TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
ሩስያ ፥ ስዊድንን እና ፊንላንድን አስጠነቀቀች።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስዊድን እና ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል ከሞከሩ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ] እንደሚኖሩ አስጠንቅቋል።

አሁን በዩክሬን እና ሩስያ መካከል ያለው ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ሩስያ ፊንላንድ እና ስዊድንን ማስፈራራቷ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ፈጥሯል።

የኃያላን ሀገራቱ ግብግብ በተለይ እንደኛ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ላይ ይዞት የሚመጣው መዘዝ እንዲሁ በቀላሉ የሚታይ አይደለም።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Photo
#ETHIOPIA

የነዳጅ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

መንግስት የነዳጅ ዋጋ ከየካቲት 19 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ባለበት እንዲቀጥል መወሰኑን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ማስታወቁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ውሳኔው ከቀላል ጥቁር ናፍጣ፣ ከባድ ጥቁር ናፍጣ እና ከአይሮኘላን ነዳጅ በስተቀር በሌሎች የነዳጅ ዓይነቶች መሸጫ ዋጋ ላይ ተግባራዊ የሚደረግ መሆኑም ነው የተገለፀው።

ይህም የኢኮኖሚና ማህበራዊ እንቅስቃሴዎች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲቀጥል ለማስቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በዓለም ገበያ የሚኖረውን የነዳጅ ዋጋ መነሻ በማድረግ እንደአስፈላጊነቱ ማስተካከያ ሊደረግ የሚችል መሆኑም ተጠቁሟል።

ሚኒስቴሩ መንግስት የነዳጅ ምርት ከገዛበት ውድ ዋጋ በግማሽ ለህብረተሰቡ በሽያጭ እያስተላለፈ ይገኛል ብሏል።

በመሆኑም ህብረተሰቡ ምርቱን በከፍተኛ ቁጠባ የመጠቀም እንዲሁም የብዙሃን ትራንስፖርትን የመጠቀም ልምድ ሊያዳብርና በነዳጅ ምርቶች ግብይት ላይ የሚፈፀሙ ህገ ወጥ ተግባራትን በማጋለጥ ከፀጥታ አካላት ጋር በትብብር ሊሠራ እንደሚገባ አሳስቧል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሩስያ ፥ ስዊድንን እና ፊንላንድን አስጠነቀቀች። የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ስዊድን እና ፊንላንድ NATOን ለመቀላቀል ከሞከሩ " ጎጂ " የሆኑ ውጤቶች [ ኢኮኖሚያዊ እና ወታደራዊ ] እንደሚኖሩ አስጠንቅቋል። አሁን በዩክሬን እና ሩስያ መካከል ያለው ጦርነት ተባብሶ በቀጠለበት ሁኔታ ሩስያ ፊንላንድ እና ስዊድንን ማስፈራራቷ ሌላ ዓለም አቀፋዊ ስጋት ፈጥሯል። የኃያላን ሀገራቱ ግብግብ በተለይ…
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#UPDATE

NATO ምላሽ ሰጪ ኃይል አባላቱን ሊያሰማራ ነው።

የNATO መሪዎች በኦንላይን ስበሳባቸው አድርገው ነበር።

ከስብሰባው በኃላ በተሰጠ መግለጫ በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ NATO " የፈጣን ምላሽ ሰጪ ኃይል (NRF) አባላቱ በምስራቅ አውሮፓ ሊያሰማራ መሆኑን ገልጿል።

ኃይሉን ሚያሰማራው በየብስ፣ በባህር እና በአየር ላይ መሆኑ ተነግሯል።

ይሄ ማለት ግን ዩክሬን ይገባሉ / ወደ ዩክሬን ገብተው ከሩስያ ጋር ውጊያ ይገጥማሉ ማለት አይደለም ምክንያቱም ዩክሬን የNATO አባል አይደለችም።

የNATO ዋና ጸሃፊው ጄንስ ስቶልተንበርግ ፤ " እያንዳንዱን አጋር እና እያንዳንዱን ኢንች የNATO ግዛት ለመጠበቅ እና ለመከላከል አስፈላጊውን እናደርጋለን " ሲሉ ተናግረዋል።

አጠቃላይ የNATO ምላሽ ሰጪ ኃይል 40 ሺህ የሚደርስ ሲሆን አሁን ላይ እንዲንቀሳቀስ የሚደረገው ምን ያህሉ እንደሆነ የታወቀ ነገር የለም። ሁሉም እንደማይሰማራ ግን ታውቋል።

