#ነዳጅ
ቤንዚን በሊትር 61 ብር ከ29 ሳንቲም ገባ።
የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ማስተካከያ ማድረጉን አሳውቋል።
ሚኒስቴሩ ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ዓ.ም ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ በሚደረገው የዋጋ ክለሳ ዝቅተኛ ገቢ ላለው ሕብረተሰብ የሚሰጠው ድጎማ እንዲጨምር መደረጉንም ገልጿል።
በዚህም በአንድ ሊትር ቤንዚን ሲሰጥ የነበረው ድጎማ ከብር 15 ከ 76 ሳንቲም ወደ ብር 17 ከ 33 ሳንቲም እንዲሁም የአንድ ሊትር ናፍጣ ድጎማ ከብር 19 ከ02 ሳንቲም ወደ ብር 22 ከ 68 ከፍ እንዲል መደረጉ ተገልጿል።
በቀጣይ ፤ ሦስተኛ ዙር እና ከዛሬ ታኅሣሥ 30 ቀን 2015 ከሌሊቱ 6 ሰዓት ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ተግባራዊ የሚሆነው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ÷
- ቤንዚን በሊትር 61 ብር ከ29 ሳንቲም፣
- ነጭ ናፍጣ በሊትር 67 ብር ከ 30 ሳንቲም
- ኬሮሲን በሊትር 67 ብር ከ30 ሳንቲም
- ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 49 ብር ከ67 ሳንቲም፣
- ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 48 ብር ከ70 ሳንቲም እንዲሁም የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር 67 ብር ከ91 ሳንቲም እንዲሸጥ ተወስኗል፡፡
ምንጭ፦ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር / ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopia