TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
#ነዳጅ የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር የሕዳር ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል ብሏል። ሚኒስቴሩ ከአውሮፕላን ነዳጅ በስተቀር የነዳጅ ዋጋ #በጥቅምት_ወር በነበረው እንደሚቀጥል ገልጿል። የነዳጅ ዋጋው ከጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ሕዳር 30 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ የሚዘልቅ ነው። በሁለተኛው ምዕራፍ ከመስከረም 18 ቀን 2015…
#ነዳጅ

ቤንዚን በሊትር 61 ብር ከ29 ሳንቲም ገባ።

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረጉን አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው የዋጋ ክለሳ ዝቅተኛ ገቢ ላለው ሕብረተሰብ የሚሰጠው ድጎማ እንዲጨምር መደረጉንም ገልጿል።

በዚህም በአንድ ሊትር ቤንዚን ሲሰጥ የነበረው ድጎማ ከብር 15 ከ 76 ሳንቲም ወደ ብር 17 ከ 33 ሳንቲም እንዲሁም የአንድ ሊትር ናፍጣ ድጎማ ከብር 19 ከ02 ሳንቲም ወደ ብር 22 ከ 68 ከፍ እንዲል መደረጉ ተገልጿል።

በቀጣይ ፤ ሦስተኛ ዙር እና ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ÷

- ቤንዚን በሊትር 61 ብር ከ29 ሳንቲም፣

- ነጭ ናፍጣ በሊትር 67 ብር ከ 30 ሳንቲም

- ኬሮሲን በሊትር 67 ብር ከ30 ሳንቲም

- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ67 ሳንቲም፣

- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 48 ብር ከ70 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 67 ብር ከ91 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡

ምንጭ፦ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍ ቢ ሲ

@tikvahethiopia
#China

ቻይና ከ3 ዓመታት በኋላ ለመጀመርያ ጊዜ ድንበሯን #ለጎብኚዎች ከፍት አድርጋለች።

ቻይና በመጋቢት 2020 ዓ/ም የኮቪድ  19 ወረርሽኝን ተከትሎ ነበር የጉዞ እግድ የጣለችው።

ከአሁን በኃላ ገቢ መንገደኞች ማቆያ ስፍራ መቆየት ሳያስፈልጋቸው በቀጥታ መግባት ይችላሉ። ይሁንና ገቢ መንገደኞች #በ48_ሰዓታት ውስጥ የወሰዱትን የክትባት ማስረጃ ማቅረብ እንደሚጠበቅባቸው ቢቢሲ ፅፏል።

@tikvahethiopia
#ጥምቀት

ጎንደር ከተማ በጥምቀት በዓል ሰሞን በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ እንግዶችን ለመቀበል የሚያስችላትን አስፈላጊውን ሁሉ ዝግጅት ማድረጓ አሳውቃለች።

የጎንደር ከተማ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ፤ በጥምቀት በዓል ሰሞን እስከ 2 ቢሊየን ብር በቱሪዝሙ ምክንያት ኢኮኖሚው ገቢ ያገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅም አሳውቋል።

በጥምቀት በዓል ወቅት ከ750 ሺ እስከ 1 ሚሊየን ጎብኚ ወደ ጎንደር እንደሚመጣ ይጠበቃል ያለው መምሪያው ለዚህም ከ400 በላይ ሆቴሎች እና ድንኳን የሚጣልባቸው ሥፍራዎች ዝግጁ መሆናቸውን ገልጿል።

እንደ ሚመጡ እንግዶች አቅም የማረፊያ፣ ምግብን ጨምሮ አስፈላጊ ነገሮችን መሸመቻ አማራጭ መሰናዳቱን መምሪያው አሳውቋል።

በተጨማሪ ከጥር 4 እስከ 9 ቀን 2015 ዓ.ም የባህል ሣምንት የሚከበር ሲሆን በዚህም የአካባቢውን ፣ የክልሉን ባህል፣ ወግና ትውፊት የሚያሳዩ ዝግጅቶች ይቀርባሉት ተብሏል።

እንዲሁም ጥር 6 ቀን 2015 ዓ.ም የአጼ ቴዎድሮስ ልደት ሀገራዊ አንድነትን በሚያፀና ሁኔታ እንደሚከበር መምሪያው መግለፁን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በነዳጅ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ መደረጉን ተከትሎ ከዛሬ ጥር 1/2015 ዓ/ም ጀምሮ በአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ #የታሪፍ_ማሻሻያ መደረጉን የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ማሻሻያው በጀረጃ 1 ፣ በደረጃ 2 እና በደረጃ 3 ተሸከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ የሚደረግ ሲሆን፤ በአስፋልት እና በጠጠር መንገድ ላይ የሚኖራቸውን እንቅስቃሴ ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

የአገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ አሽከርካሪዎችና ረዳቶች በተቀመጠው ታሪፍ ብቻ በማስከፈል አገልግሎት እንዲሰጡ ማሳሰቢያ ተለልፏል።

የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
ከ " ህገ ወጥ የቤቶች ግንባታ " ጋር ተያይዞ የሚስተዋለውን ያልተረጋጋ ሁኔታ ስርአት ለማስያዝ የህግ ማእቀፉን ቀድሞ መረዳት እንደሚገባ ተገለጸ፡፡

ከከተማ መሬት አስተዳደር ጋር ተያይዞ የወጣ ህግ መኖሩን እና በህጉ ላይ ያለውን የግንባታ ፍቃድ አሰጣጥ በየደረጃው ያሉ የመንግስት ሀላፊዎች ሊረዱት እንደሚገባ በከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ገልጿል።

የዳይሬክቶሬቱ ዳይሬክተር አቶ ኢትዮጵያ በዴቻ ለአሀዱ ሬድዮ ፍና ቴሌቪዥን በሰጡት ቃል ፥ከዚህ ጉዳይ ጋር ተያይዞ ለሚሰራው ስራ እጃቸው የሚያርፍበት #በርካታ_የመንግስት_ሀላፊዎች በመኖራቸው ከግንባታ ፍቃድ አስጣጥ አንሰቶ የሚስተዋለው ችግር አንዱና ዋንኛው ምክንያት እንደሆነ ጠቅሰዋል።

በመሰረታዊነት በህግ ማዕቀፉ ላይ ያለውን አሰራር በሚገባ በመረዳት ግንባታ ከመከናወኑ አስቀድሞ ሊጤን የሚገባው ጉዳይ እንደሆነም ነው የተናገሩት።

ከህገወጥ የቤቶች ግንባታ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ችግሮች በዛን ረገድ የሰዎችን ህይወት ያልተገባ ሁኔታ ውስጥ ከማስገባታቸው አስቀድሞ አሰራሩን በመረዳት ተገቢው ውሳኔ ተግባራዊ ማድረግ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ምንጭ፦ አሀዱ ሬድዮና ቴሌቪዥን

@tikvahethiopia
" በተዝካር ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስ እንዳይፈጸም "

የምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ም/ቤት የተንዛዛ ድግስንና ያለ እድሜ ጋብቻን ፣ ሌሎች ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶች ናቸው ያላቸውን ድርጊቶች ለማስቆም አዲስ ውሳኔ ማስተላለፉን ገልጿል።

በምስራቅ ጎጃም ዞን አስተዳደር ምክር ቤት የተላለፉት አዳዲስ ውሳኔዎች ፦

- ያለ እድሜ ጋብቻ እና የህግ ማእቀፍ ያላቸው ሌሎች ጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶች እንዳይፈጸሙ በወጣው ህግ መሰረት ሳይሸራረፍ ሙሉ በሙሉ ተፈጻሚ እንዲሆን፤

- ከአለባበስ ባህል አኳያ በዞኑ ስር ያሉ ሁሉም ወረዳዎች የሚመሩት ህዝብ አንድም ሰው በባዶ እግሩ እንዳይሄድና ቁምጣ ለብሶ የሚሄድ ሰው እንዳይኖር እንዲሰሩ፤

- በተዝካር ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስ እንዳይፈጸም ፤ ስርአተ በቤተክስቲያን በሚያዝዘው መሰረት ስርአተ ፍትሃት ላደረጉ ካህናት አባቶች ብቻ ቤተክርስቲያን ላይ 1 በግ/ፍየል እና 2 ሌማት ብቻ እንዲቀርብ፤

- ጋብቻ አንዱ ባህላዊ እሴት መሆኑ የሚታወቅ ስለሆነ እና ትውልድ መቀጠል ስላበት " ጋብቻ ይቁም " እንደማይባል የገለፀው ም/ቤቱ ነገር ግን በጋብቻ ስም የሚፈጸም የተንዛዛ ድግስን በተመለከተ ለአጋቢ ሽማግሌዎችና ለቤተሰብ የሚሆን 1 በግ/ፍየል እና  2 ሌማት ብቻ እንዲሆን መወሰኑን እና የቀንድ ከብት ማረድ ፍጹም #የተከለከለ መሆኑ አሳውቋል።

በውሳኔው መሰረት በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ እና የጸጥታ አመራሮች ከፍትህ ተቋሙ ጋር ተቀናጅተድ ውሳኔዎቹን እንዲያስፈፅሙ ጥብቅ መመሪያ ተሰዝትቷል።

አፈጻጸሙንም በጋራ እየገመገሙ የተገኘውን ውጤት እና የመጣውን ለውጥ እስከ ጥር 15/2015 ዓ/ም እንዲያሳውቁም መልዕክት ተላልፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ሕዝበ_ውሳኔ

በደቡብ ክልል ከሚካሄደው ህዝበ ውሳኔ ጋር በተያያዘ የምርጫ ቦርድ ዋና ሰብሳቢ ወ/ሮ ብርቱካን ሚደቅሳ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

ምን አሉ ?

- የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ላይ ለመሳተፍ 2.9 ሚሊየን መራጮች ተመዝግበዋል።

- ቦርዱ ይህን ምርጫ ለማካሄድ የሚያግደው ምንም ነገር የለም ፤ አስፈላጊ ዝግጅቶች እንደተደረጉ ነው ብለዋል።

- የመራጮች ምዝገባ በዛሬው እለት የተጠናቀቀ ሲሆን መራጮች በ3,769 የመደበኛ፣ 11 የዞኖችና የልዩ ወረዳዎች ማስተባበሪያ ጽ/ቤት አማካኝነት ተመዝግበዋል።

- የአሰራር ጥሰት የተፈጸመባቸው 24 ምርጫ ጣቢያዎች ተገኝተው ነበር ፤ ጥሰቶቹ መራጮች ካርድ መሰጠት ለሌለባቸው ሰዎች ተሰጥቷል፣ ምርጫ ጣቢያ ያልተገኙ ሰዎች በመራጭነት ተመዝግበዋል፣ ከጣቢያ ውጪ ካርዶች ሲታደሉ ተገኝተዋል።

#ሪፖርተር

@tikvahethiopia
#Mekelle #AddisAbaba

• " ክልከላው ላይ የለንበትም ፤ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገርን ነው " - የትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች

• " ስለተባለው ነገር መረጃ የለኝም። እኛ የምናውቀው ነገር የለም። ... ለአየር መንገዱ ከመንግሥት በኩልም ቢሆን ምንም አይነት ክልከላን የሚመለከት መመሪያ አልተሰጠውም " - የኢትዮጵያ አየር መንገድ

• " ዝርዝሩን ለማወቅ እናጣራለን " - የፌዴራል ፖሊስ

ካለፉት ሶስት ቀናት ወዲህ ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ በሚደረግ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የመንገደኞች በረራ ላይ በተለይም #ወጣት መንገደኞች እንዳይጓዙ ክልከላ ስለመኖሩ መንገደኞች እየገለፁ ይገኛሉ።

ትናንት ታህሳስ 30/2015 ዓ/ም ከመቐለ ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ የአየር ቲኬት ቆርጠው አሉላ አባነጋ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት የተገኙት #በርካታ_ወጣቶች ጉዟቸው መሰረዙ ተሰምቷል።

መንገደኞች እንደሚሉት ከሆነ ክልከላው ከ16 ዓመት በላይ እና ከ64 ዓመት እድሜ በታች በተለይ ደግሞ ወጣቶችን ትኩረት ያደረገ ነው።

አንድ ቃሉን ለቢቢሲ የሰጠ መንገደኛ (የአዲስ አበባ ነዋሪ) ፤ " የልጆች እናት፣ የህክምና ሪፈር ያላቸው እና በእድሜ የገፉት ግን መሄድ እንደሚችሉ ነው የፌደራል ፖሊስ አባላቱ የነገሩን " ብሏል።

ይኸው መንገደኛ ፤ አዲስ አበባ ከተማ እንደሚኖር ፤ መታወቂያውም የአዲስ አበባ እንደሆነ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ እንደሄደና አስፈላጊውን መረጃ እንዳረበ ነገር ግን ሊቀበሉት እንዳልቻሉ አመልክቷል።

የአየር መንገዱ ሠራተኞች ክልከላው ከቁጥጥራቸው ውጪ እንደሆነ ነግረውናልም ብሏል።

አንድ መንገደኛ ደግሞ አዲስ አበባ የሚያስተዳድረው ተቋም መኖሩን የሚገልፅ መረጃ ካሳየ በኃላ በረራ እንደተፈቀደለት ለቢቢሲ ተናግሯል።

ክልከላው ከመቐለ በተጨማሪም #በሽረ ኤርፖርትም ስለመኖሩ ተገልጿል።

ጉዳዩን በተመለከተ ማን ምን አለ ?