የNATO ምላሽ ሰጪ ኃይል ለደህንነት እና የፀጥታ ችግር ፈጣን የሆነ ምላሽ ለመስጠት በቀን 24 ሰዓት በሳምንት 7 ቀን በዓመት 365 ቀናት ዝግጁ የሆነ ኃይል ሲሆን የNATO አጋሮች በየአመቱ የሚቀያየር ሃይል ያበረክታሉ።

የመሬት ፣ የአየር ፣ የባህር እንዲሁም የልዩ ኦፕሬሽን ሃይሎችን ያቀፈም ነው። NRF በአደጋ ጊዜ የማዳን ተልዕኮ ለመወጣት እና በቀውስ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት በከፍተኛ ተጠንቀቅ ላይ ያለ እጅግ የዘመኑ መሳሪያዎችን የታጠቀ ኃይል ነው።

@tikvahethiopia
#Oromia, #GujiZone📍

በኦሮሚያ ክልል ጉጂ ዞን 5 ወረዳዎች በከፊል እና ሙሉ በሙሉ በህ/ተ/ም/ቤት ሽብርተኛ ተብሎ በተፈረጀው ኦነግ ሸኔ/እራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት እያለ በሚጠራው ታጣቂ ኃይል ቁጥጥር ስር መሆኑን ነዋሪዎች እና ባለስልጣናት አሳውቀዋል።

ታጣቂዎቹ የተቆጣጠሯቸው አከባቢዎች ፦

- አርሶ አደር ማምረት አቁሟል።
- ሰዎች ለተለያዩ እንግልትና ሰቆቃ ይዳረጋሉ።
- የማህበራዊ አገልግሎትና የመንግስት ስራም በሙሉ ተቋርጧል።
- ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለዋል።
- ጤና ጣቢያዎችም አገልግሎት አይሰጡም።

በጉጂ ዞን የጉሚ ኤልዳሎ ወረዳ ነዋሪ ሳራ ጅብቻ ፦

" ... ጉሚ ኤልዳሎ በሸማቂዎቹ ስር ከገባች አራተኛ ወር እያስቆጠረ ነው፡፡

እኛ ለዓመታት በጦርነት ውስጥ ነው ያሳለፍነው፡፡ አሁንም ሰላም እንደራቀን ነው፡፡ ባንድ በኩል ድርቅ በሌላው ደግሞ ግጭት ጦርነቱ እያሳደደን ግራ በተጋባ ህይወት ውስጥ ነን፡፡

ድርቁ ከብቶቻችንን እየገደ ለርሃብ ሲዳርገን፣ የፀጥታ ችግሩ ደግሞ ትራንስፖርት እንኳ እንዳይኖር በማድረግ የተራቡት ለሞት እየዳረገ ነው፡፡

ሰው በርሃብም በጥይትም በየቀኑ ነው የሚሞተው፡፡ ስቃይ ውስጥ ነን፡፡ "

የዋደራ ከተማ ነዋሪ (ስማቸውን መግለፅ ያልፈለጉ)፦

" ... ካለሁበት ከተማ ውጪ ያሉ በርካታ የገጠር ቀበሌዎች በታጣቂዎች ቁጥጥር ስር ናቸው።

ይህቺ ከተማ ዙሪያዋ በድን የተከበበ ነው፡፡ 3 እና 5 ኪሎ ሜትር ወጣ ብትል እንኳ ታጣቂዎች ተሰግስገውበታል፡፡ ከዚህ ከተማ ሰው በየትኛውም አቅጣጫ ስወጣ እያገቱ ብር ይለቅማሉ፡፡

ሰው ያለውን ሁሉ ይዘረፋል፡፡ ከገጠር ቀበሌዎችም እየተነሱ ይሄው ወደ ከተማዋ እየተሰደዱ ነው፡፡ የመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ሲወጡ በቦታው አያገኙዋቸውም፡፡ ከመንግስት አቅም በላይ ሆኗል ለማለትም ሆነ መንግስት አከባቢውን እያስተዳደረ ነው ለማለት ተቸግረናል። ”

የጉጂ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ ኃላፊ ዮሓንስ ኦልኮ ፦

" በዞኑ 5 ወረዳዎች በከፊል እና ሙሉ በሙሉ በታጣቂዎች እጅ ስር በመውደቃቸው ከፍተኛ የሆነ ቀውስ ተከስቷል፡፡ ሰው በቁም ከመቀበር ጀምሮ በነዚህ አምስት ወረዳዎች አስከፊ የሆኑ ሰቆቃዎች በህብረተሰቡ ላይ ይፈጸማል፡፡ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የሚሰሩ ይገደላሉ፤ ተቋማቱም ይዘረፋሉ ሰዎች እየታገቱ ብር የሚጠየቅባቸው ብዙ ናቸው "

ያንብቡ : https://telegra.ph/DW-02-25

@tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Afar

የዓለም ምግብ ፕሮግራም [ WFP ] በአፋር ክልል በጦርነት ለተጎዱ ወገኖች ድጋፍ እያደረገ መሆኑን አሳውቋል።

ድርጅቱ በአፍዴራ፣ ያሎ፣ሲልሳ ለሚገኙ የውስጥ ተፈናቃዮች እና በሰመራ ከተማ ላሉ ስደተኞች እህል እያደረሰ እንደሚገኝ ገልጿል።

ባለፉት ቅርብ ሳምንታት በመላው WFP በአፋር ፦

➡️ በ14 ወረዳዎች ላሉ 520,000 ሰዎች የነፍስ አድን ምግብ አቅርቧል።

➡️ ለ80,000 እናቶች እና ህፃናት የወሳኝ ምግብ ድጋፍ አድርጓል።

በሌላ ከአፋር ጋር በተያያዘ መረጃ የተመድ የሰብዓዊ ድጋፍ ማስተባበሪያ ፥ በአፋር የተለያዩ ቦታዎች በዋነኝነት በበርሃሌ ፣ ኤሬብቲ፣ ኮነባ፣ አብዓላ ወረዳዎች እና በከልበቲ ዞኑ ሙሉ አሁንም ግጭቶች ስለመኖራቸው የከባድ መሳሪያ እና የአየር ጥቃቶች ፣ ስለመኖራቸው አመልክቷል።

በክልሉ ባለው ጦርነት እስካሁን በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች መፈናቀላቸውን አሁንም ተፈናቃዮች እየተመዘገቡ መሆኑና በዚህም ምክንያት የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎቱ በእጅጉ መጨመሩን ገልጿል።

@tikvahethiopia
#UNSC

ትላንትና ሌሊት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ሩሲያ በዩክሬን ላይ " ወረራ " ፈፅማለች በሚል ለማውገዝ በምዕራባውያን የሚመራ የውሳኔ ሃሳብ ቢቀርብም ሩስያ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን [ veto power ] በመጠቀም #ውድቅ አድርጋዋለች።

ቻይናም በውሳኔ ሀሳቡ ላይ ድምፅ ከመስጠት ታቅባለች።

የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ እነማን ደገፉት ? ማን ተቃወመ ? እነማን ድምፃቸው አቀቡ ?

#የደገፉ_ሀገራት

🇺🇸 አሜሪካ
🇬🇧 ዩናይትድ ኪንግደም
🇫🇷 ፈረንሳይ
🇳🇴 ኖርዌይ
🇮🇪 አይርላድ
🇦🇱 አልባኒያ
🇬🇦 ጋቦን
🇲🇽 ሜክስኮ
🇧🇷 ብራዚል
🇬🇭 ጋና
🇰🇪 ኬንያ

#የተቃወሙ

🇷🇺 ሩስያ

#ድምፀ_ተአቅቦ_ያደረጉ

🇨🇳 ቻይና
🇮🇳 ሕንድ
🇦🇪 ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ (UAE)

@tikvahethiopia
#EOTC

አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ህመም አጋጥሟቸው ሆስፒታል ይገኛሉ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስም ሆስፒታል በመገኘት ጠይቀዋቸዋል።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በሕመም ምክንያት በሆስፒታል ሕክምናቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙትን 4ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ዛሬ ረፋድ ላይ በሆስፒታል በመገኘት እግዚአብሔር ምሕረቱን እንዲልክላቸው ጸሎት በማድረስ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

በጉብኝቱ ብፁዕ ጠቅላይ ዋና ስራአስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ እና የልዩ ጽ/ቤት የሥራ ሓላፊዎች ቅዱስነታቸውን በማጀብ መገኘታቸውን የቅዱስ ፓትርያርኩ ልዩ ጽሕፈት ቤት ዘገባ ያመላክታል።

