TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
• " የረሃብ አደጋው ስጋት ተቀልብሷል " - የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP)

• " የረሃብ አደጋ ተቀልብሷል የሚለው አባባል ኃላፊነት የጎደለው ነው " - አቶ ጌታቸው ረዳ

ባለፈው ዓመት የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ በትግራይ ክልል አንዣቦ የነበረው የረሃብ አደጋ ስጋት መቀልበሱ የዓለም ምግብ ፕሮግራም ገለጸ።

የዓለም የምግብ ፕሮግራም ይህን ያለው በትግራይ ክልል ለሚገኙ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ መቻሉን ተከትሎ ነው።

የዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ከፍተኛ ኃላፊ ኤድሪያን ቫንዳክናብ ለቢቢሲ ከተናግሩት ፦

" የሰብዓዊ እርዳታ ማድረስ በመቻሉ፤ በትግራይ ክልል ተከስቶ የረሃብ አደጋው ስጋት ተቀልብሷል።

ይህ ማለት ግን ሁኔታዎች በዚህ ሁኔታ ይቀጥላሉ ማለት አይደለም።

አሁን ያለልው ሁኔታ እንዲቀጥል ለሰብዓዊነት ሲባል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት የሰብዓዊ እርዳታ ትግራይ እንዲደርስ ስላስቻለን፤ ይህ መቀጠል አለበት።

ለ2.1 ሚሊዮን ሰዎች ምግብ ለማድረስ ታቅዶ ለ1.1 ሚሊዮን ሰዎች ደርሷል።

ጥሩ እና መጥፎ ዜናዎች አሉ። ጥሩ ነገሩ፤ ለሰብዓዊነት ሲባል የተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት እየተከበረ ነው። ይህም የዓለም ምግብ ፕሮግራም እርዳታ ለሚያሻቸው ሰዎች ምግብ እና መሠረታዊ ቁሶችን ማድረስ አስችሏል።

የፀጥታ ሁኔታ፣ የተጨማሪ ፈንድ ጉዳይ እና የነዳጅ አቅርቦት ግን በእርዳታ አቅርቦት ሥራው ላይ አሳሳቢ ሆነው ቀጥለዋል። "

ተጨማሪ ያንብቡ : telegra.ph/WFP-07-16

የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ WFP በራሱ በመጋዘኑ ያለውን ድጋፍ በነዳጅ እጥረት ችግር ላይ ላሉ ለማድረስ መቸገሩን ይቀበለዋል ፤ የረሃብ አደጋን መቀልበስ ተችሏል የሚለው አባባል ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲሉ መልሰዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#Update

ጋዜጠኛ አላዛር ተረፈ ከታሰረ 3ኛ ቀኑን እንደያዘ ባለደረቦቹ ገልፀዋል።

" ወለጋ ላይ አማራ ተጨፍጭፏል የሚል ጹሑፍ ጽፈሃል፤ የስሪላንካን አመጽ ደግፈሃል፤ ችግኝ ተከላን ተቃውመሃል " በሚል የተጠረጠረው አላዛር ተረፈ ከታሰረ 3ኛ ቀኑን ይዟል።

ሀሙስ ዕለት ለጥያቄ እንፈልግሃለን የሚሉ ሁለት ክትትሎች ይዘውት ወደ ላምበረት ፖሊስ ጣቢያ ወስደውት ነበር።

በኋላም ቀበና ፍ/ቤት ቀርቦ በ5 ሺ ብር ዋስትና እንዲለቀቅ ቢወሰንም ፖሊስ ይግባኝ ጠይቆ ነበር።

ፖሊስ የጠየቀው ይግባኝ ውድቅ ተደርጎ በ5ሺ ብር ዋስትና እንዲወጣ የተወሰነው ውሳኔ ጸንቶ ነበር።

በመጨረሻም ጣቢያው እኛ ጋር ያለው ጉዳይ አልቋል ክ/ከተማ ግን ይፈልገዋል በሚል ክፍለ ከተማ ካደረ በኋላ 3ኛ ተወስዷል።

የስራ ባልደረቦቹ ፤ " በሚያሳዝን ሁኔታ ፍ/ቤት ከእስር እንዲለቀቅ የፈረደለትን ጋዜጠኛ ነው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የወሰዱት " ብለዋል።

