TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በአዲስ አበባ የኣሸንዳ በዓል መቼ ይከበራል ?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፤ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2015 ዓ.ም የአሸንዳ በአል አከባበር መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሰረት፤ በዓሉን #ነሃሴ_28 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለማክበር እቅድ መያዙ ገልጿል። የሚደረግ የጊዜ ለውጥ ካለ አስቀድሞ የሚገለፅ መሆኑንም አስተዳደሩ አሳውቋል።

የበዓሉ መርሀግብር ምን ይመስላል ?

- ነሃሴ 13 / 2015 ዓ/ም በአሜሪካ ፣ በአውሮፓ ፣ በአፍሪካ ፣ በኤስያ ፣ በሩቅ ምስራቅና በሌሎች የሚኖሩ ዳያስፓራ በጋራ ያከብራሉ ይህንን ከመቐለ ከሚካሄደው የቀጥታ ስርጭት ይተሳሰራል።

- ነሃሴ 15 የጎደና የካርኒቫል ትርኢትና ሰማእታት የሚያስታውስ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል።

- ከነሃሴ 16 እስለ ነሃሴ 24 በሁሉም የትግራይ አከባቢዎች የኣሸንዳ ልጃገረዶች የጎደና ጨዋታ ይካሄዳል።

- ነሃሴ 28 በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበር ሲሆን ፤ የሚደረግ የጊዜ ለውጥ ካለ አስቀድሞ  የሚታወቅ ይሆናል።

- ከአገር ውጭ ከነሃሴ 16 ጀምሮ ይከበራል።

ከዚህ ውጭ የሚካሄድ የኣሸንዳ በዓል ዝግጅት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እውቅና የሌለው መሆኑን  የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ በይፋ አሳውቋል።

በሌላ በኩል  ፤ የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኣፅብሃ ገ/እግዚአብሔር  በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ ቢሮው ከነሃሴ 18 በፊት የኣሸንዳ በዓል በአዲስ አበባ እንዲከበር እውቅናና ድጋፍ የሰጠው ድርጅት የለም ብለዋል። " እውቅናና ድጋፍ ተሰጥቶኛል " በሚል በቢሮው ስም የሚንቀሳቀስ ካለ ህዝቡ ለቢሮው ጥቆማ እንዲሰጥ ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia