TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Update

በደቡብ ክልል ከሚገኙት ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ውስጥ የ " ክላስተር " አደረጃጀትን ባለማጽድቅ ብቸኛ የሆነው የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ነገ ሐሙስ ነሐሴ 5/2014 እንደሚያካሂድ ተገልጿል።

የአስቸኳይ ጉባኤውን መጠራት የዞኑ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አርሽያ አህመድ እንዳረጋገጡ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር በድረገፁ አስነብቧል።

ድረገፁ አነጋግሬያቸዋለሁ ያላቸው ሶስት የጉራጌ ዞን ምክር ቤት አባላት በነገው አስቸኳይ ጉባኤ ላይ እንዲገኙ ጥሪ እንደተላለፈላቸው ገልጸዋል።

የጉራጌ ዞን ምክር ቤት 97 አባላት ያሉት ሲሆን ከእነርሱ ውስጥ ስድስቱ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ተመራጮች ናቸው።

ቀሪዎቹ የምክር ቤት አባላት ገዢው ብልጽግና ፓርቲን ወክለው የተወዳደሩ እና ምክር ቤቱን የተቀላቀሉ ናቸው። 

ከዚህ በፊት በነበረው ልማድ ጉባኤው ከመካሄዱ ጥቂት ቀናት ቀደም ብሎ የጉባኤውን አጀንዳዎች በያዘ ደብዳቤ ጥሪ ይደረግላቸው እንደነበር የሚያስታውሱት የም/ ቤት አባላት የአሁኑ ስብሰባ አጀንዳ ግን እንዳልተገለጸላቸው ተናግረዋል።

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የዞኑ ምክር ቤት አባል፤ የነገው አስቸኳይ ጉባኤ ዋና አጀንዳ " የአደረጃጀት ጉዳይ " ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን አስቀምጠዋል።

የነገውን ጉባኤ ዋነኛ አጀንዳ ምን እንደሆነ ጥያቄ የቀረበላቸው የዞኑ ም/ቤት አፈ ጉባኤ፤ " አጀንዳ ለምክር ቤት አባላት ብቻ ነው የሚገለጸው " የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

Credit : www.ethiopiainsider.com

@tikvahethiopia
#ብርሃን_ባንክ

ለፈጣን ግብይትዎ የብርሃን ባንክ ኤቲኤም ካርድዎን መያዝን አይዘንጉ! እንደ ስማችን ብርሃን ነው ስራችን!

Facebook: https://www.facebook.com/berhanbanksc
Telegram: https://publielectoral.lat/berhanbanksc
Instagram: https://www.instagram.com/berhanbanksc/
YouTube: www.youtube.com/channel/UCvOxWe439dzMSvNnMrjcYVQ
#ጤና_ረቡዕ

(መልዕክት)

ዛሬ ሩቡዕ በ " ጤና ረቡዕ " የውይይት ገፃችን ስለ #የአንጀት_ቁስለት ህመምና የአመጋገብ ስርዓት እንድንወያይበት እንዲሁም ጥያቄዎቻችሁ በባለሙያዎች እንዲመለሱ የቀጥታ ስርጭት ፕሮግራም ይዘን መጥተናል።

#ከምሽቱ_አንድ_ሰዓት ላይ የአንጀት ስፔሻሊስት የሆኑትን ዶ\ር ኃይለሚካኤል ደሳለኝ እንዲሁም የስነ ምግብ ህክምና ስፔሻሊስት የሆኑትን ዶ\ር ዘላለም ደበበን ይዘን ቀርበናል።

ስለባለሙያዎቹ በዝርዝር ከላይ በፎቶ አያይዘናል።

ከምሽቱ አንድ ሰዓት ላይ በ @tikvahethmagazine መከታተል ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia @ibdeth
TIKVAH-ETHIOPIA
#USAirstrike የአሜሪካ አየር ጥቃት - በጎረቤት ሶማሊያ ! በጎረቤታችን ሶማሊያ ሂራን ክልል የሶማሊያ ብሄራዊ ጦር ኃይል የፀረ ሽብር ዘመቻ እያካሄደ ሲሆን ጦሩን ለመደገፍ #አሜሪካ የአየር ጥቃት መሰንዘር መጀመሯ ተገልጿል። አሜሪካ የአየር ላይ ጥቃቱን እንድትሰነዝር የተጠየቀችው በሶማሊያ መንግስት መሆኑን የሀገሪቱ ብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል። በክስተቱ ንፁሀን ዜጎች ላይ ምንም አይነት…
#US #SOMALIA

አሜሪካ ትላንትና ማክሰኞ ፤ ከሶማሊያ መንግስት ጋር በመተባበር በፈፀመችው የአየር ድብደባ 4 የአልሸባብ የሽብር ቡድን አባላትን መግደሏን አሳውቃለች።

የአልሸባብ ታጣቂዎች የሶማሊያ ጦር ላይ በቤልድዌይኔ ጥቃት የከፈቱ ሲሆን ይህን ተከትሎ የአሜሪካ ጦር በአየር በፈፀመው ድብደባ 4 የቡድኑን አባላት መግደሉ ተገልጿል።

አሜሪካ እርምጃው በሶማሊያ መንግስት በኩል ፍቃድ ኖሮት መፈፀሙን አሳውቃለች።

በጥቃቱ በሲቪል ሰዎች ላይ ጉዳት እንዳልደረሰ / ሲቪሎች እንዳልተገደሉ ተመላክቷል።

@tikvahethiopia
#SouthWestRegion

#የብዝሃ_ዋና_ከተሞች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ በአብላጫ ድምጽ ፀደቀ።

አዲሱ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል መንግስት የብዝሃ ዋና ከተሞች ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ማፅደቁ ተሰምቷል።

ረቂቅ አዋጁ የፀደቀው በቦንጋ የክልሉ ምክር ቤት ባካሄደው 6ኛ ዙር 1ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው።

ክልሉ መንግስት አራት (4) ብዝሃ ዋና ከተሞች እንደሚኖሩት ረቂቅ አዋጁ ይደነግጋል።

የብዝኃ ዋና ከተሞች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ ቦንጋ፣ ተርጫ፣ ሚዛን አማን እና ቴፒ ከተሞች የክልሉ ብዝሃ ዋና ከተሞች እንደሚሆኑ ደንግጓል።

1. ቦንጋ ከተማ ፦ የክልሉ የፖለቲካ እና የርዕሰ መስተዳደሩ መቀመጫ፣
2.ተርጫ ከተማ ፦ የክልሉ ምክር ቤት መቀመጫ፣
3.ሚዛን አማን ከተማ ፦ የክልሉ የዳኝነት አካል መቀመጫ
4. ቴፒ ከተማ ፦ የክልሉ የብሔረሰቦች ምክር ቤት መቀመጫ እንደሚሆኑም በረቂቅ አዋጁ ላይ ተቀምጧል።

የክልሉ ብዝሃ ዋና ከተሞች 4 እንዲሆኑ የተደረገው ፍትሐዊ የኢኮኖሚ ዕድገትን ለማረጋገጥ እንደሆነ የብዝኃ ከተሞች ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጁ እንደሚጠቅስ ከክልሉ ኮሚኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopia
" የክልል እንሁን ጥያቄዎች ዘላቂ ሰላምን በሚያመጣ መልኩ ሊፈቱ ይገባል " - እናት ፓርቲ

እናት ፓርቲ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በላከው መግለጫ የ " ክልል እንሁን " ጥያቄዎች ዘላቂ ሰላምን በሚያመጣ መልኩ ሊፈቱ እንደሚገባ አሳስቧል።

