TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ኢትዮጵያ❤️

ሀገራችን ኢትዮጵያ ከፍተኛ ድል ያስመዘገበችበት የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተጠናቋል።

#ከዓለም ከአሜሪካ ቀጥላ ሁለተኛ እንዲሁም #ከአፍሪካ ቀዳሚውን ደረጃ በመያዝ ነው ያጠናቀቀችው።

በዓለም ሻምፒዮናው 4 ወርቆችን ያገኘን ሲሆን የዘንድሮው ውድድር በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሆኗል።

ከተገኙት አራት #ወርቆች 🥇 መካከል ታምራት ቶላ በማራቶን ያገኘው ወርቅ በዓለም ሻምፒዮናው በወንዶች የተገኘው #ብቸኛው ወርቅ ነው።

ለሀገራቸው ሜዳሊያ ያስገኙ አትሌቶቻችን እነማን ናቸው ?

ወርቅ 🥇

🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ጎተይቶም ገ/ስላሴ
🇪🇹 ታምራት ቶላ

ብር🥈

🇪🇹 ወርቅውሀ ጌታቸው
🇪🇹 ሞስነት ገረመው
🇪🇹 ለሜቻ ግርማ
🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ

ነሐስ🥉

🇪🇹 ዳዊት ስዩም
🇪🇹 መቅደስ አበበ

አጠቃላይ ከተገኘው 10 ሜዳሊያ ሰባቱ በሴቶች የተገኘ ነው፤ የቀረው 3 ሜዳሊያ ደግሞ በወንዶች ውድድር የተገኘ ነው።

የዓለም ሻምፒዮናው ምንም እንኳን ከፍተኛው ድል የተመዘገበበት ቢሆንም በወንዶች ውድድሮች ላይ የተሻለ መስራት እንደሚጠይቅ የሚጠቁም ነው።

የአትሌቲክስ ቡድናችን ወደ ሀገሩ ሲመለስ የጀግና ፣ የክብር አቀባበል እንደሚደረግለት ይጠበቃል።

ውድ አትሌቶቻችን ፤ ላደረጋችሁት ከፍተኛ ተጋድሎ ላስመዘገባችሁት ድል ፣ የሀገራችሁን ህዝብ ክብር ከፍ ስላደረጋችሁ ምስጋና ይገባችኃል።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !

@tikvahethiopia @tikvahethsport
TIKVAH-ETHIOPIA
#የጀግኖቹ_ወላጆች ❤️ የኢትዮጵያን ስም በዓለም ላይ ከፍ እያደረጉ ካሉት አትሌቶቻችን መካከል ቤተሰቦቻቸው የግንኙነት መስመር ከዓመት በላይ በተቋረጠበት ትግራይ ክልል ውስጥ ይኖራሉ። እነሱን ጨምሮ ሁሉም የትግራይ ህዝብ የኢንተርኔት ግንኙነት ባለመኖሩ ስሜቱን እንደኛ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ለማጋራት አልታደለም። ከከተሞች ወጣ ባሉ የትግራይ ክልል ክፍል የሚኖሩ የአትሌቶች ቤተሰቦችም የልጆቻቸውን ድል…
#ሰላም #Peace

የጎተይቶም የሰላም ምኞት !

ጎተይቶም ገብረስላሰ የሴቶች ማራቶን #የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ፦

" ... ምኞቴ ሰላም ነው። ሰላም በምንም ነገር አይገኝም።

እኛ በጣም ነው ሰላምን የምንፈልገው። ዓመት ከስምንት ወር ሆኖብናል የወላጅ ናፍቆት ቀላል አይደለም።

እናቴ እንዳለችው እኔ ናፍቆት አልችልም። ማይቻል ነገር ግን የለም። ችለን እዚህ ደረስን እንጂ እኔ ናፍቆት አልችም ነበር።

አንድ ቀን ሳልደውልላት አልተኛም። አባት፣ እናቴን በጣም እወዳለሁ፤ አባቴን በጣም ነው የምወደው በዛ የተነሳ ስልክ ሳልደውልላቸው አልተኛም ነበር።

ማይቻል ነገር የለም ብላዋለች እናቴ ናፍቆትን አትችልም እሷ ይሄን ሁሉ ተቋቁማ እዚህ መድረሷ ግን በእግዚአብሔር ኃይል ነው ያለችው ትክልል ነው ማይቻል ነገር የለም ችዬዋለሁ።

እግዚአብሔር ሰላም አምጥቶ እንዲያገናኘን ነው ምኞቴ። "

ጎተይቶም ገብረስላሰ የኢትዮጵያን ህዝብ ስሜት በተመለከተ፦

" .. እያየሁ ነበር የነበረውን ድባብ፣ የነበረውን ደስታ እንደዚህ ስንሆን ነው የሚያምርብን ፤ ሁሉን ነገር ትተን #ለሰላም ስንቆም ነው።

ለካ ይሄንን ያህል በህዝቡ ልብ ውስጥ አለን ብዬ ነበር ለራሴ ፤ ደጋግሜ እያየሁ ነበር።

እርግጥ ውድድሩ አጓጊና እልህ አስጨራሽ ነበር በጣም ፤ በዛ የተነሳ ሰው ስሜታዊ ሆኖ ነበር በጣም ነው የማመሰግነው። በፀሎትም፣ በሞራልም የደገፉኝ ሰዎች በጣም ነው የማመሰግነው።

ሁለተኛ ትልቅ ደስታ ነው የፈጠረብኝ። ይሄን ያህል ህዝብ ነበር ለካ የሚከታተለው ብዬ ለራሴ ውስጤን እንድጠይቅ ነው ያደረገኝ "

(አትሌት ጎተይቶም ለቪኦኤ ሬድዮ ከሰጠችው ቃለምልልስ)

@tikvahethiopia
#Tigray

የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ በትግራይ ሰሜናዊ ምዕራብ እና ማእከላዊ ዞኖች በግጭት የተጎዱ የውሃ አውታሮችን ወደ ነበሩበት ለመመለስ የውሃ ፓምፖች ፣ ጄኔሬተሮች እና የውሃ ማጣሪያ ኬሚካሎችን በመለገስ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ማድረጉን አሳውቋል።

#ICRCEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥያቄ #የጋራመኖሪያ_ቤቶች ብዙ ሲባልለት የነበረው የ20/80 እና የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤት ዕጣ ከብዙ መናጋገሪያ ጉዳዮች በኃላ ሙሉ በሙሉ መሰረዙ ይታወሳል። በቀጣይ ዕጣው መቼ ይወጣል ? የሚለው ለጊዜው ባይታወቅም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ " ከገጠመን ችግር ተነስተን ተገቢውን ሁሉ ጥንቃቄ በማድረግ በፍጥነት ዳግም እጣ በማውጣት በፍትሀዊነት ተደራሽ ለማድረግ እንሰራለን "…
" ለጥያቄቻችን መልስ እንፈልጋለን " - የ2005 የ20/80 ባለ3 መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች

ጥያቄ አለን ያሉን ከ2005 ጀምሮ ለ9 ዓመት እየቆጠቡ ያሉ የባለ 3 መኝታ ቤት (20/80) ተመዝጋቢዎች የአዲስ አበባ አስተዳደር እነሱን በተመለከተ ግልፅ ማብራሪያ እንዲሰጣቸው እንዲሁም በቀጣይ እጣ ላይ እንዲካተቱ እየጠየቁ ይገኛሉ።

እነዚሁ ጥያቄ አለን ያሉ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በቴሌግራም ግሩፕ በመሰበሰብ መፍትሄ ለመፈለግ ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ እየተነጋገሩ ይገኛሉ።

በ2005 የባለ ሶስት መኝታ ቤት ተመዝጋቢዎች አለን ያሉትን ጥያቄ አሳውቀናችሁ ነበር። አሁንም ለጥያቄቸው መልስ ባለማግኝታቸው ጥያቄያቸውን ማቅረባቸውን ቀጥለዋል።

ተመዝጋቢዎቹ ፤ " በ20/80 በባለ 3 መኝታ ተመዝግበን መንግስት ቃሉን አክብሮ የቤት ባለቤት እንደሚያደርገን ተማምነን " ነበር ሲሉ ገልፀዋል።

" ከልጆቻችን ዳቦ ቀንሰን ተጎሳቁለን በቤት ክራይ እየተንገበገብን ላለፉት 9 አመታት በተስፋ ተሞልተን ቁጠባችንን ሳናቋርጥ በመቆጠብ ላይ እንገኛለን " ም ብለዋል።

ነገር ግን በ13ኛው ዙር ተጀምሮ በ14ኛው ዙር ላይ በዕጣው አለመካተታቸው ከፍተኛ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው እና እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

ላለፉት 9 ዓመታ እየቆጠቡ የሚገኙት ወገኖች በ13ኛው ዙር የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ወቅት በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ በ1997 ለባለ3 መኝታ የተመዘገበ የለም ሁሉም በ2005 የተመዘገቡ ስለሆነ ወደእነሱ ይተላለፋል ተብሎ ነበር ነገር ግን በ14ኛው ዙር አለመካከተቱ ግልፅ ማብራሪያ የሚያስፈልገው መሆኑን ገልፀዋል።

ምንም እንኳን ትክክለኛ ቀኑንም ሆነ ሳምንቱ ባይታወቅም #በቅርቡ የተሰረዘው የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ በሌላ ሶፍትዌር ይወጣል ተብሎ ይጠበቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UN #NewsAlert የተመድ መርማሪዎቹ አዲስ አበባ እንዲገቡ ፍቃድ ማግኘታቸውን አስታወቁ። በሰሜን ኢትጵያ በተካሄደ ጦርነት ተፈፀሙ የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲያጣሩ የተሰየሙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪዎች አዲስ አበባ እንዲገቡ ፈቃድ ማግኘታቸውን ዛሬ ሀሙስ አስታወቁ። ሌሎችም የሀገሪቱ አካባቢዎች መግባት እንዲፈቅድላቸው ጠይቀዋል። የድርጅቱ የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤት ጦርነቱ…
#Update

የተመድ መርማሪዎች አዲስ አበባ ይገኛሉ።

ከሳምንታት በፊት በሰሜን ኢትጵያ በተካሄደ ጦርነት ተፈፀሙ የተባሉ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲያጣሩ የተሰየሙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርማሪዎች አዲስ አበባ እንዲገቡ ፈቃድ ማግኘታቸውን ማሳወቃቸው አይዘነጋም።

ይህን ተከትሎ አዲስ አበባ ይገኛሉ።

መርማሪዎቹ በአዲስ አበባ ከመንግስት የስራ ሃላፊዎችን እና አግባብነት ካላቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ላይ ይገኛሉ።

የሰብዐዊ መብቶች የባለሞያዎች ኮሚሽንን በተመለከተም የኢትዮጵያ መንግስት ኮሚኒኬሽን ያወጣው መግለጫ ከላይ ተያያዟል።

@tikvahethiopia
#ኢትዮጵያ #አሜሪካ #ሩስያ

በመጪዎቹ ቀናት ኢትዮጵያ የሩስያ እና የአሜሪካ ባለስልጣናትን ታስተናግድለች።

ነገ ማክሰኞ የሩስያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ሰርጌ ላቭሮቭ በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት ያደርጋሉ።

ለቭሮቭ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነው ነገ አዲስ አበባ የሚገቡት።

በአዲስ አበባ ቆይታቸው ፦
- በኢትዮጵያ እና ሩስያ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ውይይት ያደርጋሉ፤
- ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ እና ሩስያ መካከል የተፈረሙ ስምምነቶች ላይ ይመክራሉ፤
- ከአፍሪካ ህብረት ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ላቭሮቭ ኢትዮጵያ ሲመጡ የመጀመሪያቸው አይደለም። እ.ኤ.አ 2018 ላይ ኢትዮጵያን ጎብኝተው ነበር።

(ሰርጌ ላቭሮቭ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው ቀደም ብሎ #በግብፅ የስራ ጉብኝት አድርገዋል)

#US የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ከሐምሌ 17- ሐምሌ 25 2014 ዓ.ም ኢትዮጵያን ጨምሮ በግብፅ፣ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ጉብኝት ያደርጋሉ።

በኢትዮጵያ ግብኝታቸው የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት በሰላም ለመቋጨት ሊደረግ የታሰበው የሰላም ድርድር ላይ ይወያያሉ።

በተጨማሪ ፦
- የሰብዓዊ እርዳታ አቅርቦት ያለበትን ሁኔታ ይገመግማሉ።
- በጦርነቱ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የፈጸሙ አካላት ተጠያቂ ማድረግን በተመለከተ ይመክራሉ።

ሐመር የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ሆነው ከተሾሙ በኃላ ወደኢትዮጵያ ሲመጡ ሁለተኛቸው ይሆናል ከዚህ ቀደም ኢትዮጵያ መጥተው ከምክትል ጠ/ሚ እና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጋር መወያየታቸው አይዘነጋም።

(ማይክ ሐመር ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት #በግብፅ ጉብኝት ያደርጋሉ)

@tikvahethiopia
#AddisAbaba

የ8ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ተደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2014 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል።

ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች መካከል 63.9 ፐርሰንት ተማሪዎች 50 እና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ችለዋል፡፡ ይህም ካለፉት አመታት ከተመዘገቡት ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ውጤቶች አንጻር ሲታይ ከፍተኛ ውጤት ሆናል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ 85.5% ተማሪዎች ወደቀጣይ ክፍል ለመዛወር መቻላቸዉን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የተፈና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዲናኦል ጫላ ገልጸዋል፡፡

ተማሪዎች ውጤታቸውን ቀጥሎ ያለውን ሊንክ በመጫን https://aaceb.gov.et/%e1%8b%a88%e1%8a%9b-%e1%8a%ad%e1%8d%8d%e1%88%8d-%e1%8b%89%e1%8c%a4%e1%89%b5/ ወይም aaceb.gov.et በመጠቀም ሬጅስትሬሽን ቁጥር በማስገባት እና GO የሚለዉን በመጫን ውጤታችሁን ኦላይን ማየት ይችላሉ ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አሳውቋል።

በሌላ በኩል ፤ ተማሪዎች እና የተማሪ ወላጆች ትምህርት ቢሮው ይፋ ያደረገው የውጤት መመልከቻ ድረገፅ እየሰራላቸው እንዳልሆነ በመጠቆም ያለው ችግር እንዲስተካከል ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia