TIKVAH-ETHIOPIA
1.48M subscribers
56.4K photos
1.4K videos
202 files
3.83K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ITena

• በስትሮክ፣ በአደጋ፣ እና በሌሎች በሽታዎች ምክንያት ሙሉ ለሙሉ ወይም በከፊል ለተፈጠረ አለመንቀሳቀስ (Paralysis)
• እድሜ በመግፋት ለሚፈጠሩ ጉድለቶች እንደ አልዛይመርስ፤ ዲሜንሻ
• ከተለያዩ ቀዶ ጥገናዎች ለማገገም
• በሙሉ (Coma) ወይም በከፊል የንቃተ ህሊና መቀነስ ላላቸው ታካሚዎች እንክብካቤ
• ለካንሰር እና ተከታታይ የህክምና ክትትል ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች

👉በ 0901222233 ይደውሉልን

Telegram FB IG LinkedIn Twitter 🌍

🏥 አድራሻችን ጀሞ ከ ጀሞ ሞል 200m ገባ ብሎ፡፡
#አሁን

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት በምክር ቤቱ ተገኝተዋል፡፡

በአሁኑ ሰዓት የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት በምክር ቤቱ ተገኝተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ። @tikvahethiopia
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ከፓርላማ አባላት በርካታ ጥያቄ ተነስቶላቸው በአሁን ሰዓት ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

ከፓርላማ አባላት መካከል አቶ ክርስቲያን ታደለ መንግስት በእነ አቶ ስብሃት ነጋ ላይ የተነሰረተውን ክስ ያቋረጠው ከህግ አግባብና ከህገመንግስቱ በሚጣረስ መልኩ ስለሆነ ማስተካከያ እንዲያደርግ ጠይቀዋል።

አቶ ክርስቲያን ፥ " መንግስት መጀመሪያ ዜናውን ሲነግረን በ #ምህረት ነው የተፈቱት ያለ ሲሆን እነ አቶ ስብሃት ነጋን የመሰለ ሰው በሰው ልጆች ላይ ግፍ ፈፅሟል፣ የዘር ማጥፋት ወንጀል ፈፅሟል ተብሎ የተጠረጠረን ወይም የከሰሰውን ሰው በምህረት መልቀቅ እንደማይችል ሲረዳ በፍትህ ሚኒስትሩ በኩል ይቅርታም ምህረት አይደለም የክስ ማቋረጥ ውሳኔ ነው በሚል ማብራሪያ ሰጥቷል " ሲሉ አስታውሰዋል።

አክለውም ፥ " መንግስት የሰራውን ሀገር ያወቀው ፀሀይ የሞቀውን ስህተት ለማረም እድል አለው " ያሉት አቶ ክርስቲያን " ይህን እድል ለመስጠት ነው ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩን የምጠይቀው። እነዚህ ሰዎች እኔ በምወክለው የአማራ ህዝብ ተደራጅተው ያደረሱበት ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት የህሊና መጉሳቆል ለመዘርዘር በቂ ጊዜ የለኝም " ብለዋል።

የፍትህ ሚኒስቴር ያሳለፈው የክስ ማቋረጥ ውሳኔ ከህግ የሚጣረስ በመሆኑ ውሳኔውን ውድቅ በማድረግ ክሱ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ መንግስትና በም/ቤቱ በአሸባሪነት በተፈረጀው ህወሓት መካከል ድርድር እየተደረገ እንደሚገኝ በተለያየ ሚዲያ እየተሰማ መሆኑን ያነሱት የፓርላማው አባል፦

