TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ETHIOPIA

በሃገራችን የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር የፊታችን እሁድ ይካሄዳል !

በመጪው እሁድ ሰኔ 5/2014 በአዲስ አበባ ስቲዲዮም ለሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቁርዓን እና የአዛን ውድድር በርካታ እንግዶች እየገቡ ይገኛሉ።

ሀገራችን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስጠራው ይህ ውድድር ከ56 በላይ ሀገራት የሚወዳደሩበት ሲሆን ለውድድሩ ከፍተኛ ዝግጅት ሲካሄድ ቆይቷል ።

ውድድሩን በዘይድ እብን ሳቢት የቁርአን ማህበር አዘጋጅነትና በአገሪቱ ከሚገኙ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት እንዲሁም ታላላቅ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሚካሄድ ነው።

ውድድሩ በሦሥት ዘርፎች የሚካሄድ ሲሆን በአዛን በቁርአን ሒፍዝና በ30ጁዝዕ የድምጽ ውድድር ይካሔዳል።

እስካሁን ድረስ ባለው መረጃም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ተወዳዳሪዎች ዳኞች እንዲሁም ታዳሚዎች እንደገቡና እየገቡ መሆኑን ተገልጿል።

በዚህ ታላቅ ፕሮግራም ላይ ሁላችንም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ስታድየም በመገኘት የሃገራችንን ስም ከፍ አድርገን ለአለም ልናስተዋውቅ ይገባል።

ለበለጠ መረጃ
በዚህ ይደውሉ
0911755245
0911723051

#ኡስታዝ_አቡበከር_አህመድ

@tikvahethiopia
#ወላጆች_ለልጆች_ጥንቃቄ_እንዲያደርጉ_አሳስቧቸው !

ትናንትና በአዲስ አበባ ከተማ በጣለው ዝናብ አንድ ተማሪ በጎርፍ እንደተወሰደ ተሰምቷል።

የአዲስ አባባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ የኮሙኒኬሽን ተማሪው በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላዛሪስት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኑን አመልክቷል።

ተማሪው በጎርፍ የተወሰደው ትላንት 9 ሠዓት አካባቢ በጣለው ዝናብ መሆኑን የገለፀው ኮሚኒኬሽኑ በጎርፉ የተወሰደው ተማሪ በትምህርት መውጫ ሠዓት ላይ ከትንሽ ወንድሙ ጋር ወደ ቤት እየሄዱ እንደነበርም አስረድቷል።

እስከዛሬ ጠዋት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሠራተኞቹ ከኅብረተስቡ ጋር በመሆን ተማሪውን የመፈለጉን ሥራ ቀጥለዋል ተብሏል፡፡

ወላጆች በክረምቱ ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት ሲልኩ ሆነ ሲቀበሉ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉላቸው የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ማሳሰቡን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia
" በርካታ ንግዶች ችግር ውስጥ ገብተዋል "

በውጭ ምንዛሬ እጥረትና እጦት በርካታ ንግዶች ችግር ውስጥ መግባታቸው ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት " የውጭ ምንዛሬ እጥረት በንግድ ላይ ያሳደረው ተጽዕኖ " በሚል ርእስ ውይይት እያካሄደ ነው።

የአዲስ አበባ ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ም/ቤት ፕሬዝዳንት ወ/ሮ መሠንበት ሸንቁጤ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት በውጭ ምንዛሬ እጥረት እና እጦት ሳቢያ በርካታ ንግዶች ችግር ውስጥ ገብተዋል ።

በተለይም ፦

- የኮንስትራክሽን ፤
- የአስመጪና ላኪ
- የአገልግሎት ሠጪ ዘርፎች ክፉኛ የተጎዱ ናቸው ብለዋል።

እንደ ወ/ሮ መሠንበት ገለጻ የወጪ ንግድ እድገቱ በሚጠበቀው ልክ አለመሆን ፤ ቀጣይነት ያለው የንግድ ሚዛን አለመስፈን ፤ ህገወጥ ንግድ ፤ ደካማ የማክሮ ኢኮኖሚ አስተዳደር እና በውጭ ኩባንያዎች የሚሠሩ ሜጋ ፕሮጀክቶች ለችግሩ መነሻ ናቸው።

ጤናማ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር እንዲሁም ተመጣጣኝ አቅርቦት እና ፍላጎት እንዲፈጠር ፤ ብሔራዊ ባንክ እና የንግድ ባንኮች ለመፍትሔ እቅዶቻቸው ግብአት እንዲያገኙ መድረኩ ምቹ አጋጣሚ እንደሆነ ገልጸዋል ።

በተጨማሪ ም/ቤቱ የውጭ ምንዛሬን በሚመለከት የፖሊሲ ማስተካከያ እንዲደረግ የበኩሉን እንደሚወጣ የገለጹት ወ/ሮ መሠንበት መድረኩ ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ያለውን አቋም በይፋ የሚያሳውቅበት ይሆናል ብለዋል።

Via AACCSA

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

#የታለመለት_የነዳጅ_ድጎማ

ኢትዮ ቴሌኮም በሂደት ላይ የሚገኘውን የታለመለት የነዳጅ ድጎማ በቴክኖሎጂ በማገዝ ተግባራዊ ለማድረግ ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በጋራ እየሠራ እንደሚገኝ ገልጿል።

በዚህም መሠረት በድጎማው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለተለዩ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪ ባለንብረቶች ወይም ህጋዊ ወኪሎች አገልግሎቱ የሚሰጠው #በቴሌብር አማካኝነት መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል።

በኢትዮ ቴሌኮም የሸያጭ ማዕከላት ዋና ወይም ቅጂ #ሊብሬ እንዲሁም #የታደሰ_መታወቂያ በመያዝ የተሸከርካሪውን ባለቤት የስልክ ቁጥር በማሳወቅ የቴሌብር አገልግሎት ምዝገባ ከወዲሁ እንዲያከናውኑ እንዲሁም ተጨማሪ መረጃዎችን እንዲያሟሉ ተጠይቋል።

@tikvahethiopia
#Somalia

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በዓለ ሲመታቸው ይከናወናል።

ለዚህም በዓለ ሲመት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ ሶማሊያ ሞቃዲሾ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካቸው ጋር ሞቃዲሾ ገብተዋል።

በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ በተመራው የልዑካን ቡድን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሚኒስትር አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ይገኙበታል።

ዶ/ር ዐቢይ ዛሬ ሞቃዲሾ ከገቡ በኃላ ከፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ ጋር መገናኘታቸውን የሶማሊያ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሶማሊያ በሚኖራቸው ቆይታ በፕሬዝደንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በዓለ ሲመት ላይ ንግግር እንደሚያርጉ ፤ በተጨማሪም በበዓለ ሲመቱ ከሚታደሙ ከሌሎች የሀገራት መሪዎች ጋር የሁለትሽ ምክክር እንደሚያደርጉ ተሰምቷል።

ፎቶ ፡ Ahmed K Kosar / Somali Guardian

@tikvahethiopia
#ፓስፖርት

የፓስፖርት አገልግሎት ክፍያዎችን በ " ቴሌ ብር " አማካኝነት መፈፀም እንዲቻል በኢትዮ ቴሌኮም እና በኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መካከል ዛሬ ስምምነት ተፈፅሟል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ወ/ሪት ፍሬህወት ታምሩ ፤ ስምምነቱ አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፣ እድሳት ለመፈፀም እና ሲጠፋ ሌላ ለማውጣት አገልግሎት ሲፈልጉ በቴሌ ብር ክፍያ መፈፀም እንደሚያችል ገልፀዋል።

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሙሉጌታ በበኩላቸእ አገልግሎቱ በቀን ከ1,500 እስከ 2,000 የሚጠጉ ደምበኞች የሚስተናገዱበት መሆኑን በመግለፅ ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር የተደረገው ስምምነት አገልግሎቱን ለማግኘት የሚፈጠረውን መጨናነቅ ይቀንሰዋል የሚል እምነት እንዳላቸዉ መናገራቸው ኢትዮ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#ATTENTION 📣

ድንበር የለሽ ዶክተሮች (MSF) በአፋር ክልል እየጨመረ የመጣው የምግብ እጥረት ቀውስ ስጋት እንዳጫረበት ገልጿል።

ድርጅቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች መሠረታዊ የሚባሉ የጤና ማዕከላትን እንዲሁም ንጹህ የመጠጥ ውሃ በማያገኙበት ሁኔታ ነው የሚኖሩት ብሏል።

በተጨማሪም በርካታ ሕፃናት በከፋ የምግብ እጥረት ሕይወታቸውን አጥተዋል ሲል አመልክቷል።

የዘንድሮው ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር አራት እጥፍ ብልጫ ባለው መልኩ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ያለባቸውን ሕፃናትን መመልከቱን ገልጿል።

ከነዚህ ውስጥ 35 ሕፃናት የሞቱ ሲሆን አብዛኞቹም ወደ ሆስፒታል በገቡ በ48 ሰዓታት ውስጥ ነው ሕይወታቸው ያለፈው።

በአፋር ውስጥ ካሉ የጤና ማዕከላት አብዛኞቹ አገልግሎት ላይ እንዳልሆኑ ያስታወቀው MSF በሥራ ላይ ያሉት 20 በመቶ ብቻ  ናቸው ብሏል።

በክልሉ እየተከሰተ ያለው ቀውስ ከዚህም የከፋ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሞ የረድኤት ማኅበረሰቡ #አስቸኳይ ጣልቃ ገብነት አስፈላጊ እንደሆነ አሳስቧል።

እንደን MSF ሪፖርት በጦርነት ክፉኛ የተጎዳችው የትግራይ ክልልን ወደሚያዋስነው የአፋር ክልል የተፈጠረውን ግጭት በመፍራት በርካታ ተፈናቃዮች ወደ ክልሉ ጎርፈዋል።

በትግራይ ክልል በተከሰተው ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች የተፈናቀሉ ሲሆን የተወሰኑት ከአንድ ወር በላይ በእግር ተጉዘው አፋር ደርሰዋል።

ተፈናቃዮቹን ጨምሮ በርካታ ነዋሪዎች በአፋር ለከፍተኛ ስቃይ የተጋለጡ ሲሆን MSF አፋጣኝ ምላሽ እንደሚያስፈልግም ማሳሳቡን ቢቢሲ ድርጅቱን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

Be A Legend!

Pay with your BoA Visa card like Drogba!

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://publielectoral.lat/BoAEth
TIKVAH-ETHIOPIA
#Somalia አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ ሞሀመድ በዓለ ሲመታቸው ይከናወናል። ለዚህም በዓለ ሲመት የተለያዩ ሀገራት መሪዎች ወደ ሶማሊያ ሞቃዲሾ በመግባት ላይ ይገኛሉ። ዛሬ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ከልዑካቸው ጋር ሞቃዲሾ ገብተዋል። በጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ በተመራው የልዑካን ቡድን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ፣ የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ፣ የጠቅላይ…
ፎቶ ፦ አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀሙድ በዓለ ሲመት ስነስርዓት በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በዚሁ በዓለ ሲመት ፦

- የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፣
- የኬንያ ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ፣
- የጅቡቲ ፕሬዜዳንት ኢስማኤል ኦማር ጌሌ፣
- የግብፅ ጠ/ሚ ሙስጠፋ ማድቡሊ፣
- የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ (UAE) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ሻኽቦውት ቢን ናህያን እና የሌሎችም ሀገራት ተወካዮች የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ተገኝተዋል።

በበዓለ ሲመቱ የኢትዮጵያ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ንግግር ያደረጉ ሲሆን ፥ #ኢትዮጵያ ለአዲሱ የሶማሊያ ፕሬዜዳንት ያላትን ድጋፍ አረጋግጠዋል። በሶማሊያ ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር በማየታቸውም ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል።

" ባለፉት ዓመታት በ2ቱ ሀገራት (ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ) መካከል በዲፕሎማሲው መስክ የተመዘገቡት ድሎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ እርግጠኛ ነኝ " ብለዋል።

@tikvahethiopia
#ጥንቃቄ_ያድርጉ

በክረምት ወቅት ከጉዞ በፊት መደረግ የሚገባቸው አንዳንድ ጥንቃቄዎች ፦

➽ መስታዎች በሙሉ ጹዱ መሆናቸውን ያረጋግጡ ፤

➽ ጎማዎች በቂ ጥርስ እንዳላቸው ወይንም ሊሾ አለመሆናቸውን ይፈትሹ፤

➽ የዝናብ መጥረጊያ በትክክል መሰራቱን፣ ውሃ በቋት ውስጥ መኖሩንና ጐሚኒዎች በትክክል ማጽዳታቸውን ያረጋግጡ ፤

➽ መብራቶችና አንፀባራቂዎች በትክክል መስራታቸውን ይፈትሹ፤

(የኢትዮጵያ መንገድ ትራፊክ ደህንነት)

@tikvahethiopia