TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ችሎት

በአዲስ አበባ ከተማ ከጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር በዋሉ ግለሰቦች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ተፈቀደ።

ከኮንዶሚኒየም ቤቶች ዕጣ አወጣጥ ጋር በተያያዘ በቁጥጥር ስር የዋሉ ስምንት ግለሰቦች ፦
- የቴክኒክ ሙያ ስልጠና አይሲቲ ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ አቶ አብርሐም ሰርሞሌ
- የቤቶች ልማት ዳታ ቤዝ ቡድን መሪ አቶ ስመኘው አባተ
- የሶፍትዌር ባለሙያዎች ፦
• ሀብታሙ ከበደ
• ዮሴፍ ሙላት
• ጌታቸው በሪሁን
• ቃሲም ከድር
- የቤቶች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ሚኪያስ ቶሌራ
- የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ICT ኃላፊ አቶ ኩምሳ ቶላ ላይ የ14 ቀናት የምርመራ ጊዜ በፍርድ ቤት ተፈቅዷል።

የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 11/2014 የዋለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ነው። 

ችሎቱ የምርመራ ጊዜውን የፈቀደው የፌደራል ፖሊስ እና የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ባለፈው ሳምንት አርብ ሐምሌ 8/2014 ያደረጉትን ክርክር ከመረመረ በኋላ ነው።

የጊዜ ቀጠሮ ችሎቱ በዛሬ ውሎው የተጠርጣሪዎቹ በዋስትና መውጣት “ምርመራው የተፈለገውን ውጤት እንዳያስገኝ ሊያደርግ ስለሚችል” በሚል ጠበቆች ያቀረቡትን የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ማድረጉን " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር " ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#እቪኤላስ_ፈርኒቸር

በዘመናዊ መንገድና ጥራት የቤትና የቢሮ እቃዎችን እንደፍላጎትዎ የሚያመርተዉ አቪኤላስ የቤትና ቢሮ እቃ ማምረቻ ባዳዲስ ዲዛይን ቤትና ቢሮዎን ያስዉባል።

ኪችን፣ ቁምሳጥ፣ ቲቪ ስታንድ፣ በሮች፣ ፓርቲሽኖችና የተለያዩ የእንጨት ስራዎች ሲፈልጉ ይደውሉልን።

ቴሌግራም ቻናል ጆይንና ሼር በማድረግ አዲስ ምርት ማዬት ይችላሉ 👉 https://publielectoral.lat/furnituremakers

ስልክ 0118220767 / 0911427052 /0985931325 /

እድራሻ : ቦሌ ቡልቡላ 93 ማዞሪያ
ቅዱስ ቡዙአየሁ ኮሜርሻል ሴንተር 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁ 24
#SFP

የሲዳማ ፌደራሊስት ፓርቲ (ሲፌፓ) ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ባወጣው መግለጫ ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጊዚያዊ የምዝገባ ፈቃድ ማግኘቱን አመልክቷል።

አስተባባሪ ኮሚቴው በላከው መግለጫ ክልሉ በፖለቲካዊ፣ በኢኮኖሚያዊ፣ በማህበራዊ ፣በባህላዊና በፍትህ ዘርፎች ትክክለኛ መስመር አለመያዙን ተገንዝቢያለሁኝ ያለ ሲሆን በተለይ ምክንያታዊ ያልሆኑ የስራ አጥነት ቀውስ፣ ፍትህ እጦት፣ ሙስና፣ ጎሰኝነት፣ አድሎአዊ አሰራር፣ ጥሎ የማለፍ ፖለቲካ ስርዓታዊ (systemic) እየሆነ መጥቷል ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ በክልሉ ውስጥ ህዝቡን አደራጅቶ የሚታገል ጠንካራ ተፎካካሪ ፖርቲ እንደሌለ መገንዘቡን ገልጾ ፦
- ሁሉን የህብረተሰብ ክፍል ያቀፈ ፣
- የሲዳማ እሴቶችን መርህ ያደረገ፣
- በዴሞክራሲያዊና የህዝብ ስልጣን ባለቤትነትን ተግባራዊ እንዲሆን የሚታገል፣
- በሀሳብ ብዙሃነትና በመነጋገር የሚያምን፣
- እውነተኛ የሆነ ህብረብሔራዊ ፌደራሊዝም የሚከተልና እውን ለማድረግ ተመሳሳይ ዓላማ ካላቸው ሀገራዊ ፖርቲዎች ጋር የሚሰራ ክልላዊ የፖለቲካ ፖርቲ ማቋቋም አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት ጊዜያዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ጊዜያዊ ፈቃድ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አግኝቶ የማቋቋሙን ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በአሁኑ ጊዜ ኮሚቴው ሙሉ ፈቃድ ለማግኘት የሚያስፈልጉ ስራዎች እያጠናቀቀ እንደግሚገኝና የአባላት ምዝገባ እያካሄደ መሆኑን አመልክቷል።

