TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#እንድታውቁት የአዲስ- አዳማ የክፍያ መንገድ የአዳማ ዋና መውጫ ላልተወሰነ ጊዜ ዝግ መሆኑን የኢትዮጵያ የክፍያ መንገዶች ኢንተርፕራይዝ አስታውቋል፡፡ መንገዱ የተዘጋው ትላንት ምሽት ከደረሰ አደጋ ጋር በተያያዘ ነው። ኢንተርፕራይዙ ባወጣው መግለጫ ትላንት ሰኞ ምሽት 4:45 ላይ ወደ አዳማ አረቄ ጭኖ እየተጓዘ ክፍያ በር ላይ በተገለበጠ ተሽከርካሪ ምክንያት ባጋጠመ የእሳት አደጋ በህይወትና ንብረትላይ…
ፎቶ ፦ ትላንት ሰኞ ፤ ምሽት 4 : 45 በአዲስ አበባ - አዳማ የፍጥነት መንገድ ላይ የ " ሐበሻ አረቄ " ጭኖ ሲጓዝ በነበረ ኤፍ ኤስ አር ተሽከርካሪ ላይ የደረሰው አደጋ ለአራት ሰዎች ህይወት ማለፍ እና አስር / 10 ሚሊዮን ብር ለሚገመት ንብረት ውድመት ምክንያት ሆኗል።

ይህን አደጋ ተክትሎ የአዲስ - አዳማ ዋና መውጫ ላልተወሰነ ጊዜ ተዘግቷል።

Photo Credit : OBN

@tikvahethiopia
" የወይብላ ቅድስት ማርያምና ቅዱስ ሚካኤል የጥምቀት በዓል በተለመደው ቦታ ይከበራል " - ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂ የቅዱስ ሲኖዶስ አባል "እንኳን ለጌታችን መድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓል አደረሳችሁ" ሲሉ መልእክት አስተላልፈዋል።

በመልዕክታቸው፤ የጥምቀት በዓል በአደባባይ ሲከበር 1500 ዓመታትን አስቆጥሯል ብለዋል።

ብፁዕነታቸው፤ በአዲስ አበባ ደረጃ ከጃንሜዳ በተጨማሪ 83 የጥምቀተ ባሕረ ማክበሪያ ቦታዎች መኖራቸውን ገልጸው ጥር 10 ቀን ታቦታቱ ከመንበረ ክብራቸው ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በመውረድ ቃና ዘገሊላን ጨምሮ ለ3 ቀናት በየባሕረ ጥምቀቱ እንደሚከበር ተናግረዋል።

በ2014 ዓ.ም የጥምቀት በዓል የወይብላ ማኅደረ መለኮት ቅድስት ማርያም እና ቅዱስ ሚካኤል ታቦታት ከኦሮሚያ ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ከሌሎች ታቦታት ጋር አድሮ ሲመለስ ተፈጥሮ በነበረው ግጭት የሰው ሕይወት የመጥፋትና የአካል መጉደል አደጋ በዚህ ዓመት አይደገምም ብለዋል።

በዚህ ዓመት በአደባባይ የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ሰላማዊ ለማድረግ ከኦሮሚያ ክልል የመንግሥት ባለሥልጣናትና ከአዲስ አበባ መስተዳድር ኃላፊዎች ጋር ስለበዓሉ አከባበር ሰፊ ሥራ መሠራቱን አውስተው የማኅደረ መለኮት ወይብላ ማርያም በዓልም በዚያው በተለመደው የማክበሪያ ቦታ እንደሚከበር ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው፤ መላው ኦርቶዶክሳዊ ክርስቲያን በተለይ በልዩ ልዩ መልክ የተደራጁ የወጣት ማኅበራት ኅብረት፣ ለበዓሉ ድምቀት በሁለንተናዊ ሥራ እየተሳተፉ የሚገኙ ወጣቶችና የሰ/ት/ቤት አባላት ከጸጥታ አካላት ጋር በመናበብና በጋራ በመሥራት " የክብረ በዓሉን መንፈሳዊ ድባብ እናስጠብቅ " ሲሉ አሳስበዋል።

ምንጭ፦ አ/አ ሀገረ ስብከት

@tikvahethiopia
ዛሬ እነማን ይሾሙ ይሆን ?