የትግራይ ክልልን እያስተዳደሩ ያሉ አካላት ፤ ለክልሉ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ትግራይ ቴሌቪዥን) በሰጡት ቃል በዚህ ክልከላ እንደሌሉበት እና የክልከላው እርምጃ በፌደራል መንግስት የተወሰደ እንደሆነ ገልፀዋል።

በጉዳዩ ዙርያ መፍትሄ እንዲሰጥ ከፌደራል መንግስት እየተነጋገረ መሆኑን አሳውቋል።

#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ የንግድ ዘርፍ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ለማ ያደቻ (ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል) ፦

" ስለተባለው ነገር መረጃ የለኝም። እኛ የምናውቀው ነገር የለም።

እንደምታውቁት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የእድሜና ጾታ ክልከላ የለውም። ምክንያቱም በሕግ እና በሥርዓት ነው የሚተዳደረው። እስከ ዛሬ እንዲህ አይነት ክልከላ የለንም። ወደ ድረ ገጻችን ብትገቡም ምንም አይነት ክልከላ እንደሌለ ታያላችሁ።

በተጨማሪም ለአየር መንገዱ ከመንግሥት በኩልም ቢሆን ምንም አይነት ክልከላን የሚመለከት መመሪያ አልተሰጠውም።

ምናልባት #የአካባቢው_መመዘኛ_ወጥቶ እንደሆነ የክልሉ ባለሥልጣናትን ብትጠይቁ የሚሻል ይመስለኛል።

በእኛ በኩል ግን እስካሁን የደረሰን ምንም አይነት መረጃ የለም። ከመንግሥት የተሰጠ ትዕዛዝም የለም። "

የፌደራል ፖሊስ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጄይላን አብዲ (ለቢቢሲ አማርኛ ክፍል) ፦

" መረጃው የለኝም።

ተጓዦች በእድሜ ተለይተው በአውሮፕላን እንዳይጓዙ ተከልክለዋል የሚለውን መረጃ አሁን ከእናንተ ነው የምሰማው።

ዝርዝሩን ለማወቅ እናጣራለን። "

በጦርነት ምክንያት ለረጅም ወራት ያህል ተቋርጦ የነበረው ወደ መቐለ እና ሽረ እንደስላሴ የሚደረገው የመንገደኞች በረራ በቅርቡ ዳግም መጀመሩ የሚዘነጋ አይደለም።

@tikvahethiopia
#Mekelle

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች እና የትግራይ ክልል ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን የያዘ የልዑካን ቡድን ነገ ማክሰኞ ጥር 2/ 2015 ዓ/ም ወደ ትግራይ ክልል መዲና ፤ መቐለ እንደሚጓዝ " ኢትዮጵጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

የልዑካን ቡድኑ የሚመራው በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አትሌት ደራርቱ ቱሉ ሲሆን ወደ መቐለ የሚጓዘው የክልሉ ተወላጅ የሆኑ አትሌቶችን ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለማገናኘት መሆኑ ተነግሯል።

ቡድኑ ወደ መቐለ ነገ ረፋድ በአውሮፕላን የሚጓዝ ሲሆን በመቐለ ከተማ የሚኖረው ቆይታ የአንድ ቀን ብቻ መሆኑን በጉዞው ላይ ተሳታፊ የሆነ አንድ አትሌት ተናግሯል።

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ የሆኑት አቶ ቴዎድሮስ ለገሰ ለድረገፁ በሰጡት ቃል ፤ የፌዴሬሽኑ አመራሮች እና አባላት በአንድ ቀን ቢመለሱም እዚያው የሚቆዩ አትሌቶች ግን ይኖራሉ ሲሉ አረጋግጠዋል።

በዚህ ጉዞ ላይ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አመራሮች፣ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት እና የተለያዩ የስራ ክፍል አባላት ተሳታፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በነገ ጉዞ ከሚሳተፉ የትግራይ ክልል ተወላጅ ከሆኑ አትሌቶች መካከል ፦

- አትሌት ለተሰንበት ግደይ፣
- አትሌት ጎተይቶም ገብረ ስላሴ
- አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ እንደሚገኙበት ተናግሯል።

ምንጭ፦ https://ethiopiainsder.com/2023/9310/

@tikvahethiopia