TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
" ' ስንፈልግሽ ትመጫለሽ ' በሚል እንደፈቷት ነግራኛለች " - አቶ ለሚ ታዬ

የ " ፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ " የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ሰቦንቱ አህመድ ዛሬ ረፋዱን ከእስር መለቀቋን የጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ለሚ ታዬ ተናግረዋል።

ጋዜጠኛ ሶቦንቱ የተለቀቀችው በቢሾፍቱ ከተማ ከሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ መሆኑን ገልጸዋል።

ጋዜጠኛ ሶቦንቱ በፖሊስ ቁጥጥር የዋለችው ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ግንቦት 18/2014 አመሻሽ ላይ ከስራ ቦታዋ ስትወጣ መሆኑን በወቅቱ ተገልጾ ነበር።

በ " ፊንፊኔ ኢንተግሬትድ ብሮድካስቲንግ " ቴሌቪዥን ጣቢያ ዜና አንባቢ እና የመዝናኝ ፕሮግራም አዘጋጅ የሆነችው ሰቦንቱ በማግስቱ ወደ ቢሾፍቱ ከተማ መወሰዷን የጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ተናግረው ነበር።

ያለፉትን ሶስት ቀናት በእስር ያሳለፈችው ሰቦንቱ ዛሬ ሰኞ ግንቦት 22 ከጠዋቱ አራት ሰዓት ተኩል ገደማ በዋስ መለቀቋን አቶ ለሚ ገልጸዋል።

ጋዜጠኛዋ ከእስር ከተለቀቀች በኋላ በስልክ እንዳነጋገሯት የገለጹት የቴሌቪዥን ጣቢያው ዋና ዳይሬክተር ፖሊስ " ስንፈልግሽ ትመጫለሽ " በሚል መፈታቷን እንደነገረቻቸው አስታውቀዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር (www.ethiopiainsider.com)

@tikvahethiopia
#Ashewa

አሸዋ ቴክኖሎጂ የድጅታል ኢኮኖሚው ላይ የሚሰራ የዘልማዱን ግብይት በአፍሪካ ላይ የሚቀይር፣ ህይወት የሚያቀል፣ የሚያዘምን፣ የሚያሻግር ነው። ባሁኑ ሰአት በአገራችን ያለውን የንግድ ሰንሰለት ችግር ሊቀርፍ፣ አምራቹን በቀጥታ ከሸማቹ ጋር ከኑሮ ውድነት ሊገላግል ብዙ የክፍያ እና ደሊቨሪ አማራጮችን ይዞ በኢኮሜርሱ ዘርፍ በኩል ስራውን መጀመሩን ስናበስራችሁ ትልቅ ኩራት ይሰማናል።

ግዙ ሽጡ በአዲስ አበባ ላይ https://bit.ly/3smsyrx

ድርጅቱ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ እና ትርፍ ተካፋይ ለመሆን Ashewatechnology.com
ስልክ ፦ 0976005500 or 0976005100

Join our telegram channel
t.me/ashewatechnology
#አቢሲንያ_ባንክ

Be A Legend!

Pay with your BoA Visa card like Drogba!

የአቢሲንያ ባንክን ትክክለኛ የቴሌግራም ቻነል ይቀላቀሉ! https://publielectoral.lat/BoAEth
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ችሎት ፍርድ ቤት በብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ለግንቦት 22 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አመልካች የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍና በተጠሪ ብርጋዴል ጄኔራል ተፈራ ማሞ መካከል በነበረው የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ሀሳብ አዳምጧል። ፍርድ ቤቱም ፤ ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ውስጥ 10 ቀን በመፍቀድ ለግንቦት 22 ቀን…
#Update #ችሎት

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 22/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ተመልክቷል።

የመርማሪ ቡድኑ ምርመራዬን ስላልጨረስኩ የተለያዩ ማስረጃዎችን ከባንክ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከኢሳት እና ከሌሎች ተቋማት የምንሰበስባቸው መረጃዎች ስላሉ የ14 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው አስፈላጊ ናቸው የተባሉ መረጃዎችን ለመሰብሰብ መረጃው የሚሰበሰብባቸው ተቋማት የመንግስት ስለሆኑ ያን ያህል ጊዜ ስለማይዎስዱ ተከሳሽ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ በዋስትና እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

የምርመራ ቡድኑ የጠበቃውን በዋስትና ይለቀቁልኝ ክርክር በመቃዎም ተከሳሹ ከእስር ቢለቀቁ የተለያዩ ማስረጃዎችን ያጠፉብናል በዚህ ምክንያት በእስር ሊቆዩ እና የጠየቅነው የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድላቸው ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱን ስላመነበት የምርመራ ቡድኑ ከጠየቀው የ14 ቀን ውስጥ 4 ቀን ቀንሶ 10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለሰኔ 2/2014 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ በፌደራል ፖሊስ አባላት ተያዘች። " ሮሃ ሚዲያ " የተሰኘው የዩቲዩብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና ባለቤት የሆነችው መዓዛ መሐመድ ዛሬ ጠዋት በፖሊስ ተይዛ መወሰዷን የስራ ባልደረባዋ እና ጓደኛዋን ዋቢ አድርጎ " ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ድረገፅ " ዘግቧል። የጋዜጠኛዋ እስር በኢትዮጵያ ከሰሞኑ በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ስር የዋሉ ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ሰራተኞችን ቁጥር 19 አድርሶታል።…
#Update #ችሎት

ጋዜጠኛ መዓዛ መሃመድ ፍርድ ቤት ቀርባለች።

ባሳለፍነው ቅዳሜ በፀጥታ ሃይሎች የተያዘችው መዓዛ መሃመድ ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው የቀረበችው።

ፖሊስ በመዓዛ መሃመድ ላይ " ሁከትና ብጥብጥ ማስነሳት " የሚል ክስ ያቀረበባት ሲሆን በጉዳዩ ላይም መረጃ ለማሰባሰብ የ14 ቀን ቀጠሮ ይሰጠኝ ሲል ጠይቋል።

የጋዜጠኛዋ ጠበቆች ጋዜጠኛዋ ሰራች የተባለው ወንጀል ተፈፅሞ ቢሆን እንኳን ጉዳዩ ሊታይ የሚገባው በመገናኛ ብዙሀን አዋጅ ነው ፤ በእስር እንድትቆይ ህጉ አይፈቅድም ሲሉ ተከራክረዋል።

አክለውም ጋዜጠኛዋ ከወራት በፊት ታስራ ማስረጃ ሊቀርብባት ባለመቻሉ ነፃ መደረግዋን አስታውሰው አሁንም ሞጋች ጋዜጠኛ መሆኗ እንጂ የሰራችው ወንጀል የለም ይሄንን ፍ/ቤቱ ሊመለከተው ይገባል ሲሉ ሞግተዋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር አዳምጦ የ7 ቀናት የምርመራ ጊዜ መፍቀዱን የምትሰራበት " ሮሃ ሚዲያ " ዘግቧል።

በሌላ በኩል ፦ በጋዜጠኛ ሰለሞን ሹምዬ ላይ የሰባት ቀናት የምርመራ ጊዜ ተፈቅዷል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
🫂 ከጭልጋና አካባቢው ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖች ወደ ቦታቸው እየተመለሱ ይገኛሉ። በጭልጋና አካባቢዋ ተፈናቅለው የነበሩ የህብረተሰብ ክፍሎችን ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሠራ እንደሚገኝ ተነግሯል። ከትላንት አንስቶ ከአይከል እና በዙሪያዋ ተፈናቅለው የነበሩ 11 ሺህ 938 የህበረተሰብ ክፍሎች ወደ ቦታቸው የመመለስ ስራ እየተሰራ ሲሆን ወደ አይከል ከተማ ሲገቡ ማህበረሰቡ በነቂስ ወጥቶ ተቀብሏቸዋል።…
#Update

በአዳኝ አገር ጫቆ ወረዳና አካባቢው ተፈናቅለው የነበሩ የህበረተሰብ ክፍሎች ወደ ቀያቸዉ ተመለሱ።

በምዕራብ ጎንደር ዞን አዳኝ አገር ጫቆ ወረዳ ነጋዴ - ባህር ከተማ በወቅታዊ የፀጥታ ችግር ምክንያት ተፈናቅለው አይከልና ሰራባ ጊዜያዊ መጠለያ የነበሩ የህበረተሰብ ክፍሎች ዛሬ ወደ ቀያቸዉ ተመልሰዋል።

ከአካባቢያቸው ተፈናቅለው የነበሩ ወገኖች ነጋዴ - ባህር ከተማ ሲደርሱ የነጋዴ ባህር ከተማ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ደማቅ አቀባበል እንዳደረገላቸው ተገልጿል።

Photo Credit : ጭልጋ ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopia
#እንድታውቁት

በጥሬ ዕቃ ምክንያት ላለፉት 3 ሳምንታት ተቋርጦ የነበረው አዲስ የተሽከርካሪ ሠሌዳ የመስጠት አገልግሎት ከ1 ሣምንት በኋላ መሥጠት ይጀመራል ተብሏል።

የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎት የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን አንባቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት (ኤፍቢሲ) በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦

" በጥሬ ዕቃ ምክንያት እና በውጭ ምንዛሬ ዕጥረት ላለፉት 3 ሣምንታት አዲስ የተሽከርካሪ ሠሌዳ መስጠት አልተቻለም።

አሁን ላይ ግን የውጭ ምንዛሬ ተፈቅዶ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ከጀርመን ሀገር ለማስመጣት ዝግጅት ተጠናቋል።

በርካታ ደንበኞች አዲስ የተሽከርካሪ ሠሌዳ ለመውሰድ ተራ እየጠበቁ በመሆኑ በፍጥነት ተጨማሪ የማጓጓዣ ታሪፍ ተከፍሎ በአውሮፕላን እንዲመጣ ይደረጋል።

የተሽከርካሪ ሠሌዳ እየተጠባበቁ ያሉ ደንበኞች ከ1 ሣምንት በኋላ ማግኝት ይችላሉ "

@tikvahethiopia
#ችሎት

ባለሀብቶችን በመሰለል፣ በማገት እና በማስፈራራት ገንዘብ በጠየቁ እና በተቀበሉ አራት የመከላከያ ሚኒስቴር አባላትና ግብረአበሮቻቸው ላይ ስልጣንን አላግባብ በመገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ስር ክስ ተመሰረተ።

የመከላከያ መኪና በመያዝ ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሃብት ማስመለስ የመጣን ዐቃቤ ህጎች ነን ህገ ወጥ ዘይት߹ ስኳር እና የጦር መሳርያ ስለምትሸጡ በወንጀል ትፈለጋላችሁ በማለት 8 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በጠየቁ የመከላከያ ሚኒስቴር አባላትና ግብረ አበሮቻቸው ላይ ክስ ተመስርቷል።

የተለያዩ የምርምራ ሂዶትችን ከፖሊስ ጋር ሲያከናውን ቆይቶ በግለሰቦች ላይ ክሱን የመሰረተው ደግሞ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ነው ።

ወንጀሉን ፈጽመዋል በሚል ክስ የተመሰረተባቸው በመከላከያ ሚኒስቴር በ93ኛ እና 94ኛ እግረኛ ክፍለ ጦር አባል የሆኑት ፦

• 1ኛ መቶ አለቃ ሀጂ ቱሉ ߹
• 2ኛ ኦፊሰር መንግስቱ በቀለ ߹
• 3ኛ ሻምበል ካህሊ መላክ ߹
• 4ኛ ሻለቃ ዱጉማ ዲምሳ እና በተለያዩ የንግድ ስራዎች ውስጥ ተሰማርተው የሚገኙት ግብረ-አበሮቻቸው ከ5ኛ-8ኛ ስማቸው በክሱ የተጠቀሰው ተከሳሾች ሹምበዛ ፍቃዱ፣ አዲስ አለሙ፣ ተስፋዬ ለሚ እና አሸናፊ ወልደ ሰማያት ናቸው፡፡

➡️ ተከሳሾች ከጳጉሜ 03/2013 ዓ.ም እስከ የካቲት 13/2014 ዓ.ም ባሉት ጊዚያት ውስጥ በቡድን በመደራጀት ባለሀብቶችን ኢላማ አድርገው ጥናት በማድረግ የማይገባቸውን ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በዐቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመለከተው 2ኛ ፣ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች ታርጋ የለጠፈ የመከላከያ መኪና ይዘው ወደ ግል ተበዳይ መኖርያ ቤት በመሄድ ተበዳይ በወንጀል እንደተጠረጠረ በማስመሰል በመኪና አግተው ከወሰዱት በኋላ ህገ ወጥ ዘይት߹ ስኳርና የጦር መሳርያ ትሸጣለህ እንድንለቅህ የምትፈልግ ከሆነ 5 ሚሊየን ብር ክፈል ካልከፈልክ ግን ልጆችህን ጭምር እንገላቸዋለን ብለው ካስፈራሩ በኋላ 710,000 ( ሰባት መቶ አስር ሺ ) ብር ተቀብለዋል።

➡️ በሌላ ሁለተኛ ክስ ደግሞ ሌላ ተበዳይ መኪና እያሽከረከረ እያለ 5ኛ እና 7ኛ ተከሳሽ በመከላከያ መኪና ሲከተሉት ስጋት ስለገባው ለላፍቶ ፖሊስ ጣቢያ ኣዛዥ ጉዳዩን ያስረዳ ቢሆንም ሁለቱ ተከሳሾች የፖሊስ ጣቢያ አዛዡን ”ከደህንነት ነው የመጣነው” ግለሰቡ በብዙ ወንጀሎች ይፈለጋል አለቃችንም እየመጣ ነው ካሉ በኋላ 8ኛ ተከሽ አንደ አለቃቸው ሆኖ በመምጣት ፖሊስ ጣቢያ እንደሚታሰር ገልፀው ተበዳይ እህቱን አንዲጠራት ካደረጉ በኋላ እህቱንም ጭምር በመያዝ ይሄ የሕይወት ጉዳይ ነው እህትህን እንድንለቃት የምትፈልግ ከሆነ 3 ሚሊየን ብር ክፈል ብለውታል።

➡️ በ3ኛ ክስ ቀኑ በውል ባልታወቀ በመስከረም ወር 2014 ዓ.ም ደግሞ ወ/ሮ አዜብ በርሔ የተባለች ግለሰብን 5ኛ እና 7ኛ ተከሳሽ ”ከጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ሃብት ማስመለስ ዐቃቤ ህጎች ነን” በማለት ተበዳይን ባለቤትሽ ጄነራል ነው ትግራይ በመሄድ እያዋጋ ነው ቤትሽን በተመለከተም እያጣራን ስለሆነ አጠቃላይ የቤት ካርታና ሌሎች ሰነዶችን ኮፒ አድርገሽ አምጭ ብለው ከተቀበሏት በኋላ እንድንረዳሽ ከፈለግሽ 500 ሺህ ብር ክፈይ ሲሏት የመክፈል አቅም እንደሌላት ገልፃ ህጋዊነታቸውን ስትጠይቃቸው 8ኛ ተከሳሽን አናግሪው በማለታቸው 8ኛ ተከሳሽ የመከላከያ ታርጋ የለጠፈ መኪና ይዞ በመምጣት ተበዳይን አግኝቶ “ሰዎቹ ህጋዊ ናቸው የሚሉሽን አድርጊ እኔ የመከላከያ ሚኒስቴር አባል ነኝ አሁን ሃብት ማስመለስ ስራ ላይ ነው የምሰራ ” በማለት ከሁለቱ ተበዳዮች በአጠቃላይ 405 ሺ ብር ተቀብለዋል።

በዚህም ተከሳሾች በዋና ወንጀል አድራጊነትና ተካፋይ በመሆን በፈፀሙት ስልጣንን ያለአግባብ መገልገል ከባድ የሙስና ወንጀል ነው እንደ ወንጀል ተሳትፏቸው በዐቃቤ ህግ ክስ የተመሰረተባቸው።

ከ1ኛ - 6ኛ ያሉት ተከሳሾች ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2014 በፌደራል ከፍተኛ ፍ/ቤት ልደታ ምድብ 5ኛ ወንጀል ችሎት ቀርበው የክስ ማመልከቻው አንዲደርሳቸው ተደርጎ ክሱ በንባብ እንዲሰማ ተደርጓል።

ችሎቱ በቁጥጥር ስር ያልዋሉትን 7ኛና 8ኛ ተከሳሽን ፖሊስ አፈላልጎ አንዲያቀርብ ትዕዛዝ የሰጠ ሲሆን ተከሳሾች በተመሰረተባቸው ክስ ላይ የመጀመርያ የክስ መቃወሚያ እና ባልተያዙ ተከሳሾች ላይ የፖሊስን ምላሽ ለመጠባበቅ ለግንቦት 29/2014 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰቷል።

ምንጭ፦ የፍትህ ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#የነዳጅ_ዋጋ_ጭማሪ ከነገ ሚያዚያ 30 ጀምሮ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ላይ ጭማሪ ተደርጓል። በዚህም ፦ 👉 ቤንዚን በሊትር 36 ብር ከ87 ሳንቲም ፣ 👉 ነጭ ናፍጣ በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣ 👉 ኬሮሲን በሊትር 35 ብር ከ43 ሳንቲም፣ 👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ በሊትር 52 ብር ከ45 ሳንቲም፣ 👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ በሊትር 51 ብር ከ78 ሳንቲም 👉 የአውሮፕላን ነዳጅ በሊትር…
#ሰኔ

የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ፤ በሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የቤንዚን፣ የናፍጣ እና የኬሮሲን የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በግንቦት ወር ሲሸጥበት በነበረው እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የአውሮፕላን ነዳጅ፣ የቀላል ጥቁር ናፍጣ እና የከባድ ጥቁር ናፍጣ የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በዓለም አቀፍ ዋጋ ተሰልቶ የመጣው ልዩነት ሙሉ በሙሉ ወደ ተጠቃሚው እንዲተላለፍ መወሰኑን ገልጿል።

ምንጭ፦ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር

@tikvahethiopia
#Eritrea

ባለፉት ሁለት ቀናት ከጎረቤት ኤርትራ ሠራዊት ጋር አዲስ ውጊያ መካሄዱን የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ ገልፀዋል።

አቶ ጌታቸው ዛሬ ግንቦት 22/2014 ዓ.ም አመሻሽ ላይ እንዳሉት ባለፈው ቅዳሜ እና እሑድ (ግንቦት 20 እና 21 ቀን 2014 ዓ. ም.) የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ ጥቃት ከፍቶ ነበር ብለዋል።

በውጊያው አንድ የኤርትራ ጦር ብርጌድ አዛዥ እና 3 የሻለቃ አዛዦች የሚገኙባቸው 120 ወታደሮችን እንደተገደሉ 195 ያህሉን እንዳቆሰሉ እና 4 ወታደሮችን እንደተማረኩ ተገልጿል። አንድ ድሽቃ፣ አምስት የወታደራዊ ሬዲዮ መገናኛዎች እና በርካታ የጦር መሳሪያዎች ከኤርትራ ጦር እንደተማረከም ተገልጿል።

ቅዳሜና እሁድ ተከሰተ ካሉት ወታደራዊ ግጭት በተጨማሪ ከ4 ቀናት በፊት ግንቦት 16 ቀን 2014 ዓ. ም. የኤርትራ 57ኛ እና 21ኛ ክፍለ ጦር ወደ ትግራይ ክልል ጥቃት ሰንዝሮ እንደነበርና አዲአዋላ በተባለው አካባቢ ይህንን ጥቃት መመከት እንደተቻለ አሳውቀዋል።

አቶ ጌታቸው ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ የኤርትራን መንግሥት ድርጊት በቃ እንዲለው ጥሪ አቅርበዋል።

ይህን ጉዳይ በተመለከተ የኢትዮጵያ መንግሥት ቃል አቀባይ ዶ/ር ለገሰ ቱሉ ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ተካሄደ ስለተባለው ውጊያ መረጃው እንደሌላቸው ገልጸው፣ ነገር ግን የኤርትራ ኃይሎች ጥቃት ሊፈጽሙ የሚችሉበት ሁኔታ የለም ብለዋል።

ዶ/ር ለገሰ " ህወሓቶች ራሳቸው ትንኮሳ ፈጽመው " የሚያሰሙት ክስ ሊሆን ይችላል ሲሉ ገልፀዋል። በአሁኑ ጊዜ " በኤርትራ በኩል ጦርነት ይከፈታል የሚል እምነት የለንም " ያሉት ዶ/ር ለገሰ የተከሰተ ነገር ካለም አጣርተው መረጃ እንደሚሰጡ መግለፃቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

በኤርትራ መንግስት በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

@tikvahethiopia
" የጋዜጠኞች የዘፈቀደ እስር እንቃወማለን ፤ የህግ የበላይነት ይከበር "

የመብቶች ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) እና 7 የተለያዩ ማህበራት በጋራ ባወጡት አጭር መግለጫ በጋዜጠኞች ላይ የዘፈቀደ እስር እየተፈፀመ መሆኑን በመግለፅ ድርጊቱን እንደሚቃወሙ ገልፀዋል።

በመግለጨው ባለፉት 2 ሳምንታት 18 ጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች በድንገተኛ ዘመቻ መታሰራቸውን አንስተው ፤ ጋዜጠኞች የህግ መተላለፍ ከተገኘባቸው እንደማንኛውም ዜጋ በፍትሃዊ የህግ ሂደት ተጠያቂ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

ነገር ግን በየጊዜው የሚደረጉ የጋዜጠኞች እስሮች በተደጋጋሚ የህግ አግባብ ሲጥሱ እየተስተዋለ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

አክለውም ፤ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን አዋጅ ሕግ 1238/2013 አንቀፅ 86/1 " በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የወንጀል ድርጊት በመፈፀም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል በወንጀል ስነስርዓት ህግ ድንጋጌዎች መሰረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በአቃቤ ህግ አማካኝነት ወደ ፍርድ ቤት መቅረብ አለበት " ይላል ፤ ይሁንና የታሰሩ የመገናኛ ብዙሃብ ሰራተኞች ምንም ክስ ሳይመሰረትባቸው ፣ ለቅድመ ክስ ምርመራ በሚሰጥ ቀጠሮ በአስቸጋሪ ሁኔታ ከቤተሰብና ወዳጅ ጥየቃ ርቀው እንዲቆዩ እየተደረገ ነው " ሲሉ አመልክተዋል።

ይህ የህግ አግባብን ያልተከተለ አሰራር ፣ ለህግ የበላይነት ፣ ለሚዲያ ነፃነት ፣ ለጋዜጠኞች ደህንነት እና ለኢትዮጵያ ሰላም እና መረጋጋት አደጋ የሚፈጥር ስለሆነ አጥብቀን እናወግዛለን ብለዋል።

የሚመለከታቸው አካላት በእስር ላይ የሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን አካላት በአስቸኳይ ከእስር ተለቀው የህግ የበላይነት እንዲከበር ሲሉ በመግለጫቸው ጥሪ አቅርበዋል።

(መግለጫውን ያወጡት ማህበራት ዝርዝር ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia