TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ደቡብ ክልል‼️

በደቡብ ክልል ኢትዮጵያን ከኬንያ ጋር የሚያዋስነውን ድንበር በህገ ወጥ መንገድ ሊሻገሩ ነበር የተባሉ 25 ኤርትራውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ። ወጣቶቹ በኬንያ አቋርጠው #ኡጋንዳ የመግባት እቅድ እንደነበራቸው ፖሊስ ገልጿል።

ኤርትራውያኑ ሐሙስ ዕለት የተያዙት በክልሉ በደቡብ ኦሞ ዞን፤ ሐመር ወረዳ ውስጥ ቱርሚ በተባለች አነስተኛ የጠረፍ ከተማ ላይ መሆኑን የዞኑ ፖሊስ ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር #ካሳ_ካውዛ ለDW ተናግረዋል፡፡ ኤርትራውያኑ በወጣትነት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ
መሆናቸውን ኃላፊው ገልጸዋል።

“የተያዙበት ምክንያት ባልተለመደ ሁኔታ ወደዚያ በህዝብ ማመላለሻ አውቶብስ ከደረሱ በኋላ ከምሽቱ ሶስት ሰዓት ላይ ወደ ጭነት መኪና ተዛውረው ሊጓዙ ሲሉ በፖሊስ ጥርጣሬ ተይዘዋል። ሲታዩ ያው በኬንያ በኩል ወደ ኡጋንዳ ካምፓላ መድረስ እንፈልጋለን የሚሉ ወጣቶች
ነበሩ። ወጣቶቹ እነርሱ እንደሚሉት የኤርትራ ዜጎች ነን ነው። በእጃቸው ላይ የያዙት አንዳንድ መታወቂያዎችም ከኤርትራ ትምህርት ቤት የተነሱ መሆኑን የሚያሳዩ ናቸው። አሁን ወደ ዞናችን ፖሊስ መምሪያ አስመጥተን ወጣቶቹን በዚያው በዞናችን ፖሊስ መምሪያ ግቢ ውስጥ ይገኛሉ” ሲሉ የዞኑ የፖሊስ ኃላፊ ወጣቶቹ እንዴት ሊያዙ እንደቻሉ አስረድተዋል።

ዋና ኢንስፔክተር ካሳ ወጣቶቹን በተመለከተ በቀጣይነት ምን ማድረግ እንዳለባቸው ከክልሉ መንግስት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ የኤርትራ ኤምባሲ እስከአሁን በፖሊስ እጅ በሚገኙት ኤርትራዊያን ጉዳይ ላይ ያለው ነገር አለመኖሩን ተዘግቧል።

ምንጭ፦ DW አማርኛው አገልግሎት
@tsegabwolde @tikvahethiopia