TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#እንዲያውቁት

የሎተሪ እጣ ከወንጀል ለተገኘ ሀብት መደበቂያ እየዋለ ነው።

በህገወጥ ሰዎች ዝውውር፣ በህገወጥ ምንዛሬ፣ በሙስና፣ በኢንቨስትመንት ማጭበርበር፣ በታክስ ማጭበርበርና ምዝበራ ከፍተኛ መጠን ያለው ሀብት ወንጀለኞች ያፈራሉ። በህገወጥ መልኩ ያፈሩትን ሀብትም ህጋዊ መልክ ለማላበስ ብዙ መላዎችን ይጠቀማሉ።

ከእነዚህ መላዎች አንዱ የሎተሪ እድለኞችን መጠቀም እንደሆነ ያውቃሉ?

አዎ! ወንጀለኞች የሎተሪ እድል አሸናፊዎችን ወይም እድለኞችን ተከታትለው ያገኛሉ፡፡ አሸናፊ የሚያደርገውን የሎተሪ እጣ ትኬት እጣው ከሚያስገኘው ገንዘብ በላይ ዋጋ በመክፈል ከባለ እድሉ ትኬቱን ይገዛሉ፡፡ የእጣው አሸናፊ ማግኘት ከሚገባው በላይ ገንዘብ ስለሚያገኝም ይስማማል።

በዚህ ሂደት የተለያዩ ወንጀሎችን በመፈጸም በርካታ ገንዘብ ያፈራው ግለሰብ ደግሞ የሎተሪ እድል አሸናፊ የሚያደርገውን የሎተሪ ትኬት በእጁ በማስገባት ህጋዊ የሎተሪ አሸናፊ በመምሰል ይቀርባል፡፡ በዚህም ወንጀለኛው የሎተሪ እድሉን በህገወጥ መንገድ ያገኘውን ገንዘብ ህጋዊ ለማስመሰል ይጠቀምበታል፡፡

በወንጀል ድርጊት የተገኘ ገንዘብ ወይም ንብረት ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀሎችን ለመቆጣጠር በወጣው አዋጅ ቁጥር 780/2005 ላይ ማንም ሰው ገንዘቡ የወንጀል ፍሬ መሆኑን እያወቀ ወይም ማወቅ ሲገባው የወንጀለኛውን ሀብት የደበቀ ወይም እንዲደብቅ የተባበረ በጽኑ እስራት እና በገንዘብ ይቀጣል፡፡

በመሆኑም የትክክለኛ የሎተሪ እጣ አሸናፊዎች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በዚህ መንገድ ወንጀለኞችን እንዳይተባበሩ እና ምንጩ ያልታወቀ ሀብት ባለቤት እንይሆነ መጠንቀቅ ይኖርባቸዋል ሲል የፋይናንስ ደኅንነት አገልግሎት ያሰራጨው መረጃ ያሳያል።

Via @tikvahethmagazine