በዚህ ሂደት ሚመዘግቡ ወጣቶችና አስተባባሪዎች ላይ የማስፈራሪያ ዘመቻ እየተካሄደ ነው ያለው ሲፌፓ ለድርጊቱን የክልሉን መንግስት አመራሮችን ወቅሷል፤ ከድርጊታቸው እንዲታቀቡም አሳስቧል።

@tikvahethiopia
#አቶ_ተወልደ_ገብረማርያም

አቶ ተወልደ ገ/ማርያም የህይወት ዘመን ሽልማት ተበረከተላቸው።

የቀድሞ የኢትዮጲያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ላሳዩት የላቀ አመራር ፍላይት ግሎባል የተሰኘ የእንግሊዝ ኩባንያ የህይወት ዘመን ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

ፍላይት ግሎባል " ኤርላይን ቢዝነስ " የተሰኘ ዓለምአቀፍ የአቪዬሽን መጽሔት አሳታሚ ኩባንያ ሲሆን እ.ኤ.አ 2002 ዓ.ም ጀምሮ " ኤርላይን ስትራቴጂ አዋርድ " በየአመቱ በማዘጋጀት ለአየር ትራንስፖርት ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦች እና ኩባንያዎች እውቅና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

አቶ ተወልደ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት እሑድ ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ለንደን በተዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም ላይ በመታደም ተቀብለዋል፡፡

አቶ ተወልደ እውቅናውን በማግኘታቸው ደስ እንደተሰኙ ገልፀው በአገልግሎት ዘመናቸው አብረው ለደከሙ ሁሉ ባልደረቦቻቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ፍላይት ግሎባል ባወጣው መግለጫ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም የተሸለሙት የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ባገለገሉባቸው 11 አመታት ላሳዩት የረጅም ጊዜ መርሀ ግብር እቅድ ዝግጅት እና ቀውስን የመቆጣጠር ክህሎት እውቅና ለመስጠት እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በእርሳቸው አመራር አየርመንገዱ በአራት እጥፍ ማደጉን ፍላይት ግሎባል ጠቅሷል፡፡

የኢትዮጲያ አየርመንገድ የአውሮፕላን ብዛት ከ33 ወደ 130 ፤ የመንገደኞች ቁጥር ከ3 ሚሊዮን ወደ 12 ሚሊዮን እንዳደገ ኩባንያው ጠቁሟል፡፡

አቶ ተወልደ አየርመንገዱን ለ37 አመታት ካገለገሉ በኋላ ባለፈው የካቲት ወር ከጤና ጋር በተያያዘ ከሃላፊነታቸው መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡

መረጃው የኢትዮ ንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ነው።

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ4ኛ ቀን ውድድር ዛሬ ይካሄዳል። የሀገራችን ልጆች የሚካፈሉበት ውድድር የሚከተሉት ናቸው።

🏟️ በማራቶን የሴቶች ፍፃሜ ፦

🇪🇹 ጎይቶቶም ገ/ስላሴ
🇪🇹 አባበል የሻነህ
🇪🇹 አሸቴ በክሬ

(ሰዓት - ቀን 10:15)

🏟️ 3,000 ሜትር መሰናክል የወንዶች ፍፃሜ ፦

🇪🇹 ለሜቻ ግርማ
🇪🇹 ሀይለማርያም አማረ
🇪🇹 ጌትነት ዋለ

(ሰዓት - ለሊት 11:20)

🏟️ 1,500 ሜትር የሴቶች ፍፃሜ

🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ሂሩት መሸሻ
🇪🇹 ፍሬወይኒ ሀይሉ

(ሰዓት - ለሊት 11:50)

ድል ለሀገራችን🇪🇹❤️ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ በ18ኛው የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ4ኛ ቀን ውድድር ዛሬ ይካሄዳል። የሀገራችን ልጆች የሚካፈሉበት ውድድር የሚከተሉት ናቸው። 🏟️ በማራቶን የሴቶች ፍፃሜ ፦ 🇪🇹 ጎይቶቶም ገ/ስላሴ 🇪🇹 አባበል የሻነህ 🇪🇹 አሸቴ በክሬ (ሰዓት - ቀን 10:15) 🏟️ 3,000 ሜትር መሰናክል የወንዶች ፍፃሜ ፦ 🇪🇹 ለሜቻ ግርማ 🇪🇹 ሀይለማርያም አማረ 🇪🇹 ጌትነት ዋለ (ሰዓት - ለሊት 11:20)…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

የትላንቱን የወንዶቹን ማራቶን ድል ለመድገም ቆርጦ የተነሳው የሴቶቹ የማራቶን ቡድናችን !

👉 ቡድናችን አስተማማኝ ሁኔታ ላይ ነው ያለው !

🇪🇹 በ2021 እና በ2022 ውድድር ላይ ምርጥ ብቃት አሳይታ ማለትም በበርሊን 2021 ማራቶን 1ኛ በ2022 የቶኪዮ ማራቶን 3ኛ የወጣችው በሁለቱ አመት ባስመዘገበች ውጤት በወርልድ ራንኪንግ ደረጃዋ ከአለማችን በ5ኛ ደረጃ የተቀመጠችው የኢትዮኤሌክትሪክ አትሌት የሆነችው ጎይቶቶም ገ/ስላሴን፤

🇪🇹 የ2021 ለንደን ማራቶን 3ኛ በ2022 ቶኪዮ 2ኛ የሆነችው በወርልድ ራንኪንግ ደረጃዋ 6ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው የኦሮሚያ ፖሊስ ክለብ አትሌት የሆነችው አሸቴ በከሪ፤

🇪🇹 በ2021 የኒዎርክ ማራቶን 3ኛ ፡ በ2022 የቦስተን ማራቶን 2ኛ የወጣችው በአለም አቀፍ ደረጃዋ በ12ኛ ደረጃ የተቀመጠችው የአማራ ፖሊስ ክለብ አትሌት የሆነችው አባበል የሻነውን እና ከተላይ የተዘረዘሩትን ሁለቱን አትሌቶች ኢትዮጵያ በ18ኛው የአለም አትሌትክስ ሻምፒዮና ታሰልፋለች።

ኢትዮጵያኖቹ አትሌቶች በምርጥ ብቃትና አቋም ላይ ይገኛሉ፤ የቅርብ ተፎካካሪያችን ኬኒያም በወንዶች ማራቶን ስለተሸነፉ በዚህኛው ውድድር ለማሸነፍ ይገዳደራሉ ተብሎ ይታሰባል፤ ውድድሩ ከረር ያለ እንደሚሆን ይጠበቃል።

የሀገራችን ልጆች በአሁን ሰዓት ያሉበትን የወቅቱ ብቃት ከፍ ያለ ነው። ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳሊያ ከምትጠብቅባቸው አንዱ ይኸው የሴቶች ማራቶን ውድድር ነው።

(ውድድሩ ቀን 10:15 ይጀምራል)

ድል ለሀገራችን 🇪🇹 !

#ከEthioRunner የተወሰደ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮጵያ🇪🇹 የትላንቱን የወንዶቹን ማራቶን ድል ለመድገም ቆርጦ የተነሳው የሴቶቹ የማራቶን ቡድናችን ! 👉 ቡድናችን አስተማማኝ ሁኔታ ላይ ነው ያለው ! 🇪🇹 በ2021 እና በ2022 ውድድር ላይ ምርጥ ብቃት አሳይታ ማለትም በበርሊን 2021 ማራቶን 1ኛ በ2022 የቶኪዮ ማራቶን 3ኛ የወጣችው በሁለቱ አመት ባስመዘገበች ውጤት በወርልድ ራንኪንግ ደረጃዋ ከአለማችን በ5ኛ ደረጃ የተቀመጠችው የኢትዮኤሌክትሪክ…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

የሴቶች ማራቶን እየተካሄደ ሲሆን 8 አትሌቶች ሌሎችን ቆርጠው በመውጣት የፊት መስመሩን ተቆጣጥረውት ወደፊት እየገሰሰጉ ይገኛሉ።

ከስምንቱ አትሌቶች 3ቱ የሀገራችን 🇪🇹 ልጆች ናቸው።

🇪🇹 ጎይቶቶም ገ/ስላሴ
🇪🇹 አባብል የሻነ
🇪🇹 አሼቴ በክሬ

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹❤️ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ኢትዮጵያ🇪🇹 የሴቶች ማራቶን ውድድር ቀጥሏል። ቅድም በፊት መስመር ስምንት የነበሩት አትሌቶች አሁን 3 ቀርተዋል። ከሶስቱ ሁለቱ የሀገራችን 🇪🇹 ልጆች ናቸው። 🇪🇹 ጎይቶቶም ገ/ስላሴ 🇪🇹 አባብል የሻነ አንዷ የኬንያ አትሌት ናት። @tikvahethiopia
#Update #ኢትዮጵያ🇪🇹

የሴቶች ማራቶን ውድድር ቀጥሏል።

በፊት መስመር ያሉት አትሌቶች አሁን 4 ሆነዋል።

አንድ ወደኃላ ቀርታ የነበረች የኬንያ አትሌት የፊት መስመሩን ተቀላቅላለች።

ከአራቱ ሁለቱ የሀገራችን 🇪🇹 ልጆች ናቸው።

🇪🇹 ጎይቶቶም ገ/ስላሴ
🇪🇹 አባብል የሻነ

ሁለቱ የኬንያ አትሌት ናቸው።

በኢትዮጵያ እና ኬንያ መካከል ከፍተኛ ፉክክር ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹❤️ !

@tikvahethiopia