TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#የኢትዮጵያ_አየር_መንገድ

በበረራ ቁጥር ET343 ላይ ስለነበረው ክስተት እና ከዛም ጋር ተያይዞ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ስለደረሱ ሪፖርቶች ምርመራ እየተካሄደባቸው ይገኛል።

አየር መንገዱ ምርመራውን አከናውኖ ሲጨርስ ምን እንደተፈጠረ በማረጋገጥ ተገቢውን የእርምት እርምጃ ይወስዳል ፤ እስከዛው የበረራ ሰራተኞቹ ታግደው ይቆያሉ።

በወቅቱ ምን እና እንዴት ተፈጠረ ? ስለሚለው በጉዳዩ ቀጥተኛ ባለቤት ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ መስማት የሚያስፈልግ ሲሆን ምርመራ እንደተጠናቀቀ ጉዳዩን አየር መንገዱ ይገልፃል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በድፍን አፍሪካ አንጋፋና ቁጥር አንድ ፤ በዓለም ደረጃ ተወዳዳሪ ፣ በደህንነቱ መረጋገጥ እና በአገልግሎቱ ሁሉም የሚመርጠው ፤ የሀገርን ክብር ይዞ የሚንቀሳቀስ ሀገር የሚያስተዋውቅ፣ በርከት ያለ ሀብት የሚያስገባ የኢትዮጵያ ህዝብ አለኝ የሚለው ትልቁ እና ጠንካራው ተቋም ነው።

@tikvahethiopia
ሲዳማ ክልል በስንት ዞኖች ይዋቀራል ?

ከሰሞኑን የሲዳማ ክልል ም/ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ በሰጡት መግለጫ ሲዳማ ክልል 4 ዞኖች እና 1 ከተማ አስተዳደር ይኖረዋል ብለዋል።

የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ የሀዋሳ ከተማ ዙሪያ ዞን እንዲሁም በአቅጣጫቸው የሚሰየሙ መዋቅሮች ይኖሩታል።

ይህ የዞን መዋቅር ም/ቤቱ በቅርቡ በሚያካሂደው ጉባኤ ላይ ቀርቦ ምርመራ ተደርጎበት ይፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ወ/ሮ ፋንታዬ ከበደ "ከዚህ በፊት አንድ ዞን እና አንድ የከተማ አስተዳደር ነበር፤ አሁን 4 ዞን እና አንድ የከተማ አስተዳደር በዞን ደረጃ ያለ መዋቅሮች የሚደራጁበት ነው" ብለዋል።

የዞን አደረጃጀቱን በተመለከተ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የገንዘብ ድጋፍ በግል ጥናት ያደረጉት የህግና የዓለም አቀፍ ግኝኑነት መምህር ዮሃናን ዮካሞ ስለ በአቅጣጫ መዋቀሩ ጥሩ መሆኑን ገልፀዋል።

መምህር ዮሃናን የሲዳማ አዲሱ አወቃቀር በሁሉም በፖለቲከኛውም በምሁራኑም ዘንድ መቶ በመቶ ተቀባይነት አግኝቷል ብለዋል።

ጠቀሜታውን ሲያስረዱም " ግጭት አይፈጥርም ነገ፤ በጎሳ የሚባሉ ነገሮች አይኖሩም። የህዝብ ብዝሃነትን ማስተናገድ የሚችል ነው፤ አካታች ነው፤...አብዛኛው ይስማማል በቁጥር ማነሱን፤ ሀብትንና አካባቢንም ያገናዘበ ነው " ብለዋል።

መምህሩ ዞኖቹ ሲደራጁ በባለስልጣናት ሹመት ላይ ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባው ገልፀዋል።

" በተለይ ሲያዋቅሩ በኮታ በጎሳ ቁጥር ደልድለው ስልጣን የሚሰጡ ከሆነ የኔ አንሷል የሚል ነገር ይመጣል፤ ስለዚህ ኢኮኖሚ ዘርፍ ላይ የኢኮኖሚ እውቀት ያለው፤ ጤና ላይ ዶ/ር የሚያክም የተማረ፣ አስተዳደር ላይም ብቁ የሆኑ ሰዎችን ማስቀመጥ ይገባል " ብለዋል።

ተጨማሪ፦ telegra.ph/Sidama-Region-08-19

Credit : ጋዜጠኛ ዮናታን ዘብዲዮስ (ቪኦኤ)