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያደርገው ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀረቡ ሹመቶችን መርምሮ ያፀድቃል፡፡

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን የሚያካሂደው ዛሬ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ እንደሆነ ተጠቁሟል።

በስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ሹመቶችን ከማፅደቅ ባለፈ የም/ቤቱን 2ኛ አመት የስራ ዘመን 7ኛ መደበኛ ስብሰባ ቃለ ጉባኤ መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ፦ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በቅርቡ ለተሾሙ 14 ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደሮች እና 7 አምባሳደሮች በብሔራዊ ቤተ መንግስት በተካሄደ ስነ-ስርዓት የሹመት ደብዳቤ ሰጥተዋል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ፣ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ እና ሌሎች የስራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።

ተሿሚ አምባሳደሮች በጠቅላይ ፍ/ቤት ፕሬዝዳንት ወይዘሮ መዓዛ አሸናፊ አማካኝነት ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል።

ፎቶ፦ የፕ/ት ፅ/ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዛሬ እነማን ይሾሙ ይሆን ? የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያደርገው ስብሰባ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀረቡ ሹመቶችን መርምሮ ያፀድቃል፡፡ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ 6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 2ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን የሚያካሂደው ዛሬ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ እንደሆነ ተጠቁሟል። በስብሰባው በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚቀርቡ ሹመቶችን ከማፅደቅ ባለፈ የም/ቤቱን…
#Update

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ እና ምክትላቸው አቶ ሰለሞን አረዳ " #በፍቃዳቸው ከስራቸው መልቀቃቸው " ተገለጸ።

ይህ የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው።

ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባው ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትነት የቀረቡ ዕጩዎችን መርምሮ ሹመታቸውን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት የሆኑት ወ/ሮ መአዛ አሸናፊ እና ምክትላቸው አቶ ሰለሞን አረዳ " #በፍቃዳቸው ከስራቸው መልቀቃቸው " ተገለጸ። ይህ የተገለጸው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እያካሄደ ባለው መደበኛ ስብሰባ ላይ ነው። ምክር ቤቱ በዛሬው ስብሰባው ለፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንትነት የቀረቡ ዕጩዎችን መርምሮ ሹመታቸውን እንደሚያጸድቅ…
#Update

በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ፡፡

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትን ሹመት ያጸደቀው፤ በሶስት ድምፅ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

Photo Credit : ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትን ሹመት ያጸደቀው፤ በሶስት ድምፅ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። Photo Credit : ኤፍ ቢ ሲ @tikvahethiopia
#Update

ወይዘሮ አበባ እምቢአለ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።

ምክር ቤቱ የወይዘሮ አበባ እምቢአለን ሹመት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ወ/ሮ አበባ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኛነት ፣ የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግነት፣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኛነት አገልግለዋል።

አቶ ቴዎድሮስ ምህረት (ፕሬዜዳንት) እና ወ/ሮ አበባ እምቢአለ (ምክትል ፕሬዜዳንት) በጉባኤው ፊት ቀርበው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

ነገ በመላው አዲስ አበባ ት/ቤቶች ዝግ ሆነው ይውላሉ።

በነገው እለት በሚከበረው የከተራ በዓል ምክንያት መንገዶች ስለሚዘጉ በሁሉም ትምህርት ቤቶች ትምህርት የማይኖር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
እንኳን አደረሳችሁ !

እንኳን ለጥምቀት ከተራ በዓል #በሰላም አደረሳችሁ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጎንደር ከቀናት በኃላ ለሚከበረው የጥምቅት በዓል እንግዶች ከወዲሁ ወደ ታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ መግባት መጀመራቸው ተሰምቷል። የጎንደር ከተማ እና አካባቢው ሆቴሎች፣ ሎጂዎችና ሪዞርቶች ማኅበር ፤ ላለፉት ሁለት ዓመታት በኮረና ቫይረስና በጦርነት ምክንያት ተቀዛቅዞ የነበረው የቱሪዝም እንቅስቃሴ አሁን ላይ መልሶ እየተነቃቃ መሆኑን አመልክቷል። ጎንደር እንግዶቿን በምቾት ተቀብላ ለማስተናገድ ሆቴሎቿ…
ለጥምቀት በዓል ጎንደር ገብተዋል ?

የታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ለጥምቀት በዓል ወደ ከተማው የገቡና መኝታ ቦታ ማግኘት ያልቻሉ እንግዶችን " አንድ አባወራ አንድ እንግዳ " በሚል እንደሚያስተናግዱ አሳውቀዋል።

በአሁን ሰዓት ጎንደር ሆናችሁ ምናልባት የመኝታ ቦታ ያልያዛችሁ እና መኝታ ጥበት ከገጠማችሁ የጎንደር ህዝብ ቤቱን ፣ ዶሩሙን ፣ አዳራሹን፣ ግቢውን አዘጋጅቶ እየጠበቀ ነው።

ጎንደር የገባ ማንኛውም እንግዳ ከላይ በምስሉ ላይ ስማቸው የተዘረዘረ ነዋሪዎች ለእንግዶች  መኝታ ማዘጋጀታቸውን በማወቅ በስልካቸው ላይ በመደወል ቦታውን በማግኘት መጠቀም ይችላል።

እንግዶች #ከሌላ_ቦታ_የመጡ_ስለመሆናቸው መታወቂያቸውን በማሳየት በተዘጋጀው ማረፊያ መጠቀም እንደሚችሉ ከጎንደር ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

ጎንደር በዚህ ዓመት ለጥምቀት በዓል እጅግ ከፍተኛ የእግዶችን ቁጥር እያስተናገደች እንደምትገኝ ለማወቅ ተችሏል።

እንደ አማራ ክልል ባህል እና ቱሪዝም መረጃ ፤ በጎንደር ጥምቀትን ለማክበር ቦይንግን ጨምሮ በቀን እስከ 24 በረራዎች እየተደረጉ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
#መልዕክት

የጥምቀት በዓል የቤተክርስቲያኒቱን ክብር በጠበቀ መልክና በሰላም እንዲከወን ኮሚቴዎች ተዋቅረው እየሰሩ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አሳውቃለች።

የጥምቀት በዓል የቤተክርስቲያኒቱ መገለጫና ትልቅ በዓል በመሆኑ በዓሉን ለማስፈፀም በተለያየ ዘርፍ የተቋቋሙ የበዓሉን መርሐ ግብር በተሟላ ሁኔታ የሚያግዙ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ስራቸውን እየሰሩ ይገኛሉ።

ቤተክርስቲያኗ፤በዓሉ የኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን የዓለም ህዝብም የሚያደንቀው የቤተክርስቲያን በዓል ነው ብላለች።

ከበዓሉ ላይ በተያያዘ ሊደረጉ የማይገባቸው ጉዳዮች ተነስተው መልዕክት ተላልፏል። ይህም በዋናነት የባንዲራና የአለባበስ ሥነ ሥርዓትን የሚመለከት ነው።

አለባበስን በተመለከተ ካህናት የቤተክርስቲያኒቱን ሥርዓት በጠበቀ መልኩ መልበስ እንዳለባቸው ተገልጿል።

ምዕመናንም እንደተለመደው #ነጭ_ልብስ ለብሰው መገኘት እንዳለባቸው መልዕክት ተላልፏል።

በተጨማሪ በዓሉን ላይ የሚያዙ ጥቅሶች የሚያስማሙ እንጂ የሚያጋጩ ሊሆኑ እንደማይገባቸው ቤተክርስቲያን መልዕክቷን አስተላልፋለች።

ባንዲራን አስመልክቶ ምዕመናን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ያጸደቀችው የቤተክርስቲያኒቱ አርማ ያለበትን ባንዲራ እና የፌዴራል መንግስቱን ባንዲራን መያዝ እንደሚችሉ ከዚያ ውጪ ግን ይዞ መውጣት እንዳልተፈቀደ አስገንዝባለች።

በተጨማሪ ምዕመናን የሚመጡት በዓሉን ለማክበር እንደመሆኑ በዓሉን የጸብና የመታገያ መድረክ ሊያደርጉት እንደማይገባ ማሳስቢያ ተላልፏል።

"ማንም የፖለቲካ ሀሳቡን በቤቱ  እንጂ የእምነት ማስፈጸሚያ ቦታ ላይ ሊተገብረው አይገባም፤ እንዲህ ያለ ድርጊት በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ ያስወግዛልም፤ የፖለቲካ ሀሳባቸውን ለማስፈጸሚያ የሚጠቀሙ የቤተክርስቲያኒቱ ጠላቶች ናቸውም " ተብሏል።

@tikvahethiopia