TIKVAH-ETHIOPIA
#Update በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የህግ ትምህርት ረዳት ፕሮፌሰር የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ሆነው ተሾሙ፡፡ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንትን ሹመት ያጸደቀው፤ በሶስት ድምፅ ተዐቅቦ በአብላጫ ድምጽ መሆኑን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። Photo Credit : ኤፍ ቢ ሲ @tikvahethiopia
#Update

ወይዘሮ አበባ እምቢአለ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው ተሹመዋል።

ምክር ቤቱ የወይዘሮ አበባ እምቢአለን ሹመት በሙሉ ድምፅ አፅድቋል።

ወ/ሮ አበባ በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዳኛነት ፣ የፌደራል ስነምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አቃቤ ህግነት፣ በፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በዳኛነት አገልግለዋል።

አቶ ቴዎድሮስ ምህረት (ፕሬዜዳንት) እና ወ/ሮ አበባ እምቢአለ (ምክትል ፕሬዜዳንት) በጉባኤው ፊት ቀርበው ቃለ-መሐላ ፈጽመዋል።

@tikvahethiopia