TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.3K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
ፎቶ ፦ ሀገራችን ኢትዮጵያ 🇪🇹 የደመቀችበት የቤልግሬድ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ዛሬ ቀጥሎ የተካሄደ ሲሆን ኢትዮጵያ ተጨማሪ ሜዳሊያዎችን አስመዝግባለች። ዛሬ በተካሄደ የ3000 ሜትር ውድድር ሰለሞን ባረጋ እና ለሜቻ ግርማ ተከታትለው በመግባት የወርቅ እና የብር ሜዳሊያ ለኢትዮጵያ አስገኝተዋል። የቤልግሬድ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ዛሬ ፍፃሜውን ያገኛል። ሁሉንም የስፖርታዊ ጉዳዮችን በ @tikvahethsport…
#ETHIOPIA

ኢትዮጵያ ከዓለም #1ኛ ሆና አጠናቀቀች።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮን ከዓለም አንደኛ ሆና አጠናቀቀች።

#አሜሪካ ሁለተኛ ፤ #ቤልጂየም ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ ፦

🥇4 ወርቅ፣
🥈3 ብር፣
🥉2 ነሃስ፣ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎች ማግኘት ችላለች።

እንኳን ደስ አላችሁ !

@tikvahethiopia
#አዲስ_የልብ_ህክምና

የልብዎ ጤንነት ያለበት ሁኔታ ያውቃሉ?
ሙሉ የልብ ምርመራ በማድረግ የልብዎ ጤንነት ያለበትን ደረጃ ይወቁ። ይሄን ጥቅል በመግዛት ለወዳጅ ዘመዶ ያበርክቱ

ዛሬዉኑ ደዉለዉ ቀጠሮ ያስይዙ
0952343434

Telegram 👉:https://publielectoral.lat/addiscardiachospitalplc

ለልብዎ ከልብ እንሰራለን
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA ኢትዮጵያ ከዓለም #1ኛ ሆና አጠናቀቀች። ሀገራችን #ኢትዮጵያ በቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮን ከዓለም አንደኛ ሆና አጠናቀቀች። #አሜሪካ ሁለተኛ ፤ #ቤልጂየም ደግሞ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል። በቤልግሬድ 2022 የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ኢትዮጵያ ፦ 🥇4 ወርቅ፣ 🥈3 ብር፣ 🥉2 ነሃስ፣ በድምሩ 9 ሜዳሊያዎች ማግኘት ችላለች። እንኳን ደስ አላችሁ…
#USA

አሜሪካ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላለፈች።

አሜሪካ እዚህ አዲስ አበባ በሚገኘው ኤምባሲዋ በኩል ፤ በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና አስደናቂ ብቃትን ላሳዩ መላው የኢትዮጵያ አትሌቶች " እንኳን ደስ አላችሁ " መልዕክት አስተላልፋለች።

ሀገራችን #ኢትዮጵያ በቤልግሬድ የዓለም የቤት ውስጥ ሻምፒዮን ከዓለም #አንደኛ ሆና ማጠናቀቋ ይታወቃል።

አሜሪካ ከኢትዮጵያ በመቀጠል ከዓለም ሁለተኛ ደረጃን ይዛ ነው የጨረሰችው።

@tikvahethiopia
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ምንድነው ያሉት ?

#ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት አንድ ተቀማጭነቱን ውጭ ሀገር ላደረገ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከሰሞኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈፀመውን የሰው ልጆችን በእሳት የማቃጠል ድርጊት " አረመኔያዊ " ሲሉ በማውገዝ የተሰማቸውን ከባድ ሀዘን ገልፀዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በዚህ ንግግራቸው ድርጊቱ " አለምን ያሳዘነ ፤ የአረመኔነት ድርጊት ነው " ሲሉ ገልፀዋል።

ብፁዕነታቸው " ባለፈው 2013 ዓ/ም ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ያላየነው ያልሰማነው " የለም ያሉ ሲሆን " በትግራይ ህዝብ ላይ የደረሰው መከራ እጅግ የሚያሳዝን እጅግ የሚያስለቅስ ነው፤ መፈጠረን ሁሉ የሚያስጠላ ድርጊት ተፈፅሟል " ብለዋል።

ነገር ግን የአሁኑ ድርጊት ከሁሉ የባሰ ነው ብለውታል።

ከሰሞኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከተፈፀመው ድርጊት በተጨማሪ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከዚህ ቀደም በትግራይ ክልል ተፈፅሟል ያሏቸውን የጭካኔ ተግባራት ዘርዝረዋል።

" በትግራይ ክሊኒኮች፣ ሆስፒታሎች ፣ ት/ቤቶች ፣ መድሃኒት ቤቶች ፋብሪካዎች በጠቅላላ ወድመዋል፣ የቀረ ነገር የለም አሁን ደግሞ እንደገና ህፃናት በእናቶች እቅፍ ሆነው፣ ምግብ አጥተው እያለቀሱ እንደቅጠል ደርቀው በምግብ እጦት በእናቶቻቸው እቅፍ ሲሞቱ ፤ እናቶቻቸው እያለቀሱ ጡት እንዳያጠቧቸው እነሱም እራሳቸው በረሃብ ስለደረቁ ወተት የለም እንደዚህ ያለውን ሁኔታ እያየን ነው " ብለዋል።

ብፁዕነታቸው እከዛሬ የሆነው ሆኗል ፣ የጠፋው ጠፍቷል፣ የሞተው ሞቷል፣ ያለቀው አልቋል፤ አሁን ግን ቢበቃ ሲሉ ተደምጠዋል።

" ሀዘናቸው እጅግ ከባድ " መሆኑን የገለፁት ብፁዕነታቸው " ይሄ የሁሉም የኢትዮጵያዊያን በተለይም የትግራይ ህዝብ ሀዘን ነው እና መከራው ግን በሁሉም ደርሷል ቀስ እያለ እየተስፋፋ በመላ ኢትዮጵያ ደርሷልና በቃው ከእንግዲህ ወዲህ ምናለ ለተረፈው ህዝብ ይቅርታ ቢደረግለት ወይም ደግሞ ቢያሳዝነን ለምን እንዲህ አይነት ችግር ይፈጠራል ፤ ይብቃ " ሲሉ ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው ፤ በትግራይ ክልል ስላለው ሁኔታ ለመናገር እስካሁን እድል እንዳላገኙ በመግለፅ ፤ ከዚህ በፊት ሾልኮ የወጣውን ቪድዮ ላይ ሁኔታውን ለመግለፅ ከሞከሩበት ውጭ ሌላ እድል አግኝተው እንደማያውቁ አስረድተዋል።

ከዚህ በፊት ሾልኮ በወጣ ቪድዮ ላይ ብፁዕ አቡነ ማትያስ በትግራይ ያለውን ሁኔታ ከተናገሩ በኃላ በወቅቱ ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆኖ እንደነበር አይዘነጋም።

ቅዱስ ፓትርያርኩ መነጋገሪያ ሆኖ በነበረው ቪድዮ ትግራይ ክልል ውስጥ ይሰራል ያሉት አረመኒያዊ ስራ እንዲቆም ያቀረቡት ጥይቄ አለመሳካቱን ፤ ፍቃድም እንዳልተሰጠ ገልፀው ሚናገሩት ሁሉ በተደጋጋሚ እንደሚመለስና ፍቃድ እንዳላገኙ ተናግረው ነበር።

ከዚህ በኃላም የቤክርስትያኒቱ ሲኖዶስ ዋና ፀሀፊው ብጹዕ አቡነ ዮሴፍ ሰጥተው በነበረው መግለጫ ፤ የትኛውም መልዕክት ከመተላለፉ በፊት በሲኖዶስ በሚደረግ ስብሰባ ውሳኔ ሊሰጠው እንደሚገባና አቡነ ማትያስ ያስተላለፉት የግል አቋም እንጂ የሲኖዶሱ ውሳኔ እንዳልሆነ አሳውቀው ነበር።

የቅዱስ ፓትርያርኩ ፤ የሰሞኑ ንግግር የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሚወክል ስለመሆን ፤ አለመሆኑ ቅዱስ ፓትርያርኩ በግልፅ አልተናገሩም ፤ አልያም ከዚህ ቀደም እንደነበረው በሲኖዶስ በኩል የተገለፀ ነገር እስካሁን የለም።

ቅዱስ ፓትርያርኩ የተናገሩትን ሙሉውን ያንብቡ 👇

https://telegra.ph/Holiness-Abune-Mathias-03-20
TIKVAH-ETHIOPIA
" .. የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው ይራዘምልን " - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ጠየቀ። ቢሮው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በጣም ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎቻችን ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሸላቸው እያመለከቱ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪ…
" ከ13, 862 ተፈታኞች 3,006 ተማሪዎች ብቻ ናቸው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ያስመዘገቡት " - የአዊ ብሔ/አሰ ትምህርት መምሪያ

በአማራ ክልል፤ የአዊ ብሔረሰብ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ከ13 ሺ 862 ተፈታኞች 3 ሺህ 6 ተማሪዎች ብቻ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ማስመዝገባቸዉን አሰታወቀ።

የመምሪያዉ ኃላፊ አቶ አለሙ ክህነት ፤ በ2013ዓ.ም በብሔረሰብ አስተዳደሩ በ29 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ 13 ሺህ 862 ተማሪዎች ሀገርአቀፋ ፈተና መፈተናቸውን ገልጸዋል።

ከነዚህም ዉስጥ በብሄረሰቡ ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ደረጃ 3 ሺህ 6 ተማሪዎች ብቻ ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም የመግቢያ ዉጤት ማምጣታቸውን ነዉ ሀላፊዉ የተናገሩት።

አጠቃላይ የማለፋ ምጣኔም 21.7% ብቻ መሆኑ ተገልጿል።

ከተፈተኑት የተፈጥሮ ሳይንስ 5 ሺህ 745 ተማሪዋች መካከል 1 ሺህ 943 የመግቢያ ዉጤት አምጥተዋል። በማህበራዊ ሳይንስ ደግሞ ከተፈተኑት 8 ሺህ 117 ተማሪዎች ዉስጥ 1 ሺህ 63 ወደ የመግቢያ ዉጤት ያመጡ መሆናቸዉን ተገልጿል።

የእርማት ጥራት ችግር ማሳያ 140 ያመጣ ተማሪ እንደገና ሲፈተሸ 601 ፣ የሲቪክስ ት/ት ፈተና ችግር በሌለበት አካባቢ መሰረዝ እና የፈተና አስተዳደር ስርዓቱ በአግባቡ የተመሩ ባለመሆናቸዉ ለተመዘገበዉ ዝቅተኛ ዉጤት ተጠቃሽ ሞክንያቶች መሆኑን ትምህርት መምሪያው ገልጿል።

የፈተና ስርዓቱ ስለመታወኩ በተለያዩ ቴክኖሎጂዎች ቼክ ተደርጎ እንደገና መፈተሽ እንዳለበት ከሚመለከተው ጋር እየሰራ መሆኑን መምሪያው አሳውቋል።

እስከአሁንም መምሪያዉ ከክልሉ ትምህርት ቢሮ ጋር የፈተና ሂደቱ እንደገና እንዲታይ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጾ ተማሪዎች እና የተማሪ ቤተሰቦች በትግስት እንዲጠብቁ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#NewsAlert

ቻይና ውስጥ 133 መንገደኞችን አሳፍሮ ሲበር የነበረ ቦይንግ 737 አውሮፕላን መከስከሱን የቻይና መገናኛ ብዙኃንን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል።

የቻይና ኢስተርን አየር መንገድ ንበረት የሆነው ይህ ቦይን 737 ወድቆ መከስከሱ የተነገረው ጓንግዡ ግዛት ውስጥ ነው።

አስካሁን በአደጋው ጉዳት ስለደረሰባቸው ሰዎች የታወቀ ነገር የለም።

የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት አውሮፕላኑ ወድቆ የተከሰከሰው በተራራማ አካባቢ ሲሆን በስፍራው ባለ ጫካ ላይ እሳት ተነስቷል።

ይህ ቦይንግ 737 አውሮፕላን በበረራ ቁጥር ኤምዩ5735 በቻይና የሰዓት አቆጣጠር ከእኩለ ቀን በኋላ ከኩንሚንግ ተነስቶ ወደ ጓንግዡ እያመራ ነበር ተብሏል።

የነፍስ አድን ሠራተኞች ወደ የአደጋው ስፍራ መሰማራታቸውን የቻይና ብሄራዊ ቴሌቪዝን መዘገቡን ቢቢሲ ፅፏል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
" .. የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው ይራዘምልን " - የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መግቢያ ጊዜው እንዲራዘም ጠየቀ። ቢሮው የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ውጤት ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ እጅግ በጣም ሰፊ ቁጥር ያላቸው ተማሪዎቻችን ውጤታቸው እንደገና እንዲፈተሸላቸው እያመለከቱ መሆኑን ገልጿል። በተጨማሪ…
#Update

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን ፈተና የሚያጣራ ቡድን ወደ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አግልግሎት መላኩን ዛሬ አስታወቀ።

የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የክልሉ ተማሪዎች የውጤት ችግር መግጠሙን ተከትሎ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል ብሏል።

የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ችግሩን ለመፍታት በርካታ ተግባራትን ሲፈጽም መቆየቱን ገልጾ በአሁን ሰዓት ፦
👉 ከክልሉ ትምህርት ቢሮ አመራሮቸና ባለሙያዎች ፣
👉 ከአማራ ምሁራን መማክርት ጉባኤ ፣
👉 ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን ፣
👉 ከትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራንና መምህራን የተውጣጣ ቡድን ወደ ትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አግልግሎት መላኩን አሳውቋል።

@tikvahethiopia
#አቢሲንያ_ባንክ

አፍላ ለወጣቶች የተዘጋጀ ልዩ የቁጠባ ደብተር!

ባንካችን አቢሲንያ ትኩስ ጉልበት እና ኃይል ያለቸው ወጣቶች በ አፍላ እድሜያቸው በመቆጠብ የራሳቸውን ስኬት በመገንባት ላይ እንዲያተኩሩ የሚጋብዝ የቁጠባ ደብተር አዘጋጅቶአል።

አፍላ የቁጠባ ደብተር ከፍተኛ ወለድ መጠን ያለው እንዲሁም የብድር ወለዱ አነስተኛ በመሆኑ ወጣቶች ከዛሬ ጀምረው በመቆጠብ የእድሉ ባለቤት እንዲሆኑ ባንካችን ይጋብዛል፡፡

#BankofAbyssina #YouthSavingAccount # #AddisAbaba #Ethiopia #የሁሉም_ምርጫ
#BenishangulGumuz📍

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአለም አቀፍ የስደተኞች ተቋም / IOM / እና አክሽን ፎር ዘ ኒዲ ኢን ኢትዮጵያ በተባሉ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፍ የሚካሄድ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ።

ይህ ፕሮጀክት ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት እንደተመደበለት የተገለፀ ሲሆን በክልሉ ላሉ ተፈናቃዮች የጊዜያዊ መጠለያ ግንባታ ይከናወናል ተብሏል።

ፕሮጀክቱ በመተከል እና ካማሺ ዞኖች እንዲሁም ማኦ ኮሞ ልዩ ወረዳዎች እንደሚካሄድ  ታውቋል።

ተፈናቃይ ወገኖችን ለማቋቋም የተደረገው ጥረት የሚበረታታ ቢሆንም ከተፈናቃዮች ቁጥር አንጻር  ችግሩን መፍታት እንዲቻል መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ጠይቋል።

መንግስት ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ ከማቀድ ጀምሮ  ለተፈናቃዮች የእለት ደራሽ ድጋፍ እያቀረበ መሆኑን የገለፀው የክልሉ መንግስት ጊዜያዊ መጠለያ ለመስራት የተጀመረው ፕሮጀክትም የዚሁ ማሳያ ነው ማለቱን ኢዜአ ዘግቧል።

ከክልሉ አደጋ ስጋት እና ስራ አመራር ኮሚሽን በተገኘው መረጃ በክልሉ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ተፈናቃዮች በጊዜያዊ መጠለያ እና በግለሰቦች ቤት ተጠግተው ይኖራል።

@tikvahethiopia
#SafaricomEthiopia

በቅርቡ ስራ ይጀምራል ተብሎ የሚጠበቀው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር ስምምነት ተፈራርሟል።

ስምምነቱ በአዲስ አበባ እና በመላ ኢትዮጵያ በሚገኙ ነባር የኮንክሪት ምሰሶዎች ላይ የሳፋሪኮም ኢትዮጵያን ኢንተርኔት አገልግሎት ማሰራጫ የአየር ላይ ገመድ ለመዘርጋት የሚያስችል መሆኑን ሳፋሪኮም አሳውቆናል።

ስምምነቱ 3 ዓመታት የሚዘልቅ መሆኑም ተገልጾልናል።

የአየር ላይ ገመዶች ለጥገና እና ለአገር አቀፍ ዝርጋታ አንጻራዊ ቅለት ያለው ነው፡፡

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና የሥራ አስፈጻሚ የሆኑት አኑዋር ሱሳ ፦ “ አገልግሎቶቻችን በተለያዩ ደረጃዎችና ሂደት የምንጀምር ሲሆን ይህንን ለማሳካት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ጋር አብረን በመሥራታችን ትልቅ ኩራት ይሰማናል፡፡ " ብለዋል።

አክለው ፤ " ይህ የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ የአጋርነት ስምምነት ለኔትወርክ ግንባታችን የሚያስፈልጉንን ትክክለኛ ግብዓቶች እንድናገኝ፣ ግንባታችንንም በጠንካራ መሠረተ ልማት ላይ እና ከልዩ ልዩ አጋሮች ጋር ለመሥራት ምሳሌ የሚሆን ድጋፍ ላይ ተመርኩዘን እንድንቀጥል ያስችለናል” ሲሉ ተናግረዋል።

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ አዲስ ኔትወርክ እየገነባ በሚገኝበት በዚህ ወቅት፣ በመላው ኢትዮጵያ በሁሉም ቤቶች እና የንግድ ሥራ ድርጅቶች ከፍተኛ ፍጥነት ያለው የኢንተርኔት ተደራሽነትን ለማረጋገጥ በመሠረተ ልማትና በስትራቴጂክ አጋርነት ላይ ለሚደረጉ ኢንቨስትመንቶች ቅድሚያ እየሰጠ እንደሚገኝ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ምንድነው ያሉት ? #ብፁዕ_ወቅዱስ_አቡነ_ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት አንድ ተቀማጭነቱን ውጭ ሀገር ላደረገ የቴሌቪዥን ጣቢያ ከሰሞኑን በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈፀመውን የሰው ልጆችን በእሳት የማቃጠል ድርጊት " አረመኔያዊ " ሲሉ በማውገዝ የተሰማቸውን ከባድ ሀዘን ገልፀዋል። ብፁዕ ወቅዱስ…
#Update

የኢትዮጵያ መንግሥት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ንግግርን ተቃወመ።

የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ ለዶቼቨለ በሰጡት ቃል ፤ " ያቀረቡት ትችት ለአንድ ወገን ያደላ ነው፤ መረጃውም በጣም ስህተት አለበት ፤ ሆን ብሎ መንግስት ላይ ጫና እንዲፈጠር አሁን በተለይ በአሜሪካ የተጀመረው ኢትዮጵያ ላይ ተጨማሪ ጫና ለመፍጠር / ማዕቀብ ለመጣል የሚደረገውን ሁኔታ ያግዛል ብለው ፤ ሆን ተብሎ ተዘጋጅተውበት ያደረጉት ነገር ነው እንጂ በተጨባጭ መረጃ የተደገፈ አይደለም " ብለዋል።

" ቅዱስ ፓትርያርኩ ወገንተኛ ሆነዋል " ያሉት ሚኒስትሩ የTPLFን የፖለቲካ እሳቤ የሚጋሩ ናቸው ያንን ነው እያደረጉ ያሉት ብለዋል።

ዶ/ር ለገሰ " እሳቸው ታፍኛለሁ ይላሉ ማን እንዳፈናቸው ግልፅ አይደለም ፤ እንደፈለጉ እየተናገሩ ነው። የTPLF የፖለቲካ እሳቤን የሚጋሩ በመሆናቸው ያ ሃሳብ ተጠናክሮ እንዲሄድላቸው ስለሚፈልጉ እንጂ እውነታውን ስለማያውቁ አይደለም። እውነታውን የሚናገሩ ቢሆን በአማራ ላይ ስለደረሰው ነገር ይናገሩ ነበር ፤ አፋር ላይ ስለተፈጠረው ነገር ይናገሩ ነበር። ስለዚህ የTPLF የፕሮፖጋንዳ ማሽን ሆነው ነው እሳቸው እያገለገሉ ያሉት ፣ ከሃይማኖታዊ አባትነት ውጭ ማለት ነው። ዞሮ ዞሮ መንግስት ይሄ ተገቢ አይደለም ይላል። ህዝብን ለመከፋፈል የሚያደረጉት ተገቢ አይደለም " ሲሉ ተደምጠዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከቀናት በፊት ባሰሙት ንግግር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተፈፀመውን የሰው ልጆችን በእሳት የማቃጠል ድርጊት " አረመኔያዊ " ሲሉ በማውገዝ የተሰማቸውን ከባድ ሀዘን ገልፀው ነበር። በትግራይና በትግራይ ተወላጆች ላይ ደርሷል ያሉትን ሁሉ በዝርዝር ተናግረውም ነበር።

@tikvahethiopia