TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#መግለጫ

የ2011 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ የ12ኛ ክፍል ፈተና ነሐሴ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ ተደረገ!

በ2011ዓ/ም ዓመታዊ የትምህርት ሰሌዳ መሰረት የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ (የ12ኛ ክፍል) ፈተና መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ከቅርብ አመታት ወዲህ ብሄራዊና ክልላዊ ፈተናን ደህንነት በማስጠበቅና የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በመንግሰት ከፍተኛ ርብርብ እየተደረገ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዚህም መሰረት ፈተናውን በሰላማዊ መንገድ ለማከናወን በመንግስትና በህዝቡ ሰፋፊ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በተለይም ተግባሩን በጠራ ዕቅድ የመምራትና የህብረተሰቡን ግንዛቤና ባለቤትነት የማሳደግ ብሎም ከማዕከል እስከ ትምህርት ቤት በተደራጀ ግብረሃይል መምራት ተችሏል፡፡

በዚሁ መሰረት ባለድርሻ አካላትና መላው ህዝብ ባደረጉት ርብርብ እጅግ በተረጋጋ የፈተና አካባቢ ፕሮግራሙን በማሳካቱ የአመቱ የፈተና አስተዳደር ስራው መሻሻል አሳይቷል፡፡ በመሆኑም ኤጀንሲው በፈተና አስተዳደሩ ሂደት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላደረጉ የፌዴራልና የክልል ተቋማት፣ ለፈተና አስፈጻሚዎች፣ ለመላው ተፈታኝ ተማሪዎች፣ የተማሪው ወላጆች እና በሂደቱ ለተሳተፉ ባለድርሻ አካላት በሙሉ ከፍተኛ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡

ኤጀንሲውም የፈተና ደህንነትን የማሰጠበቅ ስራውን ከፈተና ዝግጅት እስከ ውጤት ገለፃ ለማሰቀጠል በመስራት ላይ ነው፡፡ በዚሁ መሰረት ኤጀንሲው ፈተናው በተሰጠበት ወቅት የፈተና ህግ ጥሰት መፈፀማቸው በወቅቱ ከቀረቡ ሪፖርቶችና ተያያዥ መረጃዎች በመረጋገጡ የ68 ተፈታኞች ውጤት ሙሉ በሙሉ እንዲሰረዝ አድርጓል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ኤጀንሲው በኦሮሚያ፣ በደቡብ ብ/ብ/ህ፣ አማራ እና ቤንሻንጉል ክልሎች በሚገኙ የተወሰኑ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 846 ተፈታኞች የተወሰኑ የትምህርት አይነቶች ያገኟቸውን ውጤቶች ማጣራትን የሚጠይቅ ሆኖ አግኝቶታል፡፡

ኤጀንሲው በአዋጅ በተሰጠው ስልጣን መሰረት የእነዚህ ተማሪዎች ውጤት በተለዩት የትምህርት ዓይነቶች ብቻ ውጤታቸው ተይዞ ተጨማሪ ማጣራት እንዲደረግበት ወስኗል፡፡ ስለሆነም ኤጀንሲው ከሚመለከታቸው አካላት በተውጣጣ ግብረሃይል የሚያደረገው የማጣራት ስራ እንዲሳካና የጀመረውን የትምህርት ጥራት የማስጠበቅ ጅምር ስራ እንዲጠናከር የሚመለከታቸው አካላት ድጋፍ እንዳይለይው በመጠየቅ፣ ለመላ ተማሪዎች በሙሉ መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆን ይመኛል፡፡

ነሐሴ 7 ቀን 2011 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ

@tsegabwolde @tikvahethiopia
አከራካሪው ፍኖተ ካርታ!

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ትናንት ባወጣው #መግለጫ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የአማርኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ መደረጉና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሃገራዊ መሆኑን #እንደማይቀበለው ማስታወቁን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የ8ኛ ክፍል ፈተናን ሃገራዊ ማድረግም የክልሉን ሥልጣን የሚጋፋ ነው ሲል #ተችቶታል

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ትናንት ባወጣው መግለጫ በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ የአማርኛ ቋንቋ ከአንደኛ ክፍል ጀምሮ እንዲሰጥ መደረጉና የ8ኛ ክፍል ፈተና ሃገራዊ መሆኑን #እንደማይቀበለው ማስታወቁን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል። የ8ኛ ክፍል ፈተናን ሃገራዊ ማድረግም የክልሉን ሥልጣን የሚጋፋ ነው ሲል ተችቶታል።

መግለጫው አክሎም "ፍኖተ ካርታው በምሁራን የተጠና ነው በሚል ለተነሱ ጥያቄዎች በቂ ምላሽ ሳይሰጥ ወደ ተግባር እየተለወጠ ነው" ሲል ይኮንናል። ፍኖተ ካርታው የተለያዩ የትምህርት ፖሊሲውን የሚነካ ሆኖ ሳለ የሃገሪቱ ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮችና የፖሊሲ ለውጥ ላይ የሚሰሩ ባለሙያዎች ውሳኔ #ሳያሳልፉና አስተያየት ሳይሰጡበት #ወደተግባር መግባታቸው ተቀባይነት እንደሌለው በመግለጫው ተመልክቷል።

ከዚህ ባሻገርም ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ደረጃውን 6-2-4 ብሎ መግለጫ ከማውጣቱ በፊት በቂ ማብራሪያ መሰጠት ነበረበት ይላል። "ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍል ትምህርት የሚሰጠው በአፍ መፍቻ ቋንቋ ሆኖ ሳለ የ8ኛ ክፍልን ፈተና ሃገራዊ ማድረግ ምን አመጣው?" ሲልም ይጠይቃል። "የትግርኛ ቋንቋ ከአማርኛ ቋንቋ ጋር ይወራረሳል" የሚለው መግለጫው፤ የሰባት ዓመት ሕፃን እነዚህን ቋንቋዎች በአንድ ላይ መስጠት #ማደናገር ነው ብሏል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-08-24-4

Via #BBC
@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#መግለጫ

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኦሮሚያ ክልል ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል። ርዕሰ-መስተዳድሩ በምዕራብ እና ደቡብ ኦሮሚያ አካባቢ ስለሚንቀሳቀው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር እና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የኦሮሚያ ቤተ-ክሕነት ለማቋቋም ከቀረበው ጥያቄ በኋላ ከቤተ-ክርስቲያኗ ጋር ስላደረጉት ውይይት ንግግር አድርገዋል።

Via DW
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Audio
AudioLab
#መግለጫ

የእስካሁኑን የምርጫ ሂደት በተመለከተ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ የሰጡን መግለጫ

#TikvahFamily #TikvahEthiopia

@tikvahethiopia
#መግለጫ

የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና መጠናቀቅን ተከትሎ የሀገር አቀፍ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ መግለጫ ሰጥቷል።

ኤጀንሲው የ2013 ትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ዙር የ12 ክፍል ብሄራዊ ፈተና በሰላም ተጠናቅቋል ብሏል።

የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ በሀገራችን ካለው ወቅታዊ ሁኔታ አንፃር ፈተናው በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል ሲሉ ነው ያሳወቁት።

በ2 ሺ 36 የፈተና ጣቢያዎች በተሰጠው በዚህ ፈተና፣ ፈተናውን ይወስዳሉ ተብሎ ከታሰበው 617 ሺ 991 ተማሪዎች ውስጥ 565ሺ 255ቱ ፈተናውን ወስደዋል ብለዋል።

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ በዚህ የህልውና ትግል ወቅት ፈተናው በሰላም እንዲጠናቀቅ የበኩላቸውን ለተወጡ የፀጥታ አካላት፣ የትምህርት ዘርፉ ሰራተኞችና ወላጆች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

"በማህበራዊ ሚዲያ አንዳንድ ፈተናዎች ተሰርቀው ወጥተዋል የሚባለው ጉዳይ እውነት ነወይ" ተበለው በጋዜጠኞች የተጠየቁት ዋና ዳይሬክተሩ፣ የተለያዩ ምርምርራዎችና ትንተናዎች ተደርገው አስፈላጊው ማስተካከያ ስለሚደረግ ምንም የሚያስጋ ነገር የለም የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በተለያዩ ችግሮች ምክንያት ፈተና ያልተሰጠባቸው አካባቢዎች ለተማሪዎቹ የስነ ልቦና ግንባታ ስራ ተሰርቶ በሁለተኛ ዙር በመፈተን ከመጀመሪያው ዙር ተፈታኞች ጋር ወደ ዩኒቨርሲቲ ይገባሉ ተብሏል።

ምንጭ፦ ትምህርት ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#መግለጫ 👆

በአማራ ክልል ከ2014 የጥምቀት በዓል አከባበር ጋር ተያይዞ በእስልምና ተቋማት ላይ የተፈፀሙ ሃይማኖታዊ ትንኮሳዎችን በተመለከተ የአማራ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ያወጣው መግለጫ !