• ምን ያህል እውነት ነው ?
• እውነት ከሆነ ማን ከማን ጋር ነው እየተደራደረ ያለው ?
• በማን አደራዳሪነት ?
• ህወሓት አሸባሪ ተብሎ የተፈረጀ ስለሆነ መንግስት የሚያደርገው ድርድር ከህጋዊነቱ እንዴት ይታያል ?
• የድርድሩ ማህበራዊ፣ ህጋዊ እና ሞራላዊ ቅቡልነት የሚረጋገጠው ድርድሩ ግልፅ እና አሳታፊ ሲሆን ነው ድርድሩ በኢትዮጵያ ህዝብ በተለይ ቀጥተኛ ተጎጂ በሆኑት የአፋር እና የአማራ ህዝብ የሚያሳድረው ስሜቱ ተጢኗል ወይ ? ሲሉ ጠይቀዋል።

እንዲሁም በጦርነቱ የደረሰው ውድመት በአማራ እና አፋር ለማካካስ የፀደቀው የድጎማ በጀት አንድ ተቋምን ጠግኖ ወደነበረበት የሚመልስ ባለመሆኑ ባለበጀት ክልሎች እና የፌዴራል መንግስት በልዩ ሁኔታ ሀገር ለማዳን ሲሉ ከፍተኛና ቀውስ ላስተናገዱ ክልሎች ለምን በበቂ ሆኔታ በጀት መደገፍ አልቻሉም ? ሲሉ ጠይቀዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤ ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር እና ከምዕራብውያን ሀገራት ጋር ያላት ወቅታዊ የዴፕሎማሲ ግኝኑነት ምን ይመስላል ? ሀገራዊ የሰህንበት ሁኔታው ባልተቀለበሰበት ሁኔታና በተለያዩ ምክንያቶች በቂ ወታደራዊ አመራሮች ባልተፈሩበት ሁኔታ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮኖችን በአምባሳደርነት መሾሙ ያለው ተገቢነት ላይ ማብራሪያ ይሰጥ ሲሉ ጠይቀዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት በምክር ቤቱ ተገኝተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ። @tikvahethiopia
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ?

ኡስታዝ ከሚል ሸምሱ ፦

" እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ሀገራችን ከሌሎች ሀገራት ያላትን ዲፕሎማሲ ከጊዜ ወደ ጊዜ ለማሻሻል እና ዲፕሎማሲውም የሀገራትን የጋራ ጥቅም ያስጠበቀ እንዲሁም የሀገሩን ክብር እና ሉዓላዊነት በጠበቀ መልኩ እንዲጎለበት ጥረቶች እየተደረጉ ይገኛሉ።

ሆኖም ግን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሀገራትን የፖለቲካ አስተላለፍ በመከተል ወዳጅ የነበሩ ሀገራት ጎራቸውን የቀየሩበት ሁኔታዎች ይስተዋላሉ።

እንደማያሳያም በርካታ ዜጎች በተለያዩ ሀገራት ለእስር ተዳርገው ለአላስፈላጊ እንግልት እና ስቃይ እንዲሁም ለሞት እየተዳረጉ ይገኛሉ ለምሳሌ በሳዑዲ አረቢያ ፣ እንዲሁም በኤምሬት አንዳንድ ቦታዎች ያለው ችግር መጥቀስ ይቻላል።

እንዘህ ዜጎች ከእስር ተፈተው ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ በመንግስት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም በምብ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ቢገለፅልን "

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#አሁን የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ አስቸኳይ ስብሰባውን እያካሄደ ይገኛል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከህዝብ ተወካዮች ለሚቀርቡ ጥያቄዎች ማብራሪያ ለመስጠት በምክር ቤቱ ተገኝተዋል፡፡ በአሁኑ ሰዓት የምክር ቤቱ አባላት የተለያዩ ጥያቄዎችን እያቀረቡ ይገኛሉ። @tikvahethiopia
" ነዳጁንም ቦቴውንም ውረሱት ብለናል " - ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እየሰጡት ባለው ማብራሪያ " ነዳጅ ከኢትዮጵያ አውጥተው ወደ ጎረቤት ሃገር ወስደው የሚሸጡ ዘራፊዎች አሉ " ብለዋል።

" ከራሳችን አልፍ ጎረቤት ሀገር ልንደጉም አንችልም " ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ " የሁሉም ክልል ሚሊሻዎች ልዩ ሃይሎች ፤ፖሊሶች ከሃገር የሚወጣ ነዳጅ ካገኛችሁ ነዳጁንም ቦቴውንም ውረሱ ብለናል " ሲሉ ለምክር ቤቱ ተናግረዋል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ETHIOPIA የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ለሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ኮሚሽነርነት ከቀረቡት ዕጩዎች መካከል 42ቱን መለየቱን የም/ቤቱ አፈ-ጉባኤ የተከበሩ አቶ ታገሰ ጫፎ ዛሬ አሳውቀዋል። አቶ ታገሰ ፥ ከመላው የሀገሪቱ ክፍሎች 632 የእጩ ኮሚሽነሮች ጥቆማ መቅረባቸውንና አብዛኛዎቹ ስራውን ለመስራት የሚያስችል ልምድና ዕውቀት ያላቸው መሆኑን መገንዘብ መቻሉን ጠቁመዋል፡፡ አዋጁ ለአፈ-ጉባኤውና ለአፈ…
#አሁን

በቅርቡ ለተሾሙ የሚሲዮን መሪዎች የተዘጋጀ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ፤ በቅርቡ በተለያዩ ሀገራት ለተሾሙ የሚሲዮን መሪዎች እንዲሁም በዋናው መ/ቤት በተለያዩ የስራ ኃላፊነት ላይ ለተመደቡ የስራ ኃላፊዎች ያዘጋጀው ስልጠና ዛሬ መሰጠት መጀመሩን ገልጿል።

በቅርቡ ጄነራል ባጫ ደበሌ ፣ ጄነራል ሀሰን ኢብራሂም ፣ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ፣ አቶ ደሴ ዳልኬ እና አቶ ተፈራ ደርበውን ጨምሮ ሌሎችም ግለሰቦች የባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ሹመት እንደተሰጣቸው እንዲሁም ሌሎችም ግለሰቦች በአምባሳደርነት ሹመት እንደተሰጣቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የምክር ቤት አባላት ምን ጠየቁ ? ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ከፓርላማ አባላት በርካታ ጥያቄ ተነስቶላቸው በአሁን ሰዓት ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ። ከፓርላማ አባላት መካከል አቶ ክርስቲያን ታደለ መንግስት በእነ አቶ ስብሃት ነጋ ላይ የተነሰረተውን ክስ ያቋረጠው ከህግ አግባብና ከህገመንግስቱ በሚጣረስ መልኩ ስለሆነ ማስተካከያ እንዲያደርግ ጠይቀዋል። አቶ ክርስቲያን ፥ " መንግስት መጀመሪያ ዜናውን…
ድርድርን በተመለከተ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምን አሉ ?

ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፦

" እስካሁን የተደረገ ድርድር የለም፤ እስከዚህ ደቂቃ ድረስ ፤ ስለድርድር ብዙ ሲወራ ሰማለሁ ግን እስካሁን ድርድር አላደረግንም፤ አላደረግንም ማለት እስከነአካቴው ድርድር የሚባል ነገር አይኖርም ማለት አይደለም።

ድርድር ፣ ውይይት ማለት ችግር ተወግዷል ማለት ሳይሆን ችግር ለማስወገድ አማራጭ Alternative መንገድ አለው ወይ ብሎ ማየት ነው።

በድርድርም ኢትዮጵያን ነው የምናፀናው ፣በንትርክም ኢትዮጵያን ነው የምናፀናው በውጊያም ዋጋ የምንከፍለው ኢትዮጵያን ለማፅናት ነው። ኢትዮጵያን ለማፅናት ህይወታችንን ገንዘባችንን የምንገብር ከሆነ ኢትዮጵያን ለማፅናት ስሜቶቻችን አምቀን መነጋገር የሚቻል ከሆነ በደስታ ማየት ጥሩ ነው። "

@tikvahethiopia