TIKVAH-ETHIOPIA
የልጁን ህይወት አትርፎ ህይወቱ ያለፈው አባት ! የልጁን ሕይወት ለማዳን ከጀልባ ላይ የዘለለው እንግሊዛዊ አስክሬኑ ጣልያን ተገኘ። ዛሬ ጥዋት ቢቢሲ በደረገፁ አንድ አሳዛኝ ክስተት አጋርቷል። አረን ቻዳ የተባለ እንግሊዛዊ ልጁን ለመታደግ ከጀልባ ከዘለለ በኋላ ለሳምንታት ጠፍቶ አስክሬኑ ጣልያን ውስጥ ተገኝቷል። አረን ባለፈው ወር " ጋርዳ " የተባለ ባሕር አካባቢ ከትዳር አጋሩና ከሁለት ልጆቹ ጋር…
የልጁን ህይወት አትርፎ ህይወቱ ያለፈው አባት !

የልጁን ህይወት ለማትረፍ ናይል ወንዝ የገባው አባት አስከሬኑ ተገኘ።

ስሙ ሮበርት ክዌሲ ይባላል የኡጋንዳ ተወላጅ ዜግነቱ ደግሞ እንግሊዛዊው ነው ፤ እድሜው 48 ሲሆን በእንግሊዝ ሀገር ነዋሪ ነበር።

ሮበርት ከባለቤቱ ጀስቲን ካታንታዚ እና ከአራት ልጆቻቸው ጋር ወደ ኡጋንዳ ለእረፍት ይመጣሉ። ኡጋንዳ መጥተው እየተዝናኑ ሳለ የ12 አመት ልጁ እየዋኘ በነበረበት ወቅት በነበረው ማዕበል ችግር ስላጋጠመው አባት ልጁን ለመርዳት ዘሎ ይገባል። ምንም እንኳን አባት ልጁን ቢያተርፍም የእሱ ደብዛ ግን ከዛች ደቂቃ አንስቶ ይጠፋል።

የነፍስ አድን ሰራተኞች እና ጠላቂ ፖሊስ አባላት እንዲሁም የአካባቢው በጎ ፍቃደኞች ካለፈው ረቡዕ ጀምሮ ፍለጋ ያደርጋሉ በኃላም የሮበርትን አስክሬን አግኝተዋል።

ሮበርት ክዌሲ አስክሬኑ የተገኘው በናይል ወንዝ በአንደኛው ክፍል ነው ተብሏል።

ሮበርት በእንግዚዝ ፍሪጅ እና አየር ማቀዝቀዣዎችን በመጠገን በተቋራጭነት ይሰራ ነበር። ከባለቤቱ ጋር ጋብቻቸውን የፈጸሙት ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኡጋንዳ እንደነበር #ቢቢሲ ፅፏል።

ትላንትም አንድ እንግሊዛዊ አባት የልጁን ህይወት ለማትረፍ ሲል ከጀልባ ዘሎ ልጁን አትርፎ እሱ ግን ህይወቱ እንዳለፈ አስክሬኑም ጣልያን ውስጥ መገኘቱን የሚገልፅ መረጃ ማንበባችን ይታወሳል።

@tikvahethiopia