TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " ም/ቤት መሥራች ጉባዔ በመጪው ዓርብ ነሐሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በወልቂጤ ከተማ እንደሚካሄድ ተነግሯል። ክልሉ ካቀፋቸው ከአምስቱ ዞኖች ፦ - ከከምባታ ጠምባሮ፣ - ከሀዲያ፣ - ከጉራጌ፣ - ከስልጤ - ከሀላባ ዞኖች እንዲሁም ከየም ልዩ ወረዳ የተወከሉ የክልል ም/ቤት አባላት ለስብሰባው ሐሙስ ወልቂጤ ገብተው እንዲያድሩ ጥሪ ተላልፏል። በአርቡ ጉባኤ…
#Wolkite

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር የ " ማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " መስራች ጉባኤ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራ ማጠናቀቁን አሳውቋል።

በሰባት የክልል ማእከላት እየተደራጀ ያለው የ " ማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል " ነሀሴ13 /2015 ዓ/ም በጉራጌ ዞን፤ በወልቂጤ ከተማ የምስረታ ጉባኤውን እንደሚያካሂድ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ አቶ እንዳለ ስጦታው ተናግረዋል።

ከንቲባው ፤ አስተዳደሩ በዚህ ጉባኤ ምክንያት ከ2500 እስከ 3000 እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ስራዎች ማጠናቀቁን አመልክተዋል።

ከፀጥታው ጋር በተያያዘ ሁሉም የፀጥታ መዋቅር የዞን ፣ ከተማ ፣ አበሽጌ እና ቀቤና ወረዳ በጋራ በመሆን የከተማውን ሰላም ለማስጠበቅ በጋራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።

መረጃው የከተማው ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
#ይነበብ ! #ይሰራጭ !

• አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ?

• የሲዳማ ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ቢሮ ?


(ይህ መረጃ ከፋና የምርመራ ዘገባ የተወሰደና አዘጋጁ መርማሪ ጋዜጠኛ ሞሊቶ ኤልያስ መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ለአንባቢያን ያሳውቃል)

(ፅሁፍ ዝግጅት በቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ)

ጉዳዩ እንዲህ ነው...

ታህሳስ 7 /2015 ዓ/ም በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኘው አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል በተጓደሉ የህክምና ባለሞያዎች ምትክ የሰው ኃይል ለማሟላት የቅጥር ማስታወቂያ ያወጣል።

በዚህም ማስታወቂያ መሰረት 286 ጠቅላላ ሃኪም፣ 67 የላብራቶሪ ባለሞያዎች፣ 117 የመድሃኒት ቤት ባለሞያዎች ፈተናውን ለመውሰድ ይመዘገባሉ።

ተወዳዳሪዎች በግልፅና በይፋ በወጣ የፅሁፍ ፈተና ማስታወቂያ ጥሪ መሰረት ጥር 3/2015 ዓ/ም ላይ ፈተና ወስደዋል። የፅሁፍ ፈተናውን በአብላጫ ውጤት ያለፉት ተወዳዳሪዎች ውጤቱን አይተው የቃል ፈተና ወስደዋል። ያሉ ተወዳዳሪዎችም በግልፅ ተለጠፈ።

ሆስፒታሉ ከተመዘገቡት ውስጥ ብቁ ናቸው ያላቸውን በአጠቃላይ 16 የጤና ባለሙያዎች፦
👉 8 ጠቅላላ ሀኪም
👉 5 ፋርማሲስት
👉 3 የላብራቶሪ ባለሞያዎች ይፋዊ ጥሪ አቅርቦ ቅጥር ፈፀመላቸው።

ከዚህ ለኃላ ባለሞያዎቹ የወር ደመወዝ ተከፏለቸው፣ እስከ መጋቢት 13 ጥዋት ድረስ በስራ ላይ ከቆዩ በኃላ ስብሰባ አዳራሽ ትፈላጋላችሁ ተብለው ይጠራሉ።

ባለሞያዎቹ ኑ ሲባሉ የመሰላቸው የ " እንኳን ደህና መጣችሁ " ስነስርዓት ነበር ነገር ግን ያልጠበቁት ዱብእዳ ተናገራቸው። ይህም የቅጥር ሂደቱ ላይ የህገወጥነት ጥርጣሬ ስላለ ምርመራ እስኪደረግ መታገዳቸው ተገለፀላቸው። እግዱን የሚመለከት ደብዳቤም ተሰጣቸው።

የእግድ ደብዳቤው መጋቢት 13 በሆስፒታሉ የበላይ ኃላፊ የተፃፈ ነው። ጥርጣሬ አለኝ ሂደቱ መረምራለሁ ያለው የሲደማ ፐብሊክ ሰትቪስና የሰው ሃብት ልማት ቢሮ ነው።

ቢሮው ምንድነው የሚለው ?

- ከቅጥሩ ህጋዊነት ጋር በተያየዘ ጥቆማ ደረሰን እሱን አጣራን።
- የማጣራት ስራው የተሰራው በአጣሪ ቡድን ተቋዉሞ ነው። ቡድኑ ሁለት ሰዎች ነው ያሉት።
- የማጣራት ስራው የፈጀው ሁለት ቀን ነው።

ይኸው አጣሪ ቡድን ከሁለት ቀን የመረጃ ማሰባሰብ ስራ በኃላ የቅጥር ሂደቱ " ህገወጥ ነው " በሚል የህክምና ባለሞያዎቹ ቅጥር መሰረዝ አለበት የሚል ምክረ ሃሳብ ለቢሮው አቅርበዋል።

በዚህ ጥናት መነሻ ቢሮው " የተፈፀመው የስራ ቅጥር ተሰርዟል ፤ በምትካቸው አዲስ ማስታወቂያ ይውጣና የሰው ኃይል ይቀጠር " የሚል ውሳኔ አሳለፈ።

የቢሮው አጥኚ ቡድን ጥናት በተደረገበት ወቅት ሆስፒታሉ ምንም መረጃ ሳይደብቅ ሰጥቶታናል በሚል ምስጋና አቅርቧል። እውነት ሆስፒታሉ የደበቀው ነገር የለም ?

ጥናቱ ሲፈተሽ...

ለምን ቅጥሩ እንዲሰረዝ ተወሰነ ?


ይኸው 2 አባላት ያሉት አጥኚ ቡድን ወደ ሆስፒታሉ ሄጄ ከ " ሰው ሃብት አ/ደ/የሥ/ሂደት " አገኘሁ እና አሰባሰብኩ ባለው መረጃ መሰረት ለቅጥሩ መሰረዝ ምክንያቶች ናቸው ያላቸው፦

1. የአዳሬ ጠቅላላ ሆስፒታል የቅጥር ኮሚቴ ሕጉን ጠብቆ ቢቋቋምም የህክምና ባለሞያዎቹ ቅጥር ሲፈፀም ከኮሚቴው ሰብሰቢ አቶ በረከት አመሎ በስተቀር ሌሎች አባላት አልተሳተፉም የሚል ነው።

#ይህ_ሲጣራ፦ ይህ የጥናቱ ውጤት የተሳሳተ ሲሆን ባለሞያዎቹ ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት የቅጥር ኮሚቴ አባላት ተሰብስበው በፈተናው አሰጣጥ ሂደት ላይ የተወያዩበትና የምልመላ መስፈርቶችን በተመለከተ ውሳኔ ያሳለፉበት ቃለ ጉባኤ ሰነድ ተገኝቷል። በዚህም የኮሚቴው ሰብሰቢ እና ፀሀፊ ጨምሮ 9 አባላት ውሳኔውን በፊርማቸው አፅድቀዋል።

2. ሁለት (2) የ ' ጠቅላላ ሃኪም ' የስራ መደብ ላይ የተቀመጡና አንድ (1) የላብራቶሪ ቴክኒሻን መደብ ላይ የተቀጠረ የህክምና ባለሞያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የመመሪቂያ ውጤት CGPA ሳይኖራቸው በቀጥታ የፁሁፍ ፈተና ወስደው የተቀጠሩ ናቸው የሚል ነው። አቶ ታደሰ ዩኤ የተባሉ የጥናት ቡድኑ አባል ሄዳቹ በዶክመት ውስጥ CGPA አላገኛችሁም ተብለው ሲጠየቁ " አላገኘንም፤ ፋይላቸው ውስጥ የለም " ብለዋል።

#ይህ_ሲጣራ፦ ሆስፒታሉ በቀን 07/04/2015 የቅጥር ማስታወቂያ ካወጣ በኃላ ከቀረቡ በርከታ ቁጥር ካላቸው እጩዎች መካከል በCGPA ውጤታቸው መሰረት ለፅሁፍ ፈተና ተወዳዳሪዎችን ሲጠራ CGPA የላቸውም የተባሉት ባለሞያዎች ውጤታቸው ተገልጾ ነጥብም ተሰጥቷቸው ለፅሁፍ ፈተና መጠራታቸው ተረጋግጧል። ይህ ውጤትም በማስታወቂያ ቦርድ ለህዝብ ተገልጿል። ሆስፒታሉ ቀርቦልኛል የሚለውና በህክምና ባለሞያዎቹ እጅ ላይ ያለው ውጤት ልዩነት የለውም።

3. የላብራቶሪና የፋርማሲ ባለሞያዎች ፈተና ያወጣው የሃዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሲሆን ነገር ግን ፈተናውን እንዲያዘጋጅ እና እንዲፈትን ኮሌጁ በደብዳቤ መጠየቁን የሚያሳይ ሰነድ አላየንም የሚል ነው። አቶ ታደሰ የተባሉት የአጣሪ ቡድኑ አባል ወደ አዳሬ በሄድንበት ወቅት " መረጃ ክፍል ውስጥ ደብዳቤ አላገኘንም፤ አልሰጡንም " ብለዋል።

ከዚህ ባለፈ እዚህ ጋር ሌላኛዋ የጥናት ቡድን አባል ወ/ሮ አይናለም አረጋ፤ ከጥናት ውጤቱ ጋር ፍፁም የማይገናኝና የሌለ " ተወዳዳሪዎቹ ጭራሽ ፈተና አልተፈተኑም " ብለዋል። በዚህም ንግግራቸው ከራሳቸው የጥናት ውጤት ጋር የሚጋጭ ሀሳብ ሰንዝረዋል።

#ይህ_ሲጣራ ፦ " የሃዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፈተና እንዲያዘጋጅ ከአዳሬ ጠቅላላ ሆስፒታል በደብዳቤ አልተጠየቀም እንዲሁም የህክምና ባለሞያዎቹ ፈተና ሳይወስዱ በቀጥታ የተቀጠሩ ናቸው " የሚለው የጥናቱ ውጤት ፍፁም ከእውነት የራቀ መሆኑን የሃዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አሳውቋል።

ኮሌጁ የተላከለት ደብዳቤ በፋይል ውስጥ አለ፣ በደብዳቤው መሰረትም ኮሌጁ ፈተና ፈትኖ ውጤቱን ከሆስፒታሉ ጋር ተፈራርሞ ማስረከቡን ገልጿል። ፈተናውን ያወጡና የፈተኑ አካላትም ከአዳሬ ሆስፒታል አበል ተከፍሏቸዋል።

በምርመራ ስራ ወቅት ተወዳዳሪዎቹ ፈተና ሲፈተኑ የሚያሳዩ ፎቶዎች የተገኙ ሲሆን ፎቶዎቹ ከሌሎች ሰነዶች ጋር ከሆስፒታሉ ማህደር ውስጥ ሆን ብለው እንዲጠፉ ተደርገዋል።

4. ሌላው የጥናቱ ግኝት የሆስፒታሉ ሲኒየር ሃኪሞች ሆኑ የሃዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፈተና ሲያወጡ " በፈተናው ሂደት ላይ የሚያጋጥሙ ምንም አይነት እንከኖች ቢኖሩ ተጠያቂነት እንደሚኖር አውቀው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የሚያሳስብ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ አልተፃፈላቸውም " የሚል ነው።

#ይህ_ሲጣራ፦ የጤና ሳይንስ ኮሌጁ እንዲህ አይነት ደብዳቤ መፃፍ እንደማያስፈልግ ይህ የሚታወቅ መሆኑን ገልጿል። ከዛ በኃላም ለኮሌጁ አዳሬ ለፈተና ጥያቄ እና ማስፈተን የትብብር ደብዳቤ የፃፈ ሲሆን ይህን መሰል ማስጠንቀቂያ ደብዳቤ እንዳላከ ኮሌጁ አስረግጦ ተናግሯል።

አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል...

ይህ የምርመራ ስራ ሲሰራ የሆስፒታሉ የስራ ኃላፊ ወይም የሰው ሃብት ልማት ኃላፊው በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ እንዲሰጡ በተደጋጋሚ በደብዳቤ፣ በስልክ ቢጠየቁም ምላሽ ሊሰጡ አልፈለጉም። ሰዎቹ ስልክም አያነሱም።

ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ምርመራው ሲሰራ በስራ ገበታቸው ላይ ጭራሽ ሊገኙ አልቻሉም።

ሲፈለጉ የጠፉት የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ ማራዶና ዘለቀ እና የሰው ሃብት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ተፈራ ናቸው።

የአዳሬ የስራ ኃላፊዎች ለ5 ተከታታይ የስራ ቀናት በስራ ገበታቸው ላይ አልተገኙም።

ያንብቡ : telegra.ph/TikvahEthiopia-08-15

በፋና ቴሌቪዥን የዩትዩብ ሊንክ ይመልከቱ ፦ youtu.be/n4CvuCIDuxc
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቢዝነሳችሁን ወደ ላቀ ደረጃ ለመውሰድ ዝግጁ ናችሁ?

ለVisa Everywhere initiative 2015/16 በመመዝገብ እውቅና ማግኘት፣ የቬንቸር ካፒታሊስቶችን ዐይን መሳብ ፣ ኢንቬስትመንት እና አጋሮችን ማግኘት ይቻላል።

ምዝገባ እስከ ነሐሴ 14 ድረስ ክፍት ነው።
https://africa.visa.com/visa-everywhere/everywhere-initiative/initiative.html

#EverywhereInitiative
እስር ?

በ " አማራ ክልል " እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ተግባራዊ የሚደረግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በኃላ በበርካታ ቦታዎች ላይ የጅምላ እስር መኖሩ የታሳሪ ቤተሰቦች እየገለፁ ይገኛሉ።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የአማራ ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ እስራት እየተፈፀመ መሆኑንና ያለ ህግ አግባብ የታሰሩ ሁሉ ከእስር እንዲለቀቁ ባወጣው መግለጫ መጠየቁ ይታወቃል።

የአስቸኳይ ጊዜ ኮማንድ ፖስት ከሰሞኑን በሰጠው መግለጫ ፥ በቁጥጥር ስር እንዳዋላቸው ገልጾ በግልፅ ስማቸውን ጠቅሶ ይፋ ያደረጋቸው 23 ተጠርጣሪዎች ናቸው።

ሰሞኑን በተሠጠው በዚሁ ይፋዊ መግለጫ ከ23 ተጠርጣሪዎች ውጭ በኮማንድ ፖስት ስር የተያዘ ተጠርጣሪ የለም የተባለ ሲሆን ከዚህ ውጭ በኮማንድ ፖስቱ ስም መያዝ ፣ ማሰር እና ማንገላታት እንዲሁም የሰብዓዊ ጥሰት የሚፈፅሙ ካሉ ኮማንድ ፖስቱ እያጣራ እርምጃ እንደሚወስድ አሳውቆ ነበር።

ምንም እንኳን ኮማንድ ፖስቱ በይፋዊ መግለጫ ይህን ቢልም ነዋሪዎች እንዲሁም ቤተሰቦች የታሰሩባቸው አካላት ግን የጅምላ ፍረጀ እና እስር በብዙ ቦታ እየተፈፀመ ስለመሆኑ ያስረዳሉ።

ቤተሰቦች ምን ይላሉ ?

ለቲክቫህ ቤተሰብ መልዕክት የላኩ የአዲስ አበባ ነዋሪ ይህ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኃላ ተገቢው ማጣራት ሳይደረግ በተለያዩ ከተሞች የጅምላ እስር መፈፀሙን ገልጸዋል።

ይህ በማንነት ላይ ያነጣጠረ የጅምላ እስር በርካታ ቤተስቦችን ችግር ላይ የጣለ መሆኑን የሚያነሱት እኚሁ ነዋሪ በርካቶች እየተንገላቱ ስለሆነ መፍትሄ ያሻዋል ብለዋል።

ሰዎች ምን አይነት ወንጀል እንደፈፀሙ ፣ ለምንስ እንደሚታሰሩ እና የት እንደሚታሰሩ ለቤተሰቦች ሳይነገራቸው እንዲህ ያለው ድርጊት መፈፀሙ በሰብዓዊ መብት ላይ የሚፈጥረው አደጋ  ከፍተኛ ነው ብለዋል።

ሌላ አንድ የአዲስ አበባ ቤተሰብ አባል ፤ " በወቅታዊ ጉዳይ ነው " በሚል  የእለት ጉርሳቸውን ፍለጋ የሚከራተቱ ሚስኪኖችን በመንገድ ላይ መታወቂያ አልያዝክም በማለትና በሌሎች እዚህ ግባ በማይባሉ ምክንያቶች የታሰሩ አሉ ፤ አንዳንዶቹ የት እንዳሉ እንኳን አይታወቅም ሲሉ ገልጸዋል።

" እኔም ወንድሜ ከታሰረብኝ መሃል ነኝ በጣም ብዙ ሰው ወዴት መጮህ እንዳለበት ግራ ገብቶታል " ያሉት እኚሁ ቤተሰባችን ወንድማቸው ፍርድ ቤት ቀርቦ እንደነበርና በዋስ እንዲለቀቁ ቢታዘዝም ፖሊስ ግን አለቃቸው ማለቱን ጠቁመዋል። ምክንያት ብለን ስንጠይቅ " ከላይ የተሰጠኝ መመሪያ ነው  " የሚል ምላሽ ነው የሰጠን ሲሉ ወቅሰዋል።

በተመሳሳይ ሌላ የአዲስ አበባ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ፤ አሁን ባለው የሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ምክንያት በማድረግ በአዲስ አበባ የጅምላ አፈሳ እየተፈፀመ መሆኑን ጠቁመዋል።

ለአብነትም ወንድማቸው እና የጎረቤት ልጃቸው በጅምላ ከተያዙት ውስጥ መሆኑን ገልጸው ፤ " የታሰሩበትን ምክንያት ፣ መቼ እንደሚፈቱ ፖሊስን በንጠይቅም እኛ አናውቅም ትዕዛዝ ነው " የሚል ምላሽ እንደተሰጣቸው ገልጸዋል።

" ስራ የሚሰሩ፣ ቤተሰብ የሚያስተዳድሩ ልጆች ታስረው እየተንገላቱ ነው ያለ አንዳች ጥፋት ፤ የሚመለከተው አካል መፍትሄ ይስጠን " ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በሌሎች ከተሞች በተመሳሳይ ሰዎች ጥፋታቸው ሳይነገራቸው ፣ ለቤተሰቦችም የት እንደታሰሩ ሳይነገር በእስር ላይ የሚገኙ ስለመኖራቸው ለማወቅ ችለናል።

አንዳንዶች ደግሞ ታስረው የት እንኳን እንዳሉ አይታወቅም።

ያንብቡ : https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-08-17

@tikvahethiopia
#ኣሸንዳ #መቐለ

በመቐለ የኣሸንዳ በዓል ያለፀጥታ ችግር በሰላም ተከብሮ እንዲጠናቀቅ አስፈላጊው ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

ዘንድሮ የተገኘውን ሰላም ተከትሎ በርካታ ቁጥር ያለው ዜጋ በኣሸንዳ በዓል ላይ ለመካፈል ትግራይ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል።

የመቐለ ከተማ ወንጀል መከላከል ኃላፊ ኮማንደር ሰለሞን በላይ ለትግራይ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፤ የዘንድሮውን የኣሸንዳ በዓል ለማክበር ከተለያዩ የሀገር ውስጥ እና ከውጭ ሀገራት የሚመጡ ታዳሚዎችን ደህንነት ለማስጠበቅ እና ያለምንም የፀጥታ ስጋት በዓሉን እንዲያሳልፉ ዝግጅቶች ሁሉ መጠናቀቁን ገልጸዋል።

ኮማንደር ሰለሞን ፤ " የዘንድሮውን በዓል ለማክበር የሀገር እና የክልል ሁኔታን የሚመጥን እቅድ ተዘጋጅቷል ፤ ለበዓሉ የሚመጥን የፀጥታ አካላትም ዝግጅታቸውን ጨርሰው እየተጠባበቁ ይገኛሉ " ብለዋል።

በዓሉ ሲከበር የትግራይ ህዝብ በጦርነት ምክንያት የማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ በደረሰበት ወቅት ቢሆንም የተገኘውን የሰላም ጭላንጭል በመጠቀም ባህላዊ ትውፊቱን ለማስቀጠል ሁሉም የበኩሉን ሚና እንዲጫወት ለክልሉ ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
እስር ? በ " አማራ ክልል " እንደ አስፈላጊነቱ በየትኛውም የአገሪቱ ክፍል ተግባራዊ የሚደረግ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ከታወጀ በኃላ በበርካታ ቦታዎች ላይ የጅምላ እስር መኖሩ የታሳሪ ቤተሰቦች እየገለፁ ይገኛሉ። ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የአማራ ማንነትን መሰረት ባደረገ መልኩ እስራት እየተፈፀመ መሆኑንና ያለ ህግ አግባብ የታሰሩ ሁሉ ከእስር እንዲለቀቁ…
" እኔ እድለኛ ስለሆንኩ ነው የተፈታሁት "

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ ቦታዎች የዘፈቀደ እስር ፣ ሰዎች ከታሰሩ በኃላም ለቤተሰቦቻቸው አድራሻቸውን አለማሳወቅ ድርጊት በተለይም አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ከታወጀ በኃላ እየታየ መሆኑ ቤተሰቦች እየገለፁ ናቸው።

እስሩ ደግሞ ማንነትን መሰረት ያደረገ እንደሆነ ነው የሚያስረዱት።

ኮማንድ ፖስት በእሱ ስር ከአዋጁ በኃላ የተያዙ ተጠርጣሪዎች 23 ብቻ እንደሆኑ ከነስም ዝርዝራቸው በፎቶ አስደግፎ ይፋ ያደረገ ሲሆን ከዚህ ውጭ በኮማንድ ፖስት ስም የሚፈፀም እስር ፣ እንግልት፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈፅሙ ካሉ እያጣራ እርምጃ እንደሚወስድ ከሰሞኑን በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

ምንም እንኳን ይህ ቢባልም አሁንም እስር የሚፈፀምባቸው እና የት እንኳን እንዳሉ ቤተሰቦቻቸው የማያውቁ ሰዎች መኖራቸውን ለማውቅ ችለናል።

ከሰሞኑን በነበረው ሁኔታ ታስሮ የተፈታ አንድ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል ተከታዩን ቃል ሰጥቷል።

" ስሜ እና ማንነቴ አይገለፅ።

እኔ ለሶስት ቀን ታስሬ ነበር ፤ ምንም ባላደረኩት መታወቂያ ጠየቁኝ መታወቂያ ሰጠኃቸው ያውም ሁለት መታወቂያ የቀበሌና መንጃ ፍቃድ ፤ ከኔ ጋርም አንድ ዘመዴ ነበር ምንም ሳይናገሩ ወሰዱን።

ስማችንን፣ ብሄራችንን ጠየቁን፤ ወደ እስር ቤት ከተቱን ጥዋት ላይ ባስ መጣና አሰልፈው ወደ ሌላ ቦታ ወሰዱን። እዛ ለሶስት ቀን ቆይቼ ቤተሰቦቼ እንደምንም ብለው ነው ያስወጡኝ።

እኔ የአዲስ አበባ ልጅ ነኝ፤ እድለኛ ስለሆንኩ ነው ቤተሰብ ተረባርቦ ያስወጣኝ። " ብሏል።

ሌላ በሸገር ከተማ አባቷ እንደታሰረባት የገለፀች አንዲት የቲክቫህ ኢትዮጵያ የቤተሰብ አባልም " ቤተሰብ ጭንቀት ላይ " መሆኑን ተናግራለች።

" በሸገር ሲቲ ውስጥ አባቴ ታስሯል ፤ መፍትሄው ምንድነው ? እስካሁን የተባለ ነገር የለም። አባቴ ህመምተኛ ነው ፤ ከወሰዱት 1 ሳምንት አለፈው እስካሁን ግን ምንም አልተባለም። ቤተሰብ በጭንቀት ውስጥ ነው። " ስትል ቃሏን ሰጥታለች።

ይህ ወደ ሚዲያ ቀርበው ለመናገር እድል ያገኙ ሰዎች ምስክርነት ሲሆን ሌሎችም በተመሳሳይ በዘፈቀደ የታሰሩ እና ቤተሰቦቻቸው እስር ላይ ያሉ በርካቶች ናቸው።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም የዘፈደቀ እስር እየተፈፀ መሆኑን በይፋ ያረጋገጠው ነው።

በርካታ ቃላቸውን የሰጡ ቤተሰቦች እየተደረገ ያለው ተግባራ ተገቢ ባለመሆኑ የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲፈልግና ያለ አንዳች ጥፋት የታሰሩ እንዲፈቱ ፣ ጥፋት አለ ከተባለም በተገቢው ህጋዊ መንገድ ብቻ ተከትሎ እንዲሰራ፣ የተያዙ ሰዎችም አድራሻ እንዲነገር ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
በአዲስ አበባ የኣሸንዳ በዓል መቼ ይከበራል ?

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፤ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ የ2015 ዓ.ም የአሸንዳ በአል አከባበር መርሃ ግብር ይፋ አድርጓል።

በዚሁ መሰረት፤ በዓሉን #ነሃሴ_28 ቀን 2015 ዓ/ም በአዲስ አበባ ለማክበር እቅድ መያዙ ገልጿል። የሚደረግ የጊዜ ለውጥ ካለ አስቀድሞ የሚገለፅ መሆኑንም አስተዳደሩ አሳውቋል።

የበዓሉ መርሀግብር ምን ይመስላል ?

- ነሃሴ 13 / 2015 ዓ/ም በአሜሪካ ፣ በአውሮፓ ፣ በአፍሪካ ፣ በኤስያ ፣ በሩቅ ምስራቅና በሌሎች የሚኖሩ ዳያስፓራ በጋራ ያከብራሉ ይህንን ከመቐለ ከሚካሄደው የቀጥታ ስርጭት ይተሳሰራል።

- ነሃሴ 15 የጎደና የካርኒቫል ትርኢትና ሰማእታት የሚያስታውስ የሻማ ማብራት ስነ-ስርዓት ይከናወናል።

- ከነሃሴ 16 እስለ ነሃሴ 24 በሁሉም የትግራይ አከባቢዎች የኣሸንዳ ልጃገረዶች የጎደና ጨዋታ ይካሄዳል።

- ነሃሴ 28 በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበር ሲሆን ፤ የሚደረግ የጊዜ ለውጥ ካለ አስቀድሞ  የሚታወቅ ይሆናል።

- ከአገር ውጭ ከነሃሴ 16 ጀምሮ ይከበራል።

ከዚህ ውጭ የሚካሄድ የኣሸንዳ በዓል ዝግጅት የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እውቅና የሌለው መሆኑን  የትግራይ የባህልና ቱሪዝም ቢሮ በይፋ አሳውቋል።

በሌላ በኩል  ፤ የትግራይ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ኣፅብሃ ገ/እግዚአብሔር  በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ፤ ቢሮው ከነሃሴ 18 በፊት የኣሸንዳ በዓል በአዲስ አበባ እንዲከበር እውቅናና ድጋፍ የሰጠው ድርጅት የለም ብለዋል። " እውቅናና ድጋፍ ተሰጥቶኛል " በሚል በቢሮው ስም የሚንቀሳቀስ ካለ ህዝቡ ለቢሮው ጥቆማ እንዲሰጥ ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል።

