TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COOP

ለብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ከታች ከተዘረዘሩት የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ @coopbankoromia ቅርንጫፎች ወደ አንዱ ሲሄዱ የቀበሌ መታወቂያ፣ የመስሪያ ቤት መታወቂያ፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ እርስዎን መግለፅ የሚችል መታወቂያ መያዝ ይጠበቅብዎታል።

ለምዝገባው ምንም አይነት ክፍያ አይፈፀምም፦

1. ፊንፊኔ ቅርንጫፍ📍አፍሪካ ጎዳና፣ ፍላሚንጎ አካባቢ
2. ቀርሳ ቅርንጫፍ📍ሜክሲኮ ስኩል ኦፍ ኮሜርስ ጀርባ
3. ኃይሌ ገብሬ ቅርንጫፍ📍 ቃሊቲ ማሰልጠኛ
4. ጀሞ ቅርንጫፍ📍ጀሞ አንድ
5. መደሮ ቅርንጫፍ📍መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል ፊትለፊት
6. አየር ጤና ቅርንጫፍ📍አየር ጤና
7. ኦዳ ቅርንጫፍ 📍ባምቢስ ሱፐርማርኬት ከመስቀል አደባባይ ወደ ኡራኤል በሚወስደው መንገድ ላይ
8. መጫና ቱለማ ቅርንጫፍ 📍ልደታ አልሳም ሪል እስቴት ህንፃ ላይ
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን " ሕገወጥ " እንደሆነ ገልጻ እንዲቆም ያሳሰበችው የትግራይ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ተፈፀመ። " የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ከፍተኛ ቤተ ክህነት " ዛሬ ሃምሌ 15 / 2015 ዓ.ም  በአክሱም ከተማ የኤጲስ ቆጶሳት በአለ ሲመት አከናውኗል። በዚህም ፦ 1. ንቡረ ዕድ መሓሪ - አቡነ ሊባኖስ 2. ቆሞስ…
#Update

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን  ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ ሰጥቷል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ መግለጫው ምን አለ ?

በክልል ትግራይ በተከሰተው ጦርነት ምክንያት በክልሉ ከሚገኙት አህጉረ ስብከት ጋር ተቋርጦ የነበረውን መዋቅራዊ ግንኙነት ችግር በውይይት እንዲፈታ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪና ልዑካኑን በአካል ልኮ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ባለበት ወቅት በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አባቶች ሕገ ቤተ ክርስቲያንንና ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ ቅዱስ ፓትርያርኩ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ተብለው በሚጠሩበት በማዕከላዊ ትግራይ ዞን አክሱም ሀገረ ስብከት በርእሰ አድባራት ወገዳማት አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ሐምሌ 15 እና 16 ቀን 2015 ዓ.ም. የተከናወነው ሕገወጥ ሢመተ የኤጲስ ቆጶሳት  መፈጸሙ በእጅጉ እንዳሳዘነው ገልጿል።

የተከሰተው የዶግማ፣ የቀኖና እና አስተዳደራዊ ጥሰት አስመልክቶ ተወያይቶ ተገቢውን ለመወሰንም ለሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም. አስቸኳይ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ጥሪ አስተላልፏል።

የስብሰባው ቀን ሊራዘም የቻለው በውጭው ክፍለ ዓለማት ያሉት ሊቃነ ጳጳሳት መገኘት ስላለባቸው የጉዞ ቀኑ እንዳያጥር እና በሀገር ውስጥ የሚገኙትም ሊቃነ ጳጳሳት ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል ምክንያት ለአገልግሎት ወደ አህጉረ ስብከታቸው የሄዱ በመሆኑ ለመመለሻ የሚያስፈልገውን ጊዜ ታሳቢ በማድረግ መሆኑን አመልክቷል።

በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭው ክፍለ ዓለማት የሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በሙሉ እስከ ሐምሌ 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ተጠቃለው ወደ ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ እዲመጡ ጥብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ታያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ወደ መፈተኛ ተቋማት ገቡ።

የማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኝ ተማሪዎች ትላንት እንዲሁም ዛሬ ወደተመደቡበት የመፈተኛ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ገብተዋል።

በነገው ዕለት ገለፃ ይደረግላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ከረቡዕ ሐምሌ 19 እስከ ሐምሌ 21 ፈተናቸውን የሚወስዱ ሲሆን ከቀጣይ ቀናት ጀምሮ ወደየቤተሰቦቻቸው ይመለሳሉ።

ዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመውሰድ በኦንላይን ተመዝግበዋል ከተባሉ 869 ሺህ 765 ተፈታኞች መካከል 503,812 የሚሆኑት የማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert በጋምቤላ ክልል የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለት ቦታዎች እንዲሰጥ ተወሰነ። በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው የፀጥታ ችግር ምክንያት የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ እና በጋምቤላ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ እንደሚሰጥ የክልሉ መንግስት አስታውቋል። የክልሉ መንግሥት ፤ " በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ብቻ ሊሰጥ የነበረው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ሰሞኑን ተከስቶ በነበረው…
ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓትን ሳያከናውን ቀርቷል።

በክልሉ ባለ የፀጥታ ችግር ምክንያት የ2015 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ በዓል መሰረዙን ዩኒቨርሲቲው ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።

የምረቃ በዓሉን ሐምሌ 13/2015 ዓ.ም ለማድረግ ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም በክልሉ በተከሰተው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት የምረቃ ፕሮግራሙ መሰረዙን የተቋሙ ከፍተኛ አመራር ለቲክቫህ ተናግረዋል።

"ተማሪዎቻችንን ለማስመረቅ ተዘጋጅተን ነበር፤ ይሁን እንጂ ባለው የፀጥታ ሁኔታ የምረቃ በዓሉን ማከናወኑ ትርጉም አይኖረውም" ብለዋል ኃላፊው።

የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ እና አንድ መምህር ባለፈው ሳምንት ህይወታቸው ማለፉን ዩኒቨርሲው ማሳወቁ አይዘነጋም፡፡

ከ650 በላይ የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዲግሪ ተመራቂዎች ትምህርታቸውን በ2015 ዓ.ም በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ማጠናቀቃቸው ተገልጿል። ተመራቂዎቹ አሁን ላይ ጊዚያዊ ዲግሪ (Temporary) እየተሰጣቸው ነው።

በሌላ በኩል ዩኒቨርሲቲው የተመደቡለትን ከ6 ሺህ በላይ የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞችን ከትላንት ጀምሮ እየተቀበለ ይገኛል።

@tikvahuniversity
" ሱተን ዙሪያ ቀበሌ ድረስ ተከታትለው በመምጣት ነው የገደሉት ፤ ... ይሄን ለማን አቤት ልበል ? " - ወላጅ አባት

በኦሮሚያ ክልል፤ ደ/ምዕራብ ሸዋ ዞን  የትራፊክ ፖሊስ አባላት የጠየቁትን ያህል ጉቦ አልሰጥም ያለን አንድ አሽከርካሪ በጥይት ደብድበው መግደላቸውን የሟች ቤተሰቦችና የሥራ ባልደረቦች መግለፃቸውን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ድርጊቱ የተፈፀመው ባለፈው ዓርብ ዕለት ሲሆን በትራፊክ ፖሊስ አባላቱ በጥይት የተገደለው እና ትላንት ስርዓተ ቀብሩ ተፈፀመ የተባለው የ33 ዓመት እድሜ ያለው ሳሙኤል መረተ ነው።

ሳሙኤል መረት ነዋሪነቱ በደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ቡታጅራ ከተማ ውስጥ ነበር፡፡

ጓደኞቹ እንዳሉት ሳሙኤል ከረጅም ጊዜ አንስተቶ የአሽከርካሪነት ሥራውን ሲያከናውን የቆየው ከአዲስ አበባ ቡታጅራ በተዘረጋው መስመር ላይ ነበር።

በመስመሩ በሰበብ አስባቡ ካልቀጣንህ የሚሉትን የትራፊክ ፖሊስ አባላት ለማባበል ዝርዝር የ " ሃምሳ ብር " ኖቶችን በእጃቸው እያስጨበጠ ማለፍ የሁልጊዜ ተግባሩ እንደነበር  ጓደኞቹ ይናገራሉ።

ይህ የሃምሳ ብር ጣጣ ታዲያ  " አንሷል ጨምር አልጨምርም " በሚል ከትራፊክ ፖሊስ አባላት ጋር የገባበት እሰጥ አገባ ለህይወቱ መጥፋት ምክንያት መሆኑን ነው በሥፍራው ነበርን ያሉ ገልጸዋል።

የሳሙኤል ረዳት ምን አለ ?

የሳሙኤል መረተ ረዳት ሆኜ ሥሠራ ነበር የሚለው አንዱዓለም ሁሴን ፦

" መንገደኞችን አሳፍረን ከአዲስ አበባ ቡታጅራ በመጓዝ ላይ እያለን በኦሮሚያ ክልል ፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ተሬ ወረዳ ላይ ስንደርስ ሦስት ትራፊኮች ያስቆሙናል።

ሳሙኤል የመውጫ ወረቀት እና ሃምሳ ብር ሲሰጥ ከትራፊኮቹ አንዱ ሀምሳውን ቀይረህ መቶ አድርግ ሲለው ሰምቻለሁ።

ሳሙኤል አሁን የለኝም አልተዘጋጀሁም ሲለው ትራፊኩ አለበለዚያ የተሸከርካሪውን ሠሌዳ እፈታለሁ በማለት በቦክስ መታው፡፡

ይሄኔ በንዴት ተሽከርካሪውን አስነስተን ወደፊት መሄድ ስንጀምር ተከትለው መተኮስ ጀመሩ፡፡

ጥቂት እንደተጓዝን ተሸከርካሪውን በማቆም እኔም ሆንኩ ሌሎች መንገደኞች ደንግጠን ወረደን መሮጥ ጀመርን፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እሱን በጥይት መትተው ጣሉት " ሲል ቃሉን ሰጥቷል።

የሟች ሳሙኤል አባት አቶ መረተ ለማ በበኩላቸው ፤ ከትራፊክ ፖሊስ አባላቱ ጋር አለመግባባቱ የተነሳው በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ተሬ ወረዳ ላይ ቢሆንም ግድያው የተፈጸመው ግን በጉራጌ ዞን ሶዶ ወረዳ ሱተን ዙሪያ ቀበሌ ድረስ ተከታትለው በመምጣት  አንደሆነ ገልጸዋል።

" ይህን ለማን አቤት ልበል ? " ሲሉም ጠይቀዋል ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ደ/ምዕራብ ሸዋ ዞን የተሬ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ፈይሳ ደበላን ጉዳዩን በተመለከተ ከሬድዮ ጣቢያው ተጠይቀው ፤ ወንጀሉ የተፈጸመው እሳቸው ከሚመሩበት የተሬ ወረዳ አልፎ ጉራጌ ዞን ውስጥ መሆኑን በመጥቀስ " በዚህ ላይ እኔ የምለው ነገር የለም ፤ ባይሆን የደቡብ ክልል ፖሊስን ጠይቁ " ብለዋል።

የጉራጌ ዞን ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ጠጄ መሀመድ ፤ የወንጀሉ አድራሾች በኦሮሚያ ክልል ፤ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ውስጥ የሚገኙ የትራፊክ ፖሊስ አባላት ናቸው ብለዋል።

አሁን ላይ ድርጊቱን በመፈጸም የተጠረጠሩ ሦስት የትራፊክ ፖሊሶች በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተጣራባቸው እንደሚገኝ ገልጸዋል።

" የተከሰተው ነገር አሳዛኝ ነው " ያሉት ኮማንደር ጠጄ " የወንጀሉ ተጠርጣሪዎች ወዲያው በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ጥሩ ነገር ነው፡፡ አሁን ምርመራውን ከኦሮሚያ ክልል የሥራ ሃላፊዎች ጋር አብረን እየሠራን እንገኛለን ፡፡ ወንጀሉ የተፈጸመው በጉራጌ ዞን ውስጥ በመሆኑ ምርመራውን ወደ ዞኑ ለማዛወር በሂደት ላይ ነው ያለነው " ብለዋል፡፡

#ዶቼቨለ

@tikvahethiopia
አቢሲንያ ባንክ ፈጣን መፍትሔ ባስፈለገን ሰዓት መላ አለው! ሁሌም የቅርብ ድጋፍ ሲያስፈልገን ከአቢሲኒያ ባንክ መላ አለ!

በቅርብ ቀን…

የአፖሎን ትክክለኛ የማህበራዊ ትስስር ገጾች ይከታትሉ።
Website: https://apollo.bankofabyssinia.com/
Telegram: https://publielectoral.lat/apollodigitalproduct
Facebook: https://www.facebook.com/apollodigitalbank1
Instagram: https://www.instagram.com/apollodigitalbank/
Twitter: https://twitter.com/ApolloBoA
Tiktok: https://www.tiktok.com/@apollodigitalbank
YouTube: https://www.youtube.com/@apollodigitalbank
LinkedIn: https://www.linkedin.com/company/apollo-digital-bank/
Are you ready to seize 💪🏿 the opportunity that the Jasiri Talent Investor Program is offering?

Join this Information Session to discover what it takes to stand out in the application process as Jasiri’s Lead recruiter, Amandine Kayizali shares insights💡💡 for all candidates!

Register 📝 here for the session, bit.ly/43F9KDS

#Jasiri4Africa
የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት በወቅታዊ ጉዳይ ላይ መግለጫ ልኮልናል።

በመግለጫው ምን አለ ?

