TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
" ሞባይል ስልኮች የመማር ማስተማሩን ተግባር እንደሚያስተጓጉሉ ከሳይንሳዊ ምርምር ውጤቶች እናውቃለን " - የኔዘርላንድ ትምህርት ሚኒስትር

የሞባይል ስልኮችን ጨምሮ የመማር ማስተማር ተግባር ሊያስተጓጉሉ ይችላሉ የተባሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች #በኔዘርላንድ ታገዱ።

በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ የሞባይል ስልኮችን መጠቀም እንደታገደም የኔዘርላንድ መንግሥት አስታውቋል።

እቅዱ ከትምህርት ቤቶች ጋር በመተባበር ተግባራዊ እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን በአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመትም ይጀመራል ተብሏል።

ነገር ግን ልዩ የህክምና ፍላጎት / አካል ጉዳተኛ የሆኑ ተማሪዎች ይህ እግድ እንደማይመለከታቸው ተገልጿል።

በተጨማሪ ዲጂታል ክህሎቶች ላይ በሚያተኩሩ የትምህርት ክፍለ ጊዜውም ላይ እነዚህ የቴክኖሎጂ ውጤቶች እንደሚፈቀዱም ተጠቁሟል።

ይህ እግድ በህጉ ባለመስፈሩ በህጋዊ መንገድ ተፈጻሚ ባይሆንም ወደፊት ግን ሊካተት ይችላል ተብሏል።

የሀገሪቱ የትምህርት ሚኒስትር ምን አሉ ?

ሮበርት ዲጅግራፍ ፦

" የሞባይል ስልኮች ከህይወታችን ጋር ከሞላ ጎደል የተሳሰሩ ቢሆኑም በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ ግን መገኘት የለባቸውም።

ተማሪዎች ትኩረታቸውን በደንብ ሰብስበው በጥሩ ሁኔታ እንዲማሩ እድል ሊሰጣቸው ይገባል።

ሞባይል ስልኮች የመማር ማስተማሩን ተግባር እንደሚያስተጓጉሉ ከሳይንሳዊ ምርምር ውጤቶች እናውቃለን።

የተለያዩ ጥናቶች የልጆችን የስክሪን ቆይታ ጊዜ መገደብ ከግንዛቤ እና ትኩረት መሻሻል ጋር እንደሚያያዝ ይጠቁማሉ።

ታብሌቶችና ዘመናዊ ሰዓቶችን ጨምሮ ሌሎች የቴክኖሎጂ ውጤቶች በዚህ እገዳ ውስጥ ተካትተዋል። "

መንግሥት እነዚህን የቴክኖሎጂ ውጤቶች ሙሉ በሙሉ ማገድን በተመለከተ ትምህርት ቤቶቹ ከመምህራን፣ ወላጆች እና ተማሪዎች ጋር በመምከር ተግባራዊ ሊያደርጉ እንደሚችሉ አስታውቋል።

ይህ እቅድ በሚኒስቴሩ፣ በትምህርት ቤቶች እና ባለ ድርሻ አካላት ተቋማት መካከል የተደረሰ ስምምነት መሆኑ ተገልጿል።

እቅዱ ተግባራዊ ከሆነ በኋላ በአውሮፓውያኑ 2024/2025 የትምህርት ዘመን መጨረሻ ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ ተገምግሞም በህግ ይስፈር የሚለውም ውሳኔ ይደረስበታል ተብሏል።

በተመሳሳይ ...

ፊንላንድ የሞባይል ስልኮችን በመማሪያ ክፍሎች ውስጥ የሚያግድ ውሳኔ ባለፈው ሳምንት አስተላልፋለች።

የፊንላንድ መንግሥት በትምህርት ቤቶች ውስጥ ስልኮችን የማገዱን ሁኔታም ወጥ ለማድረግ ህጉን እንደሚያሻሽል አስታውቋል።

ዩናይትድ ኪንግደም እና ፈረንሳይን ጨምሮ ሌሎች አገራትም የመማር ማስተማር ሁኔታውን ለማሻሻል የሞባይል ስልኮችን በመማሪያ ክፍሎች የማገድ ሃሳብ አቅርበዋል።

Via BBC

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC በቅርብ ቀናት በቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ ልዑክ ወደ መቐለ እንደሚጓዝ ተሰምቷል። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ዓርብ ሰኔ 23 ቀን 2015 ዓ/ም ባካሔደው መደበኛ ስብሰባ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ የልዑካን ቡድን በሚቀጥሉት ቀናት ወደ ክልል ትግራይ…
#Update

በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራ የልዑካን ቡድን ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ.ም ወደ ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የሚመራ 13 አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ሐምሌ 3 ቀን 2015 ዓ .ም ወደ ክልል ትግራይ ርዕሰ ከተማ መቐለ ይጓዛል።

ልዑካን ቡድኑ ወደ መቐለ የሚጓዘው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሰረት ለትግራይ ክልል እንዲሰጥ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ ለማድረስና በትግራይ ከሚገኙ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በሰላም ጉዳዮች ዙሪያ ለመነጋገር መሆኑ ታውቋል።

ይህንን በተመለከተም ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጽሕፈት ቤት የተላከው ደብዳቤ ለፕሬዝዳንቱ ጽሕፈት ቤት ዛሬ ማለዳ እንዲደርስ ተደርጓል።

መረጃው የኢኦተቤ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
#ICog

AI ኮድ ያድርጉ!

የአይኮግ-ኤሲሲ 2023 የኮዲንግ ክረምት ካምፕ ምዝገባ ተጀምሯል።

የመጀመሪያ ዙር ስልጠና ሃምሌ 3 ስለሚጀመር፣ አሁኑኑ ይመዝገቡ!

ኦንላይን-4000ETB
አዲስ አበባ (በአካል)-5,500 ETB
ክልል ከተሞች-4000ETB ብር ብቻ በመክፈል ልጅዎን ያስተምሩ።

ለመመዝገብ: በስልክ ቁጥራችን
+251904262728/251901379478 በመደወል

ዌብሳይታችንን በመጎብኘት
https://icogacc.com/register

ወይም ቴልግራም ቦት ይጠቀሙ
@iCogACCsummercamp_bot

ለበለጠ መረጃ የማህበራዊ ገፆቻችንን ይከተሉ
Facebook: facebook.com/icogacc

Instagram: instagram.com/icogacc
Twitter: twitter.com/icog_acc
Linkedin: linkedin.com/company/icog-anyone-can-code/
#Threads

ሜታ ኩባንያ ፤ " ትዊተር "ን የሚገዳደር አዲስ መተግበሪያ ስራ አስጀምሯል።

ይኸው መተግበሪያ " ትሬድስ " የሚሰኝ ሲሆን የፅሁፍ መልዕክት መለዋወጫ ነው። መተግበሪያው ከ " ኢንስታግራም " ጋር የተቆራኘ ነው።

እስካሁን አገልግሎቱ በጀመረ በ4 ሰዓታት ውስጥ 5 ሚሊዮን ሰዎች መመዝገባቸውን ማርክ ዙከርበርግ አሳውቋል።

የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለመሆን የ " ኢንስታግራም " አካውንት ያስፈልጋል።

መተግበሪየው በአሜሪካን ጨምሮ 100 ሀገራት ላይ ከትላንት ጀምሮ ስራ ላይ ውሏል።

በአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ውስጥ ከቁጥጥር ጋር በተያያዘ ለጊዜው አልተጀመረም።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዚሁ የፅሁፍ መልዕክት መለዋወጫ ላይ ከቤተሰቡ ጋር የሚገናኝ መሆኑን ለማሳወቅ ይወዳል።

" ትሬድስን " ለማወረድ ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.instagram.barcelona

Tikvah-Ethiopiaን ለማግኘት http://threads.net/tikvahethiopia

@tikvahethiopia
Threads_an_Instagram_app_289.0.0.68.109_.apk
74.1 MB
#Threads_an_Instagram_App

#ማስታወሻ ፦ ከፕሌይ ስቶር / አፕ ስቶር ላይ ለማውረድ VPN አማራጮቻችሁን USA ወደሚል ወይም አፕሊኬሽኑ ወደ ተለቀቀባቸው አከባቢዎች ቀይረው ማውረድ ይችላሉ።

#META

@tikvahethiopia
#ፓርላማ

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 6ኛውን፣ 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 28ኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡

ምክር ቤቱ በስብሰባው የ27ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔን መርምሮ አጽድቋል፡፡

የምክር ቤት አባላትም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌደራል መንግስት የ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ከምክር ቤት አባላት ለሚቀርቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Via HoPR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፓርላማ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 6ኛውን፣ 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 28ኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ ምክር ቤቱ በስብሰባው የ27ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔን መርምሮ አጽድቋል፡፡ የምክር ቤት አባላትም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌደራል መንግስት…
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን ለቀው ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ ፓርላማውም እንዲበተን ጠየቁ።

ዶ/ር ደሳለኝ ኢትዮጵያ ሀገራዊ ቀውስ ውስጥ መሆኗን እና ለዚህም የዳረጋት " የብልፅግና መራሹ መንግስት እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወደቀ አመራር " ነው ሲሉ ተናግረዋል።

ሀገሪቱን ከዚህ ችግር ለማውጣት የሀገራዊ ቀውስ መፍትሄ አፈላላጊ ጉባኤ እንዲዘጋጅ ጠይቀዋል።

ብልፅግናም ሆነ ፓርላማው ሀገሪቱን ከቀውስ ማውጣት ስለማይችሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን ለጊዜያዊ የሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 60 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት በምክር ቤቱ ፍቃድ ምክር ቤቱን እንዲበትኑ እና ለአዲስ ምርጫ መንገዱን እንዲጠርጉ ጠይቀዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን ለቀው ለሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ ፓርላማውም እንዲበተን ጠየቁ። ዶ/ር ደሳለኝ ኢትዮጵያ ሀገራዊ ቀውስ ውስጥ መሆኗን እና ለዚህም የዳረጋት " የብልፅግና መራሹ መንግስት እንዲሁም የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወደቀ አመራር " ነው ሲሉ ተናግረዋል። ሀገሪቱን ከዚህ ችግር ለማውጣት የሀገራዊ ቀውስ መፍትሄ አፈላላጊ ጉባኤ እንዲዘጋጅ…
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ምን አሉ ?

የተ/ም/ቤት አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፦

" ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ መንበረ ስልጣን ከወጡበት ከመጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ እየተወሳሰቡ የሄዱት የሀገራችን ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች አሁን ላይ ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ መሸጋገራቸውን ማሸፋፈን ወደማይቻልበት ደረጃ ደርሰዋል።

ብልፅግና መራሹ መንግስትዎ ፦
- የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የሚገባበት ፣
- ነጋዴው ከቦታ ወደ ቦታ ተንቀሳቅሶ ሰርቶ እና ነግዶ የሚኖርበት
- ገበሬው ምርጥ ዘር እና ማዳበሪያ አግኝቶ አርሶ የሚበላበት እንዲሁም ከተሜውን የሚቀልብበት ሁኔታ መፍጠር አልቻለም።

የኢትዮጵያ ህዝብ በችጋር እየተጠበሰ፣ በረሃብ እየተሰቃየ ነው።

የኑሮ ውድነቱ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ወገናችንን ከእጅ ወደ አፍ የነበረውን ኑሮ እንኳን መግፋት ወደማይችልበት ደረጃ ደርሷል።

ኢኮኖሚው ታሟል፣ መካከለኛ ነዋሪ የነበረውም ተመቶ ወደ ድህነት ወለል ወርዷል።

ስራ አጥነት ተስፋፍቷል፣ የሀገራችን የነገ ተስፋ የሆኑ ወጣቶችም ሀገራቸው ውስጥ ተስፋ በማጣታቸው ስደትን ብቸኛ ምርጫ አድርገውታል።

ዜጎች በጠራራ ፀሀይ ይታገታሉ በሚሊዮን ብር ይጠየቅቸዋል፣ የመንግስት የፀጥታ መዋቅር በተለይም ፖሊስ ደግሞ አማራዎችንን እና የአማራ ልሂቃንን የአማራ ህዝብ ጥያቄዎችን በማንሳታቸውና መንግሥትን በተለያየ ማንገድ በመተቸታቸው ብቻ የፈጠራ ወንጀል እየተሰጣቸው በማንነታቸው በጅምላ ይታሰራሉ ፣ በጅምላ ይከሰሳሉ ፍርድ ቤት ነፃ ሲላቸው ፖሊስ ግለሰቦችን አስሮ ያቆያል።

