TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ጅማ⬆️የጅማ አባጅፋር ደጋፊዎች በክለባቸው ድል የተሰማቸውን ደስታ እየገለፁ ነው።

©አብርሀም ከጅማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
‹‹ዘረኝነት እና የጅምላ ጥላቻ፣ ጥልቅ ከሆነ ፍርሃት የሚመነጭ የአዕምሮ በሽታ ነው።›› ማርኩዬዝ ጋሬቭ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አልሰማሁም እዳትሉ💵የውጭ ሀገር ብሮችን በየቤታችሁ ያስቀመጣችሁ እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ የግልም ሆነ የመንግስት ባንክ ያለ ሀሳብ እየሄዳችሁ መመንዝር ትችላላችሁ ተብላችኋል በኃላ አልሰማውም እንዳትሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ለዘንድሮ ተመራቂ ተማሪዎች ከፋፊ⬇️

*ይድረስ ለአዲስ ተመራቂ ተማሪዎች*

በዚህ አመት ለተመረቃችሁ ተማሪዎች ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ። ትምህርት የሚያልቅ ባይሆንም የመጀመሪያውን ማዕረግ (ዲፕሎማ፣ዲግሪ...) ለመረከብ መብቃት አንድ ስኬት ነው። የሰው ልጅ ህይወት ከመጽሐፍ ጋር በጣሙን ይመሳሰላል። በእርግጥም ህይወታችን ራሱ መጽሐፍ ይወጣዋል። ተወልደን ይህችን ዓለም መቀላቀላችን እና የእድገታችን ሂደት አንደኛው እና ዋናው ምእራፍ ነው። መማር እና ተምረን መመረቅ ሁለተኛው የህይወታችን ምእራፍ ነው። ወደስራው ዓለም ገብተን ከኑሮ ጋር ከባድ ትግል የምንፋለምበት ረጅሙ እና ሦስተኛው ምእራፍ ነው። ማግባት፣ መውለድ...እና መሞት በተራቸው ምእራፉን ይሞሉት እና አንድ ወጥ መጽሐፍ ይወጣዋል። እናም ይሄ የትምህርት ዓለም ቆይታችሁን ምእራፍ ዘግታችሁ ሌላ አዲስ ምእራፍ ልትጀምሩ ነው።

ዛሬ ለአዲስ ተመራቂ ተማሪዎች ከራሴ ከህይወት ተሞክሮዬ(ትንሽም ብትሆን) የተማርኩትን ላካፍላችሁ ወደድኩ። ይረዳችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

ልነግራችሁ የፈለኩት ዋናው ቁምነገር "የትምህርቱ ዓለም እና አሁን የምትገቡበት የስራው ዓለም በጣም የተለያዩ "ሆድ እና ጀርባ"መሆናቸውን ስለሆነ አካላዊም ስነ ልቦናዊም ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ ነው #keep your expectation low# ።" በትምህርት ዓለም የነበራችሁ ጥረት፣ ተወዳጅነት፣ ሰቃይነት፣ ግብረ-ገብነት፣ ስኬት ወዘት.. በስራው ዓለም ሙሉ ለሙሉ ላይረዷችሁ ይችላሉ።እኔም እንደማንኛውም ተማሪ በነበርኩበት ኮሌጅ በስነ-ምግባር በጣም የተመሰገንኩ፣ የተማሪዎች መሪ(representative)፣ ተቋሙን ወክዬ ብዙ መድረኮች ላይ የቆምኩ፣ የሜዳልያ ተመራቂ ወዘተ...ነበርኩ። ያም ወደስራው ዓለም ስገባ ህይወቴን እንደሚለውጥ ተስፋ ሰጥቶኝ ነበር። የምርቃቴም ቀን ሜዳልያውን ስሸለም ብዙ ድርጅቶች የቢዝነስ ካርድ እየሰጡ "pls አብረን እንስራ" ብለውኝ ነበር። ግን ያ ሁሉ 90% ውሸት ነበር። (ይሄ እድል እና ፍላጎት እንደ ሰኔና ሰኞ የገጠመላቸውን ጥቂት ተማሪዎች አይመለከትም።) በርግጥ በጣም ከብዙ በጥቂቱ አንዳንድ እድል ይሁን አጋጣሚ ባላውቅም ከመጀመሪያው የሚሳካላቸው ልጆች እንዳሉ አስተውያለሁ። ተመርቄ ከወጣው በኋላ ወደስራው ዓለም ስገባ ያ የነበረኝ ተፈላጊነት፣ስም፣ ሜዳልያ...እዛው ካምፓስ ነው የቀረው።እንደ አዲስ ነው መጀመር የነበረብኝ።even የመጀመሪያ ደሞዜም 1000 ብር ነበር።(የማወራው ከ3 ተኩል በፊት ስለሆነ ነገር ነው።) በዚህ ደሞዝ ቤት ኪራይ፣ ምግብ፣ ታክሲ...ብቻ ከባድ ነበር።

