አይቀሬው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሶስተኛ ዙር የውሃ ሙሌት እና የግብፆቹ ሚዲያዎች የፈጠራ ወሬ !

ሁሌ ጊዜም ሀገራችን የታላቁ ህዳሴውን ግድብ ባፋጠነች እና የውሃ ሙሌቱን በየዓመቱ ባከታተለች ቁጥር የግብፅ ሚዲያዎች እንቅልፍ ይነሳቸዋል።

በቅርቡ የሶስተኛው ሙሌት መጠናቀቅ አይቀሬ መሆኑን ሲያውቁ ከወዲህ ያልተረጋገጠ መረጃ ለህዝብ ማሰራጨቱን አጥብቀው ተያይዘውታል።

አመር አዲብ የተባለ የሚዲያ ሰው በአንድ ቻናል ላይ ቀርቦ " በኢትዮጵያ ኢንደስትሪ ብዙ እምነት የለንም በግድቡ ላይ መሰነጣጠቆች እንዳሉ እና አደጋዎች ሊከሰቱ እንደሚችሉ ይነገራል " ሲል ያልተረጋገጠ መረጃ ሲናገር ተደምጧል።

" የህዳሴውን ግድብ ጉዳይ አብዛኛው ሰው ረስቶታል። የህዳሴው ግድብ ሶስተኛው ሙሌት ሊጠናቀቅ ቀናት ቀርተዋል " ሲልም አክሏል።

የዚህን ሰው ንግግር ሚዲያዎች እየተቀባበሉት እያስጮኹ ነው ፤ በእርግጥ የግብፅ ጋዜጠኞች እና ሚዲያዎች ፣ ምሁራን ከዚህም አለፍ ያሉ ብዙ የፈጠራ ወሬዎችን ሲያስወሩ ዓመታትን ያለፉ በሚሆንም በግንባታው ላይ ያመጡት ለውጥ የለም።

አሁንም ሶስተኛው የታላቁ የህዳሴ ግድብ ሙሌት መጠናቀቅ አይቀሬ መሆኑን ሲያውቁ የሚዲያ ዘመቻውን ተያይዘውታል።

#ItsMyDam🇪🇹

@tikvahethiopia