ፎቶ ፦ የነዳጅ ሰልፍ በአዲስ አበባ ከተማ !

ነዳጅ ለማግኘት ረጅም የሆኑ ሰልፎችን መጠበቅ ከተጀመረ ሰነባብቷል። ይህ ችግር በርካታ ጊዜያት ተደጋግሞ ቢነሳም መፍትሄ አልተገኘለትም።

በዚህ ምክንያት ዜጎች ሰዓታቸውን በነዳጅ ሰልፍ ሳይባክን ሰርተው ለመብላት የዕለት ገቢያቸውን ለማግኘት ፈተና እየሆነባቸው ነው።

ተሽከርካሪ ያላቸው ሰራተኞችም ስራቸውን እየተው ለነዳጅ እየተሰለፉ በመሆኑ ስራቸው እየተበደለ ነው።

ነዳጅ ላይ የዋጋ ማስተካከያ ቢደረግም በተባለው ዋጋ ለማግኘት እንኳን ፈተና ሆኗል። የዓለም ነዳጅ ዋጋ ንረት እንደተጠበቀ ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ እውነት በቂ ነዳጅ ስለሌለ/ስለማይገባ ነው ? ወይስ ያለውን በአግባቡ የማስተዳደር ችግር ? የሚለው የብዙዎች ጥያቄ ነው።

በክልል ከተሞች ማደያዎች ነዳጅ የለም ይላሉ ፤ ህገወጥ በሆነ መልኩ በየመንገዱ፣ በየሱቁ ላይ ሲሸጥ ይታያል ፤ ማደያዎች ለሊት ላይ በጄሪካን ለተለያዩ አካላት እንደሚቀዱ ነው የሚነገረው።

ይህን ለማስቆም ሰፊ ጥረት ሲደረግ አይታይም፤ ምክንያቱም ችግሩ ወራትን ስላስቆጠረ በዚህ ህገወጥ ድርጊት የሚሳተፉ እና እጃቸው ያለበት ብዙ አካላት እንዳሉ ግን እሙን ነው።

ይህ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ችግር ልጓም ካልተበጀለት የሚፈጥረው ቀውስ ከፍተኛ ነውና ትኩረትን ይሻል።

@tikvahethiopia