TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHO_SUDAN

ኢትዮጵያ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ በተከሰተ ግጭት በጠፋው የሰው ህይወት ማዘኗን ገለፀች።


ጎረቤት ሃገር ሱዳን በኢትዮጵያ ጦር 7 ወታደሮቿ እና 1 ሲቪል እንደተገደለባት ክስ አሰምታለች። ግድያው በዚህ ወር አጋማሽ የተፈፀመ ነው ብላለች።

በዚህም ለተመድ ፀጥታ ም/ቤትና ለሌሎች አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተቋም ክስ አቅርባለሁ ብላለች።

በተጨማሪ ቁጣዋን ለመግለፅ በአዲስ አበባ የሚገኙትን መልዕክተኛዋን ወደ  ካርቱም ጠርታለች፣ በአገሯ የሚገኙትን የኢትዮጵያ አምባሳደርም ጠርታ ማብራሪያ እንዲሰጡ ብላለች።

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጉዳዩን በተመለከተ ባወጣው መግለጫ፣ ግጭት የተከሰተው በህወሓት ድጋፍ የኢትዮጵያን ድንበርን አልፈው በገቡ የሱዳን መደበኛ ወታደሮች መሆኑን ገልጿል።

በሱዳን ሠራዊትና በአካባቢው ሚሊሻዎች መካከል በተከሰተው በዚህ ግጭት በጠፋው ህይወት የኢትዮጵያ መንግሥት እንደሚያዝን ገልጾ ምርመራ እንደሚደረግም አመልክቷል።

ክስተቱ በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን የጠበቀ ግንኙነት ለማደናቀፍ ሆን ተብሎ የተቀነባበረ መሆኑን በማመልከት፣ የሱዳን መንግሥትም ሁኔታውን የበለጠ ከሚያባብስ እርምጃ እንደሚቆጠብ አሳስቧል።

በሌላ በኩል ደግሞ፥ ሱዳኖቹ በአማራ ክልል ምእራብ ጎንደር ዞን አርማጭሆ ወረዳ “ገላል ውሀ” የተባለ አካባቢን በከባድ መሳሪያ ሲደበድቡ ውለዋል።

ጥቃቱ ካለፈው ሰኔ 15 ጀምሮ አልፎ አልፎ የነበረ ሲሆን ታጣቂዎቹ ተመትተው ከአካባቢው ከተባረሩ በኋላ እንደገና ዛሬ ከጠዋቱ ከ2 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት የከፋ ጉዳት ባይደርስም ጥቃት መሰንዘራቸውን ነዋሪዎች እንደገለፁ ዶቼቨለ ሬድዮ ዘግቧል።

ምንጭ፦ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ሮይተርስ፣ ዴቼቨለ እና ቢቢሲ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" ህግ ይከበር ፤ ፍትህ ይሰጠን " ለማስፋፊያ ስራ ተብሎ #ህግን_ባልተከተለ መልኩ ቤታችን ፈረሰብን ያሉ በአዲስ አበባ ከተማ ፤ ገርጂ ኮርያ ሆስፒታል አካባቢ የሚገኙ ነዋሪዎች ቅሬታ አቅርበዋል። ያሉበት ቦታ ለማስፋፊያ ስራ ይፈለጋል የተባሉ ዜጎች ለማስፋፊያ አንደሚፈለግ ያወቁት ሰኔ 29/2013 ዓ/ም አንደሆነ ከዛ በፊት ስለጉዳዩ ምንም እንደማያቁ / እንዳልተነገራቸው ፤ ጉዳዩን የሚያውቁት ከወረዳው…
#Update

• " ... ከመሬት ጋር በተያያዘ ከሳሽም ተከሳሽም ቤተክርስቲያኗ አይደለችም " - አዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን

• " የድሆችን የምስኪኖችን ቤት አስፈረሰ፤ አፈናቀለ የተባለው ፍፁም ሀሰት ከዚህም አለፈ ሲል የስም ማጥፋት ወንጀል ነው ጉዳዩን ወደ ህግ ወስጄዋለሁ " - አገልጋይ ዮናታን አክሊሉ

• " ቤቶችን ያፈረሱት የመንግስት ኃይሎች በኃይል ፣ በጉልበት እና ህግን ባልተከተለ መልኩ ነው። አሁንም ቢሆን ህግ ይከበር ነው እያልን ያለነው። የተበደሉት ሁሉ ፍትህ ያግኙ " - ነዋሪዎች

ከቀናት በፊት በአዲስ አበባ ፤ ገርጂ ኮርያ ሆስፒታል አካባቢ የሚኖሩ ነዋሪዎች ለማስፋፊያ በሚል ቤታቸው ህግን በጣሰ አካሄድ እንደፈረሰባቸው ቅሬታ ማቅረባቸው ይታወሳል።

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘ በማህበራዊ ሚዲያ ብዙ ሲባል ቆይቷል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ስሟ የተነሳው የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን ምላሽ እና ማብራሪያ ሰጥታለች።

የአዲስ ኪዳን ካህናት ቤተክርስቲያን የአምልኮ ቦታ ከመጠየቀ በዘለለ የዜጎችን ቤት እንዲፈርስ እንዳላደረገች ገልፃለች።

ቤተክርስቲያኗ የሰዎችን ቤት የማፍረስ እና አፍራሽ ግብረኃይልን የማዘዝ አንዳችም ስልጣን እንደሌላት ገልፃለች።

በተጨማሪም ፤ ቤተክርስቲያኗ ከመሬት ጋር በተያያዘ ከሳችም ተከሳሽም እንዳልሆነች፣ የወሰደችው ቦታ ሆነ ዶክመት እንደሌለ እና በቤተክርስቲያን እጅ የሚገኘው የካቢኔ ውሳኔ ብቻ መሆኑን አስገንዝባለች።

በዚህም የሰው ቤት እንዲፈርስ የምታዝበት መብትም ሆነ ስልጣን እንደሌላት ግልፅ አድርጋለች።

" መንግስት የወሰንኩላችሁ ቦታ ይሄ ነው ተረከቡና አምልኩ መብቱ ነው፣ ተገቢውን ቤት፣ ካሳ ሰጥቶ በህግ አግባብ ፣ በመመሪያ እና በአሰራር ማድረግ ያለበትን ማድረግ መብቱ ነው ቦታው ለቤተክርስቲያኗ አይገባም ማለትም መብቱ ነው፣ ወደ ሌላ ቦታ ሂዱ ማለት እንዲሁ የመንግስት መብት ነው ቤተክርስቲያኗ አንዳችም ነገር አያገባትም ፤ በመንግስት አሰራር ውስጥም ጣልቃ አልገባችም " ስትል አስገዝባለች።

አካሄዱ ትክክል ሆነ ስህተት ምንም እንደማያገባት ገልፅ አድርጋለች።

ቤተክርስቲያኗ ምንም ስለማይመለከታት በመንግሥት ጉዳይ እና ስራ ውስጥ ገብታ በዝርዝር ማብራራት እንደማይጠበቅባት ገልፃለች።

ያንብቡ ⬇️
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-06-27

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NewsAlert የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት #በሰላማዊ_መንገድ ለመፍታት ሰላማዊ ድርድሮች እንዲጀመሩ ገዢው ብልፅግና ፓርቲ አቅጣጫ አስቀመጠ። በሰሜኑ የሀገሪቱ ክፍል ላይ የተፈጠሩ ችግሮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ዉይይት በብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና በማእከላዊ ኮሚቴዉ መካሄዱን የፍትሕ ሚኒስትርና የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ አስታወቁ። ዶ/ር…
#Peace

የተደራዳሪ ቡድኑ !