ምክር ቤቱ ፤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃገራችን አንዳንድ አካባቢዎች በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅት የሰብዓዊ ድጋፍ  ሰራተኞች ላይ ጉዳት እየደረሰ መሆኑን ገልጾ ይህ ጉዳይ በከፍተኛ ሁኔታ እንዳሳሰበው ገልጿል።

ምንም እንኳን ምክር ቤቱ ዝርዝር መረጃ ባይሰጥም ፤ በቅርቡ በአፋርና አማራ ክልል  የተወሰኑ  አካባቢዎች በስራ ላይ በነበሩ የሰብዓዊ ድጋፍ ሰራተኞች ላይ  የሞት አደጋ መድረሱን አመልክቶ ድርጊቱን በፅኑ አውግዟል።

ምክር ቤቱ ምን ያህል ሰራተኞች፣ የት ፣ እንዴት ፣ በምን ህይወታቸው እንዳለፈ ያብራራው ነገር የለም።  

በሌላ በኩል፤ ከቅርብ አመታት ወዲህ በሃገራችን በተለያዩ አካባቢዎች እየተከሰቱ  ያሉ ግጭቶች የዜጎችን ህይወት እየቀጠፉ እንዲሁም   ከፍተኛ የሆነ አካላዊ ፤ ስነልባናዊ እና ቁሳዊ ጉዳት እያደርሱ ይገኛሉ ብሏል።

በቅርቡ በጋምቤላ ብሔራዊ ክልልዊ መንግስት አንዳንድ አካባቢዎች በተለይም በኢታንግ ልዩ ወረዳ፤  በጋምቤላ ወረዳ፤ በጎግ ወረዳ እና በጋምቤላ ከተማ  የተፈጠረውን ግጭት ተከትሎ ንጹሃን ዜጎች መሞታቸውን ፣ መፈናቀላቸውን  የሰብዓዊ ቀውስ እንዲሁም ከግጭቱ ጋር ተያይዞ  በዜጎች ላይ የደህንነት  ስጋት መፈጠሩን ያመለከተው ምክር ቤቱ ይህ ሁኔታ  በእጀጉ  እንዳሳሰበው ገልጿል።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትገኝበት ተለዋዋጭ የግጭት ዓውድ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት  እርብርብ፤ በተለይም የመንግስትን ልዩ ትኩረት የሚፈልግ  የወቅቱ አሳሳቢ ጉዳይ እንደሆነ አስገንዝቧል።

እንደ ሐገር ለገጠመን የግጭት አዙሪት መቋጫ እና ዘላቂ መፍትሔ  ማግኘት የሚቻለው  ሁሉን አካታች በሆነ  የሰላም እና የፖለቲካ ሂደቶች፤ ልዩነቶችን በወይይትና በሰለጠነ መንገድ ለመፍታት በሚደረጉ ጥረቶች  ፤  የግጭት ምልክቶችንና አዝማሚያዎችን ቀድሞ በመለየትና ፈጣን ምላሽ በመሰጠት ጠንካራ የግጭት መከላከል ስራዎችን በመስራት እንዲሁም አጥፊዎችን ተጠያቂ በማድረግ የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ በሚደረጉ ጥረቶች እንደሆነ እንደሚያምን ምክር ቤቱ ገልጿል።

(መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#Tigray

በትግራይ ክልል ከአንድ ሺሕ በላይ ሰዎች በረኀብ እንደሞቱ ተገለጸ።

በትግራይ ክልል የሰብአዊ ርዳታ ምግብ በይፋ ከተቋረጠ 90 ቀናትን ያስቆጠረ ሲሆን በዚህም ምክንያት ከአንድ ሺ በላይ ሰዎች በረሀብ እንደሞቱ፣ የክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በተለይ ከአምስት ዓመት በታች የኾኑ ሕፃናት እና የዕድሜ ባለጸጋ አረጋውያን፣ ይበልጥ እየተጎዱ መሆኑ ነው የተገለጸው።

በኮሚሽኑ የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና ግብረመልስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ገ/እግዚአብሔር አረጋዊ መቼ ሞቱ፣ የት አከባቢ፣ እድሜያቸው የሚሉት የሟቾች መረጃ ከተለያዩ አከባቢዎች፤ ከተፈናቃይ አስተባባሪዎች፤ ከዞንና ከክልል አስተባባሪዎች እየደረሳቸው እንደሆነ አንስተዋል።

በዚህም እስካሁን በተሰበሰበው መረጃ የሟቾች ቁጥር ከ1000 ከፍ ማለቱን አስታውቀው አሁንም ቁጥሩ እየጨመረ መምጣቱን ነው የጠቆሙት።

ዳይሬክተሩ ፥ ተመዝብሯል ከተባለው የእርዳታ እህል ጎን ለጎን ምርመራው እየተካሄደ የህይወት አድን ሥራው እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

የእርዳታ ሰጪ ተቋማት በሚፈልጉት መልኩ መረጃዎችንና ተረጂዎችን የመለየት ሥራ እየተጠናቀቀ መሆኑን የገለጹት አቶ ገ/እግዚአብሔር እርዳታው እስካሁን ባለመጀመሩ በተለይ ተፈናቃዮች በአስከፊ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ነው የተናገሩት።

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ ክልል እያካሄደው ባለው የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሥራ ማኅበረሰቡ እና ተፈናቃዮች ዋነኞቹ የሰብአዊ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች ሥራቸውን በማቋረጣቸው ከአራት እስከ ሰባት ወራት ለቆየ ጊዜ ሰብአዊ እርዳታ ያለማግኘታቸውን እና በዚህም ቀደም ብሎ የነበረው የሰብአዊ ቀውስ በከፍተኛ ሁኔታ የተባባሰ መሆኑን መግለጹ ይታወሳል።

የኢሰመኮ የክትትልና ምርመራ ዳይሬክቶሬት ሰላማዊት ግርማይ እንደገለጹት፥ " ከህክምና ተቋማት እንዲሁም በአካል በመገኘት ባለሞያዎች የተለያዩ መረጃዎች ሰብስበዋል። ነገር ግን ክትትሉና ምርመራ ሂደት ላይ ስለሆነ ቁጥሩን መግለጽ አንችልም፤ ሆኖም ባደረግናቸው ክትትሎች ችግሩ አሳሳቢ መሆኑን ታዝበናል " ብለዋል።

ኮሚሽኑ፥ መንግሥትና የእርዳታ ሰጪ ተቋማት ወቅቱን የጠበቀና ልዩ ፍላጎት ያላቸውን ወይም ለመብቶች ጥሰት ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ታሳቢ ያደረገ የሰብዓዊ ድጋፍ በፍጥነት መልሰው እንዲጀምሩ አሳስቧል። #ቪኦኤ

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ያሽከርክሩ፤ እድልዎን ይሞክሩ!

የዓመቱ ስኬታችንን ደስታ ለመጋራት፤ ስለ አብሮነታችሁ ምስጋና በቴሌብር ሱፐርአፕ የተዘጋጀው የዕጣ ሽልማት እስከ ፊታችን ዓርብ ሐምሌ 21 ይቀጥላል፤

🎁 10 ላፕቶፖች
🎁 10 ታብሌቶች
🎁 10 ስማርት ስልኮች
🎁 10 ስማርት ሰዓቶች
🎁 50 ኢርበድስ
🎁 50 ሺህ የ100 ብር ሽልማቶች

በቴሌብር ሱፐርአፕ http://onelink.to/fpgu4m ተጫውተው ያሸንፉ/ Play and win የሚለውን ይጫኑ፤ ያሽከርክሩ፤ በየቀኑ እድልዎን ይሞክሩ!

#አብሮነት በላቀ አገልግሎት
#ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ላይ
#AddisAbaba

የቅዱስ ገብርኤል ክብረ በዓል በአዲስ አበባ መንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም (ቤተመንግሥት ቅዱስ ገብርኤል) በድምቀት እንደሚከበር የገዳሙ አስተዳደር ጽ/ቤት ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

በዓሉ በሰላም እንዲከበር ከሪፐብሊካን ጋርዶች ጋር እንዲሁም ከአራዳ፣ የካ፣ ቂርቆስ የፓሊስ አካላት ጋር በመነጋገር ዝግጅት መደረጉ ተመላክቷል።

በዓሉን ለማክበር የሚመጡ ምዕመና የመኪና ማቆሚያ ችግር ሳይገጥማቸው መኪናቸውን የአንድነት ፓርክ ማቆሚያ በመጠቀም በዓሉን ማክበር ይችላሉ ተብሏል።

ለበዓሉ ጊዜያዊ ጣቢያም ፤ ክሊኒክም ያለ ሲሆን በዓሉ አዲስ አበባ ደረጃ በድምቀት እንደሚከበር የገዳሙ አስተዳደር ጽ/ቤት ገልጾልናል።

ከ126 አመት ቡኃላ ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ህንፃው ስለተጎዳ ታቦቱ ለእድሳት ወደመቃኞ መግባቱን ጽ/ቤቱ አስገንዝቧል።

@tikvahethiopia