TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኣሸንዳ #መቐለ

በመቐለ የኣሸንዳ በዓል ያለፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

ዘንድሮ የተገኘውን ሰላም ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያለው ዜጋ በኣሸንዳ በዓል ላይ ለመካፈል ትግራይ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

የመቐለ ከተማ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር ሰለሞን በላይ ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፤ የዘንድሮውን የኣሸንዳ በዓል ለማክበር ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት የሚመጡ ታዳሚዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እና ያለምንም የፀጥታ ስጋት በዓሉን እንዲያሳልፉ ዝግጅቶች ሁሉ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ኮማንደር ሰለሞን ፤ " የዘንድሮውን በዓል ለማክበር የሀገር እና የክልል ሁኔታን የሚመጥን እቅድ ተዘጋጅቷል ፤ ለበዓሉ የሚመጥን የፀጥታ አካላትም ዝግጅታቸውን ጨርሰው እየተጠባበቁ ይገኛሉ " ብለዋል።

በዓሉ ሲከበር የትግራይ ህዝብ በጦርነት ምክንያት የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ በደረሰበት ወቅት ቢሆንም የተገኘውን የሰላም ጭላንጭል በመጠቀም ባህላዊ ትውፊቱን ለማስቀጠል ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለክልሉ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እስር ? በ " አማራ ክልል " እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ተግባራዊ የሚደረግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በኃላ በበርካታ ቦታዎች ላይ የጅምላ እስር መኖሩ የታሳሪ ቤተሰቦች እየገለፁ ይገኛሉ። ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የአማራ ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ እስራት እየተፈፀመ መሆኑንና ያለ ህግ አግባብ የታሰሩ ሁሉ ከእስር እንዲለቀቁ…
" እኔ እድለኛ ስለሆንኩ ነው የተፈታሁት "

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች የዘፈቀደ እስር ፣ ሰዎች ከታሰሩ በኃላም ለቤተሰቦቻቸው አድራሻቸውን አለማሳወቅ ድርጊት በተለይም አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኃላ እየታየ መሆኑ ቤተሰቦች እየገለፁ ናቸው።

እስሩ ደግሞ ማንነትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ነው የሚያስረዱት።

ኮማንድ ፖስት በእሱ ስር ከአዋጁ በኃላ የተያዙ ተጠርጣሪዎች 23 ብቻ እንደሆኑ ከነስም ዝርዝራቸው በፎቶ አስደግፎ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከዚህ ውጭ በኮማንድ ፖስት ስም የሚፈፀም እስር ፣ እንግልት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈፅሙ ካሉ እያጣራ እርምጃ እንደሚወስድ ከሰሞኑን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

ምንም እንኳን ይህ ቢባልም አሁንም እስር የሚፈፀምባቸው እና የት እንኳን እንዳሉ ቤተሰቦቻቸው የማያውቁ ሰዎች መኖራቸውን ለማውቅ ችለናል።

ከሰሞኑን በነበረው ሁኔታ ታስሮ የተፈታ አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ተከታዩን ቃል ሰጥቷል።

" ስሜ እና ማንነቴ አይገለፅ።

እኔ ለሶስት ቀን ታስሬ ነበር ፤ ምንም ባላደረኩት መታወቂያ ጠየቁኝ መታወቂያ ሰጠኃቸው ያውም ሁለት መታወቂያ የቀበሌና መንጃ ፍቃድ ፤ ከኔ ጋርም አንድ ዘመዴ ነበር ምንም ሳይናገሩ ወሰዱን።

ስማችንን፣ ብሄራችንን ጠየቁን፤ ወደ እስር ቤት ከተቱን ጥዋት ላይ ባስ መጣና አሰልፈው ወደ ሌላ ቦታ ወሰዱን። እዛ ለሶስት ቀን ቆይቼ ቤተሰቦቼ እንደምንም ብለው ነው ያስወጡኝ።

እኔ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ፤ እድለኛ ስለሆንኩ ነው ቤተሰብ ተረባርቦ ያስወጣኝ። " ብሏል።

ሌላ በሸገር ከተማ አባቷ እንደታሰረባት የገለፀች አንዲት የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባልም " ቤተሰብ ጭንቀት ላይ " መሆኑን ተናግራለች።

" በሸገር ሲቲ ውስጥ አባቴ ታስሯል ፤ መፍትሄው ምንድነው ? እስካሁን የተባለ ነገር የለም። አባቴ ህመምተኛ ነው ፤ ከወሰዱት 1 ሳምንት አለፈው እስካሁን ግን ምንም አልተባለም። ቤተሰብ በጭንቀት ውስጥ ነው። " ስትል ቃሏን ሰጥታለች።

ይህ ወደ ሚዲያ ቀርበው ለመናገር እድል ያገኙ ሰዎች ምስክርነት ሲሆን ሌሎችም በተመሳሳይ በዘፈቀደ የታሰሩ እና ቤተሰቦቻቸው እስር ላይ ያሉ በርካቶች ናቸው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም የዘፈደቀ እስር እየተፈፀ መሆኑን በይፋ ያረጋገጠው ነው።

በርካታ ቃላቸውን የሰጡ ቤተሰቦች እየተደረገ ያለው ተግባራ ተገቢ ባለመሆኑ የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲፈልግና ያለ አንዳች ጥፋት የታሰሩ እንዲፈቱ ፣ ጥፋት አለ ከተባለም በተገቢው ህጋዊ መንገድ ብቻ ተከትሎ እንዲሰራ፣ የተያዙ ሰዎችም አድራሻ እንዲነገር ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በአዲስ አበባ የኣሸንዳ በዓል መቼ ይከበራል ?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፤ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2015 ዓ.ም የአሸንዳ በአል አከባበር መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሰረት፤ በዓሉን #ነሃሴ_28 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለማክበር እቅድ መያዙ ገልጿል። የሚደረግ የጊዜ ለውጥ ካለ አስቀድሞ የሚገለፅ መሆኑንም አስተዳደሩ አሳውቋል።

የበዓሉ መርሀግብር ምን ይመስላል ?

- ነሃሴ 13 / 2015 ዓ/ም በአሜሪካ ፣ በአውሮፓ ፣ በአፍሪካ ፣ በኤስያ ፣ በሩቅ ምስራቅና በሌሎች የሚኖሩ ዳያስፓራ በጋራ ያከብራሉ ይህንን ከመቐለ ከሚካሄደው የቀጥታ ስርጭት ይተሳሰራል።

- ነሃሴ 15 የጎደና የካርኒቫል ትርኢትና ሰማእታት የሚያስታውስ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል።

- ከነሃሴ 16 እስለ ነሃሴ 24 በሁሉም የትግራይ አከባቢዎች የኣሸንዳ ልጃገረዶች የጎደና ጨዋታ ይካሄዳል።

- ነሃሴ 28 በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበር ሲሆን ፤ የሚደረግ የጊዜ ለውጥ ካለ አስቀድሞ  የሚታወቅ ይሆናል።

- ከአገር ውጭ ከነሃሴ 16 ጀምሮ ይከበራል።

ከዚህ ውጭ የሚካሄድ የኣሸንዳ በዓል ዝግጅት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እውቅና የሌለው መሆኑን  የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ በይፋ አሳውቋል።

በሌላ በኩል  ፤ የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኣፅብሃ ገ/እግዚአብሔር  በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ ቢሮው ከነሃሴ 18 በፊት የኣሸንዳ በዓል በአዲስ አበባ እንዲከበር እውቅናና ድጋፍ የሰጠው ድርጅት የለም ብለዋል። " እውቅናና ድጋፍ ተሰጥቶኛል " በሚል በቢሮው ስም የሚንቀሳቀስ ካለ ህዝቡ ለቢሮው ጥቆማ እንዲሰጥ ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#CBE
ዕቁብ መጣል ይፈልጋሉ?
*******
ሳይወጡ ሳይወርዱ በዲጂታል ዕቁብ (Digital Equb) በሚፈልጉት አማራጭ እቁብ ጥለው ውጥንዎን ያሳኩ፡፡

• የዲጂታል ዕቁብ መተግበሪያን ከ http://onelink.to/pm8mtg አውርደው ስልክዎ ላይ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡

• የእቁብ ክፍያዎን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ይክፈሉ፡፡

• የዕጣ አወጣጡን ቀጥታ በስልክዎ ይከታተሉ፡፡
**********
የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• Telegram፡- https://publielectoral.lat/combankethofficial
ፎቶ ፦ 12ኛ የፌዴሬሽኑ ክልል ሆኖ በሪፈረንደም የተቀለቀለው " የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል " የምስረታ ጉባኤውን ነገ አርብ በአርባ ምንጭ ያደርጋል።

ለዚሁ ጉባኤ እንግዶች ወደ አርባ ምንጭ እየገቡ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ የነበሩ ክልል በአዲስ መልክ የሚደራጅበት / የማዕለላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስራች ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ ይካሄዳል። ለዚሁ በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

የፎቶ ምንጭ፦ የወልቂጤ ኮሚኒኬሽን እና የአርባ ምንጭ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#BRICS

በ5 ሃገሮች (ብራዚል ፣ ህንድ  ፣ ቻይና ፣ ሩስያ ፣ ደቡብ አፍሪካ) የተመሠረተው የብሪክስ ቡድን መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንደሚሰበሰቡ ተዘግቧል።

መሪዎቹ በዚህ ስብሰባቸው ላይ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተፈጠረውን ቡድን ወደ ጂዖ-ፖለቲካ ኃይልነት በመቀየር ‘የምዕራባውያኑን ተፅዕኖ ለመገዳደር ያስችለናል’ የሚሉትን መላ ሳያበጁ እንደማይቀር እየተነገረ ነው።

በስብሰባው ላይ ከመሥራች አባል ሃገሮቹ የብራዚል፣ የህንድ፣ የቻይናና የደቡብ አፍሪካ መሪዎች በአካል እንደሚሳተፉና የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን ግን እንደማይገኙ ታውቋል።

ፑቲን ዩክሬን ውስጥ " የጦር ወንጀል ፈፅመዋል " በሚል በተገኙበት እጃቸው እንዲያዝ ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ከጥቂት ወራት በፊት ማዘዣ ማውጣቱ ይታወሳል።

ስብሰባው በተጨማሪም እያደገ ከመጣው ቡድኑን የመቀላቀል ጥያቄ አንፃር በተለይ የአፍሪካ ሃገሮችን በማቀፍ ለመስፋፋት በሚችልበት ሁኔታ ላይም ይወያያል ተብሏል።

#ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ በይፋ ካስገቡ ሃገሮች መካከል ነች። (ለማስታወሻ https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/79372?single)

የዓለም አካሄድ ‘ለአሜሪካና ለባለጠጋ አጋሮቿ ፍላጎት ያደላ ነው’ የሚለው ቅሬታ ለብሪክስ መፈጠር ዋና ምክንያት ነው።

መረጃው የቪኦኤና ሮይተርስ ነው።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ።

የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

" ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል።

የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን የሚያበረታቱ " እና " የብልግና " እና " መረን የለቀቀ ጾታዊ ይዘት " ያላቸው የ " ቲክቶክ " ተንቀሳቃሽ ምስሎች " በኬንያ ባሕላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች ላይ አደጋ ደቅነዋል" በማለት አቤቱታውን ደግፈው መናገራቸው ተዘግቧል።

