TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"ትግራይ ውስጥ ሰዎች በረሃብ እየሞቱ ነው" - ዴቪድ ባስሌ

በተባበሩት መንግስታት የዓለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ባስሌ በጦርነት በትግራይ ክልል ውስጥ ሰዎች በረሃብ #እየሞቱ መሆኑን በይፋዊ የትዊተር ገፃቸው ላይ አሳውቀዋል።

"ጊዜው እያለቀ ነው ያሉት" ባስሌ ፤ የሰብአዊ ድጋፍ ተደራሽነትን ከፍ ለማድረግ እና አደጋን ለመከላከል ያልተገደበ እቅስቃሴ ሊኖር ይገባል ሲሉ አሳስበዋል።

አሁኑኑ ሁሉም ወገኖች በዚህ ላይ ቁርጠኝነትን በማሳየት ጥሩ ውጤት ማምጣት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

ትላንትና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተ.መ.ድ) ዋና ጸሃፊ አንቶንዮ ጉተሬዝ በርካታ የኢትዮጵያ ትግራይ ክልል አካባቢዎች ረሃብ አፋፍ ላይ መሆናቸውን መገራቸውን ይታወሳል።

@tivahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ቪድዮ : በሰሜን ኢትዮጵያ ያለው ግጭት የጤና መሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል፡፡

በአማራ ክልል የደብረ ዘቢጥ ጤና ጣቢያ በደረሰበት ጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት አቁሟል፡፡ በዚህም ህሙማን በህክምና እና መድኃኒት እጥረት #እየሞቱ ይገኛሉ፡፡

የህክምና መሰረተ ልማቶች እና ባለሞያዎች የጦርነት ኢላማ መሆን የለባቸውም፡፡

#ICRCEthiopia

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ዋግኽምራ " ድርቁ በጣም እየባሰ ነው። መታከም ያለባቸው ህፃናት ለተከታታይ 2 ወራት ምንም አልተደረገላቸውም" - ዋግኽምራ ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ በአማራ ክልል የዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ጤና መምሪያ ቢሮ ኃላፊ አቶ አሰፋ ነጋሽ በዞኑ ስላሉ አሳሳቢ ጉዳዮች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ምን አሉ ? - ድርቁ በጣም #እየባሰ ነው። ባለፈው ጥናት ካጠናን በኋላ ሊደረግ የሚገባው ግን ያልተደረገ በጣም በስፋት…
#አማራ #ዋግኽምራ

በአማራ ክልል በዋግኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን ሰሃላ ሰየምትን ጨምሮ ድርቅ በተከሰተባቸው ሌሎችም ወረዳዎች ላይ እንስሳት በመኖ እጥረት #እየሞቱ ፣ አካባቢያቸውን ለቀው #እየተፈናቀሉ መሆኑን አስተዳደሩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጧል።

የአስተዳደሩ አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረት መላኩ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፣ ከ10,000 በላይ የተለያዬ እንስሳት በውሃና በመኖ እጥረት ሞተዋል።

በአበርገሌ፣ በሮቢና፣ በበለቃ በላይኛው ተከዜ ተፋሰስ በተለይ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ ነጻ ያልወጡ፣ መንግሥት የማይቆጣጠራቸው ቀበሌዎች ላይ ሰፋ ያለ ችግር እንዳለ ገልጸዋል።

በአሁኑ ወቅት በአጠቃላይ በድርቁ ቀጥተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ያሉ እንስሳትን በሚመለከት ኃላፊው ፤ በሦስቱም ወረዳዎች ፦
* ሰሃላ ሰየምት፣
* ዝቋላ፣
* አበርገሌ በጣም የቅድሚያ ቅድሚያ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብለው የለተለዩ ወደ 791,000 አካባቢ እንደሆኑ አስረድተዋል።

ከ791,000ዎቹ ውስጥ በተለይ ሰሃላ ሰየምት ወረዳ ላይ ያሉት ክርቲካሊ የዕለትም አቅርቦት ስላጡ 171,000 ወደ ደሃና ወረዳ ተፈናቅለው እንዲሄዱና ተጠግተው ለጊዜው እንዲቆዩ መደረጉን ተናግረዋል።

" ይህን ይህል ተፈናቅሎ ከሄደ ቀሪው 620,000 ደግሞ ከዚያው #እየተላወሰ ነው ያለው " ሲሉ አክለዋል።

ያንብቡ👇
https://telegra.ph/Tikvah-Ethiopia-01-24

@tikvahethiopia