TIKVAH-ETHIOPIA
#ፓርላማ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት 6ኛውን፣ 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን፣ 28ኛ ስብሰባውን እያካሄደ ነው፡፡ ምክር ቤቱ በስብሰባው የ27ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ-ጉባዔን መርምሮ አጽድቋል፡፡ የምክር ቤት አባላትም ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በ2015 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ላይ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የፌደራል መንግስት…
" ዘንድሮ 6 ነጥብ 1 የኢኮኖሚ ዕድገት ተመዝግቧል " - ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

በዚህ ዓመት የኢትዮጵያ ምጣኔ ኃብት 6 ነጥብ 1 ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉን እና በቀጣዩ ዓመት ደግሞ 6 ነጥብ 4 የምጣኔ ኃብት ዕድገት ሊኖር እንደሚችል ዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (IMF) መተንበይ መቻሉን ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ 2ኛው የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሃ-ግብር በመተግበር ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።

የኢኮኖሚው ማሻሻያ ዋናው ግብ የግሉን ዘርፍ ለማነቃቃትና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻል ነው ብለዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ በዚህ ዓመት የኑሮ ውድነቱ 37 በመቶ ደርሶ የነበረ ሲሆን፤ በርካታ ስራዎች በመሰራታቸው ምክንያት ቁጥሩን ወደ 30 በመቶ መቀነስ መቻሉን እና እንደ ሀገር ያጋጠመውን የኑሮ ውድነት ለመግታት ወደ ገበያ የተረጨውን ገንዘብ ለመቆጣጠር መንግስት በትኩረት እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡

Via HoPR

@tikvahethiopia