TIKVAH-ETHIOPIA
#Update #ችሎት ፍርድ ቤት በብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ለግንቦት 22 ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ። የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት አመልካች የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍና በተጠሪ ብርጋዴል ጄኔራል ተፈራ ማሞ መካከል በነበረው የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ሀሳብ አዳምጧል። ፍርድ ቤቱም ፤ ፖሊስ ከጠየቀው የ14 ቀን ውስጥ 10 ቀን በመፍቀድ ለግንቦት 22 ቀን…
#Update #ችሎት

የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዛሬ ግንቦት 22/2014 ዓ/ም በዋለው ችሎት የብርጋዴል ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጉዳይ ተመልክቷል።

የመርማሪ ቡድኑ ምርመራዬን ስላልጨረስኩ የተለያዩ ማስረጃዎችን ከባንክ፣ ከብሔራዊ መረጃና ደህንነት፣ ከኢሳት እና ከሌሎች ተቋማት የምንሰበስባቸው መረጃዎች ስላሉ የ14 ቀናት ተጨማሪ የጊዜ ቀጠሮ እንዲሰጠው ጠይቋል።

የተከሳሽ ጠበቃ በበኩላቸው አስፈላጊ ናቸው የተባሉ መረጃዎችን ለመሰብሰብ መረጃው የሚሰበሰብባቸው ተቋማት የመንግስት ስለሆኑ ያን ያህል ጊዜ ስለማይዎስዱ ተከሳሽ በውጭ ሆነው እንዲከራከሩ በዋስትና እንዲለቀቁ ጠይቀዋል።

የምርመራ ቡድኑ የጠበቃውን በዋስትና ይለቀቁልኝ ክርክር በመቃዎም ተከሳሹ ከእስር ቢለቀቁ የተለያዩ ማስረጃዎችን ያጠፉብናል በዚህ ምክንያት በእስር ሊቆዩ እና የጠየቅነው የጊዜ ቀጠሮ እንዲፈቀድላቸው ጠይቋል።

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ሰምቶ የጊዜ ቀጠሮ መስጠቱን ስላመነበት የምርመራ ቡድኑ ከጠየቀው የ14 ቀን ውስጥ 4 ቀን ቀንሶ 10 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመፍቀድ ለሰኔ 2/2014 ዓ/ም ቀጠሮ ሰጥቷል።

ምንጭ፦ የአብክመ ጠቅላይ ፍርድ ቤት

@tikvahethiopia