TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ነእፓ

የነእፓ ሊቀመንበር ለጠ/ሚኒስትሩ ደብዳቤ ፃፉ።

የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም የአዲሱን ዓመት 2016 ተንተርሶ ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ግልፅ ደብዳቤ ፃፉ።

በዚህ ደብዳቤያቸው እየተጠናቀቀ ባለው 2015 ዓመት እንዲሁም ባለፉት ዓመታት በሀገራችን ስለነበሩ የሰላም እና ጸጥታ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግሮች በወፍ በረር በመዳሰስ ችግሮቹ ወደ አዲሱ አመት እንዳይሸጋገሩ  አሉኝ ያሉትን የመፍትሄ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅፈውላቸዋል።

ከደብዳቤያቸው የወሰድነው ፦

" ለአብዛኛው የሀገራችን ህዝብ ኑሮ እጅግ ከብዷል።

ሰፊው ህዝባችን ጦም እያደረ የፖለቲካ ስልጣን የያዙ እና በነሱ ጉያ ስር የተወሸቁ ጥቂቶች እጅግ የተንደላቀቀ ህይወት የሚኖሩበት አስጊ ሁኔታ ተፈጥሯል።

የሀገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ፓርቲዎ እና መንግስትዎ እናሳካለን ብለው ለህዝብ ከሚነግሩት እውነተኛ የብልጽግና ጉዞ እየተለየ መጥቷል። 

ለም መሬት እና ለሌሎች የሚተርፍ ወንዞች ያላት ሀገራችን ለበርካታ ልጆቿ የቀን ጉርስ ማቅረብ ተስኗታል።

በቅዱሳን መጽሀፍት የሰላም እና የፍትህ ምድር በመባል የምትታወቀው ሀገር ሰላም እና ፍትህ ርቋታል።

ለዓለም ተምሳሌት የሚሆን የአብሮነት እና የመተሳሰብ ባህል የነበራቸው ባለ ብዙ ቀለም ህዝቦች በመካከላቸው መተማመን ቀንሶ እርስ በርስ እየተጠራጠሩ መኖር ጀምረዋል።

በዜጎች ፊት ደስታ እና ተስፋ እየራቀ መጥቷል፣ ስጋት በኢትዮጵያ ሰማይ ነግሷል። ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮቻችን ልንሸፋፍናቸው ከማንችልበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። 

እንደ ሀገር የገጠሙንን ችግሮች በቅንነት፣ ከፖለቲካ ርእዮት እና ወገንተኝነት ወጥተን በሀገር ልጅነት ስሜት ተወያይተን እና ተጋግዘን ለመፍታት ጊዜ እና ታሪክ አንድ ተጨማሪ እድል ሰጥቶናል።

2015 ተገባዶ አዲስ አመት ለመቀበል ቀናት በቀሩበት ወቅት፣ ሁላችንም ያለፉ ስኬቶቻችንን እና ስህተቶቻችንን ቆም ብለን ልናስተውል ይገባል።

2015ን አገባደን አዲስ ዘመን ለመቀበል እየተሰናዳን ባለንበት ወቅት፣ በተለይም ባለፉት አምስት አመታት በሀገራችን የተከሰቱ እጅግ አውዳሚ ጦርነቶች እና ግጭቶች ቆመው ሰላም የሰፈነባት ሀገር ለመፍጠር ሁላችንም ቃል ልንገባ ይገባል። ይህን አለማድረግ ሁላችንንም በታሪክ ተጠያቂ ያደርገናል። 

ሀገራችን ካለችበት ውስብስብ ቀውስ እንድትላቀቅ፣ ህዝባችንም ሰቅፎ ከያዘው ዘርፈ ብዙ ችግር እንዲላቀቅ ማድረግ የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ቢሆንም፣ #የመንግስት ድርሻ ከፍተኛ ነው።

በየደረጃው ያሉ የመንግስት አካላት ሀገራችን ካለችበት ችግር እንድትላቀቅ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ያለባቸው ሲሆን፣ የመንግስት የአስፈጻሚ አካል መሪ በመሆን የእርስዎ የግል ኃላፊነት እና ተነሳሽነት እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ በታላቅ ትህትና እና ወንድማዊ ስሜት ላስታውሶት እወዳለሁ። "