በቀን ሁለት ጊዜ ፍ/ቤት ቀርቦ የነበረው ጋዜጠኛው ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጭ ከፖሊስ ጣቢያ ፖሊስ ጣቢያ እየተንከራተተ ነው ሊሉም ገልፀዋል።

" የፍ/ቤት ውሳኔ ሙሉ በሙሉ እየተሻረ ነው " ያሉቱ የስራ ባልደረቦቹ " አሁን ደግሞ ቤቱ ተፈትሾ ምንም አልተገኘም። ከዛም ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንደሚሄድና እዛው እንደሚቆይ ነው የተነገረው " ሲሉ ያለውን ሁኔታ አስረድተዋል።

ጋዜጠኛ አልዓዛር የተባባሩት አረብ ኤሜሬትስ ሚዲያ የሆነው " አል አይን " የኢትዮጵያ የአማርኛ አገልግሎት ዘጋቢ ነው።

@tikvahethiopia
አይቀሬው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት እና የግብፆቹ ሚዲያዎች የፈጠራ ወሬ !

ሁሌ ጊዜም ሀገራችን የታላቁ ህዳሴውን ግድብ ባፋጠነች እና የውሃ ሙሌቱን በየዓመቱ ባከታተለች ቁጥር የግብፅ ሚዲያዎች እንቅልፍ ይነሳቸዋል።

በቅርቡ የሶስተኛው ሙሌት መጠናቀቅ አይቀሬ መሆኑን ሲያውቁ ከወዲህ ያልተረጋገጠ መረጃ ለህዝብ ማሰራጨቱን አጥብቀው ተያይዘውታል።

አመር አዲብ የተባለ የሚዲያ ሰው በአንድ ቻናል ላይ ቀርቦ " በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ብዙ እምነት የለንም በግድቡ ላይ መሰነጣጠቆች እንዳሉ እና አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይነገራል " ሲል ያልተረጋገጠ መረጃ ሲናገር ተደምጧል።

" የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ አብዛኛው ሰው ረስቶታል። የህዳሴው ግድብ ሶስተኛው ሙሌት ሊጠናቀቅ ቀናት ቀርተዋል " ሲልም አክሏል።

የዚህን ሰው ንግግር ሚዲያዎች እየተቀባበሉት እያስጮኹ ነው ፤ በእርግጥ የግብፅ ጋዜጠኞች እና ሚዲያዎች ፣ ምሁራን ከዚህም አለፍ ያሉ ብዙ የፈጠራ ወሬዎችን ሲያስወሩ ዓመታትን ያለፉ በሚሆንም በግንባታው ላይ ያመጡት ለውጥ የለም።

አሁንም ሶስተኛው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌት መጠናቀቅ አይቀሬ መሆኑን ሲያውቁ የሚዲያ ዘመቻውን ተያይዘውታል።

#ItsMyDam🇪🇹

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

በ18ኛው የ #ኦሬገን አለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ2ኛ ቀን ውድድር ዛሬ ይካሄዳል። የሀገራችን ልጆች የሚካፈሉበት ውድድር የሚከተሉት ናቸው።

🏟️ 3,000 ሜ መሠ. ሴቶች ማጣሪያ ፦

🇪🇹 ሲምቦ አለማየው
🇪🇹 መቅደስ አበበ
🇪🇹 ወርቅውሃ ጌታቸው

(ሰዓት - ምሽት 2:35)

🏟️10,000 ሜ ሴቶች #ፍፃሜ

🇪🇹 ቦሰና ሙላቴ
🇪🇹 እጅጋየሁ ታዬ
🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ

(ሰዓት - ምሽት 4:20)

🏟️ 1,500 ሜ ወንዶች ማጣሪያ ፦

🇪🇹 ሳሙኤል አባተ
🇪🇹 ሳሙኤል ተፈራ
🇪🇹 ታደሰ ለሚ

(ሰዓት - ለሊት 10:30)

🏟️ 1,500 ሜ ሴቶች ግማሽ ፍፃሜ ፦

🇪🇹 ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 ፍሬወይኒ ኃይሉ
🇪🇹 ሂሩት መሸሻ

(ሰዓት - ለሊት 11:05)

ድል ለሀገራችን ኢትዮጵያ ❤️ !