ፓርቲው የክልልነት ጥያቄን በተመለከተ የሀገሪቱን ተጨባጭ ኹኔታና የሕዝቡን ጥያቄ ከግምት ውስጥ በማስገባት የሚከተሉትን የመፍትሔ ሀሳቦች ጠቁሟል።

የመፍትሄ ሀሳቦች ፦

1. የሀገሪቱ አብዛኛው ችግር የሚመነጨው ከሕገ መንግሥቱ " የክልል አወቃቀር " ጋር በተያያዘ መሆኑ ታውቆ ከጊዜያዊ መፍትሔ ይልቅ ዘለቄታዊ መፍትሔና የችግሩ ምንጭ ላይ ያተኮረ አፋጣኝ ተግባራዊ እንቅስቃሴ እንዲጀመር ጠይቋል።

2. በአሁኑ ሰዐት የክልልነት ጥያቄ እየጠየቁ ላሉ የማኅበረሰባችን ክፍሎች መንግሥት የኃይል አማራጭን ከመከተል ይልቅ ከሕዝቡ ጋር በቅርበት በመነጋገርና በመግባባት ብቻ ችግሩን ለመፍታት ጥረት እንዲያደርግ አሳስቧል።

3. ሰላም ወዳድ የሆነው ሕዝብ የሚያነሳቸውን ጥያቄዎች እጅግ #ሰላማዊ በሆነ መንገድ ውጤት ላይ መድረስ እንጂ አላስፈላጊ መሥዋዕትነት ከሚያመጡ ድርጊቶች እንዲቆጠብ ጥሪ አስተላልፏል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
ነፃ የትምህርት ዕድል !

የሳንድፎርድ ኢንተርናሽናል ት/ቤት በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር በሚገኙ የመንግሥት ት/ቤቶች በመማር ላይ ከሚገኙ #በትምህርታቸውና #በፀባያቸው የተመሰከረላቸውን ተማሪዎች አወዳድሮ የነፃ ትምህርት ዕድል ለመሥጠት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ አሳውቆናል።

ተወዳዳሪ ተማሪዎች ለነፃ ትምህርቱ ውድድር ለመመዝገብ ሲመጡ የሚከተሉትን መስፈርቶች አሟልተው የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት መግለጫ ኮፒ ይዘው መምጣት ይጠበቅባቸዋል።

1. በአ/አ ከሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ተማሪ መሆን

2. ተማሪው የተወለደው እ.ኤ.አ ነሐሴ 31/2008 ድረስ 14 ዓመት የሚሞላዉ ነገር ግን 15 ዓመት በታች የሆነ ይህንንም የሚያረጋግጥ የልደት የምሥክር ወረቀት ይዘው መቅረብ የሚችሉ

3. በ2014 የትምህርት ዘመን መጨረሻ የ8 ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና አማካይ ወጤት ከ95% በላይ የሆነ

4. የ7ና 8 የክፍል ትምህት ለየብቻው አማካይ ውጤቱ ከ90% በላይ የሆነ

5. ስለመልካም ሥነምግባሩ ወይም ፀባዩ ከሚማርበት ት/ቤት የጽሁፍ ማስረጃ በሳንድፎርድ ተቀባይነት ሲያገኝ ማምጣት የሚችል

6. ት/ቤቱ የሚሰጠውን የመግቢያና ቃለመጠይቅ ፈተናዎችን የተሻለ ዉጤት ማስመዝገብ

7. የወላጅ/የአሳዳጊ ሙሉ ፈቃድ ያገኘ

8. አሸናፊ የሚሆነው ተማሪ በአሥረኛ (10) ክፍል በት/ቤቱ ተመዝግቦ ለመማር ፈቃደኛ የሆነ ናቸዉ።

9. የምዝገባ ሰዓት ጠዋት 2፡30 - 6:00 ከሰዓት ከ7:30 - 9:30

መስፈርቱን ያሟሉ ተማሪዎች ነሐሴ 19/2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ላይ ለፅሁፍ ፈተና ይቀርባሉ።

ቦታ፦ ዳግማዊ ሚኒሊክ ሆስፒታል አካባቢ በሳንድፎርድ ት/ቤት እስከ ነሐሴ 18 ከቀኑ 6 ሰዓት ድረስ በአካል በመቅረብ መመዝገብ ይቻላል።

@tikvahethiopia
#WeCare

ከፍተኛ የስኳር መጠን እየወሰዱ እንደሆነ የሚያሳዩ 7 አደገኛ ምልክቶች !!

@WecareET የስልክ መተግበሪያ ስመጥር እና የ አመታት ልምድ ያላቸው ሐኪሞችን በቀላሉ ካሉበት ቦታ ሁነው ማማከር የሚችሉበት መተግበሪያ ነው።

ዛሬውኑ ይሞክሩት ! መተግበሪያውን ለማውረድ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጠቀሙ : https://play.google.com/store/apps/details?id=com.icare.patient

ጤና ነክ መረጃዎችን ለማግኘት ወይንም ሐኪሞችን 👨🏽‍⚕️👩‍⚕️ ለማማከር 📞 9394 ላይ ይደውሉ ።
#Balderas

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፕ/ት አቶ እስክንድር ነጋ ፤ በመንግስት ጫና በአባልነትም ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችሉበት ደረጃ ላይ መድረሳቸው አሳወቁ።
አቶ እስክንድር ሀምሌ 16/2014 ዓ/ም ካሉበት ቦታ ሆነው ፃፉት በተባለውና በፓርቲው የፌስቡክ ገፅ ላይ በተሰራጨ ደብዳቤ በመንግስት ጫና ሳቢያ በፓርቲያቸው በአመራርነትም ሆነ በአባልነት መስራት የማይችሉበት ድረጃ መድረሳቸውን ገልፀዋል።

" ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እንድትሻገር ለዓመታት የበኩሌን አስተዋጽዖ ሳደርግ መቆየቴ ይታወሳል። " ያሉት አቶ እስክንድር " በአሁኑ ጊዜ ግን፣ ተረኛው ጨቋኝ መንግስት በባልደራስም ሆነ በሃገር አቀፍ ደረጃ በፈጠረው የለየለት አምባገነናዊ ጫና ሳቢያ፣ በአባልነት ሆነ በአመራርነት መስራት የማልችልበት ደረጃ ላይ ደርሻለሁ። " ብለዋል።

በዚህም " የፓርቲው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ፣ አባላት፣ በየደረጃው ያሉ የፓርቲው አመራር አባላት፣ መላ አባላትና ደጋፊዎች፣ እንዲሁም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ከፓርቲው ምክትል ፕሬዝደንት አቶ አምሃ ዳኘው ጋር ሙሉ ለሙሉ በመተባበር ስራቸው የተቃና እንዲሆን እንድትተባበሯቸው በትህትና እጠይቃለሁ። " ብለዋል።

በእቅድ ላይ ያለው የባልደራስ ጠቅላላ ጉባኤ በተሳካ ዝግጅት እንዲከናወን ያላቸው ተስፋ የገለፁት አቶ እስክንድር " ባልደራስ በሃገር አቀፍ ፓርቲነት አድጎ የማየት ተስፋችን ወደ ተግባር ተተርጉሞ ለማየት የፈጣሪ መልካም ፈቃድ ይሁን " ሲሉ መልዕክታቸውን አጠቃለው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ... ለዩትዩብ (YouTube) ሽቀላ ተብሎ የሚደረጉ ቅስቀሳዎች መቆም መቻል አለባቸው " - አቶ ጃዋር መሀመድ የኦፌኮ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ ፦ " ...በዳይስፖራ ሆነ በተለያዩ ቦታዎች ያሉ ሚዲያዎች ለዩትዩብ ሽቀላ ተብሎ የሚደረጉ ቅስቀሳዎች መቆም መቻል አለባቸው። ተመልከቱ ሀገር ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር እነኚህ ጦርነቶች ካልቆሙ ሩዋንዳን የሚያስንቅ ፣ ሶሪያን የሚያስንቅ በጣም…
" ለሰላም መስፈን የምንሰራው ስራ ይቀጥላል " - አቶ ጃዋር መሀመድ

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ እና ም/ ሊቀመንበር አቶ ጃዋር መሀመድ በአውሮፓ ሀገራት እና በሰሞን አሜሪካ ሲያካሂዱት የነበረውን " Galatoomaa Tour " ማጠናቀቃቸው ተሰምቷል።

አቶ ጃዋር መሀመድ በአውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ የነበራቸውን ቆይታ በማጠናቀቅ ወደ ሀገራቸው በሰላም መመለሳቸውን ዛሬ አሳውቀዋል።

ምክትል ሊቀመንበሩ በተለያዩ ከተሞች በነበሩ ህዝባዊ ውይይቶች ላይ ለተካፈሉ ያላቸውን ፍቅር እና አድናቆት ገልፀው ለሰላም መስፈን የሚሰራው ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

እነ አቶ ጃዋር መሀመድ ፤ በአውሮፓ እና ሰሜን አሜሪካ በተለያዩ ከተሞች ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ጋር በኢትዮጵያ ጉዳይ የመከሩ ሲሆን በእስር ቤት ቆይታቸው ድምፅ ለሆኗቸው፣ አብረዋቸው ለነበሩ " ምስጋና " አቅርበዋል።

ከማህበረሰቡም ዘንድ ሲነሱ ለነበሩ ጥያቄዎችም መልስ ሲሰጡ ቆይተዋል።

በተለይም በየመድረኩ ላይ በተነሱላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ስለ ጦርነት ማቆም፣ ስለ ሰላም እና ድርድር አስፈላጊነት ፅኑ አቋማቸውን በተደጋጋሚ አስረግጠው ተናግረዋል።

ሚዲያዎችም እንዲሁም ደግሞ ከኢትዮጵያ ርቀው በውጭ ሀገር ያሉ ሰዎች በሀገሪቱ አስተማማኝ ሰላም እንዳይኖርና በቀጣይ የማያባራ እልቂት እንዲፈጠር ከሚያደርጉ ድርጊቶች እንዲቆጠቡም በማሳሰብ ለሀገሪቱ ህዝብ ሲሉ በ #ሰላም ጉዳይ አበክረው እንዲሰሩ ጥሪ ሲያቀርቡ ነበር።

@tikvahethiopia
ኢትዮጵያ እና የፋይናንስ ሴክተሯ !

በ2014 በጀት ዓመት ማለቂያ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ሴክተር እውነታዎች ፦

• የባንኮች ብዛት 👉 30

• የባንክ ቅርንጫፎች ብዛት 👉 8,944

• ጠቅላላ የባንኮች ካፒታል (በብር) 👉 199.1 ቢሊዮን ብር

• ጠቅላላ የባንኮች ሀብት (በብር) 👉 2.4 ትሪሊዮን ብር

• ጠቅላላ ተቀማጭ ገንዘብ (በብር) 👉 1.7 ትሪሊዮን ብር

• የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ብዛት 👉 16.3 ሚሊዮን

• የዴቢት ካርድ ተጠቃሚዎች ብዛት 👉 30.7 ሚሊዮን

• የሞባይል ገንዘብ ተጠቃሚዎች ብዛት 👉 43.3 ሚሊዮን

• የኤቲኤሞች (ATM) ብዛት 👉 6,902

• የፖስ ብዛት 👉 11,760

• የኢንሹራንስ ተቋማት ብዛት 👉 18

• የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ብዛት 👉 40

መረጃ ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

@tikvahethiopia