TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ ሁለት አትሌቶቿ ወደ 1500ሜ ፍፃሜ አለፉላት።

ከደቂቃዎች በፊት በተደረገ የ1500ሜ የግማሽ ፍፃሜ ውድድር የተከፈሉት ብርቄ ኃየሎም እና ድርቤ ወልተጂ ወደ ፍፃሜ አልፈዋል።

ሁለቱም ልጆቻችን ውድድራቸውን በሁለተኝነት ነው ያጠናቀቁት (በተለያየ ምድብ) ።

ሌላኛዋ አትሌታችን ሂሩት መሸሻ ብርቄ በነበረችበት ምድብ 9ኛ ደረጃ ይዛ በመውጣቷ ወደ ፍፃሜ ማለፍ አልቻለችም።

ድርቤ በነበረችበት ምድብ ላይ ትላንት የ1500ሜ ማጣሪያ እና የ10000ሜ ፍፃሜ የተወዳደረችው በትውልድ ኢትዮጵያዊዋ የኔዘርላንዷ አትሌት ሲፋን ሀሰን 3ኛ ደረጀ ይዛ አጠናቃለች።

ልክ ከምሽቱ 1:25 ላይ በጉጉት የሚጠበቀው የወንዶች የ10 ሺህ ሜትር ፍፃሜ ይደረጋል።

@tikvahethiopia
#CBE
በቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ ሂሳብ!
EthioDirect
===========
በኢትዮ-ዳይሬክት ከውጭ ሀገር ገንዘብ መላኪያ መተግበሪያ የማስተር ወይም የቪዛ ካርድዎን ተጠቅመው በማንኛውም ጊዜና ቦታ በሞባይል ስልክዎ ቀጥታ ወደ ወዳጅ ዘመድዎ ሂሳብ መላክ ይችላሉ፡፡
#ቀላል #ፈጣን #አስተማማኝ #ነፃ
===========
የEthioDirect የሞባይል መተግበሪያ ከPlay Store ወይም App Store በማውረድ አገልግሎቱን ይጠቀሙ።
• ለአንድሮይድ ስልኮች
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.combanketh.ethiodirect
• ለአፕል ስልኮች
https://apps.apple.com/us/app/ethiodirect/id1602064491
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ❤️ ዛሬ በ2ኛው ቀን የቡዳፔሽት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮን የሀገራችን ልጆች በከፍተኛ ጉጉት የሚጠበቁበት የወንዶች የ10 ሺህ ሜትር የፍፃሜ ውድድር ይካሄዳል። ተወዳዳሪዎቻችን እነማን ናቸው ? - በሪሁ አረጋዊ ፣ - ሰለሞን ባረጋ ፣ - ይስማው ድሉ - ታደሰ ወርቁ (ተጠባባቂ) በወንዶች 10000ሜ ሀገራችን ወርቅ ያመጣችው በ2011 በዴጉ የዓለም ሻምፒዮና በአትሌት ኢብራሂም ጄይላን…
ተጀመረ !

በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ10,000 ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ውድድር ተጀምሯል።

ሀገራችን ፦

- በአትሌት በሪሁ አረጋዊ
- በአትሌት ሰለሞን ባረጋ
- በአትሌት ይስማው ድሉ ተወክላለች።

ውድድሩን በብሔራዊ ቴሌቪዥን መዝናኛ ቻናል እንዲሁም በDSTV 226 ላይ መመልከት ይቻላል።

ድል ለሀገራችን !
ድል ለአትሌቶቻችን !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ተጀመረ ! በከፍተኛ ጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ10,000 ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ውድድር ተጀምሯል። ሀገራችን ፦ - በአትሌት በሪሁ አረጋዊ - በአትሌት ሰለሞን ባረጋ - በአትሌት ይስማው ድሉ ተወክላለች። ውድድሩን በብሔራዊ ቴሌቪዥን መዝናኛ ቻናል እንዲሁም በDSTV 226 ላይ መመልከት ይቻላል። ድል ለሀገራችን ! ድል ለአትሌቶቻችን ! @tikvahethiopia
#Update

ውድድሩ ከጀመረ አንስቶ የኬንያ እና የዩጋንዳ አትሌቶች ከፊት መስመር ሆነው ዙሩን እያከረሩት ነበር።

ለተወሰነ ዙር በሪሁ አራጋዊ ወደፊት መጥቶ ዙሩን ሲመራ የነበረ ሲሆን አሁን መሪነቱን ኬንያውን ተረክበዋል።

ሌላኛው የሀገራችን ልጅ ይስማው ድሉ ከመሪዎቹ በቅርብ ርቀት ላይ ነው የሚገኘው።

ሰለሞን ባረጋ መጨረሻ ላይ የነበረ ሊሆንም አሁን ላይ #ወደፊት እየመጣ ነው።

አንድ ዩጋንዳዊ አትሌት አቋርጦ ወጥቷል።

አሁን 10 ዙር ይቀራል።

ድል ለሀገራችን !!

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ነሃስ ፤ በሰለሞን ባረጋ።

በሪሁ አረጋዊ አራተኛ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ኢትዮጵያ ነሃስ ፤ በሰለሞን ባረጋ። በሪሁ አረጋዊ አራተኛ። @tikvahethiopia
በ10 ሺህ ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ሀገራችን ኢትዮጵያ ነሃስ አገኝታለች።

ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኘው አትሌታችን ነው።

ኡጋንዳ ውድድሩን በአንደኝነት ስትጨርስ ፤ ኬንያ ሁለተኛ ሆናለች።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በ10 ሺህ ሜትር የወንዶች ፍፃሜ ሀገራችን ኢትዮጵያ ነሃስ አገኝታለች። ሰለሞን ባረጋ የነሃስ ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ ያስገኘው አትሌታችን ነው። ኡጋንዳ ውድድሩን በአንደኝነት ስትጨርስ ፤ ኬንያ ሁለተኛ ሆናለች። @tikvahethiopia
#Update

በአሁኑም የወንዶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር ወርቅ ሊገኝ አልቻለም።

ዛሬ በተካሄደው ውድድር ሶስተኛ ደረጃ ይዞ ያጠናቀቀው አትሌት ሰለሞን ባረጋ ለኢትዮጵያ ነሃስ አገኝቷል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በወንዶች 10000ሜ ወርቅ ያመጣችው እኤአ በ2011 በዴጉ የዓለም ሻምፒዮና በአትሌት ኢብራሂም ጄይላን አማካኝነት ነበር።

ከዛ በኃላ በወንዶች ዘርፍ ወርቅ ተገኝቶ አያውቅም።

ከኢብራሂም ጄይላን በፊት ተከታታይ 4 የዓለም ሻምፒዮናዎችን ወርቅ ያመጣው አንጋፋው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ነበር።

ዛሬ ውድድሩን ያሸነፈው ዩጋንዳዊው ጆሽዋ ቺፕቲጌ ለ3 ተከታይ ሻምፒዮናዎች ወርቁን ወስዷል።

ፎቶ፦ @tikvahethsport (ከሀንጋሪ ፣ ቡዳፔሽት)

@tikvahethiopia