@tikvahethiopia
#መግለጫ

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማኅበር ዛሬ " ለዜጎች መብት መከበር የሚሟገተው ጋዜጠኛ መብት ይከበር " በሚል መግለጫ አውጥቷል።

ማህበሩት ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በኢትዮጵያ የፕሬስ ነጻነት መሻሻል እያሳየ እንደነበርና ዓለም ዓቀፍ ተቋማት ሲመሰክሩ እንደነበር አስታውሷል።

ይሁንና ይህ መሻሻል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየተሸረሸረ መሄዱን በብዙ ማሳያዎች መግለጽ እንደሚቻል እና ይህንንም የተለያዩ ማሳያዎች በመጥቀስ አብራርቷል።

(ከማህበሩ የተላከውን ሙሉ መግለጫ በዝርዝር ከላይ ያንብቡ)

@tikvahethiopia
#መግለጫ

የብሔራዊ ደህንነት ምክር ቤት በወቅታዊ ሀገራዊ የደህንነትና ፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከመከረ በኋላ መግለጫ  አውጥቷል።

ም/ቤቱ ፤ ከሰላምና ከሀገር ደኅንነት  በተቃራኒው ተሰልፎ የሚገኝ ማንኛውም ሰው ፣ አካል እና ቡድን ላይ ሕጉ የሚፈቅደውን ተገቢውን ሕግና ጸጥታ የማስከበር ሥራ ይሰራል ሲል አሳስቧል።

የጸጥታ እና ደኅንነት ተቋማት በተሻለ ቁመና ላይ እንደሚገኙ የገለፀው መግለጫው " አስፈላጊ በሆነ ሰዓት ሁሉ ተመጣጣኝ ምላሽ ከመስጠት ወደኋላ አንልም " ብሏል።

በተጨማሪ የደህንነት ምክር ቤቱ የምግብና ልዩ ልዩ ሸቀጦች ዋጋ እንዲንር በሕገ ወጥ መንገድ ምርት የሚያከማቹ፣ በኮንትሮባንድ መልክ ነዳጅና ሌሎች ምርቶችን ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚያሾልኩ ሕገ ወጥ ነጋዴዎች ላይ ተገቢው እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#መግለጫ

ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሞያዎች ማህበር መግለጫ

" ... ጋዜጠኞችን በሥራቸው ምክንያት ብቻ የመሰወር፣ የማሰር፣ የማንገላታትና የመደብደብ ድርጊት ተባብሶ ታይቷል፡፡

ጋዜጠኞች በሰውነታቸው ጥፋት አያጠፉም የሚል ድምዳሜ ባይኖርም የሕዝብን ጥቅም ፣ መብት እንዲከበር እና ሙያውን ለማሳደግ ፣ አገር በሕግ እንዲመራ በሚያደርጉት መሠረታዊ ሥራ የመንግሥት አካል ቁጡ ሊሆን የተገባ አይደለም።

ጋዜጠኞች በሕግ ጥሰት ከተጠረጠሩ እና ተጠያቂነት ካለባቸው ብሎም በወንጀል ከተፈለጉ በሕግ አግባብ መያዝ እና መጠየቅ ሲገባቸው፣ በጸጥታ አካላት በቁጥጥር ስር ውለው ከቤተሰቦቻቸውና ከባልደረቦቻቸው እየተሰወሩ ቀናትን በጨለማ እንዲያሳልፉ መደረጉ መንግሥት ይህንን ዘርፍ ለማቀጨጭ ፍላጎት ብቻ ሳይሆን ሥራዬ ብሎ የያዘው አስመስሎበታል። "

🔻

" ... አንዳንድ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋዜጠኞችንና የመገናኛ ብዙኃን ተቋማትን የአገር ችግር ፈጣሪ አድርጎ የመሳል አዝማሚያ በግልጽ እየታየ ሲሆን ይህም ከንግግር ባለፈ በተግባር እየተስተዋለ ይገኛል። የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ማሕበር በአሁን ወቅት ጋዜጠኞች የሚደርስባቸው ያልተገባ ወከባ እና እንግልት እንዲቆም ይጠይቃል "

