TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#አቡበከር_ናስር 🇪🇹

#Nasir_is_Yellow 🟡

የዋልያዎቹ የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር ወደ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ያደርገውን ዝውውር ክለቡ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ይፋ አድርጓል።

More : @tikvahethsport
#Ethiopia #US

የማይክ ሐመር ስለ ኢትዮጵያ ቆይታቸው ምን አሉ ?

አሜሪካ የኢትዮጵያን #ሉዓላዊነቷን እና #የግዛት_አንድነቷን_በማክበር ኢትዮጵያን ለመደገፍ ያላትን ፍላጎት እንደሚያረጋገጡ የሀገራቸውን አቋም ገልፀዋል።

በአሜሪካ ህዝብ ለጋስነት ሀገሪቱ ለተቸገሩ ኢትዮጵያውያን ሰብዓዊ ድጋፍ እያደረገች መሆኑን አመልክተዋል።

ሰላምን በማረጋገጥ በኩል የጋራ ፍላጎቶችን በሚመለከቱ ጉዳዮች ዙሪያ ከመንግስት ጋር የመነጋገር እድሉን ማግኘታቸውን እንደሚያደንቁ ገልፀዋል።

ሀመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ልማት እቅዶች ይበልጥ እንዳወቁና እንደተማሩ አሳውቀዋል።

በአፍሪካ ኅብረት ጥላ ስር ባለ ዲፕሎማሲ፣ በናይል ወንዝ ዳር የሚኖሩትን ሁሉ የሚያገለግል ስምምነት ላይ መድረስ ይቻላል ብለዋል።

ሀመር በኢትዮጵያ ለሁለት ሳምንት የሚጠጋ ጊዜ የቆዩ ሲሆን ቆይታቸው አሜሪካ ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ረጅም የግንኙነት ታሪክ እና በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ለአፍሪካ ህብረት የምታደርገውን ጥረት የሚያንፀባርቅ መሆኑን በአ/አ የአሜሪካ ኤምባሲ ገልጿል።

ሀመር በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከእነማን ጋር ተገናኙ ?
- ከፕ/ት ሳህለወርቅ ዘውዴ
- ከም/ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚ/ር አቶ ደመቀ መኮንን
- ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ዋና ስራ አስፈፃሚ ሌንሳ ቢየን
- ከተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ቡድኖች
- ከተመድ መርማሪዎች (በአ/አ)
- ከAU የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ኦባሳንጆ
- ከመንግስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች
- ወደ ትግራይ ተጉዘው ክልሉን እያስተዳደሩ ካሉት ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እና ሌሎች የህወሓት አመራሮች ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል።

https://telegra.ph/US-08-09

@tikvahethiopia
#ባልደራስ

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ አመራር አቶ ስንታየሁ ቸኮል በ100 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈቱ ከፍተኛ ፍ/ቤት ውሳኔ ማሳለፉን ፓርቲው ገልጿል።

ፓርቲው አመራሩ ለ40 ቀናት በግፍ እንደታሰረበት ገልጾ በ100 ሺ ብር ዋስ እንዲፈታ እንደተወሰነለት አመልክቷል።

የአቶ ስንታየሁ ቸኮልን ፤ መፈታት እውን ለማድረግ ፓርቲው የዋስትናውን ገንዘብ/ ክፍያ ለማስፈፀም በሂደት ላይ እንደሚገኝ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#KenyaElection🇰🇪

የኬንያን ምርጫ እየታዘቡ የሚገኙ #ኢትዮጵያውያን እነማን ናቸው ?

ኬንያ እያካሄደች ያለችውን 5ኛው ዙር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ለመታዘብ ኢትዮጵያውያን ኬንያ ይገኛሉ።

🇪🇹 አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ፦

የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃለማርያም ደሳለኝ መቀመጫውን ደቡብ አፍሪካ ያደረገውን 'ብሬንትረስት ፋውንዴሽን'ን በመወከል ምርጫውን እየታዘቡ ናቸው።

አቶ ኃይለማርያም በሚመሩት ልዑክ ውስጥ እውቁ ኡጋንዳዊ ፖለቲከኛ እና ሙዚቀኛ ቦቢ ዋይን ይገኝበታል።

🇪🇹 ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ፦

የቀድሞው የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ደግሞ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት (ኢጋድ) ታዛቢ ቡድንን በመምራት ኬንያ ናቸው።

🇪🇹 ፕ/ር መረራ ጉዲና ፦

የተቃዋሚው የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ መሪ እና አንጋፋው ፖለቲካኛ ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና በኬንያ ተገኝተው ምርጫውን እየታዘቡ ይገኛሉ።

🇪🇹 ሌንሳ ቢየና ፦

የኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ዋና ስራ አስፈጻሚ ሌንሳ ቢየና የኤን ዲ አይ/አይ አር አይ (NDI/IRI) ዓለም-አቀፍ ምርጫ ታዛቢ ልኡክ አካል ሆነው በኤልዶሬት ከተማ በዩዜን ጊሹ ካዉንቲ የሚደረገዉን ምርጫ በመታዘብ ላይ ይገኛሉ፡፡

መረጃው ከቢቢሲ እና ከኢትዮጵያ የህግ ባለሙያ ሴቶች ማህበር ያገኘነው ነው።

@tikvahethiopia
#Gambella

• 2 ሰዎች ተገድለዋል።
• 1 ሰው ቆስሎ ሆስፒታል ህክምና ላይ ነው።
• 2 ህፃናት ታፍነው ተወስደዋል።

በጋምቤላ ከደቡብ ሱዳን የሚነሱ የ "ሙርሌ ጎሳ" ታጣቂዎች ድንበር አቋርጠው በመግባት ጥቃት አድርሰዋል።

በዲማ ወረዳ ኡኩጉ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ ላይ ድንበር ተሻግረው በመጡ የሙርሌ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ የ2 ሰው ህይወት ሲያልፍ አንድ ሰው ቆስሎ 2 ህፃናት በታጣቂዎች መወሰዳቸውን የክልሉ ፖሊስ አሳውቋል።

ታጣቂዎች ጥቃቱን የፈፀሙት ከትናንት በስቲያ ከምሽቱ 4:30 ላይ ሲሆን ክልሉ በአሁኑ ሰዓት ልዩ ኃይሉንና ሚሊሻ በመጠቀም ሰላምና ፀጥታ የማስከበር ስራውን እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

ጥቃት አድራሾች ላይ እርምጃ ለመውሰድም በትኩረት እየተሰራ እንደሚገኝ ፖሊስ ገልጷል።

#ድንበሩ_ሰፊ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈጸም መንግስት ከሚያደርገው ጥረት በተጓዳኝ ህብረተሰቡ በንቃት አካባቢውን እንዲጠብቅ ማሳሰቢያ ተላልፏል።

የጋምቤላ ፖሊስ ፥ በፀጥታ አካላት ከሚሰራው የመከላከል ስራ ጎን ለጎን የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግስት ጋር በመሆን ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ ለማበጀት ከደ/ሱዳን መንግስት ጋር ውይይት እየተደረገ ነው ማለቱን ከክልሉ ፕሬስ ሴክሬተሪያት ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የመንገደኞች እንግልት እና የመንግስት አካላት ምላሽ ! ከአማራ ክልል በተለይም #ከሰሜን እና #ደቡብ_ወሎ አካባቢዎች ወደ አዲስ አበባ ለመግባት ብዙዎች እየተንገላቱ ነው። ይህ ጉዳይ አንድ ወቅት ጠንከር አንዴ ላላ ፤ ያዝ ለቀቅ እያደረገ አሁንም ድረስ ቀጥሏል። አንዳንዶች በብዙ ልመና ነው የሚያልፉት። ወደ መጣችሁበት ተመለሱ የሚባሉ ወገኖች ምክንያት ቢጠይቁም በግልፅ አስረድቶ የሚነግራቸው አላገኙም።…
ከአማራ ክልል በተለይ ከሰሜን እና ደቡብ ወሎ አካባቢዎች ወደ አ/አ በሚገቡ ዜጎች ላይ እየደረሰ ያለው መንገላታት አሁንም ዘላቂ መፍትሄ እንዳላገኘ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አሳውቀዋል።

ከጥቂት ቀናት በፊት ከተለከው ጥቆማ በተጨማሪ ሰሞኑን በስራ ፈተና፣ ለትምህርት ጉዳይ እና ለህክምና ወደ አ/አ መግባት የነበረባቸው ወገኖች ወደ ኃላ እንዲመለሱ ተደርገዋል።

አንድ የቤተሰባችን አባል ከእህቱ ጋር (ለእህቱ ህክምና) መናሻውን ኮምቦልቻ አድርጎ ወደ አ/አ ጉዞ እያደረገ ነበር ሸኖ ላይ የአዲስ አበባ/የኦሮሚያ መታወቂያ ከሌላችሁ አትገቡም በመባለቸው ወደ ኮንቦልቻ ተመልሰው በፕሌን ለመሄድ መገደዳቸውን ገልጿል።

" እባካችሁ መሪ ካለን ይምራን እኛ ምን አደረግን ይሄ ነገር ደግሞ የሁለቱን ክልል እና የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደርን ይመለከታል " ሲል ቅሬታውን አቅርቧል።

በተጨማሪ ትላንት ከደሴ ወደ አ/አ እየመጣ የነበረ የቤተሰባችን አባል ጫጫ ላይ የአ/አ መታወቂያ ስላለው ማለፉን ነገር ግን እዛው የቀሩ ሴቶች፣ አዛውንቶችን ጨምሮ ብዙ ሰዎች እንደነበሩ አመልክቷል።

የፌዴራል መንግስት ኮሚኒኬሽን ከቀናት በፊት ለቪኦኤ በሰጠው ቃል ጥብቅ ቁጥጥርና ፍተሻ እየተደረገ ያለው በተለይ አዲስ አበባ ላይ የተቃጣ የጥፋት እቅድ (በህወሓትና ሸኔ) መኖሩ ለደህንነት አከላት መረጃ በመድረሱ መሆኑን ገልጿል። በዚህ ሳቢያ በዜጎች ላይ እንግልት እያጋጠመ እንደሆነ አልሸሸገም።

በፀጥታ አካላት በኩል የፍተሻ አፈፃፀም ለዜጎች ምሬት ምክንያት እየሆነ በመምጣቱ የደህንነት ስራው አፈፃፀም ላይ ማሻሻያ መደረግ እንዳለበት፤ በተጨማሪ የደህንነትና የፀጥታ መዋቅሩን ማጥራት እንደሚገባ ታምኖበት እየተሰራ ነው ብሏል። በዋነኝነት ግን ስራው የዜጎችን ደህንነት ከማስጠበት ውጭ ሌላ ዓላማ እንደሌለው ገልጿል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ከክልልነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በትላንትናው ዕለት በጉራጌ ዞን መቀመጫ ወልቂጤ ከተማ የስራ ማቆም አድማ መመታቱ ይታወቃል። በዚህም መደበኛ እንቅስቃሴ ቆሞ ነበር።

ዛሬ ሩቡዕ የንግድ ድርጅቶች ፣ ባንኮች ፣ የተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት እና የትራንስፖርት አገልግሎት ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ መግባታቸው ተሰምቷል።

የስራ የማቆም አድማው የተደረገበት ምክንያት ፤ መንግስት እየተጠየቀ ያለውን ህጋዊ የክልልነት ጥያቄ በአግባቡ ምላሽ እንዲሰጥና ዞኑንም በክልል እንዲያደራጅ ለመጠየቅ እንዲሁም ዞኑን ከሌሎች አጎራባች ዞኖች ጋር በክልል ለማደራጀት የቀረበውን ሀሳብ በመቃወም ነበር።

በዞኑ ህዝብ ዘንድ አሁንም ድረስ የ " ክልል እንሁን " ጥያቄ የቀጠለ ሲሆን ዞኑን ከአጎራባች ዞኖች እና ልዩ ወረዳ ጋር አንድ ላይ በክልል ለማደራጀት በቀረበው ሀሳብ ላይ እስካሁን የዞኑ ምክር ቤት ተሰብስቦ አለመከረም / አላፀደቀም ።

#Update : በአገና እና እምድብር ከተሞች የስራ ማቆም አድማ መመታቱን በአካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ገልፀዋል።

ፎቶ ፦ የከተማው ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia