TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ወላጆች_ለልጆች_ጥንቃቄ_እንዲያደርጉ_አሳስቧቸው !

ትናንትና በአዲስ አበባ ከተማ በጣለው ዝናብ አንድ ተማሪ በጎርፍ እንደተወሰደ ተሰምቷል።

የአዲስ አባባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ የኮሙኒኬሽን ተማሪው በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላዛሪስት የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርት ቤት ተማሪ መሆኑን አመልክቷል።

ተማሪው በጎርፍ የተወሰደው ትላንት 9 ሠዓት አካባቢ በጣለው ዝናብ መሆኑን የገለፀው ኮሚኒኬሽኑ በጎርፉ የተወሰደው ተማሪ በትምህርት መውጫ ሠዓት ላይ ከትንሽ ወንድሙ ጋር ወደ ቤት እየሄዱ እንደነበርም አስረድቷል።

እስከዛሬ ጠዋት የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሠራተኞቹ ከኅብረተስቡ ጋር በመሆን ተማሪውን የመፈለጉን ሥራ ቀጥለዋል ተብሏል፡፡

ወላጆች በክረምቱ ልጆቻቸውን ወደ ት/ቤት ሲልኩ ሆነ ሲቀበሉ ተገቢውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉላቸው የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ማሳሰቡን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

#ኤፍቢሲ

@tikvahethiopia