TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ፎቶ ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሁለታት ዓመት በላይ ተቋርጦ የነበረውን የሽረ የመንገደኞች በረራ ዛሬ ዳግም ጀምሯል።

Photo Credit : ENA

@tikvahethiopia
🤔

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ፍቃደኛ አለመሆን የሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎችን ለማጣራት እያደረግኩት ባለው ጥረት ላይ እንቅፋት ሆኖብኛል ሲል የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ማስታወቁን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አስነብቧል።

የቢሮ ኃላፊ አቶ አሥራት አዳሮ ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፦

" በክልሉ ውስጥ ተቀጥረው የሚሠሩ #ባለሙያዎችንና #ኃላፊዎችን የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን በመያዝ ትምህርታቸውን ባጠናቀቁበት ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች ድረስ በመሄድ ማስረጃዎቹ ሐሰተኛ ናቸው ወይስ አይደሉም የሚለውን ለማጣራት ሙከራ ብናደርግም የግል ትምህርት ተቋማት ፈቃደኞች አይደሉም፡፡

ከ5 እና 6 ወር በኋላ ተመልሳችሁ ኑ የሚል ምላሽ ስለሚሰጡን ወደ ትምህርት ተቋማቱ የምንልካቸው ባለሙያዎች ለእንግልት እየተዳረጉ ነው።

ሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃ የትምህርት ጥራትን ከመጉዳትም ባሻገር የተማረ የሰው ኃይል በተፈለገው ቦታ ላይ እንዳይሠራና ጥራት ያለው አገልግሎት ለኅብረተሰቡ እንዳይሰጥ የሚያደርግ ነው።

በሐሰተኛ የትምህርት ማስረጃዎች ተቀጥረው በሥራ ላይ በሚገኙ #አመራርና #ባለሙያዎች ሕዝቡ ትክክለኛ አገልግሎት እንዳያገኝ ሲያደርጉ ነበር ፤ ክልሉ የሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች የትምህርት መረጃን አጣርቶ በሚያገኘው ውጤት መሠረት ከሥራ እና ከደመወዝ ከማገድ ባሻገር በሕግ እንዲጠየቁ ይደረጋል።

የማጣራቱን ውጤት ከአንድ ሳምንት ባነሰ ጊዜ ውስጥ ከ6ቱም ዞኖች የተጠቃለሉ መረጃዎችን በማደራጀት ምን ያህል አመራርና ባለሙያ በሐሰተኛ ትምህርት ማስረጃ ተቀጥሮ ሲሠራ እንደነበር ለሕዝቡ ይፋ ይደረጋል።  "

#EPA

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

አዲስ አበባ ፦

#ከመገናኛ ወደ #ቦሌ በሚወስደው መስመር ላይ የሚገኘው የኢምፔሪያል ተሸጋጋሪ ድልድይ የቀኝ ክፍል ከዛሬ ጥዋት ጀምሮ ለትራፊክ ክፍት ሆኗል።

የአዲስ አበባ መገዶች ባለስልጣን ፤ የተሸጋጋሪ ድልድዩን የግራ ክፍልና ሌሎች የመንገድ ግንባታውን ቀሪ ሥራዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማጠናቀቅ እየተሠራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

Credit : AARA

@tikvahethiopia
#AGOA

የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ባይደን አስተዳደር ኢትዮጵያ አሁን ያለችበትን ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ ከዚህ ቀደም ከAGOA ተጠቃሚነት ጋር በተያያዘ በተላለፈው ውሳኔ ላይ ማስተካከያ እንዲያደርግና ተመልሳ እንድትገባ እንዲያደርግ የአሜሪካ ኢትዮጵያውያን የሕዝብ ግንኙነት ኮሚቴ በደብዳቤ ጠይቋል።

ሙሉ መግለጫው ከላይ የተያያዘ ሲሆን በመግለጫው የተነሱት ሀሳቦች የሚከተሉት ናቸው ፦

- ኢትዮጵያን ከAGOA ዝርዝር ውስጥ ማስወጣት እስካሁን ከ200 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን የስራ ዕድል እንዳሳጣ፣ በረዥም ጊዜ ተፅዕኖዎች ተጨማሪ በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች ለኑሯቸው መሰረት የሆነውን የስራ ዕድል ሊያጡ እንደሚችሉ ይጠበቃል ብሏል።

