TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ከመልሚ

በከተሞች ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ለሚጠቀሙበት መንገድ የአገልግሎት ክፍያ የሚከፍሉበት ስርዓት እየተዘረጋ ነው።

ይህ ስርዓት ከተሞች ገቢያቸውን ለማሳደግ ሊሠሯቸው ይገባል ተብለው በዕቅድ ከተያዙ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱ ነው ተብሏል።

ሥርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግ የመጨረሻው የጥናት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የከተሞች ገቢ ሪፎርም ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ ወ/ሪት አፀደ ኃይሉ ተናግረዋል።

የከተማ መንገድ የአገልግሎት ክፍያ ሥርዓትን ለመዘርጋት የሚደረገው ጥናት የአዳማ፣ የድሬዳዋ እና የባህር ዳር ከተሞችን ናሙና በመውሰድ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀዋል።

በጥናቱ በአጠቃላይ በከተሞች ውስጥ ያለው የተሽከርካሪዎች ምልልስና በመንገዶች ላይ የሚያሳድሩት ጫና የሚዳሰስ ሲሆን መንገዶቹ ጥገና ሆነ መልሶ መገንባት ሲያስፈልጋቸው ከተጠቃሚዎች በሚያገኙት ገቢ የሚሠሩበትን ሥርዓት ለመዘርጋት ያለመ ነው ብለዋል።

በ3ቱ ከተሞች በሚወሰደው ናሙና መሠረት አዲስ አበባን ጨምሮ በሁሉም ከተሞች፣ የከተማ መንገድ ተጠቃሚዎች ክፍያ ይጠይቃሉ ብለዋል።

ወ/ሪት አፀደ ኃይሉ ፤ ሁሉም ተሽከርካሪዎች ተመሳሳይ ክፍያ ባይከፍሉም በጥናቱ ግኝት መሠረት በመንገዶች ላይ እንደሚኖራቸው ተፅዕኖ ክፍያ ይጠየቃሉ ያሉ ሲሆን " ክፍያው ሁሉንም ባለ ሞተር ተሽከርካሪዎች ብቻ ያካትታል። ሞተር የሌላቸው ተሽከርካሪዎች በዚህ ሥርዓት ውስጥ አልተካተቱም " ብለዋል።

ጥናቱ ሲጠናቀቅ የትኞቹ ተሽከርካሪዎች ምን ያህል መክፈል አለባቸው የሚለው ሆነ መቼና የት ይከፍላሉ የሚለው እንደሚለይና ሥርዓቱም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተግባራዊ ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅ መግለፃቸውን #ሪፖርተር_ጋዜጣ አስነብቧል።

@tikvahethiopia