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት #በሰላም_ድርድር እንዲፈታ ገዢው የብልፅግና ፓርቲ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወቃል።

በዚህም መሰረት በፌዴራል መንግሥት በኩል የሰላም ተደራዳሪ ቡድን መሰየሙ ተረጋግጧል።

የቡድኑ አባላት ፦

1ኛ. አቶ ደመቀ መኮንን ➡️ ሰብሳቢ
2ኛ. ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዎስ ➡️ አባል
3ኛ. አቶ ተመስገን ጥሩነህ ➡️ አባል
4ኛ. አምባሳደር ሀሰን አብዱልቃድር ➡️ አባል
5ኛ. አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ➡️ አባል
6ኛ. ሌ/ል ጀኔራል ብርሀኑ በቀለ ➡️ አባል
7ኛ. ዶ/ር ጌታቸው ጀምበር ➡️ አባል መሆናቸውን የኢፕድ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
" አሶሳ ሰላም ናት "

የቤንሺንጉል ጉሙዝ ክልል ፤ መዲና የሆነችው አሶሳ ሰላም መሆኗን እና ህብረተሰቡ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በመሰራጩ ሀሰተኛ መረጃዎች ሳይደናገጥ ለክልሉ ሰላም የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

ክልሉ አሶሳ ላይ የፀጥታ ችግር እንደተፈጠረ ተደርጎ መሰረተቢስ እና ሀሰተኛ መረጃ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እየተሰራጨ ነው ብሏል።

ነገር ግን ከተማይቱ ውስጥ አንዳችም የፀጥታ ችግር እንዳልተፈጠረና ፤ እንደ ወትሮ ሁሉ የከተማው ነዋሪ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

ነዋሪዎችም ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በሚሰራጩ ሀሰተኛ እና መሰረተቢስ መረጃዎች ሳይደናገጥ ለክልሉ ሰላም መረጋገጥ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጠይቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ጎረቤት ሱዳኖች የጦርነት ጉሰማ ላይ ናቸው !

የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር መጎብኛታቸው ተነግሯል።

ቡርሀን ትንሹ ፋሻጋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙት አል ዑስራ እና ዋድ ኮሊ አካባቢዎች የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር ነው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ/ም የጎበኙት፡፡

ጉብኝቱ ሱዳን ፤ "ምርኮኛ ወታደሮቼ በኢትዮጵያ ጦር ተገደሉብኝ " ማለቷን ተከትሎ የተካሄደ ነው፡፡ " የአጸፋ ምላሽንማ ሳንሰጥ አንቀርም " ስትልም ዝታ ነበር።

ጄነራል አልቡርሃን ፤ በጉብኝታቸው ጦሩ የሃገሩን ዳር ድንበር ለመጠበቅ የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ ቁርጠኛ ስለመሆናቸው ገልጸዋል፡፡

ለሃገራቸው ሲሉ መስዋዕትነትን የሚከፍሉ የጦሩ አባላት ደም "በከንቱ ፈስሶ" አይቀርም ሲሉም ዝተዋል። ሁኔታው ተጨባጭ መልስ እንደሚያገኝ ቃል በመግባት ከሰሞኑ በአል ዑስራ ያጋጠመው ፈጽሞ አይደገምም ብለዋል፡፡

በሱዳን መሬቶች ላይ ሚደረግ ምንም ዐይነት እንቅስቃሴ እንዳይኖር ሲሉም ትዕዛዝን አስተላልፈዋል፡፡

አል ፋሽቃ፤ ኢትዮጵያ እና ሱዳን የባለቤትነት ጥያቄ የሚያነሱበት ሰፊና ለም መሬት ሲሆን ኢትዮጵያ ጦርነት ላይ መሆኗን ተከትሎ ወደ አካባቢው ዘልቆ የገባው የሱዳን ጦር መሬቱን ይዞ ለቅቄ አልወጣም ብሏል።

ከዚህ አልፋ ሀገሪቱ መሰረተ ልማቶችን ለመገንባት ጥረት እያደረገች መሆኑን #አል_አይን_ኒውስ ዘግቧል።

ከሰሞኑን ፤ ሱዳን ሞቱብኝ ያለቻቸው ወታደሮች ፤ የኢትዮጵያን ድንበርን አልፈው የገቡና (ጠብ አጫሪዎች እራሳቸው ናቸው) ከአካባቢው ሚሊሻ ጋር ግጭት የፈጠሩ የሱዳን መደበኛ ወታደሮች ሲሆኑ ኢትዮጵያም በጠፋው የሰው ህይወት ማዘኗን መግለጿ ይታወቃል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ከእስር ተፈቷል። ዛሬ የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 2ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ማዘዙ ይታወሳል። ይኸው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ተከብሮ ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ከእስር መፈታቱን ጠበቃው ታደለ ገብረመድህን አረጋግጠዋል፡፡ @tikvahethiopia
" ዛሬ ጥዋት ሲቪል በለበሱ ሰዎች ነው ከመኖሪያ ቤቱ የተወሰደው " ጠበቃ ታደለ ገ/መድህን

ከጥቂት ቀን በፊት በዋስ ከእስር የተለቀቀው ጋዜጠኛ ያየሰው ሽመልስ ዛሬ በድጋሚ መታሰሩን ለማወቅ ተችሏል።

ጠበቃ ታደለ ገ/መድህን ፥ ዛሬ ጥዋት ከመኖሪያ ቤቱ ሲቪል የለበሱ የፀጥታ አካላት እንደወሰዱትና ወዴት እንደወሰዱት እንደማያውቁ ገልፀዋል፤ ያለበትን ቦታ ለማወቅም እያፈላለጉ መሆኑን አክለዋል።

በሌላ መረጃ ፦ ጋዜጠኛ በቃሉ አለምረው በ10 ሺህ ብር ዋስ ከእስር እንዲፈታ ፍርድ ቤት ወስኗል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጎረቤት ሱዳኖች የጦርነት ጉሰማ ላይ ናቸው ! የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር መጎብኛታቸው ተነግሯል። ቡርሀን ትንሹ ፋሻጋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙት አል ዑስራ እና ዋድ ኮሊ አካባቢዎች የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር ነው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ/ም የጎበኙት፡፡…
" የሱዳን ጦር የሚነዛው መረጃ መሰረተ ቢስ ነው " - የኢትዮጵያ 🇪🇹 ሀገር መከላከያ

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የምርኮኞችን አያያዝ ባልጠበቀ መንገድ ወታደሮቼን ገድሏል በሚል የሱዳን ጦር የሚነዛው መረጃ መሰረተ ቢስ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በቦታው እንዳልነበርና #የኢትዮጵያን_ግዛት_ዘልቆ የገባው የሱዳን ኃይል ከአካባቢው ሚሊሻዎች ጋር መጋጨቱ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ ፤ ሕወሓት ሰሜን ዕዝ ሰራዊት ላይ ጥቃት በፈፀመበት ወቅት የሱዳን ጦር በኢትዮጵያ ግዛት ላይ ወረራ መፈጸሙን አስታውሶ፤ ጦሩ በተለያየ ጊዜ ውስጣዊ ችግሮች ባጋጠሙ ቁጥር በኢትዮጵያ ላይ ትንኮሳዎችን ሲያደርግ መቆየቱን ገልጿል።

ሰሞኑ ደግሞ የሱዳን ኃይል ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ዘልቆ በመግባት በአካባቢው በነበሩ የኢትዮጵያ ሚሊሻዎች ላይ ጥቃት ማድረሱንና ከሁለቱም ወገን ጉዳት መድረሱን ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ገልጿል።

ነገር ግን የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት በስፍራው ባልነበረበት ሁኔታ " ምርኮኞችን ገደለ " በሚል የሱዳን ጦር ክስ ማቅረቡ ተቀባይነት የሌለውና መሰረተ ቢስ መሆኑ አስገንዝቧል።

የደረሰውን ጥቃት በተመለከተ ማጣራት የሚፈልግ አካል ካለ ከሁለቱ ሀገራት መከላከያ ሠራዊት ተወካዮች የተውጣጣ ኮሚቴ ተዋቅሮ እንዲጣራ ለመተባበር የኢትዮጵያ ሠራዊት ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሚኒስቴር አረጋግጧል።

#ENA

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጎረቤት ሱዳኖች የጦርነት ጉሰማ ላይ ናቸው ! የሱዳን ጦር አዛዥ እና የሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ከኢትዮጵያ ድንበር አቅራቢያ የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር መጎብኛታቸው ተነግሯል። ቡርሀን ትንሹ ፋሻጋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በሚገኙት አል ዑስራ እና ዋድ ኮሊ አካባቢዎች የሚገኘውን የሃገራቸውን ጦር ነው ዛሬ ሰኞ ሰኔ 20 ቀን 2014 ዓ/ም የጎበኙት፡፡…
ግብፅ ?

ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሳ ገብታ ከአካባቢ ሚለሻ ጋር ተጋጭታ ወታደሮቿን ካጣች በኃላ የኢትዮጵያ ጦር ወታደሮቼን ገደለብኝ ስትል ክስ አሰምታለች።

ኢትዮጵያ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንዲሁም በሀገር መከላከያ ሚነስቴር በኩል በሰጠችው ምላሽ በተፈጠረው ሁኔታ እና የሰው ህይወት በመጥፋቱ አዝናለሁ ነገር ግን ሱዳን እራሷ የፈፀመችውን ጠብ አጫሪ ትንኮሳ ወደ ኢትዮጵያ ማላከኳ ተቀባይነት የለውም በተጨማሪ መከላከያው ባልነበረበት የመከላከያውን ስም እያነሳች የምትነዛው ወሬ መሰረተ ቢስ ነው ስትል አስረግጣ ተናግራለች።

የሱዳንን በኢትዮጵያ ጦር ወታደሮቼ ተገደሉብኝን የሚለውን መሰረተ ቢስ ክስ ተከትሎ የግብፁ መሪ " በወታደሮቹ ሞት እጅጉን አዝኛለሁ " ሲሉ የሀዘን መልዕክት ለሱዳኖቹ ልከዋል።

የግብፁ ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታህ አልሲሲ ፤ በመልዕክታቸው በወታደሮቹ ሞት ልባዊ ሀዘን እንደተሰማቸው ለሱዳን ጦር አዛዥና ለሃገሪቱ ሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀመንበር ሌ/ጄ አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን እና ለሱዳን ህዝብ ስለመግለፃቸው ዴይሊ ኒውስ ኢጅብት ዘግቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#AddisAbaba : የላዳ ታክሲዎችን በአዲስ የመተካት ስራ በታያዘው ዓመት አጋማሽ ድረስ ለማጠናቀቅ እንደታሰበ የአ/አ ትራንስፖርት ቢሮ አሳውቋል። ረጅም አመታት በከተማው አገልግሎት የሰጡ ላዳ ታክሲዎች አሁን ላይ እርጅና ተጫጭኗቸው በገበያው ውስጥ ከመጡ ሌሎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች ጋር መወዳደር እየተሳናቸው ነው። ባለንብረቶቹ ችግሩን ለከተማው አስተዳደር በማሳወቅ የመፍትሄ ሃሳቦች ሲቀርቡ መቆየቱንም…
#ቅሬታ

በአዲስ አበባ ከተማ ፤ የላዳ ታክሲዎቻቸው በአዲስ እንደሚቀየርላቸው ቃል የተገባላቸው አሽከርካሪዎች እስከ አሁን ምላሽ አላገኙም።

መንግሥት ከኤል አውቶ መኪና አስመጭ ድርጅት ጋር በመነጋገር የላዳ ታክሲዎች በአዲስ እንደሚቀየርላቸው ተነግሯቸው የነበረ ቢሆንም፣ ምላሽ ማግኘት እንዳልቻሉ የላዳ ታክሲ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች ቅሬታ አሰምተዋል።

የላዳ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች 30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ ከባንክ ጋር በማገናኘት ክፍያውን ከፈጸሙ በኋላ አዲስ ታክሲ እንደሚሰጣቸው እና 70 በመቶውን በየወሩ እየሠሩ ከሚያገኙት ገቢ ላይ እንደሚከፍሉ ተነግሯቸው ነበር። ሆኖም የታዘዙትን ክፍያ ከመፈፀም ባለፈ ተግባራዊ የተደረገላቸው ነገር የለም።

አንድ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የኤል አውቶ መኪና አስመጪ ድርጅት ሰራተኛ፤ ድርጅቱ ለመቀየር የተስማማቸውን መኪኖች ለማስመጣት ሥራ የጀመረ ቢሆንም፣ ሥራ ከጀመረ በኋላ አዲስ መመሪያ እና ለውጥ በመውጣቱ በመንግሥት በኩል ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ የተፈቀዱ መኪኖች ታግደው ከወደብ ማውጣት እንዳልቻሉ ተናግረዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተነጋገሩ መሆኑን አስታውቀዋል።