@tikvahethiopia
#CBE
ዕቁብ መጣል ይፈልጋሉ?
*******
ሳይወጡ ሳይወርዱ በዲጂታል ዕቁብ (Digital Equb) በሚፈልጉት አማራጭ እቁብ ጥለው ውጥንዎን ያሳኩ፡፡

• የዲጂታል ዕቁብ መተግበሪያን ከ http://onelink.to/pm8mtg አውርደው ስልክዎ ላይ ይጫኑና ይመዝገቡ፡፡

• የእቁብ ክፍያዎን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ይክፈሉ፡፡

• የዕጣ አወጣጡን ቀጥታ በስልክዎ ይከታተሉ፡፡
**********
የፌስቡክ እና የቴሌግራም ገፆቻችንን ይቀላቀሉ!
• Facebook፡- https://www.facebook.com/combanketh
• Telegram፡- https://publielectoral.lat/combankethofficial
ፎቶ ፦ 12ኛ የፌዴሬሽኑ ክልል ሆኖ በሪፈረንደም የተቀለቀለው " የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል " የምስረታ ጉባኤውን ነገ አርብ በአርባ ምንጭ ያደርጋል።

ለዚሁ ጉባኤ እንግዶች ወደ አርባ ምንጭ እየገቡ ይገኛሉ።

በሌላ በኩል ደግሞ የነበሩ ክልል በአዲስ መልክ የሚደራጅበት / የማዕለላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመስራች ጉባኤ በወልቂጤ ከተማ ይካሄዳል። ለዚሁ በቂ ዝግጅት መደረጉ ተገልጿል።

የፎቶ ምንጭ፦ የወልቂጤ ኮሚኒኬሽን እና የአርባ ምንጭ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#BRICS

በ5 ሃገሮች (ብራዚል ፣ ህንድ  ፣ ቻይና ፣ ሩስያ ፣ ደቡብ አፍሪካ) የተመሠረተው የብሪክስ ቡድን መሪዎች በሚቀጥለው ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ውስጥ እንደሚሰበሰቡ ተዘግቧል።

መሪዎቹ በዚህ ስብሰባቸው ላይ ምጣኔኃብት ተኮር ሆኖ የተፈጠረውን ቡድን ወደ ጂዖ-ፖለቲካ ኃይልነት በመቀየር ‘የምዕራባውያኑን ተፅዕኖ ለመገዳደር ያስችለናል’ የሚሉትን መላ ሳያበጁ እንደማይቀር እየተነገረ ነው።

በስብሰባው ላይ ከመሥራች አባል ሃገሮቹ የብራዚል፣ የህንድ፣ የቻይናና የደቡብ አፍሪካ መሪዎች በአካል እንደሚሳተፉና የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላዲሚር ፑቲን ግን እንደማይገኙ ታውቋል።

ፑቲን ዩክሬን ውስጥ " የጦር ወንጀል ፈፅመዋል " በሚል በተገኙበት እጃቸው እንዲያዝ ዓለም አቀፉ የወንጀል ችሎት ከጥቂት ወራት በፊት ማዘዣ ማውጣቱ ይታወሳል።

ስብሰባው በተጨማሪም እያደገ ከመጣው ቡድኑን የመቀላቀል ጥያቄ አንፃር በተለይ የአፍሪካ ሃገሮችን በማቀፍ ለመስፋፋት በሚችልበት ሁኔታ ላይም ይወያያል ተብሏል።

#ኢትዮጵያ ብሪክስን ለመቀላቀል ጥያቄ በይፋ ካስገቡ ሃገሮች መካከል ነች። (ለማስታወሻ https://publielectoral.lat/tikvahethiopia/79372?single)

የዓለም አካሄድ ‘ለአሜሪካና ለባለጠጋ አጋሮቿ ፍላጎት ያደላ ነው’ የሚለው ቅሬታ ለብሪክስ መፈጠር ዋና ምክንያት ነው።

መረጃው የቪኦኤና ሮይተርስ ነው።

@tikvahethiopia