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዝርፊያ የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ዜጎች በተለያየ ጊዜ ዘረፋን ጨምሮ እስከ ግድያ የሚደረስ ወንጀል ይፈፀምባቸዋል። ከዚህ ቀደም ተደጋጋሚ የወንጀል ድርጊት ሲፈፀም ሰምተናል። ከሰሞኑን አንድ በዚሁ በኤሌክቶኒክ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ሚሰራ ሰራተኛ ዝርፊያ እንደተፈፀመበት አመክቷል። ስሙ ሚኪያስ ተፈሪ የተባለው ወንድማችን ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚሰራባትን መኪና…
የመኪና ዝርፊያ !

ከጥቂት ቀናት በፊት በአዲስ አበባ ከተማ የኤሌክትሮኒክ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ወገኖች ላይ የሚፈፀመው ዝርፊያ አሳሳቢ መሆኑን አመልክተን ነበር።

በወቅቱ አንድ የቤተሰባችን አባል ራሱንና ቤተሰቡን ለማስተዳደር የሚሰራባትን መኪና ዘራፊዎች በስለት አስፈራርተውት እንደዘረፉት መግለፁ አይዘነጋም።

ትናንት አርብ ምሽት 4:00 ላይ ደግሞ ሌላ አንድ ወንድማችን ከፍየል ቤት ወደ ሀያሁለት ከመገድ ላይ ሰው ጭኖ አውራሪስ አካባቢ ሲደርስ አንገቱን አንቀው እራሱን እንዲስት በማድረግ ከመኪናው አሰወጥተው በመወርወር መኪናውን ይዘው ተሰውረዋል።

ትላንት የተዘረፈው መኪና Silver Toyota Vitz የታርጋ ቁጥር B05107 ሲሆን መኪናው የተሰረቀበት ወንድም ይህንን መኪና ያየ በዚህ ስልክ ቁጥር 0972203638 \ 0931719404 እንዲያሳውቁት ተማፅኗል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ በ18ኛው የ #ኦሬገን አለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና የ2ኛ ቀን ውድድር ዛሬ ይካሄዳል። የሀገራችን ልጆች የሚካፈሉበት ውድድር የሚከተሉት ናቸው። 🏟️ 3,000 ሜ መሠ. ሴቶች ማጣሪያ ፦ 🇪🇹 ሲምቦ አለማየው 🇪🇹 መቅደስ አበበ 🇪🇹 ወርቅውሃ ጌታቸው (ሰዓት - ምሽት 2:35) 🏟️10,000 ሜ ሴቶች #ፍፃሜ ፦ 🇪🇹 ቦሰና ሙላቴ 🇪🇹 እጅጋየሁ ታዬ 🇪🇹 ለተሰንበት ግደይ (ሰዓት - ምሽት…
#ኢትዮጵያ🇪🇹

በአሁን ሰዓት የሴቶች 10 ሺ ሜትር ፍፃሜ ውድድር እየተካሄደ ይገኛል።

🇪🇹 ለተሰበንት ግደይ
🇪🇹 እጅጋየሁ ታዬ
🇪🇹 ቦሰና ሙላት ሀገራችንን ባለድል ለማድረግ ከፍተኛ ፉክክር እያደረጉ ይገኛሉ።

13 ዙር ይቀራል።

ውድድሩን በDSTV ልዩ ቻናል እንዲሁም በብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ መዝናኛው ቻናል እንዲሁም በዩትዩብ KBC ቻናል ላይ በቀጥታ መከታተል ይቻላል።

More : @tikvahethsport

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ለተሰንበት ወርቅቅቅ !!!
ለተሰንበት ግደይ ወርቅ !!!

በሴቶች 10 ሺ ሜትር ለተሰንበት ግደይ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያ የወርቅ ሜዳሊያ አስገኝታለች።

እንኳን ደስ አለን 🇪🇹❤️ !!

@tikvahethiopia