🔻

" ... ፍርድ ቤቶች ጋዜጠኞች በዋስትና እንዲለቀቁ የወሰኑት ውሳኔ በፖሊስ እንዳይተገበሩ መደረጋቸው የተቋሞቹን ታማኝነት ጥያቄ ውስጥ የሚከት በመሆኑ እንዲታረም፣ መንግሥት በጎ ሲሰራ አወድሰው ፣ ጥፋትና ያልተገቡ አካሄዶችን ሲመለከቱ የሚሞግቱትን ጋዜጠኞችን በማሰርና በመደበቅ ፣ በማፈንና በማሸማቀቅ የሚያመጣው ለውጥ ለአገር የማይበጅ በመሆኑ መሰል እርምጃዎች እንዲቆሙ ማህበራችን ያሳስባል፡፡ "

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#መግለጫ

ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በሚገኘው የአካል ጉዳተኞች ጠቅላላ የመብቶች ጥሰት በተመለከተ የኢትዮጵያ የሕግ ባለሞያ አካል ጉዳተኞች ማህበር ጋዜጣዊ መግለጫ አውጥቷል።

ማህበሩ በላከልን መግለጫ ፥ የተደራሽነት መብትን ጨምሮ የትምህርት፣ የጤና፣ የስራ እና የቅጥር መብቶች እና ሌሎች የአካል ጉዳተኞች መብቶች በየግዜው እየተጣሱ እና ለጥሰቶቹ ሀላፊነት የሚወስድ አካል ሳይኖር እንዲሁም ጥፋተኞችም ተጠያቂ ሳይደረጉ የመብት ጥሰቶቹ ተድበስብሰው በመታለፍ ላይ ናቸው ብሏል።

የአካል ጉዳተኞችን የመብት ጥሰቶችን ተከትሎ ተጠያቂነት ባለመኖሩም ጥሰት የሚፈጸምባቸው ሰዎች ሳይካሱ እየቀሩ እና ጥሰት ፈጻሚዎችም ድርጊታቸውን ትክክል አድርገው እንዲወስዱትና የመብት ጥሰቱም ያለከልካይ እንዲቀጥል ምክንያት ሆኗል ብሏል።

አሁን በተግባር እንደሚታየው የአካል ጉዳተኞች የመብት ጉዳዮች በግለሰቦች መዳፍ ላይ የተንጠለጠሉ በመሆናቸው፤ አካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ መብቱን እንደምጽዋት እንዲጠይቅና እንዲቀበል ተገዷል ሲልም ገልጿል።

ማህበሩ ፥ በአካልጉዳተኛ ግለሰቦች ላይ ከሚፈጸሙ አይነተብዙ የመብት ጥሰቶች በተጨማሪ ከመንግስት በኩል አካል ጉዳተኞችን በቁልፍ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ከአካታችነት መሻት በሚመነጭ ተነሳሽነት የማካተት ስራዎች በበቂ ሁኔታ እየተሰሩ አይደለም ብሏል።

ከሀገሪቱ ህዝብ ቁጥር ከ17.6 በላይ የሚሸፍነው አካል ጉዳተኛው ማህበረሰብ እንደሆነ ያታወቃል ያለው ማህበሩ የተለየ በጀት የማይበጀትለት መሆኑና የመብት ጥያቄ በሚያነሳበት ግዜም ፖለቲካዊ ውክልና የሌለው ማህበረሰብ መሆኑን ተከትሎ ምላሽ ሳይሰጠው በመቅረት ላይ ነው ብሏል።

ማህበሩ እየተባባሰ መጥቷል ላለቸው የመብቶች ጥሰት መፍትሄ ያለውን በዝርዝር አስቀመጧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#መግለጫ

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም ሚኒስትር ዴኤታዎች የፈተናውን አጀማመርና አጠቃላይ ያለውን ሂደት በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸው ምን አሉ ?

- በ130 ማዕከላት ከ560 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሄራዊ ፈተና እየወሰዱ ነው።

- በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ በምስራቅ ጎጃም እናርጅና እናውጋ ወረዳ ተማሪዎች ፈተናው ከመጀመሩ በፊት " #አንፈተንም " በሚል ለቀው ወጥተዋል፤ ምክንያቱን በአግባቡ አጣርተን የሚወሰደው እርምጃ ይገለፃል።

- በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ በዋናው ግቢ የሚገኝ ድልድይ ተደርምሶ በተወሰኑ ተማሪዎች ላይ አደጋ ደርሷል። በአደጋው ጉዳት ያጋጠማቸው ተማሪዎች ህክምና እየተደረገላቸው ነው፤ ተማሪዎቹ ካገገሙ በኋላ ፈተናውን እንዲወስዱ ይደረጋል።

- ከተጠቀሱት (#ሀዋሳ እና #መቅደላ_አምባ) አካባቢዎች #በስተቀር በሌሎች ትምህርት ቤቶች ፈተናው በሰላምና በተረጋጋ መልኩ እየተሰጠ ነው።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#መግለጫ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) ፤ በተቋሙ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ላይ የተፈጸመውን ህገ-ወጥ እስር አስመልክቶ ዛሬ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቶ ነበር።

ኢሰመጉ በመግለጫው ፥ መንግስት በአራት የኢሰመጉ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ላይ ህገ-ወጥ እስር የፈጸሙ፣ እንዲፈጸም ትዕዛዝ በሰጡ እና በአስቸኳይ ከእስር እንዳይለቀቁ ባደረጉ የፖሊስ አባላት እና አመራሮች ላይ ተገቢውን ምርመራ በማድረግ በህግ ተጠያቂ እንዲያደርግ አሳስቧል።

በተጨማሪ መንግስት ተቀዳሚ ሃላፊነቱ ሰብዓዊ መብቶችን ማክበር፣ ማስከበር እና ማሟላት አንደሆነ በመረዳት በተቃራኒው ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ በሚሰሩ አንደ ኢሰመጉ ባሉ ተቋማት ላይ የሚፈጽማቸውን ጫናዎች፣ ዛቻዎች፤ ማስፈራራቶች፣ ማንገላታቶች፣ ማዋከቦች፣ እስሮችና መሰል ጥሰቶችን መፈጸም እንዲያቆም አስገንዝቧል።

ኢሰመጉ ከባለሙያዎቹ ተወስደው በፖሊስ እጅ የሚገኙ የተለያዩ ሰነዶች መኖራቸውን አመልክቶ ይህ በፖሊስ እጅ ላይ የሚገኙ ሰነዶች ጉዳይ እደሚያሳስበው ገልጿል።

መንግስት ወደፊት መሰል ከህግ አግባብ ውጪ የሆኑ አስሮች እና “ጫናዎችን እንዳይፈጽም ይህንን ድርጊት በሚያደርጉ ስልጣናቸውን አላግባብ በሚጠቀሙ አካላት ላይ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድም ኢሰመጉ በመግለጫው አሳስቧል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ካህኑን ማን ገደላቸው ? " ኃይሌ ጋርመንት " የሁርሲሳ ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ቀዳሽ ካህን ቀሲስ ዐባይ መለስ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ አካላት በተፈፀመባቸው ጥቃት ተገድለዋል። ካህኑን የሚያውቋቸው አገልጋዮች /ምዕመናን  ስለነበረው ሁኔታ / ስለጥቃቱ ምን አሉ ? (ለማህበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ከተናገሩት የተወሰደ) ቃላቸውን የሰጡ ምዕመን አንድ ፦ " ትላንት/መጋቢት…
#መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶኮስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፤ መንግስት የቄስ ዓባይ መለሰን ገዳዮች ተከታትሎ ለፍርድ ያቅርብ አለ።

ሀገረ ስብከቱ በሰጠው መግለጫ ፤ " መንግሥት የቤተ ክርስቲያን አገልጋይ በመሆናቸው ምክንያት በአሰቃቂ ሁኔታ በመንገድ ላይ ተደብድበው ሕይወታቸው እንዲያልፍ የተደረጉት የቄስ ዐባይ መለሰ ገዳዮችን ተከታትሎ ለፍርድ ያቅርብ " ብሏል።

አክሎም ፤ " ችግሩን ከሥር ከመሠረቱ በመፍታት የአገልጋዮችንና የምእመናን መብት እንዲያስከብር " ሲል ጠይቋል።

ከዚህ ባለፈ በሸገር ከተማ አስተዳደር አብያተ ክርስቲያናትን የማፍረስ ድርጊት እየተፈፀመ መሆኑን በመግለፅ ይህ ድርጊት በአስቸኴይ እንዲቆም እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።

እስካሁን የፈረሱትን አብያተ ክርስቲያናት ቦታ ተመላሽ እንዲያደርግ እና የፈረሰውን ቤተ ክርስቲያንም በራሱ ወጪ እንዲያሠራ እንዲደረግ ሀገረ ስብከቱ ጠይቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia