TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፎቶ ፦ የነዳጅ ሰልፍ በአዲስ አበባ ከተማ !

ነዳጅ ለማግኘት ረጅም የሆኑ ሰልፎችን መጠበቅ ከተጀመረ ሰነባብቷል። ይህ ችግር በርካታ ጊዜያት ተደጋግሞ ቢነሳም መፍትሄ አልተገኘለትም።

በዚህ ምክንያት ዜጎች ሰዓታቸውን በነዳጅ ሰልፍ ሳይባክን ሰርተው ለመብላት የዕለት ገቢያቸውን ለማግኘት ፈተና እየሆነባቸው ነው።

ተሽከርካሪ ያላቸው ሰራተኞችም ስራቸውን እየተው ለነዳጅ እየተሰለፉ በመሆኑ ስራቸው እየተበደለ ነው።

ነዳጅ ላይ የዋጋ ማስተካከያ ቢደረግም በተባለው ዋጋ ለማግኘት እንኳን ፈተና ሆኗል። የዓለም ነዳጅ ዋጋ ንረት እንደተጠበቀ ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ እውነት በቂ ነዳጅ ስለሌለ/ስለማይገባ ነው ? ወይስ ያለውን በአግባቡ የማስተዳደር ችግር ? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።

በክልል ከተሞች ማደያዎች ነዳጅ የለም ይላሉ ፤ ህገወጥ በሆነ መልኩ በየመንገዱ፣ በየሱቁ ላይ ሲሸጥ ይታያል ፤ ማደያዎች ለሊት ላይ በጄሪካን ለተለያዩ አካላት እንደሚቀዱ ነው የሚነገረው።

ይህን ለማስቆም ሰፊ ጥረት ሲደረግ አይታይም፤ ምክንያቱም ችግሩ ወራትን ስላስቆጠረ በዚህ ህገወጥ ድርጊት የሚሳተፉ እና እጃቸው ያለበት ብዙ አካላት እንዳሉ ግን እሙን ነው።

ይህ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ችግር ልጓም ካልተበጀለት የሚፈጥረው ቀውስ ከፍተኛ ነውና ትኩረትን ይሻል።

@tikvahethiopia
" የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት በሚያዚያ ወር 12.8 ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ ተደርጓል " - የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን

የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ፤ የዓለም ነዳጅ ዋጋ ባሻቀበበት በዚህ ወቅት መንግሥት በሚያዚያ ወር ብቻ የነዳጅ ዋጋን ለማረጋጋት ከ12.8 ቢሊዮን ብር በላይ ድጎማ ማድረጉ ገልጿል።

ይህን የተገለፀው ከቀናት በፊት የነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን ስለ አዲሱ የታለመ የነዳጅ ድጎማና ዋጋ ማሻሻያ በተመለከተ ለሚዲያ አካላት በተዘጋጀ መድረክ ላይ ነው።

እስከ ሚያዚያ ወር ማጠናቀቂያ ድረስ በአንድ ወር ብቻ ከ12.8 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ድጎማ መደረጉ ታውቋል።

ከሐምሌ 2014 ዓ.ም. አንስቶ በጠቅላላው ባለፉት አሥር ወራት በመንግሥት የተደረገው የተመዘገበ የድጎማ መጠን ከ73.5 ቢሊዮን ብር በላይ መድረሱን ሪፖርተር ጋዜጣ የነዳጅ እና ኢነርጂ ባለስልጣን ዋቢ አድርጎ አስነብቧል።

https://telegra.ph/Reporter-05-08

@tikvahethiopia
#ጥቆማ

ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና !

በቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ኮሌጅ የዓይን ህክምና ትምህርት ክፍል HCP በተባለ ግብረሰናይ ድርጅት እገዛ 500 የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና /CATARACT SURGERY/ ከሰኔ 6 እስከ ሰኔ 12/2014 ዓ.ም ለማድረግ አስቧል፡፡

ይህን ነፃ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ቀዶ ህክምና ለማድረግ ቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ በግንቦት ወር ባሉት ቅዳሜና እሁድ ቀናቶች ማለትም (ግንቦት 6፣ 7፣ 13፣ 14፣20፣ 21፣27 ፣28 ) ይካሄዳል።

በኮሌጁ የስልክ አገልግሎት 976 በመደወል ለቅድመ ምርመራ፣ ልየታና ምዝገባ ቀጠሮ ማስያዝ ይቻላል።

#ማሳሰቢያ ፡- በስልክ ቀጠሮ ያልተሰጠዉ ታካሚ ቅድመ ምርመራም፣ ልየታም ይሁን ምዝገባ ማድረግ አይችልም ተብሏል።

(ውድ ቤተሰቦቻችን መልዕክቱን አጋሩ)

@tikvahethiopia
የብሬንት ድፍድፍ ነዳጅ ዋጋ ፦

🛢️ከአንድ አመት በፊት 👉 68 የአሜሪካ ዶላር
🛢️አሁን 👉 113 የአሜሪካ ዶላር

ለነዳጅ ዋጋ እንዲህ መናር ሩስያ እና ዩክሬን የገቡበት እና ዛሬም ድረስ መቋጫ ያላገኘው ጦርነት ዋነኛው ሲሆን ጦርነቱ በአጠቃላይ ዓለምን አናግቷል ማለት ይቻላል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ሌተናል_ኮሎኔል_ፍሥሐ_ደስታ በድረግ ዘመነ መንግስት ኢትዮጵያን በምክትል ፕሬዝዳንትነት የመሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። የቀድሞው መሪ ኮሎኔል መንግሥቱ ኃ/ማሪያም ምክትል በመሆን የኢሕዲሪ ምክትል ፕሬዝዳንት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል ፍሰሐ ደስታ፣ ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ ለ20 ዓመታት ያህል በእስር ቆይተዋል። ቤተሰቦቻቸው ለቢቢሲ በሰጡት ቃል ፤…
ፎቶ ፦ ዛሬ የቀድሞ የኢትዮጵያ ምክትል ፕሬዜዳንት ሌተናል ኮለኔል ፍስሐ ደስታ የቀብር ሥነ ስርዓት በቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተፈጽሟል።

በቀብር ስነ ስርዓቱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እንዲሁም የቀድሞ የስራ ባልደረቦች እና ወዳጅ ዘመዶቻቸው ተገኝተው ነበር።

ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ በህይወት ሳሉ " አብዮቱ እና ትዝታዬ " በተሰኛው መፃፍ ላይ ከፃፉት ፦

" ቂምን ቋጥሮ ቁርሾን ተሸክሞ ዴሞክራሲና ሀገር ለመገንባት ፣ እድገትን እና ብልፅግና ለማምጣት የማይታሰብ ነው። በመሆኑም በዚያ አስከፊ የርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ያለፍነው ሁሉ የታሪኩ አካልና የትውልዱ አባል በመሆናችን የታመቁ ቅራኔዎችን ከማራገብ ይልቅ ያለፈውን ታሪካችንንና ያለንበትን ሁኔታ በቅንነትና በንፁህ ሕሊና በመገምገም ይቅር ለታሪክና ለትውልድ መባባል አለብን "

▪️ሌተናል ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ ከአባታቸው ብላታ ደስታ ወልደማርያም ከእናታቸው ወ/ሮ ሕርይተሥላሴ ትኩዕ ሚያዚያ 13/1933 ትግራይ ዓድዋ ከተማ ነው የተወለዱት ፤ አርብ ሚያዚያ 28/2014 ዓ. ም. እኩለ ሌሊት በ81 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፤ ሌ/ኮሎኔል ፍሥሐ ደስታ ባለትዳርና የ1 ልጅ አባት ነበሩ▪️

@tikvahethiopia
የአሠልጣኞች ሥልጠና ጥሪ - #CARD

ለሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የሥነ ዜጋና ሥነ ምግባር ትምህርት መምህራን መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ፅንሰ-ሐሳቦች ላይ ያተኮረ የአሠልጣኞች ሥልጠና !

የመብቶች ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (CARD) በአዲስ አበባ፣ ቢሾፍቱ ፣ አዳማ፣ ደብረብርሀን፣ ድሬዳዋ፣ ሀዋሳና ሀረሪ ክልሎች ውስጥ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የስነዜጋና ስነምግባር ትምህርት መምህራን የሰብዓዊ መብቶች ፅንሰ-ሐሳቦች ላይ ያተኮረ የአሠልጣኞች ሥልጠና ለመስጠት አቅዷል።

ሥልጠናው “የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አዲስ ትውልድ’’ የተባለውና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ላይ ትኩረቱን አድርጎ የሚሠራው ፕሮጀክት አንዱ አካል ነው መሆኑን ገልጿል።

ከስልጠናው በኋላ ተቋሙ በተጠቀሱት አካባቢዎች በቀጣይነት ለሚኖረው የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች መሰረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ስልጠና ሂደቶችን በማስተባበር ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ለማድረግ አቅዷል።

ለመመዝገብ https://bit.ly/3vu4rZK

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዲቪ (DV) 2023 ይፋ ሆኗል። የ2023 ዲቪ ሎተሪ ዛሬ ማታ ይፋ የሆነ ሲሆን ሞልታችሁ ስትጠባበቁ የነበራችሁ በሙሉ የዲቪ ውጤታችሁን በዚህ ሊንክ https://dvprogram.state.gov/ESC/Default.aspx መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል። @tikvahethiopia
#ዲቪ_ሎተሪ

ዳይቨርሲቲ ቪዛ ሎተሪ (ዲቪ) አሜሪካ በዕጣ የምትሰጠው የቪዛ መርሀ ግብር ሲሆን ከተወሰኑ ሀገራት በስተቀር ከመላው ዓለም በየዓመቱ ከ50 ሺህ በላይ ፍልሰተኖች አሜሪካ ገብተው የመኖር እና የመስራት ፍቃድ ያገኛሉ።

የአሜሪካ መንግስት ከዐለም የተለያዩ ሀገራት ዜጎችን የዲቪ ሎተሪን እየተጠቀሙ ወደ ግዛቱ እንዲገቡ ማድረግ ከጀመር በርካታ አመታት ተቆጥረዋል።

ለተሻለ ኑሮና ጥሩ የሆነ ግቢ አግኝቶ ሰርቶ ቤተሰብን ለመቀየረ የዲቪ ሎተሪ የሚያመለክቱ በየዓመቱ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ናቸው።

አሜሪካ ከተወሰኑ ሀገራት በቀር በመላው ዓለም ላሉ ሀገራት በምታመቻቸው ከ50 ሺህ በላይ የቪዛ ዕድል አንድ ሀገር የሚደርሰው ከሰባት በመቶ የማይበልጥ ነው።

ከሀገራችን ኢትዮጵያ ለዚህ ዕድል የሚያመለክቱ እጅግ በርካቶች ናቸው።

ለዲቪ የሚያመለክቱ አንድም በትምህርት አልያም በስራ ልምድ የሚወጡ መስፍርቶችን እንዲያሟሉ የሚጠበቅ ሲሆን በትምህርት ደረጃ ቢያንስ የ2ኛ ደረጃን ማጠናቀቅ አለባቸው፤ የኮሌጅና የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ቢሆኑ ደግሞ ጥሩ ነው፤ የትምህርት መመዘኛውን የማያሟሉ በስራ ልምድ ማካካስ የሚችሉ ሲሆን የስራ ልምድ ማስረጃ መያዝ አለባቸው።

በየዓመቱ የዲቪ ሎተሪ ሲሞላ አልያም ሲወጣ የማጭበርበር ድርጊቶች በስፋት ይስተዋላል፤ አጭበርባሪዎች ሰዎችን " የዲቪ እድል ደርሷችኃል " በማለት ያጭበረብራሉ፤ ማንኛውም ሰው ለዲቪ ሲያመለክት ሆነ ውጤት በሚታያይበት ወቅት የአሜሪካ መንግስት ለዚህ ክትትል አንዳች ክፍያ አያስከፍልም።

የ " 2023 የዲቪ ሎተሪ ዕጣ " ትላንት ምሽት ይፋ የተደረገ ሲሆን በዚህ ሊምክ መመልከት ይቻላል : https://dvprogram.state.gov/ESC/Default.aspx

@tikvahethiopia
#iጤና

• በስትሮክ፣ በአደጋ፣ እና በሌሎች በሽታዎች ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ለተፈጠረ አለመንቀሳቀስ (Paralysis)
• እድሜ በመግፋት ለሚፈጠሩ ጉድለቶች እንደ አልዛይመርስ፤ ዲሜንሻ
• ከተለያዩ ቀዶ ጥገናዎች ለማገገም
• በሙሉ (Coma) ወይም በከፊል የንቃተ ህሊና መቀነስ ላላቸው ታካሚዎች እንክብካቤ
• ለካንሰር እና ተከታታይ የህክምና ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች

👉 በ0901222233 ይደውሉልን
Telegram | FB | IG | Twitter 🌍
🏥 አድራሻችን ጀሞ ከ ጀሞ ሞል 200m ገባ ብሎ፡፡
በሀገራችን በተለይ በአዲስ አበባ እጅግ በጣም ሙስና ስር ከሰደደበት አንዱ የመሬት ዝውውር ጉዳይ ነው።

በዚህ ሂደት አንዳንድ የአስተዳደሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ደላላ ሆነው የተገኙበት ጊዜ መኖሩ ተጠቁሟል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ " " በመሬት ጉዳይ ብልሹ አሰራሮች በከተማው ተስፋፍቷል፣ በተለይ ደላላ የበዛበትና ለሙስና የተጋለጠ የመሬት ዝውውር ስርዓት በከተማዋ ታይቷል " ብለዋል።

አክለው፥ አንዳንድ የከተማ አስተዳደሩ አመራሮችና ባለሙያዎች #ከባለሃብት_ጋር_በመመሳጠር መሬትን በህገወጥ መንገድ ለማስተላለፍ የሚደረጉ ሙከራዎች በተደጋጋሚ መታየታቸውን ተናግረዋል።

ወ/ሮ ሂክማ ፤ በመረጃ በተደገፈ ሁኔታ የተያዙ አመራሮችና ባለሙያዎች ወደሕግ እንዲቀርቡ መደረጉንም ለኢፕድ ጋዜጣ ገልጸዋል።

እነዚህ ተይዘው ወደህግ ቀረቡ የተባሉ አመራሮች እና ባለሞያዎች እነማን እንደሆኑ በምን አይነት የኃላፊነት ቦታ እንደነበሩ በግልፅ ዘገባው ላይ የተብራራ ነገር የለም።

የከተማው አስተዳደር ፤ የመሬት አገልግሎትን በተመለከተ በቀጣይነት ሁለት አይነት አሰራር እንደሚተገበር የተጠቆመ ሲሆን ፥ መሬትን ዲጂታላይዝ በማድረግ የግልጸኝነት አሰራርን ማስፈን እና የመረጃ አያያዝ ሥርዓቱን በማጠናከር ሕዝብ እያንዳንዱን መረጃ እንዲያገኝ ማድረግ የትግበራው አካል መሆኑንም ነው የተገለፀው።

መሬት ለሌላ አካል የሚተላለፍበት መንገድ ህዝብን እንዲያሳትፍ አቅጣጫ መቀመጡንም ተነግሯል።

ያንብቡ : https://telegra.ph/EPA-05-09

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በሀገራችን በተለይ በአዲስ አበባ እጅግ በጣም ሙስና ስር ከሰደደበት አንዱ የመሬት ዝውውር ጉዳይ ነው። በዚህ ሂደት አንዳንድ የአስተዳደሩ አመራሮችና ባለሙያዎች ደላላ ሆነው የተገኙበት ጊዜ መኖሩ ተጠቁሟል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪስና ሰው ሃብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ሂክማ ከይረዲን ለኢፕድ በሰጡት ቃል ፥ " " በመሬት ጉዳይ…
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ ከመሬት አገልግሎት ጋር በተያያዘ ወ/ሮ ሂክማ ከይረዲን ከተናግሩት ፦

" ... በአዲስ አበባ ከተማ በእጅ መንሻ፣ በዝምድናና በተለያዩ ህገወጥ አካሄዶች ጉዳዮቻቸው #በፍጥነት የሚፈጸምላቸው ሰዎች አሉ። በአንጻሩ ደግሞ ህግን ተከትሎ የሚመጣው ደንበኛ ሲንገላታ ይስተዋላል። ችግሩ በተለይ በክ/ከተሞችና ወረዳዎች ላይ ሰፊውን ህዝብ ለእንግልት እየዳረገው ነው። በመሆኑም ከተማ አስተዳደሩ አፋጣኝ ማስተካከያዎችን እየወሰደ ይገኛል። "

#EPA

@tikvahethiopia
APS-Call-for-Applications_FY2022-final-1.pdf
280.5 KB
#ጥቆማ

በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ በፐብሊክ ዲፕሎማሲ በኩል የገንዘብ ድጋፍ እድሎች መኖራቸውን ጠቁሟል።

ማንኛውም ሰው በአሜሪካና ኢትዮጵያ መካከል ያለውን " የባህል ግንኙነት የሚያጠናክር " ፕሮፖዛል የጋራ እሴቶችን በሚያጎላ እና የሁለትዮሽ ትብብርን በሚያበረታታ የባህል ወይም የሚዲያ ልውውጥ በኩል ማቅረብ ይችላል።

👉 Funding Opportunity Title : U.S. Embassy Addis Ababa PAS Annual Program Statement

👉 Funding Opportunity Number : PAS-APS-FY22

👉 CFDA Number : 19.040-Public Diplomacy Programs

👉 Date Opened: March 21, 2022

👉 Deadline for Applications: June 01, 2022

👉 Maximum for Each Award :$200.000

👉 Federal Agency Email: PASAddisGrants@state.gov

ከላይ በPDF በተያያዘው ፋይል መመሪያዎችን በጥንቃቄ አንብበው ይከተሉ ፤ የመጨረሻው የፕሮፖዛል የማስረከቢያ ቀን እ.ኤ.አ. ሰኔ 18፣ 2022 ነው።

@tikvahethiopia
#አብን

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ከድርጅት ህገ-ደንብ እና አሰራር ውጭ በመሆን አፍራሽ ድርጊቶችንና የዲሲፕሊን ጥሰቶችን ፈፅመዋል ባላቸው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ላይ የእርምት ውሳኔ ማሳለፉን አሳውቋል።

የፓርቲው ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በ29/8/2014 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ነው በፓርቲው መዋቅር የተለያዩ የሃላፊነት እርከኖች ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ የዲሲፕሊን እና ድርጅታዊ መርህ ጥሰቶችን በተመለከተ ተወያይቶ የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ የተለያዩ ድንጋጌዎችን መሰረት በማድረግ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ያሳወቀው።

ፓርቲው በዚህ ውሳኔው የንቅናቄው የስራ አስፈጻሚ አባል አቶ ክርስቲያን ታደለን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ የሰጣቸው ሲሆን " የንቅናቄው ከፍተኛ አመራር ሆነው ሳለ ፣ የተጣለባቸውን ከፍተኛ ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው በተለያዩ አፍራሽ ድርጊቶች ላይ የተሳተፉ ሲሆን ፣ ከዚህ ቀደም ከድርጊታቸው እንዲታቀቡ ሁለት ጊዜ የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸዋል " ሲል ገልጿል።

" ይሁን እንጂ አሁንም በንቅናቄው ሥራ አስፈፃሚነታቸውም ሆነ በማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነታቸው በጋራ ለሚወሰኑ ውሳኔዎች ተገዥ ባለመሆን እና ንቅናቄውን ለማፍረስ ከሚንቀሳቀሱ አንጃኞች ጋር ሕብረት በመፍጠርና ፣ ንቅናቄው የሃሳብና የተግባር አንድነት እንዳይኖረው በሚያደርጉ ተግባራት ላይ ተሰማርተው ስተለገኙ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንዲሰጣቸው ተወስኗል " ብሏል።

በሌላ በኩል ፤ ፓርቲው 10 የመካከለኛ አመራሮች እና አባላትን ከድርጅቱ ያገደ ሲሆን ለሁለት የቋሚ ኮሚቴዎች አባላት ጥብቅ ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል።

(ተጨማሪ ዝርዝር መረጃ ከላይ በደብዳቤው ተያይዟል)

@tikvahethiopia