TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#አቶ_ተወልደ_ገብረማርያም

አቶ ተወልደ ገ/ማርያም የህይወት ዘመን ሽልማት ተበረከተላቸው።

የቀድሞ የኢትዮጲያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ ላሳዩት የላቀ አመራር ፍላይት ግሎባል የተሰኘ የእንግሊዝ ኩባንያ የህይወት ዘመን ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

ፍላይት ግሎባል " ኤርላይን ቢዝነስ " የተሰኘ ዓለምአቀፍ የአቪዬሽን መጽሔት አሳታሚ ኩባንያ ሲሆን እ.ኤ.አ 2002 ዓ.ም ጀምሮ " ኤርላይን ስትራቴጂ አዋርድ " በየአመቱ በማዘጋጀት ለአየር ትራንስፖርት ዘርፍ የላቀ አስተዋጽኦ ላደረጉ ግለሰቦች እና ኩባንያዎች እውቅና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡

አቶ ተወልደ የተዘጋጀላቸውን ሽልማት እሑድ ሐምሌ 11 ቀን 2014 ዓ.ም ለንደን በተዘጋጀው የሽልማት ፕሮግራም ላይ በመታደም ተቀብለዋል፡፡

አቶ ተወልደ እውቅናውን በማግኘታቸው ደስ እንደተሰኙ ገልፀው በአገልግሎት ዘመናቸው አብረው ለደከሙ ሁሉ ባልደረቦቻቸው ምስጋና አቅርበዋል።

ፍላይት ግሎባል ባወጣው መግለጫ አቶ ተወልደ ገ/ማርያም የተሸለሙት የኢትዮጵያ አየርመንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ ሆነው ባገለገሉባቸው 11 አመታት ላሳዩት የረጅም ጊዜ መርሀ ግብር እቅድ ዝግጅት እና ቀውስን የመቆጣጠር ክህሎት እውቅና ለመስጠት እንደሆነ አስታውቋል፡፡

በእርሳቸው አመራር አየርመንገዱ በአራት እጥፍ ማደጉን ፍላይት ግሎባል ጠቅሷል፡፡

የኢትዮጲያ አየርመንገድ የአውሮፕላን ብዛት ከ33 ወደ 130 ፤ የመንገደኞች ቁጥር ከ3 ሚሊዮን ወደ 12 ሚሊዮን እንዳደገ ኩባንያው ጠቁሟል፡፡

አቶ ተወልደ አየርመንገዱን ለ37 አመታት ካገለገሉ በኋላ ባለፈው የካቲት ወር ከጤና ጋር በተያያዘ ከሃላፊነታቸው መልቀቃቸው ይታወሳል፡፡

መረጃው የኢትዮ ንግድና ኢንቨስትመንት መድረክ ነው።

@tikvahethiopia