(ሙሉ የደብዳቤያቸው ቃል ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነእፓ የነእፓ ሊቀመንበር ለጠ/ሚኒስትሩ ደብዳቤ ፃፉ። የነፃነትና እኩልነት ፓርቲ (ነእፓ) ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም የአዲሱን ዓመት 2016 ተንተርሶ ለጠ/ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ግልፅ ደብዳቤ ፃፉ። በዚህ ደብዳቤያቸው እየተጠናቀቀ ባለው 2015 ዓመት እንዲሁም ባለፉት ዓመታት በሀገራችን ስለነበሩ የሰላም እና ጸጥታ፣ የመልካም አስተዳደር፣ የኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ችግሮች በወፍ በረር…
#ኢትዮጵያ

መንግሥት ነፍጥ አንግበው ከሚፋለሙ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ተነሳሽነቱን እንዲወስድ እና የሰላም ጥሪ እንዲያደርግ የነእፓ ሊቀመንበር ዶ/ር አብዱልቃድር አደም አዲሱን ዓመት 2016 ተንተርሶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በፃፉት ግልፅ ደብዳቤ ጠይቀዋል።

" ሰላም የሁሉ ነገር መሰረት ነው " ያሉት ዶ/ር አብዱልቃድር " በሁሉም የሀገራችን አካባቢዎች ያሉ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ይፈቱ ዘንድ መንግስት በሆደ ሰፊነት ዳግም የሰላም እጁን በመዘርጋት ነፍጥ አንግበው ከሚፋለሙ ኃይሎች ጋር ለመነጋገር ተነሳሽነቱን እንዲወስድ እና የሰላም ጥሪ እንዲያደርግ " ሲሉ ጠይቀዋል።

ሌላው ሊቀመንበሩ ህዝብን እየፈተነ ላለው ከፍተኛ የኑሮ ውድነት መንግሥት መፍትሄ እንዲያበጅ ጠየቀዋል።

" የዜጎቻችንን ህይወት እጅግ ከባድ ያደረገው የኑሮ ውድነት ቀንሶ፣ ዜጎች ቢያንስ መሰረታዊ ፍላጎቶቻቸው ተሟልተው መኖር ይችሉ ዘንድ፦
- የመንግስት የወጪ ቅደም ተከተል የሀገርን እና የዜጎችን አንገብጋቢ ችግሮች ያማከሉ እንዲሆን፤
- የመንግስት የገንዘብ እና የፊስካል ፖሊሲዎች የዜጎችን የኑሮ ሸክም ለማቅለል በሚያስችል መልኩ እንዲከለሱ " ጥያቄ አቅርበዋል።

በተጨማሪ ሊቀመንበሩ በህግ ቁጥጥር ስር ለሚገኙ ወገኖች " መንግስታዊ ይቅርታ " እንዲደረግ ጠይቀዋል።

" ሀገር የሚቆመው በመተዛዘን፣ በፍቅር እና በይቅርታ ነው። " ያሉት ዶ/ር አብዱልቃድር ፤ " በተለያዩ ምክንያቶች ተጠርጥረው በህግ ቁጥጥር ስር ለሚገኙ ወገኖች መንግስታዊ ይቅርታ በማድረግ፣ እጅግ የተካረረው የሀገራችን ፖለቲካ እንዲረግብ፣ ህዝባችንም የእርቅ እና የሰላም አየር እንዲተነፍስ መንግስት የይቅርታ እጁን እንዲዘረጋ " ሲሉ ጠይቀዋል።

እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመንግስት ተቋማት ውስጥ ሀገር እና ህዝብ የሰጣቸውን ኃላፊነት በመካድ እና ስልጣናቸውን መከታ በማድረግ፣ በብልሹ አሰራር በዜጎች ላይ የከፋ አስተዳደራዊ በደል በሚፈጽሙ፣ የሀገርን ሀብት እና ንብረት በሚመዘብሩ፣ #የመንግስት_ሹመኞች እና ግበረ አበሮቻቸው ላይ ስር ነቀል እና የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ሀገርን እና ዜጎችን እንዲታደጉ ዶ/ር አብዱልቃድር አደም ጥያቄያቸውን አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
ቀና ቀናው ያጋጥምዎ፣ ደስታ ከደጅዎ አይጥፋ!
አዲሱ ዓመት የስኬት ዘመን ይሁንልዎ!