@tikvahethiopia
#Woldia

የእሳት አደጋ ባልና ሚስትን ህጻን ልጃቸውን ጨምሮ ለሞት ዳረገ።

ወልድያ ከተማ በ06 ቀበሌ " ጎልጎታ " ተብሎ በሚታወቀው ሰፈር የካቲት 18 ለ19/2014 ዓ.ም አጥቢያ ሌሊት በደረሰ የእሳት አደጋ ባልና ሚስትን ህጻን ልጃቸው ጨምሮ ለሞት ሲዳርግ 3 ሰዎችን በቃጠሎ ለቁስለት ዳርጓል።

3ቱ ቁስለኞች በወልድያ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

የእሳት አደጋው መንስኤና ንብረት ላይ የደረሰውን አጠቃላይ ጉዳት እየተጣራ መሆኑን የወልዲያ ከተማ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ሄሜቲ ሞስኮ ምን ይሰራሉ ? የጎረቤታችን ሀገር ሱዳን ሉአላዊው የሽግግር ም/ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ሩስያ፣ ሞስኮ ይገኛሉ። የሄሜቲ የሩስያ ጉብኝት በምዕራባውያን ሀገራት እና በሱዳን ወታደራዊ ክንፍ መካከል ውጥረት ባለበት እንዲሁም በዩክሬን ጉዳይ ምዕራባውያን ሩስያን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማግለል ማዕቀብም ለመጣል እየዛቱ ባሉበት ወቅት ነው። ሄሜቲ በትዊተር…
#SUDAN #RUSSIA

የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ም/ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ሩስያ ሞስኮ የሚገኙ ሲሆን ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል።

ሄሜቲ ከሩስያ ምክትል ጠ/ሚ አሌክስአንደር ኖቫክ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

ይኸው ጉዧቸው ሀገራቸውና ወታደራዊ መንግስታቸው ከምዕራብ ሀገራት ያገኝ የነበረው የገንዘብ ድጋፍ ስለተቋረጠ ከሩሲያ ድጋፍ ለማግኘት እየጣረ መሆኑ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

ሳመህ ሳልማን የተባሉ የምጣኔ ኃብት ተንታኝ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የሄሜቲ የሞስኮ ጎብኝት በምጣኔ ሃብት ቅውስ ውስጥ ከምትገኘው ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር እንደሚታይ ያስረዳሉ።

አሜሪካ እና ምዕራብ ሀገራት ይሰጡት የነበረውን የገንዘብ ድጋፍ ካቋረጡ እና የሱዳንን ብድር ለመሰረዝ ያስተላለፉት ውሳኔ ከሰረዙ ወዲህ የሱዳን ምጣኔ ኃብቷ ይዟታ በእጅጉ እንደተዳከመ ገልፀዋል።

የሀገሪቱ መገበያ ገንዘብ #ከዶላር ጋር ያለው ንጽጽር እየሰፋ በመጣበት በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የሸቀጦች ውድነት ከቀዳሚዎቹ መካከል ሆኗልም ብለዋል።

አሜሪካ በጀነራል ሄሜቲ እና ሌ/ ጄኔራል አብድል ፈታ አልቡራንን በመሰሉ የጦር አመራሮች ላይ ድንገት ማዕቀቦች ከጣለች በሚል ሱዳን የሩሲያን ድጋፍ ለማግኘት እየጣረች ሊሆን ይችላል ሲሉ ሳማህ ሳልማን ጠቁመዋል።

ካሜሮን ሀድሰን የተባሉ አትላንቲክ ካውንስል ውስጥ የሚሰሩ የአፍሪካ ጉዳዮች ተንታኝ በበኩላቸው የአሁኑ የሱዳንና ሩሲያ ግንኙነት ከኢኮኖሚ ፍላጎት በዘለለ የስትራቴጂ ሽግሽግ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ለቪኦኤ ጠቁመዋል።

ፎቶ ፦ የሄሜቲ ትዊተር ገፅ

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update " ብቻችንን አጋፍጠውናል " - ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌኒስኪ " ብቻችንን አጋፍጠውናል " ሲሉ ምዕራባውያንን ወቅሰዋል። ዜሌኒስኪ " ሃገራችንን ለመጠበቅ በብቸኝነት እየተዋጋን ያለነው እኛው ነን " ሲሉ ተናግረዋል፡፡ " ማን አግዞን ከጎናችን ሆኖ ተዋጋ? " ሲሉ የሚጠይቁት ፕሬዝዳንቱ " ማንም "ሲሉ መልሰዋል። " ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደተወን ነው የተሰማኝ፤…
#Ukraine #USA

" ከሀገር እናስወጣህ " - አሜሪካ

" ውጊያው ያለው እዚህ ነው። የምፈልገው የጦር መሳሪያ እንጂ የማምለጫ መንገድ አይደለም " - የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ


እንደ ዋሽንግተን ፖስት መረጃ አሜሪካ ፕሬዝዳንት ዜሌንስኪን ከሀገራቸው እንዲወጡ ለመርዳት ተዘጋጅታ ነበር ነገር ግን እሳቸው ከሀገራቸው ንቅንቅ እንደማይሉ ገልፀዋል።

ፕሬዜዳንቱ ትላንት በሰጡት መግለጫ ላይ #ምዕራባውያንን ክፉኛ መተቸታቸውና ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ እንደተዋቸው እንደሚሰማቸው መግለፃቸው ይታወሳል።

ፕሬዜዳንቱ ፥ " እንደሚደግፉን ነበር ቃል ሲገቡልን የነበሩት፤ ሆኖም ሞትን እንድንጋፈጥ ብቻችንን ትተውናል " ሲሉ መናገራቸው አይዘነጋም።

@tikvahethiopia
#Japan

ንብረትነቱ የጃፓን የሆነ የእቃ መጫኛ መርከብ ከዩክሬን በስተደቡብ በሚገኘው ጥቁር ባህር ላይ በሚሳኤል መመታቱን ጃፓን ታይምስ ዘግቧል።

አንድ የመርከቡ አባልም ቆስሏል።

ሮይተርስ እንደዘገበው የሩስያ ሚሳኤል የመርከቧን የኋላ ክፍል በመምታቱ መርከቧ በእሳት እንድትያያዝ ሆናለች።

የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር በይፋዊ ፌስቡክ ገፁ ላይ በፓናማ የተመዘገበችው የጭነት መጓጓዣ " Namura Queen" አርብ እለት በጥቁር ባህር ላይ መመታቷን አሳውቋል።

መርከቧ በምዕራብ ጃፓን ኢሂሜ ግዛት ኢማባሪ ከተማ የሚገኘው የመርከብ ድርጅት ስትሆን አንድ የኩባንያው ባለስልጣን ሁሉም 20 አባላት ፊሊፒናውያን እንደሆኑና አንደኛው በትከሻው ላይ መቁሰሉን ቀሪዎቹ 19 ሰዎች ምንም እንዳልተጎዱ ተናግረዋል።

የጃፓን የመሬት፣ የመሠረተ ልማት፣ የትራንስፖርት እና የቱሪዝም ሚኒስቴር የጥቃቱን ዝርዝር ሁኔታ እያጣራ መሆኑን ገልጿል።

በሩስያ በኩል እስካሁን የተባለ ነገር የለም።

በሌላ መረጃ ከዩክሬን ጦርነት ጋር በተያያዘ ጃፓን በሩስያ ላይ የግለሠቦችን፣ የባንኮችን ሀብት ማገድ ጨምሮ ሌሎችንም ማዕቀቦች ጥላለች።

@tikvahethiopia
#ASTU #AASTU

ሁለቱ የኢትዮጵያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈትነው ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሚያስገባ ነጥብ ያዝመዘገቡ ተማሪዎችን ለመቀበል በዛሬው ዕለት ጥሪ አቅርበዋል።

ዩኒቨርሲቲዎቹ የ2014 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ አውጥተዋል።

የመመዝገቢያ መስፈርቱ የሲቪክስ ትምህርትን ሳይጨምር የስድስት ትምህርት ድምር ውጤት ከዚህ በታች እንደተገለፀው ነው።

ለታዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤ/ጉሙዝ ፣ ጋምቤላ) ፦

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 395 ለሴት 390
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 385 ለሴት 380


ለሌሎች ክልሎች ፦

- ኢንጂነሪንግ ለወንድ 400 ለሴት 395
- አፕላይድ ሳይንስ ለወንድ 390 ለሴት 385


የምዝገባ ጊዜው ከየካቲት 21 ቀን 2014 ዓ/ም እስከ የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ሲሆን ምዝገባው የካቲት 30 /2014 ዓ/ም ከለሊቱ 6 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል ተብሏል።

ከላይ የተቀመጠውን የምዝገባ መስፈርት የሚያሟሉ ተማሪዎች በማንኛውም ስፍራ ሆነው በኢንተርኔት www.aastu.edu.et እና www.astu.edu.et ላይ መመዝገብ ይችላሉ።

ፈተናው መጋቢት 7 ቀን 2014 ዓ/ም እንደሚሰጥ ተነግሯል።

(ተጨማሪ መረጃ ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia