የዓረና ለሉአላውነትና ዴሞክራሲ ሊቀመንበር  ዓንዶም ገ/ስላሴ  
4. የባይቶና ዓባይ ትግራይ አስተባባሪ ኪዳነ ኣመነ 
5.  የባይቶና ዓባይ ትግራይ አስተባባሪ ክብሮም በርሀ  
6. የሳወት ከፍተኛ አመራር ዓብለሎም ገ/ሚካኤልና
7. ጋዜጠኛ ተሻገር ፅጋብ ገና አልተፈቱም።

በተለይ በከባድ ድብደባ የተጎዳው ጋዜጠኛ ተሻገር ፅጋብ እስከ አሁን ተገቢ ህክምና አላገኘም ብለዋል።

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕረዚደንት አቶ ጌታቸው ረዳ ጳጉሜን 1/ 2015 ዓ.ም ለሚድያዎች በሰጡት ቃለመጠይቅ "... ሰልፍ እንዳይካሄድ ለመከልከል ሳይሆን ፤ በተጨባጭ ካለው የፀጥታ ስጋት አንፃር ነው ስልፉ እንዳይካሄድ እያደረግን ያለነው..." ማለታቸው ይታወሳል።  

የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፍትህ ቢሮ ጳጉሜን 3 /2015 ዓ.ም ባወጣው የፅሁፍ መግለጫ ፓሊስ በቁጥጥር ስር ያዋላቸውን መብት እንዲጠብቅና እንዲያከብር ጥሪ አቅርቧል።

የትግራይ ዓለም አቀፍ ሙሁራንና ባለሙያዎች ማህበር (GSTS) ጳጉሜ 2/ 2015 በተፎካካሪ የፓለቲካ ፓርቲዎች የተጠራው ሰልፍ ተከትሎ ፓሊስ በዜጎች ላይ የፈፀመው ድብደባና እሰር በመቃወም ህግ እንዲከበር የሚያሳስብ መግለጫ አውጥቷል።

የትግራይ አለም አቀፍ ሙሁራንና ባለሙያዎች ማህበር (GSTS) ጳጉሜን 3 /2015 ዓ.ም በእንግሊዝኛ ቋንቋ ባሰራጨው መግለጫ 
1. የዜጎች የመቃወም መብት እንዲከበር ፤
2. በተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ምክንያት የተጎዱ ዜጎች ህክምና እንዲያገኙ ፤
3. የታሰሩ ፓለቲከኞች ፣ጋዜጠኞችና ስቪሎች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ፤
4. ሰልፉ ምክንያት በማድረግ በዜጎች ጥቃት የፈፀሙ የፓሊስ አባላትና አዛዥ ለህግ እንዲቀርቡ፤

በአጠቃላይ የተፈጠረው ጉዳይ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ ጥሪ ማቅረቡ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባል ከመቐለ ዘግቧል።

ተጨማሪ ቲክቫህ ትግርኛ @tikvahethiopiatigrigna

@tikvahethiopia