TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update ኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ

የመጀመሪያው አጋማሽ⬇️

.ቅዱስ ጊዮርጊስ 1– 0 ሐዋሳ ከነማ

.ጅማ አባ ጅፋር 2-0 አዳማ ከተማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የኦሮሚያ እና ሱማሌ ድንበር! የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒሰትር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በሰጡት ትዕዛዝ መሰረት የኦሮሚያና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሳና መስተዳደሮች በክልሎቹ አጎራባች አካባቢዎች የፌዴራል የጸጥታ አካላት በአፋጣኝ ገብተው የሰላምና መረጋጋት ሥራ እንዲሰሩ ተስማሙ።

ጠቅላይ ሚኒሰትር ዶ/ር አብይ አህመድ አልፎ አልፎ የሚታየው የዜጎች ሕይወት መጥፋት እንዲቆም፣ ይህንን የሚያባብሱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ፣ በአጠቃላይ አሁን የተፈጠረውን ብሩህ ተስፋ ለማስቀጠል በፍቅርና አብሮነት ሕዝቡ እንዲተጋ፤ ከዚህ በተቃራኒው የሚፈጸሙ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶችን ለመከላከል የኢፌዴሪ መከላኪያ ሠራዊትና የፌዴራል ፖሊስ ሕግ የማስከበር ሥራቸውን በኃላፊነት ስሜት እንዲወጡ ትዕዛዝ መስጠታቸው ይታወቃል።

ጠቅላይ ሚኒሰትሩ የሰጡትን መመሪያ ተሪከትሎም የኦሮሚያ ክልል ርዕስ መስተዳደር አቶ ለማ መገርሳና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዲ መሐመድ ዑመር ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም ግጭት በተፈጠርባቸው አጎራባች አካባቢዎች የፌዴራል የጸጥታ ኃይል በመግባት የጸጥታ፣ የሠላምና መረጋጋት ሥራ እንዲሰራ፤ እንዲሁም የሕግ ማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ መስማማታቸውን የመንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በላከው መግለጫ አስታውቋል።

ለአፈጻጸሙ የሁለቱም ክልል የመንግሥት መዋቅሮች ከፌዴራል የጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ችግሩን ለመፍታት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚወጡ ርዕሳና መስተዳደሮቹ ማረጋገጣቸውን የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ ሚኒሰትር አቶ አህመድ ሺዴ ገልጸዋል።

በተለይ የሕግ-ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ እንደሚሰራና የሁለቱም ክልል ሕዝብ እንደወትሮው የለውጥ ሂደቱን በመጠበቅ ለመፍትሄው ኃላፊነቱን በተገቢው መንገድ እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል።

በቀጣይ በበርካታ እሴቶች የተሳሰረውን የሁለቱ ክልል ሕዝብ ከመሰል ግጭቶች በመከላከል ለዘላቂ መፍትሄ፣ ለሰላምና ፍቅር አብሮ የሚሰራበትን ሁኔታ ለማስቀጠል ተከታታይ የሕዝብ ለሕዝብ ኮንፍረንሶችን በአፋጣኝ ለማካሄድም ርዕሰ መስተዳደሮቹ ወስነዋል።

ምንጭ፡-(ኤፍቢሲ)
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፎቶ⬆️በፕሬዘዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የተመራው ልዑክ አስመራ ገብቷል። ታሪካዊ እንዲሁም ስኬታማ ጉብኝት እንደነበረም ተነግሯል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update ኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ

ሁለተኛው አጋማሽ ቀጥሏል⬇️

.ቅዱስ ጊዮርጊስ 1– 0 ሐዋሳ ከነማ

.ጅማ አባ ጅፋር 3-0 አዳማ ከተማ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ

⌚️76'
ቅዱስ ጊዮርጊስ 2⃣-0⃣ ሀዋሳ ከተማ
⚽️ሳልሀዲን በርጊቾ 35'
⚽️ሙሉአለም መስፍን 59'

⌚️75'
ጅማ አባጅፋር 4⃣-0⃣ አዳማ ከተማ
⚽️ኦኪኪ አፎላቢ 9' 53' 66'
⚽️ተመስገን ገብረኪዳን 32

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#Update ኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ

⌚️ተጠናቀቀ
ቅዱስ ጊዮርጊስ 2⃣-0⃣ ሀዋሳ ከተማ
⚽️ሳልሀዲን በርጊቾ 35'
⚽️ሙሉአለም መስፍን 59'

ተጠናቀቀ'
ጅማ አባጅፋር 5-0⃣ አዳማ ከተማ
⚽️ኦኪኪ አፎላቢ 9' 53' 66' 84
⚽️ተመስገን ገብረኪዳን 32

@abdiloth
@tikvahethiopia @tsegabwolde
ጅማ አባጅፋር የ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሜርሊግ ዋንጫን አነሳ።

የከተማው ህዝብ እንዲሁም የክለቡ ደጋፊዎች እንኳን ደስ አላችሁ!

@tsegabwolde @tiovahethiopia
ጥንቃቄ! ዛሬ የጅማ አባጅፋርን ድል ተከትሎ የክለቡ ደጋፊዎች፣ የከተማው እና አካባቢው ነዋሪዎች ደስታችሁን እየገለችሁ እንደሆነ እየሰማሁ ነው።

ደስታ አገላለፃችን ጉዳት በማያደርስ መልኩ ሊሆን ይገባል። በደስታ አገላለፁ ወቅት ህፃናት፣ እናቶች እና ሴቶችን ጉዳት እንዳይደርስባቸው እየተጠነቀቃቹላቸው።

*ደሳታችሁን ሊበርዝ የሚችል ምንም አይነት ነገር ሊፈጠር አይገባም።

በድጋሚ እንኳን ደስ አላችሁ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
CCD⬆️

"አዎ ፀጋ ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ለገጣፎ በመጡበት ሰዐት የጎበኙት እኔን ጨምሮ ከ 7000 በላይ ሰራተኞች የሚያስተዳድር ድርጅት ነዉ ccd (country club developers) ቴዲ አፍሮ የሚኖረዉም እዚሁ ግቢ ነዉ አምለሰት ከልጆቿ ጋር በመሆን ጠቅላይ ሚኒስቴሩን አግኝተዉታል፡፡"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ህገ ወጥ ሽጉጦች ተያዙ⬆️

በህገ ወጥ መንገድ ሲዘዋወሩ የነበሩ 53 ሽጉጦች በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለፀ።

የጦር መሳሪያዎቹ በአይሱዙ የጭነት ተሽከርካሪ ተጭነው ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ሰሜን የሀገሪቱ ክፍል በመጓጓዝ ላይ እያሉ ነው በቁጥጥር ስር የዋሉት።

የጦር መሳሪያዎቸቹ በቁጥጥር ስር የዋሉትም ህብረተሰቡ ያደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ ፖሊስ ባደረገው ፍተሻ መሆኑንም ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ንግድ በተለያዩ ቦታዎች እየተስተዋለ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በመተባበር እንደዚህ አይነት ህገ ወጥ ተግባራትን እንዲከላከልም ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ፦ ኦ.ቢ.ኤን
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀርቀሎዎች ዛሬም ጨለማ ውስጥ ናቸው⬇️

"ኣረ ፀግሽ ሀረቀሎዎች ዛሬም ጨለማ ውስጥ ነን መብራት ከጠፋ 1ወር አለፈን ስራ ፈተናል ሀይ ባይ አጣን ሪች ነኝ ከሀረቀሎ"

@tsegabwolde @tikvahethiopia