ሁለት ዓመት ድርጅት እየቀያየርኩ የተሻለ ነገር ፈለኩ። ግን ተቀጥሮ እስከተሰራ ድረስ ያው ነው።ከባድ ጥረት እና ጊዜ ይፈልጋል። እናም ቁም ነገሮቹን ባጭሩ ላስቀምጥላችሁ።

1፦ልክ በካምፓስ እንዳለው የተማሪ ለተማሪ ፉክክር ሁሉ በስራውም ዓለም ከባድ የሆነ ፉክክር አለ። ሰዎች ራሳቸውን ለማሳደግ ከባድ የሆነ ትግል ያደርጋሉ። እናም አዲስ የተማረ የሰው ኃይል ገበያው ላይ ሲጨመር ፉክክሩን ይበልጥ ያከረዋል። በዚም የቅጥር ገበያው (employment market) ላይ ያሉ ሰዎች በትንሽ ደሞዝ ፣ ብዙ ስራ፣ ለረጅም ሰአት፣ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው ይሰራሉ። ይህ ደሞ ለአዲሱ ተመራቂ ከዛም በታች ወርዶ እንዲሰራ ይዳርጋል። የሆነም ነገር ነው። እናም ባጭሩ ብዙ ነገር expect ማድረግ ሞራልን ይጎዳል። ጠንክሮ ለመስራት እና ተፎካካሪ ለመሆን መዘጋጀት ያስፈልጋል።

2፦ ሁልጊዜም ራሳችሁን ማሳደግ ላይ (personal development) መስራት አትርሱ። ባላችሁበት መርገጥ በገቢም በእውቀትም ወደኋላ ያስቀራል። ውሃም አንድ ቦታ ሲረጋ ይሸታል። በማንበብ፣ለሚድያዎች ቅርብ በመሆን፣ በመጠየቅ፣ ከሰዎች ጋር መረጃ በመለዋወጥ፣ በመማር ራሳችሁን በየለቱ አሳድጉ። ያኔ ተፈላጊነትም ይመጣል። የሀገሪቱም (የዓለምም) ኢኮኖሚ በየሳምንቱ እና በየወሩ ይዋዥቃል። እናም ከኢኮኖሚካል ጥቅሙ ለመጠቀም ፤ከጉዳቱም ለማምለጥ መረጃ ወሳኝ ነው። በዚህ አንድ ዓመት ውስጥ እንኳን የ"ብር" ዋጋ ምን ያህል inflate እንዳደረገ ማየት ይቻላል። ስለሰራተኞች ደሞዝም ብትጠይቁ እንዲሁ ነው። ስለዚህ በእውቀትም በሙያም ሁሌም ራሳችሁን ገንቡ። አንድ ቦታ ብቻ ተቀጥሮ መስራት አንድ ሙያ ብቻ ነው የሚያስጨብጣችሁ፤ ስራ ስትቀያይሩ ግን እውቀትም ታገኛላችሁ፤ ሰውም ትተዋወቃላችሁ፤ የስራውን ገበያም ታውቁታላችሁ።

3፦ማንኛውንም ስራ ለመስራት ተዘጋጁ። ስራ አይናቅም። ብዙ ሰዎች በተመረቁበት field አደለም እየሰሩ ያሉት። እናም "በተመረኩበት ካልሰራሁ" ካላችሁ መቸገራችሁ አይቀርም። ያገኛችሁትን ስራ እየሰራችሁ የምትፈልጉትን ስራ በዛው ታፈላልጋላችሁ። "Love what you መሄድን do,'till you do what you love" እንደሚባለው።

4፦ ሁልጊዜም ለወርቁ ሩጡ (Go for the gold)። ለምቾት ሳይሆን ለስኬት ስሩ፤ ለብር ሳይሆን ለመስራት ስሩ። ስራችሁን ጥንቅቅ አድርጋችሁ ከሰራችሁ "ብር" ራሱ ወደእናንተ ይመጣል። ትንሽ ነገር ስታገኙ ራሳችሁን እዛው አትገድቡት፤ dig for more። የእኔ ጓደኞች ከተመረቅን በኋላ በየገቡበት ድርጅት እንደገቡ "በቃን" ብለው ከ4000 ብር ባልበለጠ ደሞዝ ለማብቃቃት እየሞከሩ አሁንም እዛው ናቸው። ከዛ በላይ አልሞከሩም። እኔ ግን በተቻለኝ መጠን ብዙ ቦታዎች ሞከርኩ። በርግጥ ከባድ risk አለው። ያላችሁን ነገር ታጡ ይሆናል። የቤት ኪራይ ምከፍለው አጥቼ ተባርሬ አውቃለሁ። ኪሴ ባዶ ሆኖ ብዙ ቀናት ጾም አድሬአለሁ። ከስራ ስራ ስቀይር ነገሮች ዝብርቅርቅ ብለውብኛል።ያ ግን ለስኬቴ ግብዓት እና ጥንካሬ ሆኖኛል። ዛሬ ባለአምስት አሃዝ ደሞዝ አገኛለሁ። ንብረትም(Asset) እየገነባሁ ነው። ይሄ የሆነው ሩጫዬ ለወርቁ ስለነበር ነው። እናም እግዚአብሔር በተፈጥሮ ትልቅ አቅም ሰጥቶናል። dont wast it by stucking somewhere.

5፦ በመጨረሻም የምታገኙትን ገንዘብ በአግባቡ manage ማድረግ መልመድ ያስፈልጋል። ብዙ...በጣም ብዙ ሰራተኞች የሚቸገሩበት ጉዳይ ነው። ደሞዝ ከወር እስከ ወር አልደርስ ይላል። ደሞዛቹህ እጃቹህ ከመግባቱ በፊት እቅድያገኛችሁትን አውጡለት፤ መድቡት። ከዛ እጃቹህ ውስጥ ሲገባ ወደተመደበለት ቦታ አውሉት። በምንም ተአምር ገንዘብ ከቁጥጥራችሁ ውጭ እንዳይሆን፤ እንዲቆጣጠራችሁ አታድርጉ። አንዴ ከቁጥጥራችሁ ውጭ ከሆነ በጣም አስቸጋሪ ነው። መጨረሻችሁ ተበዳሪ መሆን ነው።

በእኔ እምነት "ገንዘብ" ከእድሜያችን ጋር ይገናኛል። ገንዘብ/ደሞዝ ለማግኘት ከህይወታችን ላይ 30 ሙሉ ቀናትን ሰጥተን በምትኩ የምናገኘው "የእድሜያችን ቅያሪ" ነው።እናም ይህን ያህል የእድሜያችንን portion የወሰደ ነገር እንዴት ያለአግባብ እናወጣዋለን?!?! ስለዚህ ለፍታችሁ ሰርታችሁ የልፋታችሁን ዋጋ ቁም ነገር ላይ ማዋል ይገባል። ለዚህ ደግሞ በጣም recommend የማደርገው እቁብን ነው። እቁብ ስትጥሉ save እያደረጋችሁ ነው። ብሩ ተጠራቅሞ ሲመጣ አቅም ይሰጣችኋል። ያኔ ጠንከር ያለ ነገር ማድረግ ትችላላችሁ። ሌላው...ጥሬ ገንዘብን(cash) ወደ ቁሳቁስ መቀየርም አንዱ ብርን ማዳኛ እና ለረጅም ጊዜ ማቆያ ዘዴ ነው።ባጭሩ የምታገኟትን እያንዳንዷን ገንዘብ save ማድረግ እና ቁምነገር ላይ ማዋል ነው።

6፦last but not least... በየሃይማኖታችሁ ፈጣሪ በጥረታችሁ እንዲያግዛችሁ፣ ትርጉም ያለው ኑሮ መኖርን እንዲያሳያችሁ፣ ለሰዎች መ
ሰናክል ሳይሆን አርአያ እንድትሆኑ፣ ኑሯችሁ እንዲባረክ መጸለይ በጣም ይረዳል።ጸሎት ልክ እንደ leverage ነው። ጥረታችንን በእጥፍ ያባዛው
እና ስኬታችንን ቅርብ ያደርገዋል።

ከራሴም ህይወት፣ ከብዙ ሰዎች የህይወት ተሞክሮ እና የሚያሰሙት ቅሬታ እና ከተለያዩ መጽሐፍት ላይ የተረዳኋቸው ቁም ነገሮች ከብዙ በትንሹ እነዚህ ናቸው። ብዙ ብጽፍ እና ይበልጥ ብገልጸው ደስ ይለኝ ነበር። ረዝሞ እንዳያሰለች ሰጋሁና በዚሁ ቋጨሁት። እነዚህን መጽሐፍት ብታነቡ ስራን እና ኑሮን እንዴት አስማምታችሁ መሔድ እንዳለባችሁ እውቀትን ያስጨብጧችኋል።

@ሰባቱ የስኬታማ ሰዎች ባህሪያት
@25 የስኬት ቁልፎች(ዶ/ር ኢዮብ ማሞ)
@Rich dad Poor dad(robert kiyosaki)
@The monk who sold his ferrari(robin sharma)
@You can win (shiv keyra)

ጽሑፉ ይረዳችኋል ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።

መልካም የስራ ዘመን! መልካም እድል!!!
@Fafi_G21

@tsegabwolde @tikvahethiopia
"ሰው ይሞታል፤ ሁሌም ሟች ደሃ ነው። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የምንናገር ሰዎች ሳንሆን በየሰፈሩ ያለ ደሃ እኛን አምኖና ሰምቶ ህይወቱን ባልተገባ ሁኔታ ስለሚገብር ሰዎች እንዳይሞቱና ንብረት እንዳይወድም፤ ሁላችንም ተባብረን መስራት ይገባናል"

🔳▫️ዶክተር አብይ አህመድ▫️🔳

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እጅግ በርካታ ሰዎች በጠየቃችሁት መሰረት⬇️

የሀጫሉ ሁንዴሳ እና የሚሊኒየም አዳራሽ መልእክቱ።
-----
ተደመሩ ብለውን ተመደርንላቸው
ታዲያ ጠላቶቻችንን ማን ከለከላቸው
ይሄው ሚኤሶ ገብተው
በጥይት ይቆሉናል
ይኸው ጭናክሰን ገብተው
በጥይት ይቆሉናል
ይኸው ሞያሌ ገብተው
በጥይት ይቆሉናል
ማን ይከልክልልን እሺ
እንዲያው ምን ይበጀናል
ከልክልልን ለማ
ላንተ አቤት ብያለሁ
ከልክልልን አቢይ
ላንተ አቢይ እላለሁ
ካልከለከላችሁልን
ቄሮ ጋ እሄዳለሁ።

(ሃጫሉ ሁንዴሳ፣ ሃምሌ 9፣ 2010)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
እደግመዋለሁ📌

አልሰማሁም እዳትሉ💵የውጭ ሀገር ብሮችን በየቤታችሁ ያስቀመጣችሁ እስከዚህ ሳምንት መጨረሻ ድረስ የግልም ሆነ የመንግስት ባንክ ያለ ሀሳብ እየሄዳችሁ መመንዝር ትችላላችሁ ተብላችኋል በኃላ አልሰማውም እንዳትሉ።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዘንድሮም በነፃ⬆️አልበርት የማጠናከሪያና የበጎ አድራጎት ማዕከል። #አዳማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ከያሬድ ሹመቴ⬇️

የትናንት ምሽቱ ኮንሰርትና የቴዲ አፍሮ እውነታዎች!

~"ወደ መድረክ ጋብዞ የጀርባ በር ቆልፎ"

በትናንትናው ምሽት በኢትዮጵያና ኤርትራ የሰለም ኮንሰርት ላይ በእንግድነት ዝግጅቱን እንዲታደም ተጋብዞ የነበረው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በማህበራዊ መገናኛ ብዙሀን በርከት ያሉ የተዛቡ መረጃዎች እየቀረቡበት ነው።

ከነዚህም መካከል ሙዚቃዎቹን በብዛት አለማቅረቡና ወደ መድረክ እንዲወጣ ከተጋበዘ በኋላ ‘ታዳሚውን ለብዙ ደቂቃዎች አስጠብቋል’ የሚሉት ዋናዎቹ ሲሆን በእለቱ በስፍራው አብሬ በመኖሬ ትክክለኛውን መረጃ በአጭሩ እነሆ።

• ቴዲ አፍሮ የዝግጅቱን መግቢያው ካርድ ያገኘው ዝግጅቱ መካሄድ ከጀመረ በኋላ ነው።

• የመግቢያ የይለፍ ወረቀቱን አትላስ አካባቢ ያስቀመጡልን የጠቅላይ ሚንስትር ጽህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ፍፁም አረጋ ፍፁም ተባባሪ ሆነው አምሽተዋል።

• መግቢያ ካርዱ ከተገኘ በኋላ ሚሊንየም አዳራሽ ስንደርስ ለረዥም ደቂቃዎች እንዳንገባ ተከልክለናል።

• ተፈቅዶልን ግቢ ውስጥ ከገባን በኋላ ወደ አዳራሹ ለመግባት ቢያንስ ከ15 ደቂቃ በላይ መግቢያው ላይ እንድንቆም ተደርጓል።

• ወደ ክብር እንግዶች ማረፍያ ከገባን በኋላም ወንበር እስኪዘጋጅ ጠብቁ ተብለን በድጋሚ ለመጠበቅ ተገደናል።

• ወ/ሮ ዝናሽ (ቀዳማዊት እመቤት) እንደገባን በፈገግታ ለቴዲ እጃቸውን እያውለበለቡ ሰላምታ በመስጠታቸው እሱም በአክብሮት አፀፋውን መልሷል።

• የተዘጋጀልን የመቀመቻ ስፍራ ወደ ታዳሚው የተጠጋ በመሆኑና በስክሪን ቴዲ በመታየቱ ቴዲ ተነስቶ ለህዝቡ ሰላምታ ሰጥቶ ተቀምጧል።

•ህዝቡ በተደጋጋሚ እንዲዘፍን ስለጠየቀ ቴዲ ፍቃደኛ መሆኑን ተናግሮ ወደ መድረኩ ለመሔድ ተነሳን።

• መድረክ መሪው የቴዲን ፍቃደኝነት ከሰማ በኋላ እንደ አዲስ ልምምጥ በሚመስል መንገድ ተደጋጋሚ ጥሪ ማድረጉ አስገራሚ ነበር።

• ቴዲ ዶ/ር አብይን ሰላም ብዬው ልሂድ ብሎ ሁለት ግዜ ጠይቆ የፌደራል ፖሊስ ዋና አዛዡ አቶ ዘይኑ ቢፈቅዱም የፕሮቶኮሉ ሹም ፍቃደኛ ሳይሆን በመቅረቱ ለሰላምታ ሳይፈቀድ ቀርቷል።

• አዳራሹን ዙረን ባክ ስቴጅ ላይ ስንደርስ የጀርባው በር ተቆልፎ ጠበቀን።

• በቦታው የነበሩ ሰዎች ለማስከፈት ቢሞክሩም በሩን የዘጋው ሰው አልከፍትም ብሎ ብዙ ቆመናል። ለጀርባው መግቢያ አማርጭ ናቸው የተባሉ ሌሎች ሶስት በሮችንም እየተዘዋወርን ለመግባት ብንሞክር የሚቻል አልሆነም።

• የብሄራዊ ትያትር ስራ አስኪያጅ አቶ ነብዩ ባዬ "ላስቸግራችሁ በህዝቡ መሀል ይዛችሁት ኑ?" ብለው ሀሳብ በማቅረባቸው፤ ከመድረኩ በስተቀኝ በኩል በህዝብ መሀል ይዘነው ለመግባት ተገደናል።

• በቂ ጥበቃ ባለመኖሩ የከበበውን ህዝብ አልፎ ወደ መድረኩ ለመድረስ በጣም አስቸጋሪ ፈተና ሆኖብን ነበር።

• በመከራ በህዝብ መሀል አልፈን ከመድረክ ጀርባ ብንደርስም እዚያም የነበሩ የቴዲ አድናቂዎች አላሳልፍ ብለው ግርግር ተፈጥሮ ነበር።

• የመድረክ መሪው ግሩም ጫላ በተደጋጋሚ ቴዲን የሚያሳጣ ጥሪ ሲያደርግ እኛ ግን ቴዲን ይዘን ለመድረስ ከባድ ፈተና ላይ ነበርን። ቴዲ የለበሰው ልብስ እስኪጨማደድ ድረስ ግፊያውንን ተቋቁሞ ወደ መድረኩ ደርሷል።

• ሙዚቀኞቹ በመድረክ መሪው ጋባዥነት "ኢትዮጵያ" የተሰኘውን የቴዲን ዜማ ያለ እሱ ፍቃድ መጫወት ሲጀምሩ በቦታው ደርሰናል።

• ባንዱ እየተጫወተ የነበረውን ሙዚቃ አቋረጠ። መድረክ መሪው የቴዲን ስም ጠርቶ ወደ መድረኩ ሲጠራው ቴዲ መድረክ ላይ ወጣ።

• መድረክ ላይ ከህዝቡ የተወረወረለት ኮከብ አልባ ሰንደቅ አላማ በሴኪዩሪቲ በፍጥነት እንዲነሳ ተደርጓል።

• አንዲት እናት ያዘጋጁለትን ስጦታ መድረክ ላይ ሊሰጡት እያለቀሱ መጡ ስጦታውን እንደተቀበለ ለህዝቡ የስንብት ሰላምታ ሰጥቶ ወደ ጀርባ ገባ።

• ቀደም ብሎ የተቆልፈብንን በር ለመውጣት ሲሆን ከፈቱልንና በጀርባ በኩል ወጣን።

ይህ ሁሉ ሲሆን ቴዲ አፍሮ ግን ባልተዘጋጀበት መድረክ ከዚህ በፊት ገጥሞት የማያውቅ ውክቢያ ደርሶበት፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ለማክበር ሲል ራሱን በማረጋጋት መልዕክቱን አስተላልፎ፤ ፊዮሪናን ዜማ ተጫውቶ ዛሬም የህዝብ ልጅነቱን አስመስክሯል::

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተፈናቃዮቹ በቂ ድጋፍ እየተደረገላቸው አይደለም⬆️

"ሀይ ፀግሽ ዛሬ ከጉጂ ዞን የተፈናቀሉትን ሰዎች ለማየት ተጉዘን ነበር። በጣም ያማል መንግስት ምንም ድጋፍ እያደረገላቸውን አይደለም። በጣም ያማል፤ ይከብዳል። በአስቸኳይ ወደ ቦታቸው መመለስ አለባቸው። በአንድ ክፍል ውስጥ 30 የወለዱ እናቶች እያደሩ ነው። በአንድ ክፍል ውስጥ ከ100 በላይ ሰው ይኖራል። እነ ለማ በአስቸኳይ መፍትሄ መፈለግ አለባቸው።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እኛ ልክ እንደዚ⬆️ፐዝል ነን። ፐዝል ሲገጣጠም እንደ ሚያምር እና ትርጉም እንደሚኖረው ሁሉ እኛም አንድ ስንሆን ነው የሚያምርብን።

+++++አንድ እንሁን+++++

©ራሄል
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#OLF ኦነግ ትላንት ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ከሳምንት በፊት በተናጠል የወሰነውን የተኩስ ማቆም አዋጅ ለመጣስ መገደዱን አስታውቋል። ኦነግ የተኩስ ማቆም አዋጅ ባለመቀበል ሊደርስ ለሚችለው ጉዳት ሁሉ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግስት ይሆናል ሲልም አስጠንቅቋል።

ሙሉ መግለጫውን🔄
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሞ ነጻነት ግንባርን የተኩስ ማቆም ኣዋጅ ባለመቀበል ሊደርስ ለሚችለው ጉዳት ሁሉ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግስት ይሆናል⬇️

(የኦነግ መግለጫ - ሓምሌ 16, 2018)

በኢትዮጵያ መንግስትና በኦሮሞ ነጻነት ግንባር መካከል የተጀመረውን ውይይት ለማሳካት ሲባል ሃምሌ 12 ቀን 2018ዓም የኦሮሞ ነጻነት ግንባር በበኩሉ ለጊዜው ተኩስ ለማቆም ወስኖ የተኩስ ኣቁም መግለጫ ማውጣቱ ይታወሳል።

በኦሮሞ ነጻነት ግንባር የታወጀው የተኩስ ኣቁም ኣዋጁ በበርካታ ኣለም-ኣቀፍ ሚዲያዎች በስፋት ተዘግቧል።

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ይህንን የወሰነው ሰሞኑን በኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር. ኣብይ ኣህመድና በኦነግ ሊቀ-መንበር ኣቶ ዳውድ ኢብሳ በሚመራው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ልዑካን ቡድን መካከል የተጀመረው ውይይት ቀጥሎ የተፈለገውን ውጤት እንዲያስገኝ በመመኘት ነው።

ይሁን እንጂ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ ለዚህ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር የተኩስ ማቆም ኣዋጅ ተመሳሳይና ገንቢ ምላሽ ባለመስጠት በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ላይ ጦርነት ማካሄዱን ለመቀጠል በምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ ሰፊ ዘመቻ/ስምሪት በማካሄድ ላይ ነው። በዚህም የጦር ሃይሉን ከነቀምቴ፣ ከኣሶሳና ከጋምቤላ በብዛት በማሰማራት በመላው ምዕራብ ወለጋና ቄሌም ወላጋ ዞኖች ውስጥ ህዝባችንን በማወክ ላይ ይገኛል።

በኦነግ በወጣው የተኩስ ማቆም መግለጫ ውስጥ እንደተገለጸው በዚህ ኣካባቢ የሚገኘው ሃይላችን(የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት) እና ሕዝባችን ይህንን ጦርነት በሚቻለው ሁሉ ከመከላከል ውጪ ሌላ ኣማራጭ የሌለው መሆኑን ኦነግ ያሳውቃል። በዚህ ሁኔታ መሃል ለመረጋጋት መታጣትና ሊደርስ ለሚችለው ጉዳት ሁሉ ተጠያቂው የኢትዮጵያ መንግስት መሆኑን የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኣጥብቆ ያስገነዝባል።

ዘመኑ የጭቆና ፍጻሜ ዘመን ነው !
ድል ለኦሮሞ ህዝብ !
የኦሮሞ ነጻነት ግንባር
ሓምሌ 16, 2018

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አሰብ! የአሰብ ወደብን ለመጠቀም ፈጣን እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ ነው ይህንን የገለፁት።

አቶ መለስ በመግለጫቸው የአሰብ ወደብን ለመጠቀም በአሁኑ ወቅት የተለያዩ ስራዎች እየተሰሩ ነው፤ የመንገድ ጥገና ስራም እየተካሄ ይገኛል ብለዋል።

አቶ መለስ አክለውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን መደበኛ በረራም በነገው እለት በይፋ እንደሚጀምር ገልፀዋል።

በነገው የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራም 465 ሰዎች ወደ አስመራ ይጓዛሉም ብለዋል።

ምንጭ፦ FBC
@tsegabwolde @tikvahethiopia