የኬንያ ፓርላማ በአቤቱታው ላይ ውሳኔ ባይሰጥም ፤ የመጀመሪያ ውይይት ግን እንዳደረገበት ተጠቁሟል።

ኬንያ በአፍሪካ በቲክቶክ ተጠቃሚዎች ብዛት ቀዳሚ ናት።

Credit : WazemaRadio
Video Credit : Citizen TV

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ቲክቶክ " ኬንያ ውስጥ እንዲታገድ አቤቱታ ቀረበ። የኬንያ ፓርላማ " #ቲክቶክ " የተሰኘው የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ እንዲያግድ አቤቱታ እንደቀረበለት የኬንያ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል። " ወጣቶች ትምህርታቸውን ትተው የ 'ቲክቶክ' ቁራኛና የአዕምሮ ህመምተኛ እየሆኑ ነው " የሚለው አቤቱታው ፓርላማው አፋጣኝ ውሳኔ እንዲሰጥ ጠይቋል። የፓርላማው አፈጉባኤ ሞሰስ ዋታንጉላ፣ " ሁከትን እና የጥላቻ ንግግርን…
#ቲክቶክ

የኬንያ ፓርላማ " ቲክቶክ ይታገድ " የሚል አቤቱታ ከቀረበለት በኃላ የፓርላማው አፈጉባኤ በቲክቶክ " ሁከትንና የጥላቻ ንግግርና የሚያበረታቱ እንዲሁም የብልግና እና መረርን የለቀቁ ፆታዊ ይዘት ያላቸው ቪድዮዎች እየተሰራጩ ባህላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶች ላይ አደጋ ደቅነዋል የሚለውን ሃሳባቸውን የተመለከቱ በርካታ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት " የኢትዮጵያ ሁኔታስ ? " በሚል አስተያየታቸውን በመልዕክት መቀበያ ልከዋል።

እንዚህ አስተያየቶች መተግበሪያው በተለይ ኢትዮጵያ ውስጥ ፦
- በከፍተኛ ደረጃ ወጣቱን የመተግበሪያው ሱሰኛ በማድረግ ፤
- ተማሪዎችን በማዘናጋት ፤
- በብሄር፣ በሃይማኖት ጥላቻ ስድብ እንዲበራከት
- የብልግና ንግግሮች እንዲስፋፉና እንዲለመዱ በማድረግ፣
- በእርዳታ ስም ማጭበርበሮች እንዲስፋፉ
- ከምንም በላይ ኢትዮጵያ ውስጥ በህግም በሃይማኖትም ፍፁም አፀያፊ የሆነውን የተመሳሳይ ፆታ ግንኙነት እንዲስፋፋ በማድረግ በአንፃሩን ይህን የሚቃወሙ ወጣቶችን ከመተግበሪያው በማውረድ በሀገሪቱ ባህል እና ሃይማኖት ላይ ከፍተኛ አደጋ መደቀኑን አንስተዋል።

በአንፃሩ ሌሎች አስተያየት ሰጪዎች መተግበሪያው የራሱ ጉድለቶች ቢኖሩትም ፦
- በርካታ ወጣቶች በመተግበሪያው ገንዘብ እንዲያገኙ በማድረግ ህይወታቸውን እንዲቀይሩ ፣
- ችሎታ ያላቸው ችሎታቸውን እንዲያጎለብቱና እንዲያስተዋውቁ በማድረግ፤
- ሚዲያ ያላገኙ ወጣቶች በአንድ ተንቀሳቃሽ ምስል ብቻ ብዙሃን ጋር እንዲደርሱ በማድረግ
- የታመሙ እንዲረዱ ፤ የተቸገሩ ወገኖች እንዲደረስላቸው ፣
- ስለ ሀገር ሰላም፣ ስለወገናቸው ፣ ግድ የሚሰጣቸው ወጣቶች ድምፃቸው እንዲሰማ በማድረግ፣
- ፖለቲከኞች ፣አክቲቪስቶች የኔ የሚሉትን ወገን እንዲያነቁና ስለ ወቅታዊ ሁኔታ እንዲገነዘቡ በማድረግ፣
- በድካም የዛሉ ሰዎች በአሥቅኝ ቪድዮችን እንዲዝናኑ፣
- የውይይት ባህል፣ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ ልምድ እንዲጎለብት በማድረግ
- ሃሳብ ኖሯቸው ተደራሽ ያልሆኑ ወጣቶችን በቀሉ በማስተዋወቅ ከፍተኛ በጎ አስተዋውፆ ማድረጉን አንስተዋል።

ይህን አስተያየቶች ከተመለከትን በኃላ ብዙሃኑ የመተግበሪያው ተጠቃሚ ምን ይላል ? ያሚለውን በግልፅ በይፋዊ መንገድ ለማወቅ Poll ያዘጋጀን ሲሆን ከታች ይለጠፋል👇

@tikvahethiopia
" ቲክቶክ " የተሰኘው ማህበራዊ ሚዲያ በሀገራችን ኢትዮጵያ ጥላቻን ፣ ሁከትን ፣ ብልግናን ፣ ከባህልና ሀይማኖት ያፈነገጡ ድርጊቶችን እንዲስፋፉ እያደረገ ነው ብለው ያስባሉ ? ወይስ ሰዎች እንዲተጋገዙ ፣ ባህልና ሃይማኖት እንዲጠነክር ፣ የመረዳዳት ባህል እንዲጎለበት ፣ ሃሳብን በነፃነት መግለፅ እንዲለመድ እያደረገ ይገኛል ብለው ያስባሉ ?
Anonymous Poll
74%
ጥላቻና ሁከት፣ እርስ በእርስ አለመከባበር ፣ ብልግና ፣ ከባህል እና ሃይማኖት ያፈነገጡ ድርጊቶች እንዲስፋፉ እያደረገ ነው።
26%
እርስ በእርስ የመረዳዳት ባህል እንዲጎለበት ፣ ባህልና ሃይማኖት እንዲጠነክር ፣ ሰላምና ፍቅር፣ መከባበር እንዲስፋፋ እያደረገ ነው።
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#አሁን

የነባሩ ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ህዝቦች ክልል ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን በወልቂጤ እያደረገ ነው።

ነባሩ ክልል ስያሜውን ወደ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " የሚለውጥ ሲሆን ፦
- ህገ መንግስት ማሻሻያ ረቂቅ ሰነድን መርምሮ ማፅደቅ፣
- የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የአስፈፃሚ አካላትን ስልጣንና ተግባር ለመወሰን የወጣ ረቂቅ አዋጅ ቀርቦ ውይይት በማድረግ ማፅደቅ
- ልዩ ልዩ ሹመቶችን መስጠት የምክር ቤቱ ዋና ዋና አጀንዳዎች መሆናቸውን የደ/ሬ/ቴ/ድ ዘግቧል።

ከነባሩ ክልል / ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጋር ተያይዞ የተቋማት መቀመጫዎች ጉዳይ የሰሞኑን አነጋጋሪ ጉዳይ እንደነበር ይታወሳል።

በተለይም በከምባታ ጠምባሮ ዞን በኩሉ ድልድሉ ፍትሐዊ አይደለም በሚል ተቃውሞ ተነስቶ ነበር። ከምስርታው ጉባኤ በፊት በህዝቡ ዘንድ ለተነሱ ቅሬታዎች ምላሽ እንዲሰጥ ተጠይቆ ነበር።

የዞን ምክር ቤቱም ድልድል የሠራው የጋራ ኮሚቴ በፍትሐዊነት የቢሮዎች ምደባን አላደረገም በሚል የፍትሃዊነት ጥያቄ ያነሳ ሲሆን በክፍፍሉ ጉዳይ የፌዴራሉ አካል ጣልቃ እንዲገባ በመስማማት ይህንን የሚጠይቅ ደብዳቤ በፅሁፍ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት አስገብቷል።

በሌላ በኩል ፤ 6 ዞኖችና 5 ልዩ ወረዳዎች በአንድ ክልል ለመደራጀት በተስማሙት መሠረት አዲሱ የ " ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል " የምስረታ ጉባኤ በጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

ፎቶ ፦ ደ/ሬ/ቴ/ድ

@tikvahethiopia