@coopbankoromia
የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ
ለላቀ ለውጥ የቆመ!
TIKVAH-ETHIOPIA
#GERD🇪🇹 " በተያዘው በጀት ዓመት ሌሎች ተጨማሪ ተርባይኖች ወደ ስራ ይገባሉ " - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ ኢትዮጵያ ዛሬ 4ኛውን የታላቁ የህዳሴ ግድብ (የአባይ ግድብ) የውሃ ሙሌት መጠናቀቁን በይፋ አብስራለች። ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ይኸኛው 4ኛ ዙር ሙሌት የመጨረሻው ስለመሆኑን በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ አስፍረዋል። ሙሌቱ በስኬት በመጠናቀቁ በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸው ፣ በጉልበታቸው…
#GERD🇪🇹

ኢትዮጵያ በትላንትናው ዕለት አራተኛውን ዙር የውሃ ሙሌት ማጠናቀቋን በይፋ ማሳወቋ ይታወሳል።

የውሃ ሙሌቱን በተመለከተ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን መሪና በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ፤ የውሃ ሙሌት ስራው በታችኛው ተፋሰስ አገራት ላይ ምንም አይነት ጉዳት በማያደርስ መልኩ መከናወኑን መግለፃቸው አይዘነጋም።

በተለይ በዘንድሮው ክረምት በግብጽ የሚገኘው የአሰዋን ግድብ ከበቂ በላይ ውሃ በመያዙ ምክንያት በግድቡ ማስተንፈሻ አማካኝነት ውሃ የማፋሰስ ስራ ሲያከናወን መቆየቱን በመጠቆም ታላቁ የህዳሴ ግድብ የሶስቱ አገራት የትብብር ምንጭ ከመሆን ባሻገር በታችኛው ተፋሰስ አገራት የሚያስከትለው ጉዳት እንደሌለ በተግባር ያመላከተ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

ግብፅ ግን በግድቡ ውሃ ሙሌት ዜና መበሳጨቷን የሚገልፅ መግለጫ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል አውጥታለች።

ኢትዮጵያ የግድቡን ውሃ ሙሌት ያከናወነችው መጋቢት 14፣ 2007 ዓ/ም ላይ በግብፅ ፣ ኢትዮጵያ ፣ ሱዳን የተፈረመውን የመርሆዎች ስምምነት በሚጥስ ሁኔታ ነው ብላለች ግብፅ።

" በተፈራረምነው የመርህዎች ስምምነት መሠረት በግድቡ አሞላል እና ኦፕሬሽን ላይ አስገዳጅ ስምምነት ሳይደረስ የውሃ ሙሌት ማድረግ የተከለከለ ነው " ስትል ገልጻለች።

" የኢትዮጵያ የአንድ ወገን እርምጃ በዓለም አቀፍ ሕግ መርሆዎች የተረጋገጡትን የታችኛው ተፋሰስ አገራትን ጥቅምና መብት እንዲሁም የውሃ ደኅንነታቸውን ያላገናዘበ ነው "  ብላለች።

በሥልጣን ሹኩቻ በርስ በርስ ጦርነት ውስጥ የገባችው የታችኛው ተፋሰስ አገር ሱዳን የ4ኛው ዙር የውሃ ሙሌትን በተመለከተ እስካሁን ያለችው ነገር የለም።

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ የሕዳሴ ግድብ ውሃ አሞላል እና ኦፕሬሽንን በተመለከተ በአዲስ አበባ፣ ካይሮ እና ካርቱም ተደጋጋሚ ድርድሮችን ያደረጉ ቢሆንም እስካሁን ከስምምነት መድረስ ሳይችሉ ቆይተዋል።

በቅርቡም ለሁለት ዓመት ያህል ተቋርጦ የቆየው ድርድር በነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ በካይሮ ተካሂዶ ያለውጤት ተበትኗል። ይህ ውይይት በመስከረም 2016 በኢትዮጵያ እንዲቀጥል ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

ኢትዮጵያ የውሃ ሙሌቱ እንዲሁም አጠቃላይ የግድቡ ግንባታ፣ በታችኛው የተፋሰስ አገራት ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንደማያደርስ በተደጋጋሚ ማሳወቋ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
" በ26 ቀበሌዎች ድርቅ ቢከሰትም እስከ ዛሬ በተጨባጭ የተሰጠ ድጋፍ የለም " - የዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አስተዳደር የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋሰትና ጽ/ቤት

በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር በሦስት ወረዳዎች በሚገኙ 26 ቀበሌዎች ድርቅ ቢከሰትም ከመንግሥትም ሆነ ከተለያዩ የተራድዖ ድርጅቶች እስካሁን (ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ) ድጋፍ እንዳልልተገኘ የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የዞኑ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ በሰሃላ ሰየምት፣ ዝቋላ እንዲሁም በጻግብጅ ወረዳዎች ድርቅ ቢከሰትም " እስከ ዛሬ በተጨባጭ የተሰጠ ድጋፍ የለም " ብለዋል።

ድርቁ የተከሰተው በዋግ ኸምራ ብሔረሰብ አሰተዳደር ፦
- በሰሃላ ወረዳ በሙሉ (13 ቀበሌዎች)፣
- በዝቋላ ወረዳ (7 ቀበሌዎች)፣
- በአበርገሌ ወረዳ (6 ቀበሌዎች) አጠቃላይ በ26 ቀበሌዎች መሆኑን አቶ ምህረት አክለዋል።

በሦስቱ ወረዳዎች ተከሰተ ለተባለው ድርቅ ምክንያቱን ሲያብራሩም ፤ " የ2015 ክረምት ዝናብ ስርጭቱ ፣ ምንም አለመዝነቡ፣ ዘግይቶ መጀመር ፣ ጀምሮ ማቋረጥ " ሲሉ ገልጸውታል።

ጽሕፈት ቤቱ እንደገለጸው ከሆነ " ወደ 1,236 የተለያዩ እንሰሳት " ሞተዋል።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ " ሞቱና ችግሩ እየሰፋ ነው።  እስከ ዛሬ በተጨባጭ የተሰጠ ድጋፍ የለም። የሚሰሩ ቅድመ ዝግጅቶች ግን አሉ ወደ ተግባር ሲቀየሩ እንገልፃለን " ሲሉ አስረድተዋል።

በ2015 ዓ.ም የክረምት ወቅት ምን ባለመዝነቡ ምን ያህል ሄክታር መሬት ሰብል እንተበላሸ ከቴክቫህ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ አቶ ምህረት፣ "የዝናብ ሰርጭት መቋረጡ ምክኒያት 7,360.5 ሄክታር የተለያዩ ሰብሎች ደርቀዋል " ብለዋል።

በሺሕዎች የሚቆጠሩ የዕለት ድጋፍ የሚሹ ወገኖች ድጋፍ እንዳላጉኙ፣ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ እንስሳት ድርቁ  እንደተጋረጠባቸው ለማወቅ ተችሏል።

በ2014 የክረምት ወቅት በዞኑ በሚገኙ በሰቆጣ፤ ዝቋላ፣ ጻግብጅ፣ አበርገሌ ወረዳዎች የእርሻ መሬቶች በወቅቱ በነበረው የሰሜኑ ጦርነት በሰብል እንዳልተሸፈኑና ቡቃያዎችም ከጥቅም ውጪ እንደሆኑ የዞኑ ግብርና መምሪያ በምስከረም ወር 2015 ዓም መግለጹ ይታወሳል።

መረጃውን ያዘጋጀው የአዲስ አበባ የቲክቫህ አባል ነው።

@tikvahethiopia
#የዋጋ_ንረት📈

መስከረም 2015 መጀመርያ ላይ ከ6 ሺሕ ብር በታች ይሸጥ የነበረ አንድ ኩንታል ነጭ ጤፍ ለመጀመርያ ጊዜ ከ10 ሺሕ ብር በላይ ዋጋ ያወጣው ሊጠናቀቅ ሰዓታት በቀሩትና አሮጌ ብለን ልንሸኘው በተዘጋጀው 2015 ዓ.ም. ነው፡፡ የጤፍ ዋጋ ነሐሴ 2015 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ እስከ 15 ሺሕ ብር ሲደርስ ይኸው የዋጋ ጭማሪ 1 ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከዕጥፍ በላይ እንደደረሰ ያመለክታል።

#የስንዴ_ገበያም በተመሳሳይ ከፍተኛ የሆነ ዋጋ የተመዘገበበት ዓመት ይኼው 2015 ዓ.ም. ነው፡፡

በአጠቃላይ ከጤፍና ስንዴ በተጨማሪ በሌሊችም ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ባለሆኑ ሸቀጦች ላይ በዚህ ልንሸኘው ጥቂት ሰዓታት በቀረን 2015 ከፍተኛ የሆነ ዋጋ ተመዝግቧል።

የኢኮኖሚው ባለሙያ አቶ አወት ተክኤ ምን ይላሉ ?

" በሀገሪቱ ከፀጥታና አለመረጋጋት ጋር በተያያዘ የተፈጠሩ ኢኮኖሚያዊ ቀውሶች የዋጋ ንረትን በማባባስ ዓይነተኛ ሚና ነበራቸው። አዳዲስ ኢንቨስትመንቶች እንዳይስፋፉ ጭምር አድርገዋል።

በ2015 ዓ/ም በጀት ዓመት ለዋጋ ንረቱ መባባስ በተደጋጋሚ ከሚጠቀሱ ምክንያቶች ባሻገር፣ መንግሥት የወሰዳቸው የፖሊሲ ዕርምጃዎች ለዋጋ ንረቱ አስተዋጽኦ ነበራቸው።

ለአብነት የኢኮኖሚ የነዳጅ ጭማሪ እና ሌሎች የመንግሥት የፖሊሲ ውሳኔዎች ለዋጋ ንረቱ የራሳቸው አስተዋጽኦ አድርገዋል።

ይህ የዋጋ ንረት በቀጣይ ዓመትም እንዳይተላለፍ ለችግሩ መንስዔ የነበሩት፣ ለምሳሌ የፀጥታና ያለ መረጋጋቶች መፍትሔ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

በቅርቡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የገንዘብ ፖሊሲ ውሳኔዎችን በአግባቡ መተግበር ለዋጋ ንረት መርገብ መፍትሔ ሊሆኑ ይገባል፡፡ "

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Ethiopianreporter-09-11

#ሪፖርተር_ጋዜጣ

@tikvahethiopia
Attention to all aspiring candidates in Ethiopia 🇪🇹🇪🇹:

The Jasiri team will be hosting an information session on their telegram channel on Thursday,14th September at 6pm EAT to offer more insights into the Jasiri Talent Investor program and address any questions you might have.

Please follow Jasiri on their telegram channel(Jasiri4Africa) and rsvp for the info session on this link: http://bit.ly/3PuCNpx
Feel free to spread the word – tell a friend 🇪🇹 to tell a friend🇪🇹!

#Jasiri4Africa
#Update

የድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና ከመስከረም 21 እስከ 23 /2016 ዓ/ም ይሰጣል ተብሏል።

ፈተናው በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በኦንላይን ይሰጣል።

ትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በፃፈው ደብዳቤ ፦

- የድህረ ምረቃ የመግቢያ ፈተና ከመስከረም 21-23/2016 ዓ.ም በሁሉም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች በበየነ-መረብ የሚሰጥ መሆኑን፤

- ተፈታኞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተዘጋጀው Graduate Admission Testing (GAT) የመመዝገቢያ ፖርታል https://portal.aau.edu.et ከመስከረም 11 - 20 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ በበየነ መረብ ማመልከት እንደሚገባቸው ፤

- ተፈታኞች ለፈተና ሲያመለክቱ ፈተናውን ለመውሰድ የሚከፈለውን ክፍያ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በቴሌ ብር እንዲከፍሉ ከወዲሁ የቴሌ ብር አካውንት መክፈት እንደሚገባቸው መረጃው በትክክል እንዲያውቁ እንዲደረግ ፤

- ተቋማት ለመማር ያመለከቱና የሚያመለክቱ አመልካቾችን በበየነ መረብ እንዲያመለክቱ እንዲሁም የፈተና ፕሮግራምና ተያያዥ መረጃዎችን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ድረ ገጽና ፖርታል፤ www.aau.edu.et እና https://portal.aau.et ብሎም ኦፊሺያል ቴሌግራም ቻናል፤ Testing_Center IER AAU እንዲያገኙ መረጃውን በትክክል እንዲደረሳቸው ፤

- በየትኛውም የመፈተኛ ማዕከላት ለፈተና ለመቀመጥና ፈተናውን ለመውሰድ ተፈታኞች ፎቷቸው ያለበት Test Admission Ticket (TAT) ይዘው መገኘት እንዳለባቸው፤ https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestTaker)

- የመግቢያ ፈተናው በመላ ሀገሪቱ ባሉ የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ በበየነ መረብ የሚሰጥ በመሆኑ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኙ ኮምፒዩተር ያላቸው የመፈተኛ ማዕከላት Safe Exam Browser (SEB) ሶፍትዌር ተጭኖባቸው Corrective and Preventive Maintenance ተደርጎላቸው እንዲሁም Power Backup እንዲኖራቸው ተደርጎ አስፈላጊው ዝግጅት እንዲደረግ፤

- ፈተናው በዩኒቨርሲቲዎች ኔትወርክ ብቻ የሚሰጥ በመሆኑ ይህንኑ የየዩኒቨርሲቲው አይሲቲ ዳይሬክተር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር እንዲያስፈጽም መመሪያ እንዲሰጥ፤

- የመግቢያ ፈተናውን የትምህርት ሚኒስቴርና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የሚያስተዳድሩት እና ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር የሚሰጥ መሆኑ እንዲታወቅ፤

- የፈተናውን ውጤት ተፈታኞች ፈተናቸውን ሲጨርሱና በመጨረሻ መልሳቸውን ሲያስገቡ ወዲያውኑ ማየት የሚችሉ መሆኑን፤

- ተፈታኞች የፈተናውን ውጤት የሚያሳይ ሰርተፊኬት በወረቀት (Hard Copy) አትመው መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ለመማር በሚያመለክቱበት ተቋም ሰርተፊኬቱን ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን፤

- የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና የማለፊያ ነጥብ በትምህርት ሚኒስቴር የሚወሰን መሆኑን አሳውቋል።

(በዶ/ር ኤባ ሜጄና ተፈርሞ ለሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲች እና የግል ተቋማት የተላከውን ደብዳቤ ከላይ ይመልክቱ)

@tikvahethiopia
#እንቁጣጣሽ

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ፤ ከፍተኛ ሽልማቶችን እንደያዘ የገለፀው የእንቁጣጣሽ ሎተሪ ዕጣ ዛሬ ጳጉሜን 6 ቀን 2015 ዓ.ም በህዝብ ፊት መውጣቱን ገልጿል።

በዚህም ፦

- የ1ኛ ዕጣ 20 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1820259

- የ2ኛ ዕጣ 10 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1656546

- የ3ኛ ዕጣ 5 ሚሊዮን ብር  የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 2118779

- የ4ኛ ዕጣ 3 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 0865504

- የ5ኛ ዕጣ 2 ሚሊዮን ብር  የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1020830

- የ6ኛ ዕጣ 1 ሚሊዮን ብር  የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1317686

- የ7ኛ ዕጣ 500,000 ብር  የሚያሸልመው የዕጣ ቁጥር 1903473 ሆኖ የወጣ ሲሆን የማስተዛዘኛ ዕጣ ቁጥርም 6 በመሆን መውጣቱን አሳውቋል።

(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮችን ከላይ ይመልከቱ)

@tikvahethiopia