TIKVAH-ETHIOPIA
ሄሜቲ ሞስኮ ምን ይሰራሉ ? የጎረቤታችን ሀገር ሱዳን ሉአላዊው የሽግግር ም/ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ሩስያ፣ ሞስኮ ይገኛሉ። የሄሜቲ የሩስያ ጉብኝት በምዕራባውያን ሀገራት እና በሱዳን ወታደራዊ ክንፍ መካከል ውጥረት ባለበት እንዲሁም በዩክሬን ጉዳይ ምዕራባውያን ሩስያን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማግለል ማዕቀብም ለመጣል እየዛቱ ባሉበት ወቅት ነው። ሄሜቲ በትዊተር…
#SUDAN #RUSSIA

የሱዳን ሉአላዊ የሽግግር ም/ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ጄነራል መሐመድ ሃምዳን ዳጋሎ (ሄሜቲ) ሩስያ ሞስኮ የሚገኙ ሲሆን ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር ውይይት አድርገዋል።

ሄሜቲ ከሩስያ ምክትል ጠ/ሚ አሌክስአንደር ኖቫክ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ተገናኝተው መክረዋል።

ይኸው ጉዧቸው ሀገራቸውና ወታደራዊ መንግስታቸው ከምዕራብ ሀገራት ያገኝ የነበረው የገንዘብ ድጋፍ ስለተቋረጠ ከሩሲያ ድጋፍ ለማግኘት እየጣረ መሆኑ ማሳያ ተደርጎ ተወስዷል።

ሳመህ ሳልማን የተባሉ የምጣኔ ኃብት ተንታኝ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል የሄሜቲ የሞስኮ ጎብኝት በምጣኔ ሃብት ቅውስ ውስጥ ከምትገኘው ሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር እንደሚታይ ያስረዳሉ።

አሜሪካ እና ምዕራብ ሀገራት ይሰጡት የነበረውን የገንዘብ ድጋፍ ካቋረጡ እና የሱዳንን ብድር ለመሰረዝ ያስተላለፉት ውሳኔ ከሰረዙ ወዲህ የሱዳን ምጣኔ ኃብቷ ይዟታ በእጅጉ እንደተዳከመ ገልፀዋል።

የሀገሪቱ መገበያ ገንዘብ #ከዶላር ጋር ያለው ንጽጽር እየሰፋ በመጣበት በአሁኑ ሰዓት በሀገሪቱ ውስጥ ያለው የሸቀጦች ውድነት ከቀዳሚዎቹ መካከል ሆኗልም ብለዋል።

አሜሪካ በጀነራል ሄሜቲ እና ሌ/ ጄኔራል አብድል ፈታ አልቡራንን በመሰሉ የጦር አመራሮች ላይ ድንገት ማዕቀቦች ከጣለች በሚል ሱዳን የሩሲያን ድጋፍ ለማግኘት እየጣረች ሊሆን ይችላል ሲሉ ሳማህ ሳልማን ጠቁመዋል።

ካሜሮን ሀድሰን የተባሉ አትላንቲክ ካውንስል ውስጥ የሚሰሩ የአፍሪካ ጉዳዮች ተንታኝ በበኩላቸው የአሁኑ የሱዳንና ሩሲያ ግንኙነት ከኢኮኖሚ ፍላጎት በዘለለ የስትራቴጂ ሽግሽግ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ለቪኦኤ ጠቁመዋል።

ፎቶ ፦ የሄሜቲ ትዊተር ገፅ

@tikvahethiopia