የአዲስ አበባ የትራንስፖርት ቢሮ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር እፀገነት አበበ በበከላቸው ቢሮው የላዳ ታክሲ አገልግሎት ሰጪ አሽከርካሪዎች እና ታክሲ የሚያቀርቡ ድርጅቶችን የሚስማሙበትን ሂደት የመፍጠር ኃላፊነት ተወጥቷል ብለዋል።

ይህም አሽከርካሪዎች 30 በመቶ ቅድሚያ ክፍያ እንዲፈፅሙ እና 70 በመቶ እየሠሩ የሚከፍሉበትን ሂደት ተነጋግረው እንዲስማሙ የሚያስችል እድል እንደፈጠረ እና መስማማት ላይ መድረሳቸውን ኃላፊዋ ገልፀዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ (https://addismaleda.com/archives/29249)

@tikvahethiopia
#ቹ

በዓለም በስፋት (በተናጋሪ ብዛት) ከሚነገሩ ቋንቋዎች በአንደኝነት የሚቀመጠውን፣ የተባበሩት መንግስታት የስራ ቋንቋ የሆነውን፣ ቻይንኛ ቋንቋን ይማሩ!!

* ቻይንኛ እና ቻይንኛ ብቻ የሚማሩበት የከተማችን የቋንቋ ት/ቤት ነው፡፡
*ለተማሪዎች በክረምት ወቅት የሚሰጥ ልዩ ፕሮግራም አዘጋጅተናል።

አድራሻ፡
*ቦሌ፡ ፋንቱ ሱፐር ማርኬት አካባቢ፣ ሳይ ኬክ ቤት ያለበት ህንጻ፣ 1ኛ ፎቅ
*ስታድየም፡ ትንሸዋ ስታድየም ጀርባ፣ ናሽናል ታወር ፣ 3ኛ ፎቅ
*አያት 49 የአየር መንገድ ቤቶች ፊት ለፊት ማይ ፕላዛ ህንጻ፣ 1ኛ ፎቅ
ለበለጠ መረጃ በ 0947202020 ይደውሉ፡፡
TIKVAH-ETHIOPIA
#OromiaRegion ጊምቢ ወረዳ በርካታ ሰዎች ተገደሉ። በዛሬው ዕለት #በምዕራብ_ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ውስጥ በርካታ ንፁሃን በታጣቂዎች መገደላቸው ተሰምቷል። መልዕክታቸውን የላኩ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት በአካባቢው ይንቀሳቀሳል ያሉት የታጠቀ ቡድን ጥቃት ከፍቶ #በርካታ ሰዎች መገደለቸውን (ትክክለኛ ቁጥሩን ለማወቅ አዳጋች ነው) ታግተው የተወሰዱ መኖራቸውን እንዲሁም ነፍሳቸውን ለማትረፍ…
ሰኔ 11 በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ በተፈፀመው ጥቃት ከተገደሉት ንፁሃን ህፃናት በተጨማሪ ወላጆቻቸውን ተነጥቀው ወላጅ አልባ የሆኑ በርካታ ህፃናት ስለመኖራቸው የአካባቢው ነዋሪዎች ገልፀዋል።

40 ወላጅ አልባ ህፃናት መስጅድ ውስጥ እንደሚገኙ ተነግሯል።

በቶሌ ቀበሌ ቢላል መስጂድ ውስጥ የሚያገለግሉት ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ ኢማም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፥ " ወላጅ አልባ ሆነው የተቀመጡት ከ2 ዓመት እስከ 5 ዓመት ያሉ ናቸው። እስከ አርባ ይደርሳሉ " ብለዋል።

" ምንም የሚበላ ነገር የለም " ያሉት ኢማሙ በራሳቸው አልሚ ምግብ ለመስጠት መጣራቸውን በኃላም ቀይ መስቀል መጥቶ ትንሽ ነገር መስጠቱን ነገር ግን ሊዳረስ አለመቻሉን አስረድተዋል።

አንድ ስሙ እንዲገለፅ ያልፈለገ ሌላ የአከባቢው ነዋሪ ፥ " ሁለቱንም ወላጆቻቸውን በሞት ያጡና ወላጆቻቸው የት እንዳሉ የማይታወቅ ተበትነው ያሉ ህፃናት ቁጥር በመቶዎች የሚቆጠር መሆኑን ገልፀው ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚያደርጉ ድርጅቶች ጥሪ አቅርበዋል።

" እናታቸው አምስት ልጆች አባትም እናትም የሌላቸው አውቃለሁ። የጁምአ ቀን ተወልዳ ቅዳሜ እናቷ የተገደለችባት ህፃንም አለች "

ወላጆቻቸውን ካጣቱ በተጨማሪ አካለ ጎደሎ የሆኑ መኖራቸውን የገለፁት ነዋሪው በቂ ድጋፍ እየተደረገ እንዳልሆነና ጎረቤቶቻቸው እየተንከባከቧቸው መሆኑን ገልጿል።

የህክምናም ችግር አለ መቶ በመቶ የሚንከባከባቸው ሰው የለም ሲል አክሏል። ከ11 ቀን ጨቅላ እስከ 12 ዓመት እድሜ ያላቸው ህፃናት ሰብሳቢ ማጣታቸውን የገለፁት እኚሁ ነዋሪ አንዳንዶቹ ለከፋ የሰነልቦና ችግር መጋለጣቸውን ጠቁሟል።

ብሬል፣ ድሽቃ ሲተኮስባቸው የቆዩ ህፃናት አንዳንዶቹ በድንጋጤ ምክንያት መታመማቸውን፤ የማይናገሩ ህፃናትም፤ አንዳንዶቹ ብቻቸውን የሚያወሩም መኖራቸውን ለቪኦኤ ተናግሯል።

@tikvahethiopia
#እንዲያውቁት

የሎተሪ እጣ ከወንጀል ለተገኘ ሀብት መደበቂያ እየዋለ ነው።

በህገወጥ ሰዎች ዝውውር፣ በህገወጥ ምንዛሬ፣ በሙስና፣ በኢንቨስትመንት ማጭበርበር፣ በታክስ ማጭበርበርና ምዝበራ ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብት ወንጀለኞች ያፈራሉ። በህገወጥ መልኩ ያፈሩትን ሀብትም ህጋዊ መልክ ለማላበስ ብዙ መላዎችን ይጠቀማሉ።

ከእነዚህ መላዎች አንዱ የሎተሪ እድለኞችን መጠቀም እንደሆነ ያውቃሉ?

አዎ! ወንጀለኞች የሎተሪ እድል አሸናፊዎችን ወይም እድለኞችን ተከታትለው ያገኛሉ፡፡ አሸናፊ የሚያደርገውን የሎተሪ እጣ ትኬት እጣው ከሚያስገኘው ገንዘብ በላይ ዋጋ በመክፈል ከባለ እድሉ ትኬቱን ይገዛሉ፡፡ የእጣው አሸናፊ ማግኘት ከሚገባው በላይ ገንዘብ ስለሚያገኝም ይስማማል።

በዚህ ሂደት የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈጸም በርካታ ገንዘብ ያፈራው ግለሰብ ደግሞ የሎተሪ እድል አሸናፊ የሚያደርገውን የሎተሪ ትኬት በእጁ በማስገባት ህጋዊ የሎተሪ አሸናፊ በመምሰል ይቀርባል፡፡ በዚህም ወንጀለኛው የሎተሪ እድሉን በህገወጥ መንገድ ያገኘውን ገንዘብ ህጋዊ ለማስመሰል ይጠቀምበታል፡፡

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀሎችን ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 ላይ ማንም ሰው ገንዘቡ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የወንጀለኛውን ሀብት የደበቀ ወይም እንዲደብቅ የተባበረ በጽኑ እስራት እና በገንዘብ ይቀጣል፡፡

በመሆኑም የትክክለኛ የሎተሪ እጣ አሸናፊዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በዚህ መንገድ ወንጀለኞችን እንዳይተባበሩ እና ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ባለቤት እንይሆነ መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል ሲል የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ያሰራጨው መረጃ ያሳያል።

Via @tikvahethmagazine