@tikvahethiopia
#የ12ኛ_ክፍል_ብሔራዊ_ፈተና

የ2014 ዓ.ም የኢትዮጵያ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተናን በተመለከተ ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ምክክር ሲካሄድ ውሏል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በሀገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ ዩኒቨርስቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዚዳንቶች እና ከየክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች እና የፈተና ጉዳይ አስፈጻሚዎችና ከትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ባለሙያዎች ጋር በፈተናው አሰጣጥ ላይ ምክክር ማካሄዱን አሳውቋል።

በውይይቱ ላይ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የውይይት መነሻ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በሠነዱ ዙርያ የተለያዩ አስተያቶች እና ጥያቄዎች ተነስተው ግልጽነትና የጋራ መግባባት ተፈጥሯል ተብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ፈተናውን ለመስጠት አስፈላጊው ቅድመ ዝግጅት ሁሉ ከሚመለከታቸው ባለሚና አካላት ጋር በመሆን እየተከናወነ እንደሚገኝ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የልጁን ህይወት አትርፎ ህይወቱ ያለፈው አባት ! የልጁን ሕይወት ለማዳን ከጀልባ ላይ የዘለለው እንግሊዛዊ አስክሬኑ ጣልያን ተገኘ። ዛሬ ጥዋት ቢቢሲ በደረገፁ አንድ አሳዛኝ ክስተት አጋርቷል። አረን ቻዳ የተባለ እንግሊዛዊ ልጁን ለመታደግ ከጀልባ ከዘለለ በኋላ ለሳምንታት ጠፍቶ አስክሬኑ ጣልያን ውስጥ ተገኝቷል። አረን ባለፈው ወር " ጋርዳ " የተባለ ባሕር አካባቢ ከትዳር አጋሩና ከሁለት ልጆቹ ጋር…
የልጁን ህይወት አትርፎ ህይወቱ ያለፈው አባት !

የልጁን ህይወት ለማትረፍ ናይል ወንዝ የገባው አባት አስከሬኑ ተገኘ።

ስሙ ሮበርት ክዌሲ ይባላል የኡጋንዳ ተወላጅ ዜግነቱ ደግሞ እንግሊዛዊው ነው ፤ እድሜው 48 ሲሆን በእንግሊዝ ሀገር ነዋሪ ነበር።

ሮበርት ከባለቤቱ ጀስቲን ካታንታዚ እና ከአራት ልጆቻቸው ጋር ወደ ኡጋንዳ ለእረፍት ይመጣሉ። ኡጋንዳ መጥተው እየተዝናኑ ሳለ የ12 አመት ልጁ እየዋኘ በነበረበት ወቅት በነበረው ማዕበል ችግር ስላጋጠመው አባት ልጁን ለመርዳት ዘሎ ይገባል። ምንም እንኳን አባት ልጁን ቢያተርፍም የእሱ ደብዛ ግን ከዛች ደቂቃ አንስቶ ይጠፋል።

የነፍስ አድን ሰራተኞች እና ጠላቂ ፖሊስ አባላት እንዲሁም የአካባቢው በጎ ፍቃደኞች ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ፍለጋ ያደርጋሉ በኃላም የሮበርትን አስክሬን አግኝተዋል።

ሮበርት ክዌሲ አስክሬኑ የተገኘው በናይል ወንዝ በአንደኛው ክፍል ነው ተብሏል።

ሮበርት በእንግዚዝ ፍሪጅ እና አየር ማቀዝቀዣዎችን በመጠገን በተቋራጭነት ይሰራ ነበር። ከባለቤቱ ጋር ጋብቻቸውን የፈጸሙት ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኡጋንዳ እንደነበር #ቢቢሲ ፅፏል።

ትላንትም አንድ እንግሊዛዊ አባት የልጁን ህይወት ለማትረፍ ሲል ከጀልባ ዘሎ ልጁን አትርፎ እሱ ግን ህይወቱ እንዳለፈ አስክሬኑም ጣልያን ውስጥ መገኘቱን የሚገልፅ መረጃ ማንበባችን ይታወሳል።

@tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-MAGAZINE
#አድማስ_ዲጅታል_ሎተሪ !

የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአድማስ  ድጅታል ሎተሪ የአንደኛ ዙር ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ/ መውጣቱን ገልጿል።

የወጡ ዕድለኛ የሚያደርጉ ቁጥሮች ፡-

👉 የ1ኛ ዕጣ የ1.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002031699514

👉 2ኛ ዕጣ  የ800 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002294990063

👉 3ኛ ዕጣ የ350 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002318579148

👉 4ኛ ዕጣ የ200 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002210849268

👉 5ኛዕጣ የ160 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002133487616

👉 6ኛ ዕጣ የ120 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002305487051

👉 7ኛ ዕጣ የ90 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002137548817

ሌሎችም በርካታ ዕጣዎች መውጣቱን የገለፀው ብሄራዊ ሎተሪ ሙሉውን ዝርዝር በቀጣይ እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ExitExam

የትምህርት ጥራት #ፈተና_በመስጠት ብቻ ይረጋገጣል ?

ከ2015 ዓ/ም ጀምሮ የመውጫ ፈተና መሰጠት እንደሚጀመር ይታወቃል።

ለመሆኑ ፈተና በመፈተን ብቻ የትምህርት ጥራት ማምጣት ይቻላል ? ትምህርት ሚኒስቴር በዚህ ጉዳይ ምላሽ አለው።

የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር) ለብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ (ኢቲቪ) የተናገሩት ፦

" የትምህርት ጥራት ፈተና ብቻ በመስጠት የሚሳካ ፤ የሚረጋገጥ ነገር አይደለም።

በአጠቃላይ ግን በትምህርት እና ስልጠና ዘርፉ በተለይም በትምህርቱ ዋና ችግር አለ ተብሎ የተለየው ዋና የትምህርት ሴክተሩ ስብራት ነው ተብሎ የተለየው ትምህርታችን ጥራትም ተገቢነትም ጎሎታል።

ስለዚህ አስመርቀን የምናስወጣው በሙሉ ባይባልም የጥራት ፣ የብቃት ችግር አለበት ይሄንን መፍታት ያስፈልጋል።

ለዚህ የሚሆን በሁሉም ደረጃ ከግብዓትም ጋር ከሂደቱም ጋር የሚያያዝ እንደዚሁም ውጤቱን ከማረጋገጥ ጋር የሚያያዝ ስራዎች መሰራት አለባቸው ተብሎ በመንግስት ቁልፍ የሪፎርሞች ተጀምረዋል አንደኛው ከመውጫ ፈተና ጋር የሚያያዝ ነው።

ይሄ የመውጫ ፈተና በዋናነት የሚመለከተው የመጀመሪያ ዲግሪ ምሩቃንን ነው ሁለተኛ ዲግሪ እና ሌሎችን አይመለከትም የሚጀምረው በ2015 ሰፋ ብሎ ነው እንጂ ከዚህ በፊትም የተጀማመሩ ስራዎች አሉ የተጀመሩ ፕሮግራሞች አሉ።

ዋናው ቁም ነገሩ በግብአት ደረጃ ጥራቱን ማረጋገጥ ያስፈልጋል የምሩቁን ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባውን የመማር ማስተማር ሂደቱ ጥራትን በሚያረጋግጥ መልኩ መምራት እና መስጠት ያስፈልጋል።

በጥሩ ግብዓት ከተደገፈ እና ጥሩ ሂደት ካለው በውጤቱ ማረጋገጥ ይገባል ከሚል መነሻ የተጀመረ የሪፎርም ስራ ነው "

@tikvahethiopia
የገቢዎች ሚኒስቴር አዲስ ሚኒስትር ተሾሞለታል ፤ አዲሷ ሚኒስትር ማን ናቸው ?

የገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ ዓይንዓለም ንጉሴ ናቸው።

ሹመቱ አቶ ላቀ አያሌው በትምህርት ምክንያት ወደውጪ ሀገር ለመሄድ በሚኒስተሮች ምክር ቤት መሸኘታቸውን ተከትሎ የተሰጣቸው መሆኑ ተገልጿል።

ወ/ሮ ዓይንዓለም ንጉሴ በምን ኃላፊነት ላይ አገልግለዋል ?

• በወሎ ዩንቨርሲቲ ምክትል ፕሬዘዳንት ፤
• የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ
• በአማራ ክልል በኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪነት ሰርተዋል።

አዲሷ ሚኒስትር የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን የማኔጅመንት አባላት በተገኙበት ከቀድሞ ሚኒስትር የስራ ርክክብ አካሂደዋል።

Credit : Ministry of Revenues of Ethiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አድማስ_ዲጅታል_ሎተሪ ! የብሄራዊ ሎተሪ አስተዳደር የአድማስ  ድጅታል ሎተሪ የአንደኛ ዙር ዛሬ ነሐሴ 13 ቀን 2014 ዓ/ መውጣቱን ገልጿል። የወጡ ዕድለኛ የሚያደርጉ ቁጥሮች ፡- 👉 የ1ኛ ዕጣ የ1.5 ሚሊዮን ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002031699514 👉 2ኛ ዕጣ  የ800 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር -002294990063 👉 3ኛ ዕጣ የ350 ሺህ ብር የሚያሸልመው ዕጣ  ቁጥር…
#DigitalLottery

የብሔራዊ ሎተሪ አስተዳደር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ያስጀመረው " አድማስ " የተሰኘው ድጂታል ሎተሪ የመጀመሪያው ዙር እጣ ትላንት ማውጣቱን አሳውቋል

የዲጂታል ሎተሪ ዕጣው ቀጣይነት እንዳለው የገለፀው አስተዳደሩ የሁለተኛ ዙር  ዕጣው  መስከረም 11 ቀን 2015 የሚወጣ መሆኑን ገልጿል።

የአድማስ ዲጅታል ሎተሪ በአንደኛ ዕጣው 1.5 ሚሊዮን ብር፣ በሁለተኛ 800 ሺህ ብር፣ በሶስተኛ 350 ሺህ ብር ጨምሮ ሌሎችም የገንዘብ ዕጣዎችን ያካተተ ነው።

ከብሄራዊ የሎተሪ አስተዳደር እንዳገኘነው መረጃ ዕጣው በ605 ላይ ማንኛውም ፊደል በመላክ ወይም በቴሌብር ወደ *127# በመደወል በ3 ብር ነው የሚቆረጠው።

(ከላይ በትላትናው ዕለት የወጣው የመጀመሪያ ዙር ዕጣ #ሙሉ የባለዕድለኞች ቁጥር ተያይዟል)                            

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ጥንቃቄ

የወገኖቻንን ህይወት እየቀጠፈ ፤ ንብረትም እያወደመ ያለው የጎርፍ አደጋ !

በያዝነው ክረምት በተለያዩ የሀገራችን አካባቢዎች ላይ በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት እያለፈ ንብረትም እየወደመ ነው።

ለአብነት በአዲስ አበባ በተለያየ ጊዜ ህፃናት በጎርፍ አደጋ ህይወታቸው አልፏል ንብረት ወድሟል፣ በአማራ ክልል በተለያዩ ወረዳዎች በደረሰ የጎርፍ አደጋ የሰው ህይወት ጠፍቷል ፣ የአርሶ አደሮች ንብረትም እንዳልነበር ሆኗል።

ከትላንት በስቲያ ደግሞ ከወደ ኦሮሚያ ክልል፣ ጅማ ዞን ማና ወረዳ ሃሮ ቀበሌ እንደተሰማው የአንድ ቤተሰብ አባላትን የሆኑ ወገኖቻችን በጎርፍ ተወስደው ህይወታቸው አልፏል።

ከወረዳዋ ከተማ የቡ ተነስተው ሃሮ ወደተባለች ቀበሌ 3 ልጆቻቸውን ይዘው ሲጓዙ የነበሩ ቤተሰብ አንድ የ13 ዓመት እና ህጻን ልጅ በደራሽ ጎርፍ ሲወሰዱ አንድ ታዳጊ በህይወት ማግኘት ተችሏል።

በጎርፉ ከተወሰዱት የቤተሰብ አባላቱ የአባት አስከሬን በዕለቱ ሲገኝ፤ የሟች እናትና ሁለት ልጆች አስከሬን ትላንት ጠዋት ተገኝቷል።

የቤተሰብ አባላቱ ፤ በጎርፉ የተወሰዱት ዘመዶቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ስፍራው ሲያቀኑ በነበረበት መሆኑን ዶቼ ቨለ ሬድዮ ጣቢያ የወረዳውን ኮሚኒኬሽን ዋቢ አደርጎ ዘግቧል።

በአማራ ክልል በአምባሰል ወረዳ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እና በመሬት መንሸራተት ከቤታቸው ተፈናቅለዋል ፤ ንብረታቸው ወድሟል።

በአጠቃላይ 150 አባወራዎች እና እማወራዎች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው በትምህርት ቤቶች፣ በቀበሌ ማዕከል፣ በገበሬ ማሰልጠኛዎችና በዘመድ ቤት ተጠልለው ይገኛሉ ብለዋል።

በወረዳው በቂ ለድጋፍ የሚሆን ሐብት ባለመኖሩ ለተጎጅዎች የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድጋፋቸውን እንዲያደርጉ ተጠይቋል።

በሌላ በኩል ደግሞ ከሰሞኑን በአፋር ክልል በጎርፍ አደጋ የወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል ፤ ወገኖቻችን ተፈናቅለዋል፤ ከፍተኛ የሀብት ጥፋትም ደርሷል።

በሠመራ ከተማ ብቻ ጎርፍ ባስከተለው አደጋ በትንሹ የሶስት ሰዎች #ህይወት_አልፏል

በኤሊደአር  ወረዳ  ዶቢ ቀበሌ ደግሞ በጎርፍ አደጋ ከ3 መቶ ሺ ኩንታል በላይ የጨው ምርት ሙሉ በሙሉ ወድሟል።

በአካባቢው ላይ ከ300 በላይ የሚሆኑ ባለሀብቶች በጨው ምርት ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ሲሆን አሁን ላይ ሁለት መቶ  የሚሆኑት አምራቾች በጎርፉ ምክንያት ኪሳራ ደርሶባቸዋል።

በተጨማሪም ጨው ለማምረት ተዘጋጅተው የነበሩ የጨው ማምረቻ ቦታወችም በጎርፉ ምክንያት ተበላሽተዋል።

አንድ አምራች የምርት ቦታዎችን ለማዘጋጀት ከ200 ሺ ብር በላይ ሊያወጣ ይችላል የተባለ ሲሆን ባጠቃላይ አምራቾች ላይ የደረሰው ኪሳራ ቀላል ሊባል የሚችል አይደለም።

በተጨማሪም ፤ በአሳይታና አፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላት ሳቢያ በተከሰተ የጎርፍ አደጋ በቤት እና ንብረቶቻቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አሳይታ በርጋ ቀበሌ የሚኖሩ ወገኖቻችን በጎርፍ አደጋ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል፣ ቤታቸው እንዳልነበር ሆኗል ፣ ሁለት ሺህ ሄክታር መሬት እርሻ ላይ ጉዳት አድርሶባቸዋል።

በአሁን ሰዓት ከቤታቸው ተፈናቅለው መጠለያ ውስጥ ናቸው።

የመንግስት፣ ማህበራዊ አገልግሎት ሚሰጡ ተቋማት በውሃ ውስጥ ናቸው ያሉት።

በተመሳሳይ ፤ በአፋምቦ ወረዳ ወገኖቻችን በአዋሽ ወንዝ ሙላትና በከባንድ ዝናብ ሳቢያ ቤት ንብረታቸው በጎርፍ አደጋ እንዳልነበር ሆኗል እነሱም ተፈናቅለዋል ፤ እንስሳቶቻቸው ሞተውባቸዋል ፤ እነኚህ ወገኖቻችን የመንግስት ድጋፍ እንፈልጋለን ብለዋል።

በዚሁ ወረዳ 6 ሺህ ሄክታር የጥጥ እና ሰሊጥ እርሻ ላይ ከፍተኛ የሆነ ጉዳት ደርሷል።

መረጃዎቹ የተሰባሰቡት ፦ ከአፋር ብዙሃን መገናኛ ፣ ከኤሊዲአር ወረዳ ኮሚኒኬሽን፣ ከዶቼ ቨለ ሬድዮ ፣ ከአምባሰል ወረዳ ኮሚኒኬሽን ነው።

@tikvahethiopia
የአንጀት ቁስለት ህክምና ተማሪ ስኮላር ፕሮግራም !

ክሮንስ እና ኮላይተስ ኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ እንዲሁም የአንጀት ጤና ስፔሻሊስት መሆን ለሚሹ ከአንደኛ እስከ አራተኛ አመት ህክምና ትምህርት ላይ ላሉ የተዘጋጀ ስኮላርሽፕ ፕሮግራም አጋርቶናል።

ይህ ዕድል በዓለማችን ላይ ስላሉት ከአንጀት ቁስለት ህመም ህክምና ጋር የተያያዙ ጉድለቶች እንዲሁም ከዚህ ህመም ጋር ያሉ ወጣት እና ጎልማሳ ሰዎች ምን አይነት የህክምና ትኩረት ይፈልጋሉ የሚለውን ይዳስሳል።

ስለፕሮግራሙ ዝርዝር ከላይ ተያይዟል።

ለማመልከት ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ 👉https://bit.ly/3c6VBdL

ክሮንስ እና ኮላይተስ ኢትዮጵያ ከቲክቫህ ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ስር ስለሰደዱ ህመሞች ዘወትር ረቡዕ በ @tikvahethmagazine መረጃዎችን ያቀርባል።

@tikvahethiopia