- ማዕቀቡ በግለሰቦች ላይ ያነጣጠረ ሳይሆን ፤ ብዙሃኑን የኢትዮጵያን ህዝብ የሚጎዳ ነው። አብዛኞቹ ስራ ያጡት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው በጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ ሴት ሰራተኞች ናቸው። ይህን ስራ ማጣት ለመላው ቤተሰብ እና ማህበረሰብ ድህነት እና እጦት አስከትሏል።

- የኢትዮጵያ ሕዝብ የተጠየቀውን አድርጓል። መንግሥት ታሪካዊ የሰላም ስምምነት ፈፅሟል ፤ ዕርዳታ በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል፣ አስፈላጊ አገልግሎቶች እየተመለሱ ነው፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብት ጥሰትን የሚያጣራ ኮሚሽን ባለፈው ዓመት አዲስ አበባን ጎብኝቷል።

- ኢትዮጵያን ከAGOA ለተጨማሪ አንድ አመት አስወጥቶ ማቆየት ሙሉ በሙሉ ፋይዳ የለውም። የአሜሪካ መንግስት በምትኩ ሀገሪቱ ሰላም ለማስፈን፣ ለመገንባትና ዲሞክራሲያዊትነቷን ለማስጠበቅ እየሰራች ባለችበት ወቅት ድጋፍ ማድረግ አለበት።

ኮሚቴው በመግለጫው ላይ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ውሳኔውን እንደገና እንዲያጤኑት እና በAGOA ውስጥ ኢትዮጵያ እንድትመለስ ጠይቋል።

ኢትዮጵያ ከAGOA ዝርዝር ከወጣች 1 ዓመት ተቆጥሯል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Lion #Wegagen አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ በሽረ እንደስላሴና አካባቢው የሚገኙት ቅርንጫፎቹ የባንክ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን በዛሬው ዕለት አሳውቋል። በሌላ በኩል ፤ ወጋገን ባንክ በግጭት ምክንያት አገልግሎት ተቋርጦባቸው በቆዩት በአላማጣና በራያ ጥሙጋ ቅርንጫፎች አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጿል። ባንኩ ሰቲት ሁመራ፣ አዲ ረመፅ ፣ ዳንሻ  እና ተከዜ ቅርንጫፎች ቀደም ብለው አገልግሎት…
ወጋገን ባንክ ትላንት በመቐለ በ28 ቅርንጫፎች ስራ ጀምሯል።

ባንኩ መስጠት የጀመረው አገልግሎት ከባንክ ሂሳብ ገንዘብ ማውጣት እና ማስገባት ከክልሉ ውጭ የተላከ ገንዘብ መቀበል ናቸው።

የባንኩ የመቐለ ዲስትሪክት ስራ አስኪያጅ አቶ ሃፍቶም ገ/እግዚአብሔር ለቪኦኤ የሰጡት ቃል ፦

" ከፌዴራል ሲስተም ጋር በማያያዝ ማንኛውም ተቀማጭ የነበረውን ደንበኛ ገንዘብ መውሰድ ይችላል በቀን እስከ 1,500 ብር ይሄንን ስንል ከአዲስ አበባ ከሌላም ቦታ በተለይ ከትግራይ ክልል ውጭ ያለው ማንኛውም ገቢ ያደረገ ወደ ሂሳብ እሱን እያየን መክፈል እንችላለን። ከዚህ በተጨማሪ የውጭ ሀዋላም ጀምረናል።

መቐለ የጀመርነው በ28 ቅርንጫፎቻችን ነው፤ ብሩ በጣም ትንሽ ነው፤ ሰጠን ብለንም አናስብም ዞሮ ዞሮ ግን ያሉንን ደንበኞችና ድርጅቶች እነሱን በማስተባበር የተወሰነ ገቢ ስላደረጉልን ይሄንን ገቢ በዓልም ከፊታችን ስላለ ህዝባችን የነበረውን ችግር በመጠኑ በጣም በትንሹ እንኳን ለበዓል ለዶሮም ይሁን፣ ለስጋ ይጠቅማል ከሚለው እሳቤ ስለሆነ ነው ይበቃል የሚል እምነት ግን የለንም።

ከፌዴራል ብር እየጠየቅን ስለሆነ ሲመጣ ህዝባችንን እንክሳለን።

...አሁን ከሂሳብ ወደ ሂሳብ እሱን እያስተካከልን ነው በዚህ ሁለት ቀን እጀምራለን። በቀጣይ የATM እና ሞባይል ባንኪንግና ኢንተርኔት ባንኪንግ እሱን እየጨረስን ነው ከዚህ በፊት ጉዳት የደረሰባቸውን ኤቲኤሞች የእየተካን ነው፤ በቅርብ ጊዜ ሙሉ በሙሉ የATM አገልግሎት እንጀምራለን።"

ወጋገን ባንክ ከመቐለ በተጨማሪ ከዛሬ ጀምሮ ኦዲተሮቹን፣ እቃዎቹን እስከ ዓዲግራት ባለው አካባቢ፤ በሌላው መስመር እስከ መኸኒና ዓብይ ዓዲ ያሉት ቅርንጫፎቹ እንደሚያደርስ ገልጿል። በሁለትና ሶስት ቀን ውስጥ የቀሩት ቅርንጫፎች ስራ እንደሚጀምሩ አሳውቋል።

#ቪኦኤ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#DigitalLottery አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ህዳር 23 /2015 ዓ/ም በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል። 1.5 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 005187503482 ሆኖ ወጥቷል። 👉 1.5 ሚሊዮን ብር - 005187503482 👉 800 ሺህ ብር - 005304384029 👉 350 ሺህ ብር - 005255580874 👉 200 ሺህ ብር - 005230182809…
#DigitalLottery

አድማስ ዲጂታል ሎተሪ ዛሬ ታህሳስ 25 /2015 በብሄራዊ ሎተሪ የዕጣ ማውጫ አዳራሽ በህዝብ ፊት ወጥቷል።

1.5 ሚሊዮን ብር ባለዕድለኛ የሚያደርገው የዕጣ ቁጥር 006304740687 ሆኖ ወጥቷል።

👉 1.5 ሚሊዮን ብር - 006304740687
👉 800 ሺህ ብር - 006299531220
👉 350 ሺህ ብር - 006144680758
👉 200 ሺህ ብር - 006297990128
👉 160 ሺህ ብር - 006266851201
👉 120 ሺህ ብር - 006282798312

(ተጨማሪ የዕጣ ቁጥሮች ከላይ ተያይዘዋል)

@tikvahethiopia
H. c. marketing directive draft 2nd edition (1) (1).pdf
142.6 KB
#Coffee : የውጭ ንግድ ደረጃ ያለውን ቡና በሃገር ውስጥ በውጭ ምንዛሬ ለመሸጥ የሚያስችል ረቂቅ የአፈጻጸም መመሪያ ይፋ ተደርጓል።

ይኸው መመሪያ ይፋ የተደረገው በኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለሥልጣን ሲሆን መመሪያው ለተጨማሪ ግብዓት ነው ይፋ የተደረገው።

ረቂቅ መመሪያው ከዛሬ ጀምሮ እስከ 15 ቀናት ድረስ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተመልክተውት እና አስተያየት ከተሰጠበት በኋላ ሀሳቦቹ እንዲካተቱ ይደረጋል ተብሏል።

በረቂቅ መመሪያው ዙሪያ ማንኛውም አይነት አስተያየት ያለው ectacomm@gmail.com በሚለው ኢሜይል አድራሻ እስከ ጥር 9/2015 ዓ.ም ድረስ እንዲልክ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣን ጥሪ አቅርቧል።

(ረቂቅ መመሪያው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" በእሳት አደጋዎቹ 14 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል  "

ዛሬ ከሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ በደረሱ የእሳት አደጋዎች 14 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ ተሰምቷል።

የአዲስ አበባ እሳትና የድንገተኛ አደጋዎች ስራ አመራር ኮሚሽን በሰጠው መረጃ አደጋዎቹ የደረሱት በቂርቆስና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ነው፡፡

ከደረሱት የእሳት አደጋዎች ውስጥ አንዱ በአቃቂ ቃሊቲ አካባቢ " ገነት ሼዶች " ተብሎ በሚጠራው ቦታ በማምረቻ ሼዶች ላይ የተከሰተው ድንገተኛ የእሣት አደጋ ነው።

አደጋው ከቀኑ 9:40 ሰዓት አካባቢ ላይ የደረሰ ሲሆን በአደጋው 12 ሚሊዮን ብር የሚጠጋ ንብረት ወድሟል፡፡ ኮሚሽኑ እሳቱን ለማጥፋት ባደረገው ርብርብ 90 ሚሊዮን ብር ማትረፍ መቻሉ ተገልጿል።

የእሣት አደጋው መንስኤ በመጣራት ላይ መሆኑን ኮሚሽኑ አሳውቋል።

በሌላ በኩል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አንድ ጋራጅ ላይ የእሳት አደጋ የተከሰተ ሲሆን በአደጋው 2 ሚሊዮን የሚጠጋ ንብረት ወድሟል።

አሁን ላይ የእሳት አደጋውን መማጥፋት የተቻለ ሲሆን የአደጋው መንስኤም እየተጣራ ነው።

በሁለቱም አደጋዎች ግን በሰው ህይወት ላይ የደረሰ ጉዳት ያለመኖሩን የአዲስ አበባ እሳትና የድንገተኛ አደጋዎች ስራ አመራር ኮሚሽን ስለማሳወቁን #ኤፍ_ኤም 96.3 ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

ከትላንት በስቲያ በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 ሾላ ገበያ በደረሰ የእሳት አደጋ 50 ሚሊየን ብር የሚገመት ንብረት መውደሙ የሚዘነጋ አይደለም።

ፎቶ/ቪድዮ ፦ Chere Rona , Yosef Kinfe (Tikvah Family) & Akaki Kality Communication

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዋጋ የመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ያለአገልግሎት የተከማቹ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎችን መሸጫ የዋጋ ዝርዝር ይፋ ሆኗል። 1ኛ. ስቲል - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር)  64.00 2. ካስት አይረን  - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 51.75 3. አልሙኒየም - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (ብር) 120.00 4. ስክራፕ ያደረገ…
#MinistryofFinance

የገንዘብ ሚኒስቴር እና የማዕድን ሚኒስቴር ፤ ዛሬ የተከማቹ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች ፣ በስክራፕ መልክ የሚወገዱ ተሽከርካሪዎችና ማሽነሪዎች መሸጫ ዋጋ ላይ ቅናሽ መደረጉን አሳውቀዋል።

ምን ያህል ነው ቅናሽ የተደረገው ?

ከዚህ ቀደም የነበረው ፦

1ኛ. ስቲል - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር)  64.00
2. ካስት አይረን  - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 51.75
3. አልሙኒየም - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (ብር) 120.00
4. ስክራፕ ያደረገ ተሽከርካሪ / ማሽነሪ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 51.25
5. ያገለገለ የተሽከርካሪ / ማሽነሪ መለዋወጫ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ  (በብር) 51.25

ዛሬ የተሻሻለው ዋጋ ፦

1ኛ. ስቲል - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር)  48.00
2. ካስት አይረን  - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 35.00
3. አልሙኒየም ስክራፕ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (ብር) 90.00
4. ስክራፕ ያደረገ ተሽከርካሪ / ማሽነሪ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ (በብር) 39.00
5. ያገለገለ የተሽከርካሪ / ማሽነሪ መለዋወጫ - የአንድ ኪሎ ማስረከቢያ ዋጋ  (በብር) 39.00

@tikvahethiopia
#መልዕክት

የአዲስ አበባ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ፦

" የገና በዓል ሲከበር ህብረተሰቡ ከእሳትና ድንገተኛ አደጋ አጋላጭ ነገሮች ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል።

በበዓሉ ወቅት ድንገተኛ አደጋ ቢያጋጥም በፍጥነት ለመቆጣጠር ከተለያዩ ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር ተዘርግቷል።

እሳትና ድንገተኛ አደጋ ቢያጋጥም በነጻ የስልክ መስመር 939 ፤ በቀጥታ የስልክ መስመሮች 011 155 53 00 ወይም በ 011 156 86 01 ደውሎ ማሳወቅ ይቻላል። "

#ENA

@tikvahethiopia