የኢትዮጵያ መልካፖለቲካ በሙሉ ያዳረሰ በሚባል ደረጃ ሀገራችን ሁሉም አካባቢዎች የደም ምድር ሆነዋል።

ሙሉ አማራ ክልል አዲስ የጦርነት ቀጠና ተደርጓል፣ ከፊል ኦሮሚያ ክልል የጦርነት ቀጠና ሆኖ ባጅቷል፣ ትግራይ አማራ እና አፋር ፋይዳ ባልነበረው የብልፅግናና የህወሓት የስልጣን ጦርነት ምክንያት ደቋል። ቤኒሻንጉል ፣ጋምቤላ፣ አብዛኛው የደቡብ ኢትዮጵያ አካባቢዎችም ከሌሎች የተለየ አይደለም።

በማህበራዊ ዘርፍም ወንጀል ተበራክቷል፣ ከ200 ሺህ በላይ ሰዎች / ዜጎች በመንግስት ቤታቸው ፈርሶ ጎዳና ላይ ወድቀዋል ፤ እንደ ብልፅግና ሹማምንት አባባል ' ህጋዊ ድሃ ተደርገዋል ' ።

በሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎች በሰሜኑና በምዕራቡ ሀገራችን ክፍሎች በነበረው ጦርነት እና ማንነት ተኮር ጥቃቶች የውስጥ ተፈናቃይ ሆነው የሰቆቃ ኑሮን ይገፋሉ።

ባለፉት 5 ዓመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ህይወታቸውን ተነጥቀዋል። ለዚህ ሁለንተናዊ ሀገራዊ ምስቅልቅል ቀውስ እና ውድመት ወይም ሀገራዊ መክሸፍ ዋነኛው ተጠያቂው የብልፅግና መራሹ መንግስት እና የእርሶ የወደቀ አመራር  / failed leadership ነው።

ገዢው ፓርቲ ብልፅግናን አመጣለሁ እያለ ቢምል ቢገዘትም በተግባር ለኢትዮጵያ ህዝብ ያመጣለት ግን ጉስቅልና ሆኗል።

ብልፅግና ሀገርን ከቀውስ ማውጣት ካልቻለ እና ዋነኛ ተቃዋሚ ፓርቲዎችም የብልፅግና / የአገዛዙ አገልጋይ በመሆናቸው እና የችግሩም አካል በመሆናቸው ከፓርቲዎቹ የሚጠበው መፍትሄ አይኖርም።

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ለወደቀው የእርሶ እና የብልፅግና ፓርቲዎ አመራር መፍትሄው ምንድነው ? የሀገራዊ ቀውስ መፍትሄ አፈላላጊ ጉባኤ እንዲዘጋጅ አድርገው ስይረፍድ ለሀገራዊ ቀውሱ መላ ቢበጅ አይሻልም ወይ ? እንደእኔ እንደ አንድ የህዝብ ተወካይነቴ ብልፅግና ፓርቲ መራሹም ሆነ ፓርላማው ሀገራችን ከገባችበት የፖለቲካ ቅርቃር ማውጣት ስለማይችሉ ስልጣኖን ለጊዜያዊ ሲቪል አስተዳደር እንዲያስረክቡ ፣ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላትም በኢፌዴሪ ህገመንግስት አንቀፅ 60 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት በምክር ቤቱ ፍቃድ ምክር ቤቱን እንዲበትኑ እና ለአዲስ ምርጫ መንገዱን እንዲጠርጉ መጠየቅ እፈልጋለሁ።

አመሰግናለሁ ! "

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ፓርላማ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 6ኛውን፣ 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 28ኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ ምክር ቤቱ በስብሰባው የ27ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔን መርምሮ አጽድቋል፡፡ የምክር ቤት አባላትም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌደራል መንግስት…
" ዘንድሮ 6 ነጥብ 1 የኢኮኖሚ ዕድገት ተመዝግቧል " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

በዚህ ዓመት የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት 6 ነጥብ 1 ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉን እና በቀጣዩ ዓመት ደግሞ 6 ነጥብ 4 የምጣኔ ኃብት ዕድገት ሊኖር እንደሚችል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) መተንበይ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 2ኛው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ-ግብር በመተግበር ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢኮኖሚው ማሻሻያ ዋናው ግብ የግሉን ዘርፍ ለማነቃቃትና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ ዓመት የኑሮ ውድነቱ 37 በመቶ ደርሶ የነበረ ሲሆን፤ በርካታ ስራዎች በመሰራታቸው ምክንያት ቁጥሩን ወደ 30 በመቶ መቀነስ መቻሉን እና እንደ ሀገር ያጋጠመውን የኑሮ ውድነት ለመግታት ወደ ገበያ የተረጨውን ገንዘብ ለመቆጣጠር መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡

Via HoPR

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ምን አሉ ? የተ/ም/ቤት አባል ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ፦ " ጠ/ሚ ዐቢይ ወደ መንበረ ስልጣን ከወጡበት ከመጋቢት 2010 ዓ/ም ጀምሮ እየተወሳሰቡ የሄዱት የሀገራችን ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሮች አሁን ላይ ወደ ሁለንተናዊ ቀውስ መሸጋገራቸውን ማሸፋፈን ወደማይቻልበት ደረጃ ደርሰዋል። ብልፅግና መራሹ መንግስትዎ ፦ - የኢትዮጵያ ህዝብ በሰላም ወጥቶ የሚገባበት ፣ - ነጋዴው…
" አብኖች የት ነበራችሁ ? " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

የህ/ተ/ም/ቤት አባሉ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ በሰሜኑ ክፍል ትግራይ ፣ አማራና አፋር ፋይዳ ባልነበረው ጦርነቱ መድቀቃቸውን ተናግረዋል።

ይህ ጦርነትም " #የብልፅግና እና #የህወሓት #የስልጣን ጦርነት " መሆኑን ገልጸው ነበር።

ይህ በተመለከተ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ አጭር አስተያየት ሰጥተው አልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፤ " እንደተባለው የTPLF እና የብልፅግና ችግር ከነበረ አብኖች (የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ) የት ነበራችሁ ? " ሲሉ ጠይቀዋል።

እዚህ ላይ " ለምን አታስታርቁም ነበር የሚል ጥያቄም ይነሳል። " ያሉት ዶ/ር ዐቢይ " አስታራቂ ሲጠፋ ነው ግጭት የሚበዛው " ብለዋል።

" ድግሱን #ስናፋፋም ቆይተን አሁን ጉዳዩን ለተወሰነ ወገን መስጠት ተገቢ አይደለም " ያሉት ጠቅይላይ ሚኒስትሩ " ግጭቱን ማንም ይጀምረው ማንም ጥሩ አይደለም፤ ጥፋት ነው " ብሎ መቀበል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

#TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#EOTC የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ዛሬ ረቡዕ ሰኔ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው ልዩ ስብሰባ በኦሮሚያ እና በደቡብ ክልሎች በተደራቢነት ተይዘው ለቆዩ ክፍት በኾኑና አንገብጋቢ ችግር ባለባቸው ዘጠኝ አህጉረ ስብከት ላይ የሚመደቡ ዘጠኝ ኤጲስ ቆጰሳትን ምርጫ አካሂዷል። ለኦሮሚያ ክልል 7 አህጉረ ስብከት ፦ 1. አባ ሣህለ ማርያም ቶላ - ምዕራብ አርሲ - (ሻሸመኔ) ሀገረ ስብከት 2. አባ ወልደ…
#Update

የተመረጡት ኤጲስ ቆጶሳት የተሾሙ ሲሆን በዓለ ሢመታቸው ሐምሌ 9 ቀን 2015 ዓ.ም. እንዲፈጸም ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ አስተላልፏል።

ይህ የተሰማው ዛሬ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የእጩ ኤጲስ ቆጶሳት ምርጫ በተመለከተ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ነው።

ዝርዝር መግለጫውን ከላይ ያንብቡ።

#ETOTCTV

@tikvahethiopia